29 days ago
በማንሠራራት ወደ ብልፅግና!
**************
ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ አልፋ የማንሠራራትና የትንሣኤ ጉዞዋን በማፋጠን ላይ ትገኛለች።
ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡት ዐበይት ሀገራዊ ስኬቶች የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ እየገነባን ለመሆናችን ተጨባጭ ማሳያ ናቸው።
የሀገር ውስጥ የስንዴ ፍጆታን መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል የታየበት የመስኖ ስንዴ ልማት አብዮት የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ወደ ሜካናይዜሽን የተሸጋገረበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኢትዮጵያውያን የጋራ ሕልምና ጽናት ውጤት የሆነው እና ኃይል ማመንጨት ጀምሮ ለኢንዱስትሪና ለቀጣናዊ ትስስር መንገድ የከፈተው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ባለው ትልቅ ፋይዳ “ዳግማዊ ዓድዋ” ለመሰኘት በቅቷል።
በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የተፈጥሮ ሚዛንን የመጠበቅ፣ የአፈር መሸርሸርን የመከላከል እና የደን ሽፋንን የማሳደግ ዓለም አቀፍ አርዓያነት ያለው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ሀገራችንን ወደ አዲስ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ምዕራፍ እያሸጋገራት ነው።
አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ለቱሪስቶች ሳቢ በማድረግ መልሰን የገነባንበት የኮሪደር ልማት እና ውበት ኢኒሼቲቭ ታላቅ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትርጉም ያለው የከተሞች ትራንስፎርሜሽን ሥራ ነው።
የሀገራችንን የፋይናንስ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ምህዳር በማዘመን ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ ወደ ሥራ የገባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያም የኢትዮጵያ ማንሠራራት የተፋጠነበት ደፋር እና ውጤታማ እርምጃ ነው።
በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ እና በሌሎች ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎች በመታገዝ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም እንዲያንሠራራና ተወዳዳሪ እንዲሆን የተደረገው ጥረት ለሀገራዊ ምርት ዕድገትና ለሥራ ፈጠራ ትልቅ መሠረት ጥሏል።
የጉባ ብስራቶችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ የልማት ውጥኖቻችን በግልፅ የሚያሳዩት፣ አንድነታችንን አጠናክረን ከተጋን የተፋጠነው የማንሠራራት ጉዟችን በአጭር ጊዜ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንደሚያደርሰን ነው።
#ethiopia #greenlegacy #gerd #homegrowneconomicreform #madeinethiopia #revival #prosperity #ebc

Comments