25 days ago
እንኳን ለዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን አደረሳችሁ፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
የአዲስ አበባ ሴቶች ዛሬ ማልዳችሁ ውቢቷን ቸርችል ጐዳና በመሙላት ለሰጣችሁን ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ዛሬ በዓለም አቀፍ የእናቶች ቀን መላው የከተማችን ሴቶች የተሳተፉበት በ7ኛው ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
ባለፉት 5 ዓመታት በገባነው ቃል መሰረት የሴቶች ተጠቃሚነትንና ቁልፍ ውሣኔ ሰጪነት እንዲረጋገጥ ሰርተን ተሳክቶልናል።
የእናቶችን ጫና ለመቀነስ ልጆቻችሁ ያለምንም ሃሳብ ሁሉም ነገር ተሟልቶላቸው እንዲማሩ ከተማ አስተዳደራችን እጅግ ውጤታማ ስራ ሰርቷል።
በአበበች ጎበና የተሰየመ የእናቶችና የህፃናት ሆስፒታል በመገንባት፣ የነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ልህቀት ማዕከል በመገንባት፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ለሴቶች በመገንባት፣ በአጠቃላይ ባለፉት 5 ዓመታት ከፈጠርነው 2 ሚሊዮን የሥራ ዕድል 51 በመቶው ሴቶች እንዲሆኑ በመስራት፣ የሴቶችን አይተኬ ሚና እና ክብር የሚወክል አደባባይ በመገንባት እና የመሳሰሉ የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ክብር ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ፍሬ አፍርቷል።
አሁንም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን ካቀረብናቸው እጩዎች 54 በመቶ ሴቶች ናቸው። በከተማችን ምክር ቤት ከ40 በመቶ በላይ ሴቶች በመሆናቸው ከዚህ በፊት የነበረውን ተሳትፎ በበለጠ አልቀነዋል። ይህ ደግሞ ለአጃቢነት ሳይሆን የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን በማመን ነው ።
በ7ኛው ምርጫ ብልፅግናን ስትመርጡ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ታስቀጥላላችሁ፤ ሰላማችንም ዘላቂ ሆኖ ይረጋገጣል።
የምርጫ ምልክታችን የሥንዴ ነዶ ነው። ልክ እንደ ነዶው ተደምረን፤ ማንንም ያልተወ፣ ማንንም ያልዘነጋ አካታች ልማትን እያረጋገጥን እንቀጥላለን።
ባለፉት 5 ዓመታት የከተማችንን ሠላም በማረጋገጥ፣ ልማትን በማረጋገጥ አብራችሁን ስለነበራችሁ አዲስ አበባ ከልብ ታመስግናችኋለች።
መንገዳችን መደመር፤ መደረሻችን ብልፅግና ነው!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !
#addisababa #womenempowerment #prosperityparty #adanechabiebie #ethiopia

2 months ago
''እንደ ወይን በክብር መብሰል''
📌 የሴቶችን ተፈጥሯዊ የህይወት ጉዞ የሚያከብር ልዩ መድረክ ተካሄደ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ሴቶች ዕድሜ መጨመር፣ ውበት እና ማህበራዊ ዋጋ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር ያለመ “እንደ ወይን በክብር መብሰል” የተሰኘ ልዩ ውይይት ተከናወነ።
በታዋቂዋ ጋዜጠኛ የሸዋ ማስረሻ መሥራችነት በሚመራው ኢምፓክት መልቲ ሚዲያ አዘጋጅነት የቀረበው ይህ ዝግጅት፤ ዕድሜ መጨመርን እንደ ፀጋ በመቁጠር ሴቶች በህይወት ጉዟቸው እንዲኮሩና እንዲነቃቁ ለማድረግ ያለመ ነው። በመርሀ ግብሩ ላይ ከ100 በላይ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች እና ወንዶች ተሳትፈዋል።
በመርሃግብሩ ላይ ስለ ሴቶች ዕድሜ መጨመር የሚነገሩ አሉታዊ ትርክቶችን በማስቀረት፣ ሽግግሩን በክብርና በኩራት የመቀበል ባህልን ማሳደግ ፣ ሴቶች በዕድሜ መጨመር ሂደት ውስጥ የሚያልፉባቸውን አካላዊ፣ ስሜታዊ እና ማህበራዊ ለውጦች (ለምሳሌ፦ የወር አበባ መቆም ወይም Menopause) በተመለከተ ትምህርት መስጠት ላይ ያተኮረ ሲሆን ስኬታማና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የህይወት ታሪካቸውንና የጥበብ ጉዟቸውን በማጋራት ለተሳታፊዎች ተነሳሽነትን መፍጠር ተችላል።
በትውልዶች መካከል መከባበር፣ መረዳዳት እና መደጋገፍ እንዲኖር የሚያስችሉ ውይይቶችን ማካሄድ።
ይህ መድረክ በኢትዮጵያ ስለ ውበት እና ስለ ስብዕና ያለውን ትርጉም በአዲስ መልክ የሚጽፍ ሲሆን፣ በአሳታፊ ታሪኮች እና በዲጂታል ይዘቶች የታጀበ በመሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያሳርፋል ተብሎ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#agingwithgrace #celebrateher #womenempowerment #impactmultimedia #positiveaging #menopauseawareness #breakingstereotypes #wiseandbeautiful #timelessbeauty

"ታላቋ ሴት"
በውቢቷ ሀዋሳ የደመቀው የሴቶች የክብር ምሽት!
#ethiopia | ሄራ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን በወ/ት እውነት ይሻል አዘጋጅነት፣ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሳውዝ እስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ማዕከል ያደረገ ደማቅ የሽልማትና የክብር ፕሮግራም አካሂዷል።
ሀዋሳን ያቀኑ 15 አንጋፋ ባለሀብትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች የተሸለሙ ሲሆን፣ 10 ተስፋ የተጣለባቸው ወጣት ሴቶች ደግሞ ለቀጣይ ዓመት ትልቅ ኃላፊነት ተረክበዋል።
አንጋፋዋ ዲዛይነር ወ/ሮ አበባ ዘነበ ተሰማ (የአበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ባለቤት) የሲዳማን ባህላዊ ይዘት የጠበቁ ዘመናዊ አልባሳትን በአፍሮ እና አንቅ ሞዴሎች አማካኝነት ለታዳሚው አስነኝተዋል።
የሆሊ ቤቴል ልዩ የጥርስ ሕክምና ባለቤት ወ/ሮ መስከረም አበራ ካለፉበት ከባድ ውጣ ውረድ እስከ ዛሬው ስኬታማ ደረጃ ያደረሳቸውን የጥንካሬ ጉዞ በእንባ በተሞላ ስሜት ለታዳሚው አካፍለዋል።
የ3 ዶክተሮች እናትና ስኬታማዋ የቢዝነስ ሴት ወ/ሮ አያልነሽ አለሶ እንዲሁም በኢኮኖሚና በበጎ ተግባር ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ወ/ሮ ይርጋለም አሰፋ በልዩ ተሸላሚነት ደምቀው የታዩበት ምሽት ነበር።
የአዘጋጇ መልዕክት
የሄራ ኢቨንት እና ፕሮሞሽን መስራች ወ/ት እውነት ይሻል ዝግጅቱ በየዓመቱ በሴቶች ቀን የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው፣ ለፕሮግራሙ መሳካት አብረዋቸው የቆሙትን ደጋፊ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በሙሉ ከልብ አመስግነዋል።
🙏 ልዩ ምስጋና
ሳውዝ እስታር ሆቴል፣ የደቡብ ቴሌቪዥን፣ ንጉስ ቢራ፣ ቤዛ ስፕሪንግ ዋተር፣ አበባ ሹራብ፣ የሀዋሳ ከንቲባ ጽ/ቤት እና ለሄራ ኢቨንት ቡድን አባላት፣ አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፣ አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ
#thegreatwomen #hawassa #ethiopia #heraevents #womenempowerment #successstories #fashionshow #southstarhotel #sidamaculture #inspiration #getutemesgenmedia

ሩጫ ለጤና
የክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጉብኝት
#ethiopia | ነገ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ አስመልክቶ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጎብኝተዋል።
ዓላማ፦ "AKTIVE AGAINST CANCER" የተሰኘው ንቅናቄ በሩጫ ውድድሩ አማካኝነት ሴቶች የካንሰር ህመምን ቀድሞ ለመከላከልና ጤናቸውን ለመጠበቅ እንዲተጉ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ዶክተር ኤርጎጌ እንዲህ ያሉ ትብብሮች ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ትርጉም እንዳላቸው ገልጸው፣ ቅድሚያ ለሴቶች ሩጫ ሴቶችን የሚያበረታታ መድረክ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ካንሰርን ለመከላከልና ለማገገም ያለውን ጠቀሜታ ለማስተዋወቅ ከአክቲቭ አጌንስት ካንሰር ጋር ለአራት ዓመታት የሚቆይ ስምምነት መፈራረሙ ተገልጿል።
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለካንሰር ማዕከሉ ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ቀርቦለታል።
ለ23ኛ ጊዜ የሚከናወነው የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ፣ ነገ መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
ሩጫው ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ ለጤናና ለግንዛቤ ያለውን ፋይዳ ለመጋራት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#getu #ethiopia #womenempowerment #cancerawareness #safaricom #greatethiopianrun #health #addisababa #ቅድሚያለሴቶች #ካንሰርንእንከላከል #ታላቁሩጫ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago
በፖለቲካው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ አየጨመረ ነው ተባለ
#ethiopia | ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) አስመልክቶ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሀገሪቱ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራትን ይፋ አድርጓል።
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመግለጫቸው እንደተናገሩት፣ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት ድርሻ 28 በመቶ መድረስ ተችሏል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ 60 በመቶ ያህሉ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ መደረጉን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በፖለቲካው ዘርፍም የሴቶች ተሳትፎ አበረታች ደረጃ ላይ መድረሱን የጠቆሙት ዶ/ር ኤርጎጌ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች የውክልና ድርሻ 41 በመቶ መድረሱን በዋቢነት ጠቅሰዋል።
ዘንድሮ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ በዓል፣ ከ1950ዎቹ ጀምሮ የነበረውን የታሪካዊ ጉዞና የሴቶች ተሳትፎ ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚገመግም እንደሚሆን ታውቋል።
በተለይም፦
* የሴቶችን የልማት ትልም ያመጣው ለውጥ፤
* የሴቶች የመደራጀት እንቅስቃሴ ውጤታማነት፤
* እና በሁሉም ዘርፍ የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶች በስፋት የሚዳሰሱበት መድረክ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።
በተጨማሪም ሚኒስቴሩ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና
ከተፈጸሙም በኋላ ተጎጂዎች የሚያገግሙባቸውን ማዕከላት የማስፋፋት ሥራ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ከዚሁ ጎን ለጎንም የሕግ አካሄዶችን ተከትሎ ጥቃት አድራሾችን ተጠያቂ የማድረግና የሴቶችን ደህንነት የማስጠበቅ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #የሴቶችቀን #ማርች8 #የሴቶችመብት #ልማት #landrights #womenempowerment #ethiopia

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ዳሸን ባንክ ሴት ሰራተኞቹን የማብቃት መርሃ-ግብር አካሄደ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ የሴት ሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበትና ወደ ከፍተኛ አመራርነት ለማምጣት የጀመረው "አጠቃላይ የሴቶች አቅም ማጎልበት መርሃ-ግብር" አንደኛ ዓመት የምክክር መድረክ በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሂዷል።
✅ የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በመርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት ባንኩ ላለፉት 30 ዓመታት ሴቶችን ወደ አመራር በማምጣት ተጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ አሁንም ሴቶች ለባንኩ እድገት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አረጋግጠዋል።
✅ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከ140 በላይ ሴት ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ዕድል አግኝተዋል።
✅ በአንድ አመት ውስጥ አራት የትስስር የውይይት መድረኮች የተካሄደ ሲሆን በእያንዳንዱ የውይይት መድረኮች ላይ ከ200 በላይ ታዳሚዎች ተሳትፈዋል።
✅ ዳሽን ባንክ 11 ሺህ በላይ ቋሚ ሰራተኞች መካከል ከ3,300 በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
✅ በመድረኩ ላይ ኘሮፌሰር የዓለምፀሐይ መኮንን፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ተገኝተው ለተሳታፊዎች የህይወትና የሥራ ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
ይህ መርሃ-ግብር የሴቶችን የአመራር ክህሎት በማሳደግ የባንኩን ስኬት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
📷 ከበደ መክብብ #dashenbank #womenempowerment #leadership #ethiopia #banking #genderequality

5 months ago
🎁 የበዓል ስጦታ ለ608 ህጻናት! 👗👕
"ግዮን ፋሽን፡ በ95% ሴቶች የሚመራው ሀገር በቀል ተቋም በጎ ተግባር!"
#ethiopia | ለጥምቀት በዓል ስጦታ ይሆን ዘንድ፤ በልጆች አልባሳት ምርት ላይ የተሰማራው ሀገር በቀል ድርጅት ግዮን ፋሽን (Ghion Fashion)፤ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የ608 ህጻናት አዳዲስ አልባሳትን በድጋፍ አበርክቷል።
ስለ ድጋፉ እና ተቋሙ:
ዛሬ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገው የድጋፍ መርሐግብር ላይ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል ሲሳይ እንደገለጹት፤ እነዚህ አልባሳት በተለይ ለሙዳይ ልጆች ታስበው በፋብሪካው የተመረቱ ናቸው።
ግዮን ፋሽን ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 95 ከመቶው ሴቶች መሆናቸው ተቋሙን ልዩ ያደርገዋል!
ወ/ሮ ሙዳይ ምን አሉ?
የማህበሩ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፤ "ግዮን ፋሽኖች እዚሁ ተገኝተው፣ ልጆቻችንን ጎብኝተውና በልዩ ሁኔታ ልብስ አምርተው ስላመጡልን እናመሰግናለን" ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
እንዲህ ያሉ ሀገር በቀል እና ለወገን የሚደርሱ ተቋማት ይብዙልን!
መልካም በዓል! 🇪🇹🌼
#ghionfashion #mudaycharity #donation #timket #madeinethiopia #womenempowerment #charity #muday #charity #ethiopia

🏆 10 ኢትዮጵያውያን "ዕንቁ ሴቶች" ተሸለሙ
#ethiopia | ለትውልድ እና ለሀገር ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ 10 ተምሳሌት ሴቶች፤ "ዕንቁ ሴት - ንቁ ሴት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ መርሐ ግብር በሳፋየር አዲስ ሆቴል ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዝግጅቱ ላይ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፤ "ሴቶችን ከፍ አድርጎ ስማቸውን ለመጥራት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የዘንድሮው ተሸላሚዎች እነማን ናቸው?
ዶ/ር ትዕግስት ግርማ (በጤና ዘርፍ)
ወ/ሮ አበበች አፈወርቅ (የህይወት ዘመን ተሸላሚ)
ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ (በበጎ አድራጎት)
ጋዜጠኛ በሻቱ ቶለማርያም (በሚዲያ እና ጋዜጠኝነት)
አርቲስት መሠረት መብራቴ (በኪነ-ጥበብ)
ዲዛይነር ሔዋን ቀለመ ወርቅ (በሥራ ፈጠራ)
ወ/ሪት ሳምራዊት መሐመድ (በወጣት ባለራዕይ)
ዶ/ር ሐመልማል መንግሥቱ
ወ/ሮ ገነት ገ/ሥላሴ (ከልመና ወደ ሽመና)
ልዕልት አንድሮሜዳ
እንኳን ደስ አላችሁ! 👏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#enkusetoch #womenempowerment #ethiopia #award #inspiration #strongwomen