በኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዟችን ተጨባጭ ለውጥ እያመጣንባቸው ያሉት ተኪ ምርቶቻችን
***********************
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለፉት ዓመታት የሀገራችንን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማነቃቃት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከውጭ ጥገኝነት ለማላቀቅ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመረ ግዙፍ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀጥተኛ አነሳሽነት እና መሪነት ወደ ተግባር የገባ ሲሆን፣ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ ምሰሶውም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ይህ ጥረት፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ መዋቅር ላይ ጉልህ እና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያሳየ ይገኛል።
ንቅናቄው ወደ ሥራ ሲገባ በዋናነት ትኩረት ያደረገው እና ያበረታታው የሀገር ውስጥ አምራቾችን፣ ወጣት የፈጠራ ባለቤቶችን፣ የሥራ ፈጣሪዎችን እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተመረቁ ባለሙያዎችን ነው።
ከዚህም ባሻገር ቀደም ሲል በማሽነሪ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ወይም በግብዓት እጥረት ምክንያት ከአቅማቸው በታች ያመርቱ የነበሩ በርካታ ነባር ፋብሪካዎች፣ ችግሮቻቸው ተለይተው እና ተገቢው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲሸጋገሩ አስችሏል።
አምራቾች የፋይናንስ ብድር አቅርቦት ቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉ፣ የታክስና የጉምሩክ ማበረታቻዎች መሰጠታቸው እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ምቹ የመሥሪያ ቦታዎች መመቻቸታቸው ዘርፉን በማሳደግና አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
በንቅናቄው ማዕቀፍ በተለይ በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በኬሚካል፣ በኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና በሌሎችም ቁልፍ ዘርፎች በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አምራች ኢንዱስትሪዎች ለምርታቸው የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ዘርፎች ማግኘት እንዲችሉ በማድረግ፣ የኢኮኖሚ ትስስር ሰንሰለትን ማጠናከር ተችሏል።
ይህም የሀገር ውስጥ አርሶ አደሮችና ማዕድን አውጪዎች ምርታቸውን በቀጥታ ለፋብሪካዎች የሚያቀርቡበትን ሰፊ ዕድል በመፍጠር የገበያ ትስስሩን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
በተኪ ምርቶች ላይ የተመዘገበው ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እጅግ የላቀ መዋቅራዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ዋነኛው ጥቅሙም የሀገራችን ትልቅ ፈተና የሆነውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ማቃለል መቻሉ ነው።
ቀደም ሲል ለምግብ ዘይት፣ ለዕለታዊ የፍጆታ ዕቃዎች፣ ለብረት እና ለሲሚንቶ ግዥ ወደ ውጭ ይወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በሀገር ውስጥ በማስቀረት የንግድ ሚዛን ጉድለቱን ማጥበብ ተችሏል።
በተያያዘም አዳዲስ የተኪ ምርት ኢንዱስትሪዎች ሲስፋፉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለቴክኒክና ሙያ ምሩቃን ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል።
በሌላ በኩል ተኪ ምርቶችን ከማስፋፋት አኳያ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ያበረከተው የጎላ አስተዋጽኦ፣ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችን በጅምላ ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ማስቻሉ ነው። ይህ ሒደት የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የዕውቀት ክምችትን እያፋጠነ ይገኛል።
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚነሱ የጂኦፖለቲካ ቀውሶችን፣ የዓለም አቀፍ ገበያ መዋዠቅንና የዋጋ ንረትን ተቋቁማ በራሷ እግር እንድትቆም በማድረግ የኢኮኖሚ አቅሟን በእጅጉ ያሳድገዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተጀመሩ የተኪ ምርት ሥራዎች የሀገራችንን የኢንዱስትሪ መሠረት በማጠናከር ረገድ የተለየ እና የላቀ ምዕራፍ የከፈቱ በመሆናቸው፣ የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ዕድል እጅግ ብሩህ ያደርጉታል።
ይህን ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠልም፣ ከተኪ ምርት ባለፈ የሀገር ውስጥ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በማድረግ ወደ ውጭ ገበያ በሰፊው ለመላክ የሚያስችል የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊጠናከር ይገባል።
በሄዋን ጌታቸው
#ethiopia #manufacturing #madeinethiopia #importsubstitution #valueaddition #ethiopiatamrit #ebc

23 hours ago