2 months ago
ከ“ምናባዊ ዕቅድ” ወደ ተጨባጭ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ልዕልና
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የወደፊቱን የማክሮ-ኢኮኖሚ መዋቅር እና የአፍሪካን አህጉራዊ ተወዳዳሪነት የሚወስን ስትራቴጂያዊ መሳሪያ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ያስገነዝባሉ።
ይህ አቋም፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ተዓምራዊ ለውጥ ይዞ እንደሚመጣ እና በ2036 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ እንደሚሆን በሙሉ ልበ-ሙሉነት ከገለጹባቸው መልዕክቶች ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው።
ይህ ስትራቴጂያዊ ራዕይ ቀደም ሲል “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ሲቀረጽ “መሬት የማይነካ ምናባዊ ዕቅድ ነው” በማለት ይሞግቱ የነበሩ ወገኖችን ትችት በተግባር በተረጋገጡ እውነታዎች እና ስኬቶች የቀለበሰ ነው።
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታው አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር የመንግሥት አገልግሎቶችን ግልጽነት በማረጋገጥ፣ የታክስ አሰባሰብ አቅምን በማሳደግ እንዲሁም የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት ጠቅላላ ብሔራዊ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ ላይ ይገኛል።
ለዚህም የዘመናዊ ቴሌኮም መሠረተ ልማቶች መስፋፋት፣ የአራተኛው ትውልድ (4G) እና አምስተኛው ትውልድ (5G) ኔትወርክ ተደራሽነት እንዲሁም የግዙፍ የዳታ ማዕከላት ግንባታ ዋነኛ ሞተሮች በመሆን እያገለገሉ ነው።
የዲጂታል ጉዞው ስኬት ይበልጥ ጎልቶ የሚታየው ደግሞ በዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓት እና በዲጂታል መታወቂያ ዘርፎች በተመዘገቡት ተጨባጭ እመርታዎች ነው።
የዚህ ተግባራዊ ለውጥ ማሳያዎች የቴሌብር እና የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚዎች ፈጣን ዕድገት ነው። ወቅታዊ የኢቲዮ ቴሌኮም ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፥ የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር 60.6 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የመተግበሪያው ጠቅላላ የግብይት መጠን ከ9.13 ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር አልፏል።
መተግበሪያው በቀን በአማካይ 11 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር የሚያስተናግድበት ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ከ19.72 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
በተመሳሳይ በብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም መረጃ መሠረት፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 50 ሚሊዮን ተቃርቧል። ይህ የፋይዳ አሠራር ሥርዓት ከ150 በላይ ተቋማት ጋር በመተሳሰር ከ190 ሚሊዮን በላይ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ማረጋገጫዎችን አስተናግዷል።
በዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ሰፋፊ የለውጥ ሥራዎች በመተግበር ላይ ናቸው። ከ800 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ ፖርታል የማቅረብ እና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በስፋት የማዳረስ ሥራ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ነው።
በተቋማት መካከል የዲጂታል ፊርማ እና የክላውድ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር የተቀናጀ ወረቀት-አልባ የመንግሥት አሠራር እየተዘረጋ ይገኛል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ፣ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት እና የተቀናጀ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በጋራ የሚሠሩበት ዲጂታል የሕዝባዊ መሠረተ ልማት ማዕቀፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት የቀየረ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
እነዚህን የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስኬቶች መሠረት በማድረግ የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ በ2030 የዲጂታል ኢኮኖሚውን የጥቅል ሀገራዊ ምርት ድርሻ ወደ 12 በመቶ ለማሳደግ አቅዶ ወደ ሥራ ገብቷል።
ይህ ስትራቴጂ፥ ዜጎችን እና ተቋማትን ማብቃት፣ አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትን ማፋጠን፣ ሁለንተናዊ የዲጂታል ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ኢትዮጵያን የዲጂታል የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቀዳሚ መዳረሻ ማድረግ የሚሉ ዓላማዎችን አንግቧል።
በተለይም በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ ‘ማሽን ለርኒንግ' እና የነገሮች ኢንተርኔትን (The Internet of Things) የመሳሰሉ የኢንዱስትሪ 5.0 ቴክኖሎጂዎችን በስፋት መተግበር የስትራቴጂው ዋነኛ አካል ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ጋር በመተባበር የተጀመረውን የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ስልጠና ፕሮግራም አድማስ በማስፋት 7 ሚሊዮን ኮደሮችን ለማፍራት የተያዘው ግብ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
መደበኛ ያልሆነውን ኢኮኖሚ ወደ መደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት በማስገባት እና የታክስ መሠረትን በማስፋት ኢትዮጵያ በ2036 በአፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ለመሆን የሰነቀችው ብሔራዊ ራዕይ በጠንካራ የዲጂታል መሠረት ላይ እውን እየሆነ ይገኛል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #digitaleconomy #digitalethiopia2030 #digitaltransformation #techinnovation #ebc

4 months ago
የ5ቱ ዓመታት ገፆች፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እመርታ እና የኢኮኖሚው አዲስ ምዕራፍ
*********************
ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የተከናወኑ መጠነ ሰፊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ የክፍያ ሥርዓት ላይ ታላቅ አብዮት ፈጥረዋል።
"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እና "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂዎች ይፋ ከሆኑ ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ከባህላዊው የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ያደረገችው ሽግግር አስገራሚ ዕድገት አስመዝግቧል።
ቀደም ሲል በኦፕሬተር የሚመራ የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለመኖሩ የጥሬ ገንዘብ ጥገኝነት መላቀቅ ተስኖ የነበረ ቢሆንም፣ የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጎ የኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌብር" ወደ ሥራ መግባቱ ሁኔታዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀይሮታል።
ቴሌብር በሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራቱ የሀገራችንን የዲጂታል አቅም ለዓለም ያሳየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሞባይል ዋሌት አካውንቶች ቁጥር 161 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
ይህም ከአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር በላይ መሆኑ የአገልግሎቱን ተደራሽነት የሚያሳይ ሲሆን፣ በፕላትፎርሙ የሚከናወነው የገንዘብ ዝውውርም ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 82 በመቶ ደርሷል።
ይህ የዲጂታል ክፍያ አብዮት ለሀገራዊ ኢኮኖሚው በርካታ ጥቅሞችን እያስገኘ ይገኛል።
የመጀመሪያው የፋይናንስ አካታችነት ሲሆን፣ የባንክ አገልግሎት ባልደረሰባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ዜጎች በስልካቸው ብቻ ገንዘብ መቆጠብ፣ መላክ እና መቀበል በመቻላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ወደ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው እንዲገቡ አድርጓል።
በሌላ በኩል፣ መንግሥት እንደ ነዳጅ ግብይት፣ የትራፊክ ቅጣት፣ የግብር ክፍያ እና የውኃና መብራት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ በማድረጉ ብክነትን በመቀነስ ገቢው በቀጥታ ወደ ካዝናው እንዲገባ አስችሏል፤ ለምሳሌ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ብቻ መሆኑ ሕገ-ወጥ ዝውውርን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ ለገንዘብ ሕትመትና ጥገና የሚያወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ለማዳን የተቻለ ሲሆን፣ የገንዘብ ምንጭና መድረሻው ስለሚታወቅ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከልና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር የተሻለ አቅም ተፈጥሯል።
ባጠቃላይ ይህ ዕድገት ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለምናደርገው ጉዞ ትልቅ ሞተር እየሆነ ሲሆን፣ ዘርፉ በፖሊሲ መደገፉን መቀጠሉ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት የዲጂታል ምጣኔ ሀብት ተጠቃሚ ሀገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ
#digitalethiopia #telebirr #cashlesssociety #digitaleconomy #ethiopianbroadcastingcorporation Ethiopian Broadcasting Corporation

ከባንክ ሰልፍ ወደ አንድ ንክኪ፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ እውነታዎች
**********************
ዛሬ መረጃ እና ገንዘብ ፍጥነታቸውን ጨምረው በእጅ ስልካችን ውስጥ የገቡበት ዘመን ላይ ደርሰናል።
በትናንቱ የወረቀት የገንዘብ ቁጠባ ደብተር እና በባንክ ቅርንጫፎች ረጅም ሰልፍ የምናውቃት ኢትዮጵያ፣ ዛሬ በአንድ ንክኪ ወደሚፈጸም ዘመናዊ የዲጂታል አሠራር ተሸጋግራለች።
ይህ ሽግግር የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ደኅንነት እና ነፃነት የማስከበር የ"ዲጂታል ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት" ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ሀገራችን በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ አማካኝነት እያካሄደችው ያለው ይህ አብዮት የት ደረሰ?
የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቴክኖሎጂን በመግዛት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሕዝብ፣ መንግሥት፣ ባንክ እና ቴሌኮም ተደምረው የሚፈጥሩት አዲስ ሀገራዊ አቅም ነው።
ቴሌብር ወይም የፋይዳ መታወቂያ ብቻቸውን የፋይናንስ ክፍተትን ሊሞሉ አይችሉም። ነገር ግን የፋይዳ መታወቂያ ከግብር ሥርዓቱ እና ከባንክ ጋር ሲተሳሰር የተሟላ የዲጂታል መሠረተ-ልማት ይሆናል።
ይህን መሠረት ይበልጥ ለማጠናከር የአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ኢንስቲትዩት መቋቋሙ እና አሁን ደግሞ የሰው ሠራሽ ዩኒቨርሲቲ በሂደት ላይ መሆኑ ሀገራችን በዕውቀት ላይ ለተመሠረተው የነገ ኢኮኖሚ እየተዘጋጀች መሆኗን በተጨባጭ ያሳያል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የ"5 ሚሊዮን ኮደሮች" የዘመቻ ሥልጠና ሀገራችንን ለነገው ተወዳዳሪነት እያበቃት ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ከመጭበርበር እና ከደኅንነት ሥጋት ለመጠበቅ የ"ፋይዳ" ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሂሳብ ጋር ማገናኘትን ግዴታ ማድረጉ ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን የቻሉ ሲሆን፣ የቁጥጥር ሥርዓቱም በጊዜ ገደብ እየተተገበረ ይገኛል።
በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ፣ ሐረሪ እና 25 ዋና ዋና ከተሞች የመጨረሻው የጊዜ ገደብ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የነበረ ሲሆን፣ ያላገናኙ ደንበኞች ላይ የወጪ እገዳ ተጥሏል።
በተቀሩት ከተሞች እና የገጠር ቅርንጫፎች ደግሞ የመጨረሻው የጊዜ ገደብ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ በተመሳሳይ የወጪ እገዳ ይጣልባቸዋል።
በውጭ ለሚኖሩ ዳያስፖራዎች ግን የ2 ዓመት ማቅለያ የተሰጣቸው በመሆኑ ጊዜያዊ እገዳ ሳይጣልባቸው መደበኛ ግብይት መቀጠል ይችላሉ።
በሌላ በኩል የቴሌኮም ዘርፉ ክፍት መደረግ እና የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት የቴሌኮም ሞኖፖልን በመስበር ጤናማ ውድድር ፈጥሯል።
ይህ ውድድር የ3G ኔትወርክ ሽፋንን በ50 በመቶ ሲያሳድግ፣ የ4G የሕዝብ ተደራሽነትን በ8 እጥፍ ማሳደግ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 87.1 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 49 ሚሊዮንን አልፏል።
የብሮድባንድ ኢንተርኔት ተደራሽነትም በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 20 በመቶ በታች አሁን ወደ 45 በመቶ ያደገ ሲሆን፣ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ዝርጋታም 23 ሺህ 26 ኪሎ ሜትር ደርሷል።
ከዚህም በላይ የሀገራችን የሞባይል ክፍያ አካውንት በ2012 ዓ.ም ከነበረበት 12.2 ሚሊዮን አሁን ወደ 139.5 ሚሊዮን አድጓል።
በዚህ ዘርፍ የዲጂታል ክፍያ ፈርቀዳጅ የሆነው ቴሌብር የደንበኞቹን ቁጥር 58.61 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን፣ በቴሌብር የተቀመጠው የጥቃቅን ቁጠባ መጠን 34.41 ቢሊዮን ብር ደርሶ ከመደበኛ ባንክ ውጭ ለነበሩ 16 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጥቃቅን ብድር ማድረስ ተችሏል።
ሳፋሪኮም በበኩሉ ኤም-ፔሳን (M-Pesa) ከኢትዮ ስዊች ጋር በማዋሃድ የደንበኞቹን ቁጥር ከ5.2 ሚሊዮን በላይ አድርሷል።
ይህን ዕመርታ በስትራቴጂ ለመምራት የወጣው የBRIDGE 2030 ዕቅድ ደግሞ እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ የዲጂታል ክፍያዎችን አጠቃላይ ዋጋ ከሀገራችን ጠቅላላ ምርት (GDP) አንፃር 750 በመቶ ለማድረስ አልሟል።
ኢኮኖሚውን ከጥቁር ገበያ አደጋ ለመታደግ እና የፍራንኮ ቫሉታ አሠራርን ግልጽ ለማድረግ በአዲሱ መመሪያ (FVD/01/2018 ዓ.ም) መሠረት ግዙፍ መዋቅራዊ ለውጥ ተደርጓል።
ማንኛውም የፍራንኮ ቫሉታ ግብይት ከግንቦት 2018 ዓ.ም ጀምሮ FEMoUS በተባለው የብሔራዊ ባንክ እና ጉምሩክ ኮሚሽን የተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት ውስጥ ማለፍ ግዴታ ሆኖ መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች እንዳይጠቀሙበት ተከልክሏል።
በዚህ አሠራር መሠረት የሐኪም ማዘዣ እና የጤና ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው ለሕክምና የሚሆኑ አስቸኳይ መድኃኒቶች ምንም የዋጋ ገደብ የሌላቸው ሲሆን፣ ለዳያስፖራዎች እና የውጭ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ፈቃድ እስከ 10 ሺህ ዶላር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚመጡ ዜጎች በነዋሪነት ፈቃድ እስከ 5 ሺህ ዶላር (ከቀረጥ ነፃ)፥ እንዲሁም ለንግድ ናሙናዎች ከሕጋዊ የንግድ ሥራ ጋር የሚያስተሳስር የጉምሩክ ሰነድ በማቅረብ እስከ 4 ሺህ ዶላር የገንዘብ ጣሪያ ተቀምጦባቸዋል።
በተጨማሪም መንግሥት ከብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) ጋር በመሆን 657 ሕገወጥ የባንክ ሂሳቦችን ያገደ ሲሆን፣ ሸጌ፣ አዱሊስ፣ ታጅ እና ረመዳ የተባሉ 4 ሕገወጥ የሐዋላ ድርጅቶች እንዲዘጉ አድርጓል።
ብሔራዊ የገንዘብ ሉዓላዊነትን ለማስከበር እንደ ባይናንስ (Binance) እና ሜክስክስሲ (MEXC) ያሉ የክሪፕቶ መገበያያ መድረኮች ከኢትዮጵያ ገበያ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ ተደርጓል።
ይህ ደፋር እርምጃ የሀገር ውስጥ መረጃ ማከማቻ አሠራር ከመዘርጋቱ እና የዳታ ማስተላለፊያ ፍጥነት ከ500 ጊጋ ባይት በሰከንድ ወደ 3 ቴራ ባይት በሰከንድ ከፍ ካለበት ስኬት ጋር ተዳምሮ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመታደግ አስችሏል።
ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን በማገዝ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን ወደ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል እና የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር የሚያስተምረን ትልቁ እውነት ቴክኖሎጂ በራሱ ብቻ ተዓምር እንደማያመጣ ነው።
እውነተኛ እና ዘላቂ ልማት የሚረጋገጠው ቴክኖሎጂ ከተቋማዊ ውህደት፣ ከሕግ ቁጥጥር እና ከሕዝብ ተሳትፎ ጋር በ"መደመር" ፍልስፍና ሲቀናጅ ብቻ ነው።
ይህ ቅንጅት በተሳካ ሁኔታ ሲቀጥል፣ ዲጂታል ኢኮኖሚው ሀገርን ወደ ብሔራዊ ብልጽግና የሚመራ እውነተኛ የልማት ጎዳና መሆኑ ይረጋገጣል።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #digitaleconomy #banking #digitalfinance #digitalethiopia #ebc

5 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳደግና የገበያ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረመ
ኩባንያችን በአራተኛው የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ላይ ከመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ ከጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበራት ጋር የ(B2G) የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።
ስምምነቶቹ ኩባንያችን ለቴሌኮም እና ለኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎች የሚውሉ የፋይበር ኦፕቲክስ፣ የኃይል እና የዳታ ኬብሎችን፣ ልዩ ልዩ መለዋወጫዎችን እና የሠራተኞች የደንብ ልብሶችን ከአገር ውስጥ አምራቾች ለመረከብ የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ይህም ኩባንያችን አስተማማኝና ጥራት ያላቸውን ግብዓቶች በአገር ውስጥ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ፣ አምራቾች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን እንዲያቀርቡና የአቅርቦት ሰንሰለት ማነቆዎችን እንዲቀርፉ ምቹ ዕድል የሚፈጥር ነው።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾችን የማምረት አቅም ለማሳደግ፣ ፈጠራን ለማበረታታትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ እና ዘላቂ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ይኖራቸዋል።
ኩባንያችን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሀገራዊ ዲጂታል ኢኮኖሚው ግንባታ ጉል ፋይዳ ያለው በአምራቾች መካከል ያለውን የገበያ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ "ኢ-ታምርት" የተሰኘ የB2B የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም ሥራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል።
#ethiotelecom #ministryofindustry #telebirr #ethiopiatamirt #b2bplatform #digitaleconomy #localmanufacturing #gsma #itu #worldbank #madeinethiopia Ethiopian Ministry of Industry

Sponsored by
Surafel

6 months ago
የኢትዮጵያ ምርቶች በዋይልድቤሪስ በኩል ለዓለም ገበያ ቀረቡ
#ethiopia | ለኢትዮጵያ አምራቾችና ላኪዎች አዲስ የገቢ ምንጭ ተከፍቷል! የዓለም አቀፉ የገበያ መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) የኢትዮጵያ ሻጮች ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገዢዎች እንዲያቀርቡ መድረኩን ክፍት ማድረጉን አስታውቋል።
ይህ ዕድል ምን ይዟል?
ቀጥታ የገበያ ትስስር
የሀገር ውስጥ ምርቶች (Manufactured in Ethiopia) ያለምንም መካከለኛ ደላላ ለዓለም አቀፍ ደንበኞች ይደርሳሉ።
ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን
አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች አሰራራቸውን ወደ ዘመናዊው የኢ-ኮሜርስ ስርዓት እንዲቀይሩ ትልቅ አጋዥ ይሆናል።
የግንዛቤ መድረኮች
አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን የሚያስረዱ ተከታታይ ስልጠናዎችና የግንዛቤ መድረኮች ይከናወናሉ።
የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸው ይበልጥ እንዲታወቅ የሚያደርግ ታሪካዊ ጅማሮ!
#getu #wildberriesethiopia #ecommerce #ethiopiamanufacturing #globalmarket #digitaleconomy #madeinethiopia #businessnews #addisababa #ኢኮኖሚ #ንግድ #ኢትዮጵያ #ዋይልድቤሪስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና ቢዩ ድሊቨሪ አብረው ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት አንዱ የሆነው ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ግብይት አማራጭ የሆነው ቢዩ ድሊቨሪ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው እለት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል።
ይህ ስምምነት በዋናነት የሞሐ ምርቶችን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋትና ለደንበኞች ምቹ የሆነ ግብይትን ለመፍጠር ያለመ ነው።
የስምምነቱን ዝርዝር አስመልክቶ የሞሐ የለስላሳ መጠጦች የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ሰለሞን እንደገለጹት፣ ደንበኞች ከቢዩ ድሊቨሪ ምግብ በሚያዙበት ወቅት የፔፕሲ የፕላስቲክ ምርቶችን በቀላሉ በአንድ ላይ ማግኘት የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥራል።
ሞሐ በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩኘ ስር መካተቱን ተከትሎ ባገኘው ጠንካራ የፋይናንስ አቅም፣ የማምረት ሂደቱ ምንም አይነት እክል ሳይገጥመው እየቀጠለ መሆኑን አቶ ንጉሱ ገልጸዋል።
ይህ የትብብር ስምምነት የንግድ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ፣ ከ3,500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረውን ቢዩ ድሊቨሪን አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ ይኖረዋል።
ስምምነቱ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የደንበኞችን ፍላጎት በቤትና በቢሮ ሆኖ ለማርካት ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #mohasoftdrinks #beudelivery #ethiopiabusiness #pepsiethiopia #digitaleconomy #medrocinvestmentgroup

በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል የትራንስፖርት አማራጭ ይፋ ተደረገ
#ethiopia | ይህንን አዲስ የክፍያ አማራጭ ወደ ዘርፉ ያስገባው ዘማይ የተባለው የግል ማህበር ነው።
ይህንን አማራጭ የሚፈልጉ ዜጎች ወደ 6312 የጥሪ ማዕከል በመደወል መገልገል ይችላሉ ነው የተባለው።
ማህበሩ "ዘማይ ጉዞ" እና "ዘማይ ብር " የተሰኙ ሁለት አገልግሎቶች ዛሬ በመስቀል አደባባይ ባከናወነው ስነስርአት ለህዝብ ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ስራውን በ1,680 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ቁጥራቸውን ወደ 30,000 የማሳደግ ሰፊ እቅድ መያዙን ገልጿል።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ በመሆናቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል።
የጉዞ መነሻ ዋጋው 100 ብር ሆኖ በየኪሎሜትሩ ደግሞ 12 ብር በሚታሰብበት ዋጋ ለህብረተሰቡ አቅርቢያለሁ ብሏል።
ከደህንነት አንጻርም አሽከርካሪዎቹ በቂ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ተሽከርካሪዎቹም ተሳፋሪዎች ንብረት ቢረሱ የሚጠቁም የደወል ምልክትና ገመድ አልባ የስልክ ቻርጀር የተገጠመላቸው ናቸው ተብሏል።
የመኪናዎቹ ንጽህና በዘመናዊ የእንፋሎት እጥበት የሚከናወን በመሆኑ የኤሌክትሪክ አካላቶቻቸው ከውሃ ንክኪ ተጠብቀው እንዲቆዩ ያስችላል ተብላል።
ከዚህ በተጨማሪም ዘማይ ብር የተሰኘው መተግበሪያ ከባንኮችና ከቴሌብር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለደንበኞች የ20 በመቶ ቅናሽና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭን ይዞ መጥቷል።
ድርጅቱ በሰከንድ አንድ ሚሊዮን ጥሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 6312 የጥሪ ማዕከል በማቋቋም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፊ የስራ እድልና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#zemayguzo #zemaybirr #electricvehicles #ethiopia #digitaleconomy #greentransport #techinnovation #addisababa

7 months ago
የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል የባንክ ሒሳቦች እግድ ተነሳ
* የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞው ቀጥሏል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ በሀገሪቱ ቀዳሚ የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ በሆነው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ አክሲዮን ማኅበር የባንክ ሒሳቦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ የካቻ የባንክ ሒሳቦች እንዲከፈቱ የወሰነ ሲሆን፤ ከውርርድ (Betting) ኩባንያዎች ጋር የተያያዘ 3.1 ሚሊዮን ብር ገደማ ግን ምርመራው እስኪጠናቀቅ ታግዶ እንዲቆይ አዟል።
ካቻ የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን፣ የክፍያ ሥርዓቶችን (Bill & Merchant Payment)፣ እንዲሁም ዲጂታል ብድርና ቁጠባን በሀገር በቀል ዕውቀትና ቴክኖሎጂ በማቅረብ ይታወቃል።
ስትራቴጂካዊ አጋርነት፦ ተቋሙ ከባንኮች፣ ኢንሹራንስና አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የፋይናንስ ዘርፉን በማዘመን ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ካቻ የዲጂታል ኢንሹራንስ አገልግሎትን በፈር ቀዳጅነት በማቅረብ፣ የኢንሹራንስ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ተደራሽ የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ካቻ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች በመቅረፍ፣ የጀመረውን ሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ያለ መስተጓጎል እንዲቀጥል አመቺ መደላድል የሚፈጥር ነው።
የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎትን በስልክዎ ለማግኘት፦ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!
የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ (Kacha Digital Financial Services) የባንክ ሒሳቦች እግድ በሕግ መነሳቱን ተከትሎ፣ ኩባንያው መደበኛ አገልግሎቶቹን በሙሉ አቅሙ መቀጠሉ ይታወቃል።
የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን፣ የክፍያ ሥርዓቶችን፣ ዲጂታል ብድርና ቁጠባን እንዲሁም የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን በስልክዎ ለማግኘት መተግበሪያውን (App) ከታች ባሉት ሊንኮች ማውረድ ይችላሉ፦
መተግበሪያውን ለማውረድ፦
ለአንድሮይድ (Android) ተጠቃሚዎች ከፕሌይ ስቶር፦
https://play.google.com/st...
ለአይፎን (iOS) ተጠቃሚዎች ከአፕ ስቶር፦
https://apps.apple.com/us/...
የካቻን መተግበሪያ በመጠቀም ፈጣን፣ አስተማማኝና ምቹ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ማግኘት ይጀምሩ።
#getu #ethiopia #kachadigital #financialinclusion #digitaleconomy #fintechethiopia #bankingnews #courtdecision #ካቻዲጂታል #ዲጂታልፋይናንስ #ኢትዮጵያ #የባንክእግድ #ዜና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments