13 days ago
የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅትን የቦታ እጥረት ዋነኛ ተግዳሮት መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያዎች የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅትን ጎብኝተው በማዕከሉ የሚሰጡ የሙያ ሥልጠናና ድጋፎችን ተመልክተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያው አቶ ሞገስ ገረመው፣ በማዕከሉ ያዩት የታዳጊ ወጣቶች አያያዝ፣ የቦታው ንጽህናና የሚሰጡት የሙያ ሥልጠናዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። ወጣቶቹ የተለያዩ ሙያዎችን እየተማሩ የራሳቸውን አቅም እንዲገነቡና በራሳቸው እንዲተማመኑ የሚያስችል እድል መፈጠሩንም ጠቁመዋል።
ሌላኛዋ የአስተዳደሩ ማህበራዊ አገልግሎት ባለሙያ ወይዘሮ ሄለን ብርሃን በበኩላቸው፣ ማዕከሉ ብዙ ሰዎች የሚገጥማቸውን ችግር ለማቃለል እየሰራ ያለ እና ለወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል። በጉብኝታቸውም በሙዚቃ፣ በእጅ ሥራና በሌሎች ዘርፎች ያዩት የህፃናቱ ችሎታ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሄለን፣ በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ እየደገፈ ያለው ወደ 40 የሚጠጉ ህፃናትና ወጣቶች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ፣ ማዕከሉ ተስፋፍቶ በየቤታቸው የሚገኙ ሌሎች ህፃናትም ወጥተው በችሎታቸው እንዲደገፉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ህፃናቱና ወጣቶቹ በሽመና፣ በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በስፖርት፣ በኮምፒዩተርና በኮዲንግ ዘርፎች ያዳበሩትን ክህሎትና የሚያከናውኑትን ሥራ ለጎብኚዎቹ አሳይተዋል።
የራዕይ ህፃናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ወይዘሮ ሰሎሜ ኩምሳ፣ የባለሙያዎቹ ጉብኝትና ድጋፍ ለህፃናቱ እና ድርጅቱ ለሚያከናውነው ሥራ ትልቅ ማበረታቻ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰሎሜ ገለጻ፣ ድርጅቱ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመማር ችግር ላላቸው ወጣቶች የሙያ፣ የኮምፒዩተር፣ የሙዚቃ፣ የሥነ ጥበብና የስፖርት ሥልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ይሰጣል። ድርጅቱ ባለፉት ዓመታትም ከ350 በላይ ወጣቶችን መደገፉን ገልጸዋል።
ማዕከሉ እያከናወነ ካለው ሥራ ጋር ተያይዞ የቦታ እጥረት ዋነኛ ተግዳሮት መሆኑን ወይዘሮ ሰሎሜ ጠቁመዋል። ተጨማሪ ቦታ ቢገኝ ብዙ ህፃናትን እና ታዳጊ ወጣቶችን መድረስና የሙያ ሥልጠናዎችን ማስፋት እንደሚቻል ገልጸው፣ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና የመንግሥት አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በማዕከሉ ከሰለጠኑ ወጣቶች መካከል 12ቱ በሽመና ሙያ በመሰማራት ነጠላ፣ ሻርፕና የባህል ልብሶችን እያመረቱ መሆኑ ተገልጿል። ማዕከሉ ከሙያ ሥልጠና በተጨማሪ ለወጣቶቹ የሥነ ልቦናና የሕክምና ድጋፍ፣ እንዲሁም ለወላጆችና መምህራን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።
ድጋፍ ለማድረግ፦
1000641844237 — የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
91675145 — አቢሲኒያ ባንክ
513049 — ቴሌ ብር አጭር ቁጥር
#ethiopia #visionchildrensorganization #childrenssupport #youthempowerment #communitysupport #volunteerism #skillstraining #inclusiveeducation #disabilityinclusion

16 days ago
በጎ ፈቃደኞች የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅትን ጎበኙ
#ethiopia | በጎ ፈቃደኞች የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅትን በመጎብኘት ለህፃናትና ወጣቶች የሚሰጠውን የሙያና የክህሎት ሥልጠና ተመልክተው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
በጉብኝቱ ወቅት ህፃናቱና ወጣቶቹ በሽመና፣ በስዕል፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በስፖርት፣ በኮምፒዩተርና በኮዲንግ ዘርፎች የሚያዳብሩትን ክህሎትና የሚያከናውኑትን ሥራ ለጎብኚዎቹ አሳይተዋል።
የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ወይዘሮ ሰሎሜ ኩምሳ፣ የተደረገው ጉብኝትና ድጋፍ ለህፃናቱና ድርጅቱ ለሚያከናውነው ሥራ ትልቅ ማበረታቻ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰሎሜ ገለጻ፣ ድርጅቱ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመማር ችግር ላላቸው ወጣቶች የሙያ፣ የኮምፒዩተር፣ የሙዚቃ፣ የሥነ ጥበብና የስፖርት ሥልጠናዎችን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ይሰጣል። ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ከ350 በላይ ወጣቶችን መደገፉን ገልጸዋል።
በማዕከሉ ከሰለጠኑ ወጣቶች መካከል 12ቱ የሽመና ሙያ ባለሙያዎች በመሆን ነጠላ፣ ሻርፕና የባህል ልብሶችን እያመረቱ መሆኑም ተገልጿል። ከሙያ ሥልጠናዎች በተጨማሪ ለህፃናቱ የሥነ ልቦናና የሕክምና ድጋፍ እንዲሁም ለወላጆችና መምህራን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ሥልጠናዎችን ይሰጣል።
የራዕይ የህፃናት መርጃ ድርጅት በተጨማሪም ማዕከሉ ሰፋ ያለ ቦታ ቢያገኝ በርካታ ሥራዎችን በማስፋት ብዙ ህፃናትና ወጣቶችን መደገፍ እንደሚችል ገልጿል።
በጎ ፈቃደኞቹ ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር በመሆኑ፣ በቀጣይም ተሳትፎና ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

2 months ago
የዲጂታል ኢትዮጵያ ህልም በኢትዮ ኮደርስ ሚሊዮን ወጣቶችን ለነገው ዓለም የሚያዘጋጀው ሀገራዊ የቴክኖሎጂ አብዮት
********************
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታዋን ለማፋጠን እና ወጣቶችን የቴክኖሎጂ ባለቤት ለማድረግ ካለመቻቸው ትልልቅ ኢኒሼቲቮች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳቢነት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት ጋር በትብብር የሚተገበረው የ"ኢትዮ ኮደርስ" ሥልጠና በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ የሆኑ እንደ መሠረታዊ ዳታ ሳይንስ፣ መሠረታዊ ፕሮግራሚንግ፣ መሠረታዊ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ እና መሠረታዊ አንድሮይድ ኮትሊን ዴቬሎፐር ያሉ አራት ወሳኝ የቴክኖሎጂ ዘርፎችን ያካተተው ነፃ የኦንላይን ሥልጠና፣ ሀገራችን ወደ ሙሉ ዲጂታላይዜሽን የምታደርገውን ጉዞ የማፋጠን ትልቅ አቅም አለው።
ሥልጠናው ወጣቶች መረጃዎችን የመተንተን፣ ውህድ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስን የመተግበር እና ሞባይል መተግበሪያዎችን የመሥራት አቅማቸውን በማጎልበት በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሥራ ዕድሎችን እንዲያገኙ መንገድ ከመክፈቱ ባሻገር፣ የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች (Startups) በመመሥረት ሀገራዊ ችግሮችን በዲጂታል መፍትሔዎች እንዲፈቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የኢትዮጵያ ወጣቶች ክረምታቸው በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድ የማይገባ ትልቅ ዕድል መጥቷል” ሲሉ ገልጸው፣ የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው በመሆኑ ሚሊዮኖች ቀድመው የወሰኑበትን ይህን ነፃ ዕድል ወጣቶች እንዲጠቀሙበት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
"ትውልድ ይማር፣ ትውልድ ይሰልጥን፣ ከዓለም ጋር ይፎካከር" በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ውጥን በሦስት ዓመት ለማሳካት የታቀደውን ሥልጠና በሁለት ዓመት በማሳካት፣ አሁን ግቡን ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ ማድረግ ተችሏል።
የኮዲንግ እና የሶፍትዌር ልማት መሠረታዊ እውቀቶችን በማስጨበጥ የሰው ኃይል ልማቱን የሚደግፈው ይህ ፕሮግራም፣ የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት የሚያፋጥን የክህሎት መሠረት በመጣል የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዋና ምሰሶ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በአድማሱ አራጋው
#ethiocoders #digitalethiopia #techinnovation #codingskill #youthempowerment

3 months ago
የኑኀሚን መንገድ ...
በ3,000 ብር ድጋፍ ተስፋዋን ያሳየችው ታዳጊ ተማሪ
#ethiopia | የ6ኛ ክፍልን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቀችው እና በቀጣይ ዓመት ወደ 7ኛ ክፍል የምትገባው ታዳጊ ተማሪ ኑኀሚን ግዛው ይርጋ በትንሽ የገንዘብ ድጋፍ ትልቅ ተስፋ እንዳለባት አሳይታለች።
ኑኀሚን አባቷን ከእናትዋ በመለያየቱ ምክንያት ከእናቷ ጋር በተከራይ ቤት የምትኖር ሲሆን፣ እናቷ በቀን ሥራ ተዳዳሪነት ቤተሰቡን ታስተዳድራለች።
ከከባድ የኑሮ ፈተና ጋር እየተጋፈጠችም ቢሆን፣ በወረቀት የሚሰሩ የሪባን አበባዎችን በማዘጋጀት ራሷን ለመቻል ጥረት እያደረገች ነው።
ተማሪዋ 3,000 ብር ድጋፍ ካገኘች በኋላ የሪባን አበባ ሥራ ጀምራ በሽያጭ ላይ በማቅረብ ውጤታማ መሆኗ ተገልጿል። ከሠራቻቸው ሥራዎች መካከል ሁለቱ ወዲያውኑ ተሸጠው ገቢ ማስገኘት ችለዋል።
ኑኀሚን ይህንን የእጅ ሙያ በማስፋፋት ትምህርቷን እየተከታተለች ራሷንና እናቷን ለመደገፍ ትልቅ ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል።
ተገቢ ድጋፍና የሥራ እድል ከተመቻቸላት ወደፊት የተሳካ ፈጣሪ እና ለማኅበረሰብ የምትጠቅም ወጣት መሆን እንደምትችል ይጠበቃል።
በዚህ ዘርፍ ለመተባበር፣ የእጅ ሙያዋን ለማሳደግ ወይም ምርቶቿን ለመግዛት የሚፈልጉ ወገኖች በቀጥታ ከቤተሰቧ ጋር መገናኘት ይችላሉ።
የእናትዋና እና የእርሷ ስልክ
+251-901-237060
+251-963472831
#ጌጡተመስገን #getutemesgen #ethiopia #education #youthempowerment #supportlocaltalent

የኢትዮጵያ B Boy እና B Girl የብሬክ ዳንስ ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተካሄደ
#ethiopia | አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ B Boy እና B Girl የብሬክ ዳንስ ውድድር ሰኔ 13/2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ፊት ለፊት በድምቀት ተካሂዷል።
ውድድሩ “Building Unity and Inclusive Opportunities Through Sport and Dialogue” በሚል መሪ ቃል ለስድስት ወራት እየተተገበረ ባለው ፕሮጀክት ሥር የተሳተፉ 45 የሚደርሱ ታዳጊ ወጣቶች ያቀረቡት የመጨረሻ የብቃት ማሳያ ነበር።
ተሳታፊዎቹ በብሬክ ዳንስ፣ በሕይወት ክህሎት እና በተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለወራት ሲሳተፉ ቆይተዋል።
ፕሮጀክቱ በNutrition for Education and Development (N4ED) አስተባባሪነት፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ የገንዘብ ድጋፍ እና ከሀዊ ዳንስ ኢንተርቴይመንት እና እሺ ሚዲያ ጋር በትብብር የሚተገበር ሲሆን፣ ወጣት ሴቶችን፣ ወጣት ወንዶችን እንዲሁም ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ወጣቶችን በአንድነት በማሳተፍ ተሰጥኦና ብቃትን ለማበረታታት ያለመ ነው።
በዕለቱ ተሳታፊዎች በከተማው ታዋቂ የB Boy እና B Girl ዳኞች ተገምግመው የተመረጡ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎችና ለተሳታፊዎች የተለያዩ ማበረታቻዎች በፕሮጀክቱ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚበረከቱ ተገልጿል።
የፕሮጀክቱ የመዝጊያ ፕሮግራም እና የተሳታፊ ብሬክ ዳንሰኞች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት አርብ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም. በአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴስ በሚካሄደው ዝግጅት ላይ በተጋበዙ እንግዶች ፊት ይከናወናል።
በመጨረሻም አዘጋጆቹ ለዝግጅቱ መሳካት እና ለደማቁ የጎዳና ላይ ትርኢት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ የአድዋ ድል መታሰቢያ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
#breakdance #bboy #bgirl #ethiopia #youthempowerment #n4ed #hawidanceentertainment #adwamemorial #addisababa #streetdanceculture

6 months ago
ባሕር ዳር፦ ወጣት ብሩክ የሠራው አዲሱ መኪና
#የጥበበኛ እጆች ባለቤት የሆነውና በባሕር ዳር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪክ ዘርፍ የተመረቀው ወጣት ብሩክ ወንዲፍራው፣ የማይቻል የሚመስለውን በተግባር አሳይቷል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኢንዱስትሪ ማሽኖችን የሠራው ብሩክ፣ አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች የተሠራች ባለ አራት እግር መኪና ይፋ አድርጓል።
የተሽከርካሪዋ ልዩ መገለጫዎች
ሞተር
ባለ 300 ሲሲ (CC) ሞተር የተገጠመላት።
አቅም
በአንድ ጊዜ 4 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላትና ከባጃጅ የተሻለ ፍጥነት የምትጓዝ።
ክብደት
ከ400 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት አላት።
ወጪ
ለመሥራት ከ350 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጎባታል።
የብሩክ ትልቅ ራዕይ
የብሩክ ህልም መኪና ሠርቶ ማሳየት ብቻ አይደለም። በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በጥራት ማምረት እና ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው። ድጋፍ ካገኘ ደግሞ በቀጣይ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን የማምረት ትልቅ ዕቅድ አለው።
የነገዋ ኢትዮጵያ ከመግዛት ወጥታ ወደ ማምረት የምትገባው በእንዲህ ያሉ ጀግኖች እጅ ነው።
#ቴዎድሮስ ደሴ ( አሚኮ)
#getu #innovationethiopia #bahirdar #techhero #madeinethiopia #engineeringexcellence #youthempowerment #ethiopiadecides #automotiveinnovation #ባሕርዳር #ፈጠራ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋ
የወጣቶችን ህልም የማነቃቃት ታላቅ መርሃ ግብር
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ አሻራ ካኖሩት አንጋፋው አሸናፊ ግርማ እና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዓለም አቀፍ ድልድይ በመሆን ከሚታወቁት ዮሐንስ ዘውዱ (ጆኒ ቪጋስ) ጋር በመሆን ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ተግባር ትናንት በ 35 ሜዳ መስቀል ፍላወር አከባቢ ተከናውኗል።
የዕለቱ መርሃ ግብር ለወጣቶች ቁሳቁስ ከመስጠት ባለፈ፣ በውስጣቸው ያለውን ተስፋ የማደስ፣ ህልማቸውን እንዲያሳድጉ የማነቃቃት እና የወደፊት ሕይወታቸው አሁን ካሉበት ሁኔታ በላይ መሆኑን የማሳሰብ ዓላማ ያለው ነው።
እንደ አሸናፊ ግርማ እና ዮሐንስ ዘውዱ ያሉ መሪዎች ለቀጣዩ ትውልድ አዳዲስ በሮችን በመክፈትና ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ ነው።
ወጣቶችን ማብቃት ማለት ሀገርን ማብቃት ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሩህ ተስፋ የሚጀምረው ዛሬ በእነዚህ ታዳጊዎች ላይ ከሚዘራው እምነትና ድጋፍ ነው።
ወጣቶች ማንኛውም ነገር እንደሚቻል እንዲያምኑ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
#getu #ethiopia #football #youthempowerment #ashenafigirma #johnnyvegas #ethiopianfootball #inspiration #የኢትዮጵያእግርኳስ #ወጣቶች #ተስፋ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
Sponsored by
Surafel
Comments