ከዘመናት ቁጭት ወደ ዝላይ ጉዞ
*****************
ዓለም በእንፋሎት ኃይል፣ በኤሌክትሪክ እና በኮምፒውተር አውቶሜሽን ሦስት ግዙፍ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ስታስተናግድ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በውስጥ ሽኩቻ፣ በተዘበራረቁ ፖሊሲዎችና በድህነት አረንቋ ውስጥ ታጥረን የሥልጣኔውን ባቡር በሩቁ ስንሸኝ ኖረናል።
የዓለም ሀገራት በፋብሪካ ጭስ እና በቴክኖሎጂ ግኝት ሰማይ ሲቧጥጡ፣ እኛ ያለንን የተፈጥሮ ጸጋ በባዕዳን እጅ እያስበላን፣ ላባችንን ገብረን ያመረትነውን ጥሬ ዕቃ በሳንቲም እየሸጥን መልሰን በውድ ዋጋ ስንገዛ የኖርንበት የታሪክ ስብራታችን መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም።
ይህ የዘመናት የታሪክ እንቅልፍ፣ ዛሬ ላለነው ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ቁጭትና አንገብጋቢ የለውጥ ጥማት የፈጠረ መሪር እውነት ነው።
ወደ ኋላ መለስ ብለን የኢንዱስትሪ ታሪካችንን ስንፈትሽ የባከኑ ዕድሎችን እናያለን።
በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በውጭ ባለሀብቶች የተጠነሰሰው የኢንዱስትሪ ጅምር፣ እርሾ ሆኖ ዛሬ ላይ ከፍተኛ ደረጃ የሚያደርሰን የነበረ ቢሆንም፣ በሥርዓቱ ባህርያዊ ችግር ምክንያት ከጅምር ማሳያዎች የዘለለ ዕድገት ሳያሳይ ቀርቷል።
በደርግ ሥርዓት "ካፒታል ከ500 ሺህ ብር ማለፍ የለበትም" በሚል አፋኝ ፖሊሲ የነበረውም ጅምር የግል ዘርፍ የሞት ጽዋ እንዲጠጣ ተደረገ።
በኢሕአዴግ ዘመን ደግሞ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው የነበረ ቢሆንም፣ ዘርፉ በግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫ እና በስትራቴጂ ባለመመራቱ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሲታነቅ እና በውጪ አቅራቢዎች ጥገኝነት ሥር ሲማቅቅ ቆይቷል።
ይህ የተቆራረጠ ጉዞ የኢንዱስትሪ ባለቤት ሳይሆን የባዕዳን ሸማች አድርጎን ኖሯል።
ዛሬ ግን ያ የቁጭት ዘመን እያበቃ ይገኛል፤ የዕድገቱን ባቡር ደረጃ በደረጃ ለመከተል ጊዜ የለንም።
የአሁኑ ትውልድ እና አመራር ካለፈው የታሪክ ስብራት በመውጣት "የዝላይ ስልትን" በመከተል ዕጣ ፈንታውን በእጁ ቀርጿል።
ሙሉ ትንታኔውን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል።
#ebc #ethiopia #madeinethiopia #industry #leapfrogging

19 days ago