15 days ago
ፊፋ በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ የግጥሚያ ማስተካከል አልተፈጸመም ሲል አስታወቀ
#ethiopia | የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት የግጥሚያ ማስተካከል (Match-fixing) ተፈጽሟል የሚሉ ወሬዎችን በድጋሚ በማስተባበል፣ በውድድሩ ሙሉ ጊዜ ከውርርድ ወይም ከግጥሚያ ማጭበርበር ጋር የተያያዘ ማንኛውም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ አልተገኘም ብሏል።
ፊፋ እንደገለጸው፣ በውድድሩ 104 ጨዋታዎች በሙሉ የስፖርት ታማኝነትን የሚከታተል ልዩ ቡድን ከዓለም አቀፍ የውርርድ ቁጥጥር ተቋማት ጋር በመተባበር ቁጥጥር ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉም የግጥሚያ ውጤት መቀየር ወይም ሕገ-ወጥ የውርርድ እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ አልተገኘም ብሏል።
ይህ መግለጫ የወጣው በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ በተፈጠሩ የዳኝነት ውሳኔዎችና የVAR አጠቃቀም ዙሪያ የተነሱ ክርክሮች ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተስፋፉ የ“ውድድሩ ተስተካክሏል” የሚሉ ውንጀላዎችን ተከትሎ ነው።
ቀደም ሲልም የፊፋ የዳኝነት ኃላፊ ፒየርሉጂ ኮሊና የዳኞችን ታማኝነት የሚጠራጠሩ ያልተደገፉ ክሶች በስፖርቱ ውስጥ ቦታ የላቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

23 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመጪው እሁድ በሚደረገው የ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ ለሁለተኛው አጋማሽ እስኪመለሱ የሚኖረው የእረፍት ሰዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ ከ20 እስከ 25 ደቂቃ ሊረዝም እንደሚችል ተጠቆመ።
ይህ ሊሆን የቻለው በኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ስታዲየም በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ እረፍት ወቅት፣ ልክ እንደ አሜሪካው 'ሱፐር ቦውል' አይነት የ11 ደቂቃ ግዙፍ የሙዚቃ ትዕይንት ለማቅረብ በመታቀዱ ነው።
በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ቦርድ የጨዋታ ህግ መሰረት፣ ተጫዋቾች የሚያገኙት የእረፍት ሰዓት "ከ15 ደቂቃ መብለጥ የለበትም" የሚል ደንብ አለ። ይሁን እንጂ የዓለም እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ (FIFA) ውስጥ ያሉ ምንጮች እንደገለጹት፣ በእሁዱ ጨዋታ የእረፍቱ ጊዜ 20 ደቂቃ አካባቢ ይሆናል። አሁን ላይ ባለው አንዱ አማራጭ መደበኛውን የ15 ደቂቃ እረፍት ሰጥቶ፣ የታቀደውን የ11 ደቂቃ የሙዚቃ ትዕይንት ማካሄድ ነው።
ፊፋ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥመው ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ባለፈው ዓመት በኒው ጀርሲ በተካሄደው የዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ኮልድፕሌይ፣ ጄ ባልቪን፣ ዶጃ ካት፣ ቴምስ እና ኢማኑኤል ኬሊ ያቀረቡትን ትዕይንት ተከትሎ፣ የእረፍት ሰዓቱ በአጠቃላይ 24 ደቂቃ መፍጀቱ ይታወሳል።
ለእሁዱ ትልቅ የፍጻሜ ጨዋታ እረፍት በሚቀርበው ዝግጅት ላይ ታዋቂዎቹ ድምጻውያን ማዶና፣ ሻኪራ እና የኮሪያው ታዋቂ የሙዚቃ ቡድን ቢቲኤስ በዋና አቅራቢነት የሚሳተፉ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ጃስቲን ቢበርም በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፍ ተጋብዟል።
በተጨማሪም በርና ቦይ፣ ጉስታቮ ዱዳሜል እና የፒኤስ22 ቾረስ ከኮልድፕሌይ ጋር በመሆን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። አጠቃላይ ዝግጅቱን ያቀናበረው ደግሞ የኮልድፕሌይ ድምጻዊ ክሪስ ማርቲን ነው።
የዓለም ዋንጫው የፍጻሜ ጨዋታ በአካባቢው አቆጣጠር ከቀኑ 9:00 ሰዓት (በለንደን አቆጣጠር 8:00 ምሽት) ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድሞ ከቀኑ 7:30 ሰዓት (በለንደን 6:30 ምሽት) ጀምሮ ደማቅ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።
በዚህ ታላቅ የመዝጊያ መርሃ-ግብር ላይ ተዋናይ ቶም ክሩዝ፣ ላውራ ፓውሲኒ፣ ኒኮል ሸርዚንገር፣ ሮቢ ዊሊያምስ እና ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ የሚሳተፉ ሲሆን፣ የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር ደግሞ ጄኒፈር ሁድሰን እንደምትዘምረው ታውቋል።
ስፔን ዛሬ በዳላስ በተደረገው የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜው ማለፏን ያረጋገጠች ሲሆን፤ ረ ነገ በአትላንታ ከሚገናኙት እንግሊዝ ወይም አርጀንቲና መካከል አሸናፊውን በእሁዱ ታላቅ ፍጻሜ የምትገጥም ይሆናል።

30 days ago
"ጨዋታው ተጭበርብሯል፤ ዓለም ሁሉ አይቶታል!"
— አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን
* የግብፅ–አርጀንቲና ጨዋታ በዳኝነት ውሳኔዎች መነጋገሪያ ሆነ
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የ16 ዙር ማጣሪያ አርጀንቲና ግብፅን 3 ለ 2 በሆነ አስደናቂ ውጤት አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ ብታልፍም፣ ከውጤቱ በላይ በሜዳ ላይ የታዩት የዳኝነት ውሳኔዎችና ውዝግቦች የዓለም ስፖርት ሚዲያዎችን እያናወጡ ይገኛሉ።
ከ2 ጎል መሪነት እስከ መጨረሻው ደቂቃ "ንፁህ ቀውስ" (Pure Chaos)
ግብፅ በመጀመሪያው ክፍለ ጨዋታ "እንደ ፒራሚድ ፀንታ" ድንቅ የመከላከል ብቃት በማሳየት አርጀንቲናን በከባድ ሁኔታ ፈትና ነበር። ሆኖም አርጀንቲና ከሁለት ጎሎች መመራት በኋላ ተስፋ ሳትቆርጥ ባሳየችው አስደናቂ የመመለስ ብቃት ጨዋታውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል በነበረው ከፍተኛ ውጥረት ዳኛው በስምንት ደቂቃ ውስጥ ብቻ 5 የቢጫ ካርዶችን ለመምዘዝ ተገዷል።
"ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው፤ ሜሲ እንዲቆይ ይፈልጋሉ!" — የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ቁጣ
ከጨዋታው በኋላ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን በሰጡት እጅግ ቅሬታ የተሞላበትና ያልተጠበቀ መግለጫ ፊፋንና የዳኝነት ቡድኑን በኃይለኛ ቃላት ወርፈዋል፦
*ስለ ቪአይአር (VAR) ውሳኔዎች፦
"በመሐመድ ሳላህ ላይ የተሰራው ጥፋት (የፍጹም ቅጣት ምት) በVAR ሳይታይ ቀርቷል፤
ሁለተኛው ጎላችንም ባልታወቀ ምክንያት ተሰርዟል።
ማክ አሊስተር ማሊያ ሲጎትት እያየን VAR አልተፈተሸም።"
ስለ ፈረንሳዩ ዳኛ ምደባ፦
"አርጀንቲና በ2022 ፈረንሳይን ማሸነፏን ተከትሎ በነበረው ሁኔታ የዚህን ፈረንሳዊ ዳኛ መመደብ ቀድመን ተቃውመን ነበር።"
"እውነቱን ለመናገር ጨዋታው በግልጽ የተጭበረበረ ነበር። ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው። ሊዮኔል ሜሲ በውድድሩ ውስጥ እንዲቆይ ይፈልጋሉ። አርጀንቲና እንድታሸንፍ ይህን ያህል የሚፈልጉ ከሆነ ሌላውን ቡድን ለምን ለውድድር ይጠሩታል?"
የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ውሳኔ፦
"ከደረሰብን ኢፍትሃዊነት የተነሳ ከእንግዲህ አንድም ደቂቃ የዚህን ዓለም ዋንጫ ጨዋታ አልመለከትም!"
የእግር ኳስ ተንታኞች፦
የግብፅን አስደናቂ ተጋድሎና የአርጀንቲናን እስከ መጨረሻው የመታገል መንፈስ እያደነቁ ቢሆንም፣ የዳኝነት ውሳኔዎቹ ግን ጨዋታውን መበላሸታቸውን ይስማማሉ።
የፊፋ (FIFA) ምላሽ፦
እስካሁን ድረስ ፊፋ በአሰልጣኙ ክስ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም፤ ክሶቹም በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
የአፍሪካ እግር ኳስ አፍቃሪያን!
በግብፅ ላይ የተፈጸመው የዳኝነት ውሳኔ ትክክል ነበር ወይስ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እንዳሉት አድልዎ ተፈጥሯል?
**ሀሳባችሁን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን!
አለባቸው ደሳለኝ ከለንደን 🇬🇧
**#fifaworldcup #egypt #argentina #hossamhassan #mohamedsalah #messi #africa #footballnews **

1 month ago
🇸🇳 ሴኔጋል ኢራቅን 5-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋውን አጠናከረ!
#fifa | ሴኔጋል በተደረገው ጨዋታ ኢራቅን 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ በምድቡ ውስጥ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አጠናክሯል።
የሴኔጋልን የድል ጎሎች ሃማዱ ዲያራ (4')፣ ኢብራሂማ ሳር (56')፣ ፓፕ ጉዬ (59' እና 71') እንዲሁም ኢላይማን ንዲያዬ (82') አስቆጥረዋል።
ኢራቅ ደግሞ በ13ኛው ደቂቃ ተከላካዩ ረዋንድ ሱላካ ቀይ ካርድ በማየቱ ከጨዋታው ተሰናብቶ ቀሪውን ጊዜ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገዷል።
ይህ ድል ለሴኔጋል በምድቡ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋውን በእጅጉ አሳድጎታል።

Sponsored by
Surafel
2 months ago
♦️1:45 ደቂቃ በቶሮንቶ ሠማይ ስር
♦️FIFA እና Destination Toronto በጋራ የሠጡኝ ወርቃማ የጉብኝት ዕድል(ክፍል አንድ)
♦️ቶሮንቶን ከሜዳ ውጪ(Off the Pitch)
የ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ ወደ ሌላ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮኛል FIFA እና Destination Toronto ለአለም ዋንጫ ዘገባ ከመጡ ኢንተርናሽናል ጋዜጠኞች ዛሬ የጉብኝት ዕድል ሠጥተውናል፤እኔም ይሄን ዕድል ካገኙት ጋዜጠኞች ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሆኜ ቶሮንቶን ከእግር እስከራሷ የማየት ዕድል አግኝቻለሁ ከ1:45 ደቂቃ በላይ በዘለቀው የጉብኝት መርሃ ግብር የማውቃት የሚመስለኝ ነገር እንደማላውቃት የተረዳሁበትን አስገራሚ ጉብኝት አድርጌ በግርምት እጄን አፌ ላይ ጭኜ ተመልሻለሁ።ታሪክን፣ጥንታዊነትንና ዘመናዊነትን በውስጧ ሸሽጋ የያዘችው የኢኮኖሚ፣የቢዝነስ ከተማና ከ170+ አገሮች የመጡ ሰዎች የሚኖሩባት ባህላዊውን ከዘመናዊነት ጋር አጣምራ የያዘች ተወዳጅ ከተማ ናት።
በአንድ ጎዳና ላይ እየተራመዱ ብዙ ቋንቋዎችን ከሠሙ በትክክልም እርስዎ ያሉት ቶሮንቶ ነው፤ምክንያቱ ደግሞ ከ170 በላይ ሀገሮች የሚኖሩባት ብቻ ሳይሆን የተለየ ቋንቋ የሚነገርባት ዓለምን በአንድ ቦታ ሠብስባ የያዘች ከተማ ናትና።
በምሽት የካናዳ ምልክት ተደርጎ ከሚወሠደው፣ቶሮንቶን ልዩ ውበትና ድምቀት የሚያላብሳት CN Tower በሚፈልቀው ብርሃን፣በLake Ontario የባህር ዳርቻ ከወዳጅ ወይም ከፍቅረኛ ጋር የፍቅር ማር የሚቆረጥባት ከአለማችን ለኑሮ ምቹና ሠላማዊ ተብለው ከሚጠሩ ሀገሮች አንዷ፣ በዓመት ከ25–30 ሚሊዮን፣በበጋ ወቅት ደግሞ ከ150,000 በላይ ቱሪስቶች በቀን የምትጎበኘው የቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ቶሮንቶን በToronto Double-Decker አውቶብስ አናት ላይ ተቀምጬ ታዘብኩትን የዛሬ የ1:45 ደቂቃ ጉብኝቴን በወፍ በረር ላስቃኛችሁ።
የተሳፈርንበትን Double-Decke Bus የሚዘውረው የህይወቱን ግማሽ ክፍል ለካናዳ የገበረው አቶ ፍቅሩ ብርሃኔ መሆኑ በጉብኝቴ የቤተሠብነት ስሜት እንዲሠማኝ ያደረገ ሲሆን በጣፍጭ አንደበቱ ታሪካዊ ቦታዎች የፍትፍት ያህል ፈትፍቶ ሲያጎርሠን የነበረውን አስጎብኚያችንን MASHAALን ከልብ ላመሠግነው ወደድኩ፤በቅድሚያ የጉብኝታችን መነሻ ስለነበረው
♦️University of Toronto
ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶሮንቶ ዕድሜ ጠገብ ነው፤የኛውን የቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የአሁኑን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ123 ዓመት ዬበልጠዋል፤የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ76 ዓመት አዛውንት ሲሆን ዕድሜ ጠገቡ University of Toronto ደግሞ የ199 ዓመት አረጋዊ ነው፤እንደ አስጎብኚያችን MASHAALከ102 በላይ ተማሪዎችን እቅፍ ድግፍ አድርጎ በውስጡ ይዟል፤ዩኒቨርስቲውን ከአለማችን የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ከ175 የዓለማችን ሀገሮች የመጡ ተማሪዎች መዳረሻ ብቻ ሳይሆን በባችለር፣በማስተርስና በፒኤችዲ ፕሮግራሞች በመታቀፍ ከህልማቸው የሚገናኙበት ትልቁ የዕውቀት ፋብሪካም ነው፤
በሚመደብለት ከ3.62 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በካናዳ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ቀዳሚ የሆነው University of Toronto ካሉት ከ16ሺ የበለጡ ስታፎች ከ9ሺ በላዩ አስተዳደሩን የሚዘውሩ አመራሮች መሆናቸው ቶሮንቶን ያለ አዋዜ አጣጥሞ እንደበላት በቃሉ የሚሠጠው መረጃ ከሚያሳብቅበት አስጎብኚያችን MASHAAL መረዳትም ተችሏል።
ከዓለማችን ምርጥ 30 ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት University of Toronto የአለምን በዕውቀታቸው እንዳሻቸው ከሚዘውሩ በዕውቀቱ የታጠቁ ሙሁራንን ከማፍራቱ በተጨማሪ የካናዳን ኢኮኖሚ በፍይናንስ ከሚያግዙ ተቋማት መካከልም አንዱ ነው፤በዚህም መሠረት ከ15 ቢሊየን የካናዳ ዶላር በላይ ወደ ካናዳ ፈሰስ መመድረጉ ይሄ ገቢዎች ነው?ወይስ ኢትዮ ቴሌኮም የሚል ጥያቄ ማስመዘዙ አልቀረም"
♦️TTC የቶሮንቶ ከተማ የልብ ምት
Toronto Transit Cooperation በምህፃረ ቃል TTC የደም ስር ወይም የከተማዋ የልብ ምት ቢባል ቃሉ አልተጋነነም፤በተለይም ለToronto እና አካባቢው ያበረከተው ጥቅም ከመጓጓዣነትም በላይ የሕይወት አገልግሎት ነው። ከተማዋን የሚያንቀሳቅስ ደም መስመር ተደርጎም ይቆጠራል፤TTC የከተማው የደም ሥር ነው።በቀላል አማርኛ
እንደ ደም ሥሮች ደምን ወደ ሰውነት ክፍሎች እንደሚያደርሱ ሁሉ TTC ሰዎችን ወደ ሥራ፣ ወደ ትምህርት ቤት፣ ወደ ሆስፒታል፣ ወደ ገበያ እና ወደ መዝናኛ ቦታዎች በየቀኑ በማመላለስ ህይወት በቶሮንቶ የቀለለ እንዲሆን እንዳደረገ በጉብኝታችን ወቅት ተረድተናል።
በቅርቡ የወጣ ጥናት እንደሌለ ነገር ግን የ2025ትን ጥናት መነሻ አድርጎ እንደ ነገረን አስጎብኚያችን MASHAAL መረጃ ከሆነነ የቶሮንቶን ከተማ ከጫፍ ጫፍ ለማገናኘት ማልደው የሚሠማሩት የTTC በእኛ ሀገር አጠራር የካናዳ አንበሳ አውቶቢስ አገልግሎት ከ2000 በላይ ቀይና ነጭ አውቶቢሶችን 250 የሚጠጉ ነኤሌክትሪክ፣ከ200 በላይ ረዣዥም ባሶችን ቶሮንቶ ትጠቀማለች።
የTTC የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ባይካድም ትራፊክን ይቀንሳል፣መኪና መግዛት፣ ነዳጅ መሙላት እና ፓርኪንግ መክፈል ከሚጠይቀው ወጪ ይልቅ ብዙ ጊዜ ይቀላል፤ሰዎች በቀላሉ ወደ ሥራ እና ወደ ንግድ ማዕከላት እንዲደርሱም ከማገዙም በላይ ለሁሉም ተደራሽ በመሆን በኩል መኪና የሌላቸው፣ ተማሪዎች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ከተማው እንዳያገላቸው ይልቅ እንዲጠቀሙበት ትልቅ ዕድል ይሠጣል።ይህ ነፃና የተመቻቸ የትራንስፖርት ፍሠት ያለ TTC የባቡር አገልግሎት የተሳለጠ ይሆን ነበር ብሎ ለስህተት ይዳርጋል።ምክንያቱም የTTC ባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት በዓመት ወደ ከ180 ሚሊዮን በላይ በቀን ደግሞ በየቀኑ ከ 690,000 በላይ ወይም 1ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ከአንደኛው የከተማው ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በማመላለስ የቶሮንቶ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጉብኝቴ አሳይቶኛል።
♦️በቶሮንቶ ከ110 ካሬ ኪ.ሜ. በላይ የሚሸፍን የተፈጥሮ ሸለቆዎች ያለባት ከተማ
አብዛኛው ሠው ስለ ቶሮንቶ ሲያስብ ከፊቱ ቀድሞ የሚመጣበት ወይም የካናዳና የቶሮንቶ መለያ አድርጎ የሚወስደው CN Tower ን ነው፤ከትናንቱ የሚዲያ ጉብኝቴ የተረዳሁት ትልቁ ቁምነገር ግን ቶሮንቶን ከሌሎች ትልልቅ ከተሞች የሚለየው የRavine System (የተፈጥሮ ሸለቆዎች አውታረ መረብ) ያለበት ከተማ መሆኑ ነው እላለሁ።ከላይ ለማነሳት እንደሞከርኩት ብዙ ሰዎች ስለቶሮንቶ ሲያስቡ የመጀመሪያው የሚያስታውሱት CN Tower ን ነው፣ ነገር ግን የቶሮንቶ እውነተኛ ልዩነት በከተማው መሃል ውስጥ የሚያልፉ የተፈጥሮ ሸለቆዎች መኖራቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን?በሚገርማችሁ ሁኔታ በከተማው ውስጥ በአጠቃላይ 110 ካሬ ኪ.ሜ. የሚሸፍን የሸለቆ ስርዓት አለ፤
ይህ ደግሞ የከተማውን 17% በላይ እንደሚሸፍን የአስጎብኚያችን መረጃ ይጠቁማል፤በዓለም ላይ ቀከተማ ውስጥ ካሉ የሸለቆ ስርዓቶች ትልቁ በመሆንም ቶሮንቶን ከፊት ያስቀምጣታል።ስለዚህ በቶሮንቶ አንድ ሰው በዳውንታውን ውስጥ ያሉ ቁመተ መለሎ ሠማይ ጠቀስ ፎቆች መካከል ሲሆን ከ10 ደቂቃ በኋላ በዱር ውስጥ እንዳለ ሊሰማው ቢችል አይፈረድበትም፤ይሄንን የታዘቡ ደግሞ ቶሮንቶን “city within a park” (በፓርክ ውስጥ ያለች ከተማ) ብለው እስከመግለፅ የተገደዱት።
ቶሮንቶ ሰማይን የሚነኩ ሕንፃዎችና የተፈጥሮ ዱር በአንድ ቦታ የሚገናኙባት ከተማ መሆኗ በእርግጥም የተለየች ከተማ የሚል ስያሜ እንዲሠጣት ያስገድዳል።።
የክፍል አንድ የወፍ በረር ጉብኝቴ ይሄንን ይመስላል፤በክፍል ሁለት ትዝብቴ ቀ1:45 ደቂቃ በፈጀው ጉብኝቴ የካናዳዊያን ምልክት ተደርጎ ስለሚወሠደው CN Tower፣ስለ ሮያል ኦንታሪዮ ሙዚየም፣ቶሮንቶንስላጥለቀለቁት ላይብረሪዎች፣የፍቅር ማር ስለሚቆረጥባትና የመዝናኛ ዋነኛ የልብ ምት ስለሆነችው Lake Ontario እና በካናዳ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የጉብኝት ባሳችንን Double-Decke ከሚዘውረው ኢትዮጵያዊ ህይወትና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የቃረምኩትን አካፍላችኋለሁ፤FIFA እና Destination Toronto በጋራ ይሄን ዕድል ስለሠጡኝ ከልብ አመሠግናለሁ🙏🙏...(ይቀጥላል)....
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከከናዳ ቶሮንቶ

ከአዲስ አበባ የምታንሰው ሀገር ''ኩራሳኦ'' በዓለም ዋንጫ
#ethiopia | የኩራሳኦ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጊልበርት ማርቲና፣ ሀገራቸው በሕዝብ ቁጥር አነስተኛ ሆና ለፊፋ የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup) ማለፍ የቻለች በመሆኗ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
በአጠቃላይ 156,115 የሕዝብ ቁጥር ብቻ ያላት ደሴቷ ኩራሳኦ፣ ይህንን ታሪካዊ ስኬት በማስመዝገብ በዓለም ዋንጫ ታሪክ በሕዝብ ብዛት አነስተኛዋ ሀገር መሆን ችላለች።
የምስክር ወረቀቱን ለፕሬዚዳንቱ ባስረከቡበት ወቅትም ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው የሽልማቱ አዘጋጆች ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ግብፅ በማሊያዋ ላይ ያሉትን ኮከቦች እንድታነሳ ታዘዘች
#ethiopia | የዓለም እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ያዘጋጀውን ማሊያ ተጠቅሞ መጫወት እንደማይችል በመግለጽ አስቸኳይ እገዳ ጥሏል።
ቡድኑ ከቤልጂየም ጋር ከሚያደርገው የመክፈቻ ጨዋታ በፊት በማሊያው ደረት ላይ ያረፉትን ኮከቦች እንዲያነሳና በተጫዋቾች ስም እንዲሁም ቁጥር ላይ የተጠቀመውን የወርቅ ቀለም እንዲቀይር ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ፊፋ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የዓለም ዋንጫ ደንብ ሀገራት በደረት ላይ ኮከብ ማሳረፍ የሚችሉት የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ ሲችሉ ብቻ በመሆኑ ሲሆን፣ ግብፅ ግን የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈችበትን 7 ኮከቦች በዓለም ዋንጫ ማሊያዋ ላይ በማሳረፏ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#egypt #fifa #worldcup #pharaohs #footballnews #africacupofnations

በአሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ሶማሊያዊው የዓለም ዋንጫ ዳኛ ሞቃዲሾ ሲገባ የጀግና አቀባበል ተደረገለት
በዓለም ዋንጫ ላይ እንዲዳኝ ተመርጦ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ሶማሊያዊው እውቅ የኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ዑመር አርታን ወደ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ሲመለስ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ የጀግና አቀባበል ተደረገለት።
የአፍሪካ ምርጥ ዳኞች ተርታ የሚመደበውና እ.ኤ.አ በ2025 የአህጉሪቱ ምርጥ ወንድ ዳኛ ተብሎ የተመረጠው ዑመር አርታን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ በመዳኘት የመጀመሪያው ሶማሊያዊ በመሆን ታሪክ ሊሰራ ተዘጋጅቶ ነበር።
ዳኛው ባለፈው ሳምንት በኬንያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ህጋዊ ቪዛ የተሰጠው ቢሆንም ቅዳሜ እለት ሚያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ግን በአሜሪካ የድንበርና የጉምሩክ ጥበቃ አካል "በደህንነት ማጣራት ስጋት" (Vetting concerns) ምክንያት መግቢያ ተከልክሏል።
አሜሪካ ውሳኔውን ተከትሎ ዝርዝር መረጃ ካለመስጠቷም በላይ የአንደኛዋ አስተናጋጅ ሀገር ክልከላን ተከትሎ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) ዳኛውን ከዓለም ዋንጫው የዳኞች ዝርዝር ውስጥ ለመሰረዝ ተገድዷል።
አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ የፊፋ ዕውቅና ያለውን ከፍተኛ ዳኛ ወደ ሀገር እንዳይገባ መከልከሏ በዓለም ዙሪያ ባሉ የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ውሳኔው አሜሪካ እንዲህ ያሉ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማስተናገድ ብቃት አላት ወይ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳባት አድርጓል። ሶማሊያ በአሁኑ ወቅት በትራምፕ አስተዳደር የስደተኞች ቁጥጥር ፖሊሲ ምክንያት አዲስ የጉዞ ገደብ ከተጣለባቸው 40 ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ለዚህ ክልከላ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል።
ዳኛ ዑመር አርታን ዛሬ ዛሬ ረቡዕ ጠዋት 3:30 በሞቃዲሾ አደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የስፖርት ቤተሰቦች የሶማሊያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ ለሰዓታት ሲጠባበቁት ቆይተዋል።
አውሮፕላኑ ሲያርፍም ደጋፊዎቹ በሶማሊያ ባንዲራ ያለበሱት ሲሆን፣ በፖሊስ ታጅቦ ወደ አውሮፕላን ማረፊያው የቪአይፒ (VIP) ማረፊያ አምርቷል። እዚያም በሶማሊያ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር እና በሶማሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።
ዳኛው ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ለተደረገለት ድጋፍ የሶማሊያን መንግስት፣ ህዝብ እና ፊፋን አመስግኗል። "እግዚአብሔር ከፈቀደ በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ላይ እንደምገኝ ቃል እገባላችኋለሁ፤ የሶማሊያ ህዝብ በዚህ እንዲረጋጋና በራሱ እንዲተማመን እፈልጋለሁ" ብሏል።
አክሎም "የሶማሊያን ስም የመጠበቅ ኃላፊነት የሁላችንም ነው። ሀገራችን በጥሩም ሆነ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን የእኛ ናት ያ ባንዲራና ፓስፖርትም የእኛ ነው በማለት ለወጣቱ መልዕክት አስተላልፏል።
ለዓመታት በዘለቀው የእርስ በእርስ ጦርነትና በአሸባሪው አልሸባብ ምክንያት የወጣቶቿ ተስፋ በተገደበባት ሶማሊያ የዑመር አርታን መከልከል ለብዙዎች የልብ ስብራት ቢሆንም፣ ሕልምን ተከትሎ መጓዝ ምን ያህል ትልቅ ደረጃ እንደሚያደርስ ግን ማሳያ ሆኗል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር (X) ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የደረስክበት የታሪክ ምዕራፍ ምንም ቢሆን አይቀየርም። በሙያህ ጥግ ላይ በመድረስህ ብቻ በትውልድ ሀገርህ ላለው አዲስ ትውልድ ትልቅ መነሳሳትን ፈጥረሃል በለፋህበትና በገባህበት የሜዳ ሳር ላይ እንዳትቆም መደረግህ ይህንን የታሪክ እውነት አይለውጠውም በማለት ለዳኛው ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።

የኢራን ደጋፊዎች ትኬት ተሰረዘ
#ethiopia | ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የቀረበው የስታዲየም መግቢያ ትኬት መሰረዙን የኢራን እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ትኬቱ በምን ምክንያት እንደተሰረዘ ግን አልተነገረም።
ፌዴሬሽኑ ቡድኑ ማግኘት የሚገባውን የትኬት ኮታ መከልከሉን አውግዟል።
ፊፋ የገለልተኝነት እና ፍትሀዊነት መርሆዎችን እንዲያከብርም ጠይቋል።
መሰረዙን ተከትሎ ኢራናውያን ደጋፊዎች ስታዲየም መግባት አይችሉም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #aradafm #worldcup #fifa #iran

የአፍሪካው ምርጥ እግር ኳስ ዳኛ ሶማሊያዊው ዑመር አርታን
ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እገዳ ተጣለበት
#ethiopia | በፈረንጆቹ 2025 የአፍሪካ አህጉር ምርጥ እግር ኳስ ዳኛ የመሆን ክብርን የተቀናጀው ታዋቂው ሶማሊያዊ ዳኛ ዑመር አርታን ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እገዳ ተጥሎበታል።
ይህ ያልተጠበቀ ውሳኔ በመጪው የ2026 ዓለም ዋንጫ ላይ ማናቸውንም ጨዋታዎች እንዳይመራ የሚያግደው ሲሆን በዓለም አቀፉ የስፖርት ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያና አነጋጋሪ ክስተት ሆኗል።
ለሀገሩ ሶማሊያ ትልቅ የኩራት ምንጭ የሆነው ዑመር አርታን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ጨዋታ ለመምራት የተመረጠ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ በመሆን አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውት ነበር።
ሆኖም ግን አሁን በተጣለበት የቪዛ እገዳ ምክንያት ያሰበውን ታላቅ ታሪክ ሳይሰራ ወደ ሀገሩ ለመመለስ መገደዱ በርካታ የስፖርቱ አፍቃሪያንን በእጅጉ አሳዝኗል።
ይህ አድሏዊ አሰራርን የሚያሳይ ነው የተባለው ውሳኔ የአፍሪካ እግር ኳስንና የሶማሊያን ስፖርተኞች ተስፋ የሚያጨልም ሆኖ ተገኝቷል።
በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ ሀገሩንና አህጉሩን በኩራት ሊወክል የነበረው የዑመር አርታን ጉዞ በዚህ መልኩ መቋረጡ በችሎታውና በስፖርቱ መድረክ ላይ የተጣለ ጥቁር ጥላሸት ተደርጎ እየተወሰደ ይገኛል።
#omarartan #somalia #worldcup2026 #caf #fifa #breakingnews #footballinjustice #ሶማሊያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ፊፋ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ስታዲየም ውስጥ ቩቩዜላ እንዳትነፉ አለ
#ethiopia | በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በስታዲየም ውስጥ የሚፈጠረውን ከፍተኛ የድምፅ ብክለት ለመቆጣጠር ጥብቅ መመሪያ ማውጣቱን አስታውቋል።
ባወጣው አዲስ የስታዲየም የሥነ-ምግባር ደንብ መሰረት፣ በተለይ በ2010 የደቡብ አፍሪካ ዓለም ዋንጫ ወቅት መለያ ምልክት ሆኖ የነበረውና በከፍተኛ ድምፁ የሚታወቀው ቩቩዜላ (Vuvuzela) በስታዲየሞች ውስጥ እንዳይነፋ ሙሉ በሙሉ ታግዷል። ከቩቩዜላ በተጨማሪ ማንኛቸውም ከፍተኛ ድምፅ የሚፈጥሩ የድምፅ መሣሪያዎች ወደ ስታዲየም ይዞ መግባት ክልክል ሆኗል።
ማህበሩ ለዚህ እግድ ዋና ዋና ምክንያቶች ያላቸውን ነጥቦች ይፋ አድርጓል፡-
የበጨዋታ ላይ ባሉ ተጫዋቾች፣ ዳኞች እና አሰልጣኞች መካከል የሚደረገውን የሜዳ ላይ የድምፅ ተግባቦት በቀላሉ ለማሳለጥ።
የቩቩዜላ የማያቋርጥና ከፍተኛ ድምፅ ዓለም አቀፍ የቪዲዮ እና የሬዲዮ ቀጥታ ስርጭት የሚዲያ ስራዎችን ጥራት ስለሚቀንስ።
በስታዲየም ውስጥ ድንገተኛ አደጋዎች ቢከሰቱ የሚተላለፉ የአደጋ ጊዜ ማስታወቂያዎች በደጋፊዎች ዘንድ በግልጽ እንዲሰሙ ለማድረግ።
ፊፋ የደጋፊዎችን ስሜት እና የተጫዋቾችን ደህንነት ለመጠበቅ ካወጣው ደንብ መካከል፣ ከተመልካች ወንበር ወደ ሜዳ በመወርወር የተጫዋቾችን አይን ላይ የሚበሩ ሌዘር ፖይንተሮች (Laser Pointers) ላይም ጭምር ጥብቅ እግድ ጥሎባቸዋል።
ይህ እርምጃ ከ16 ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ ወቅት በቩቩዜላ ድምፅ ሳቢያ በዓለም ዙሪያ ካሉ ተመልካቾች እና ስፖርተኞች የተነሳውን ከፍተኛ ቅሬታ በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመሆኑም የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ከበዛ ጩኸት ይልቅ በስፖርታዊ ጨዋነት እና በክፍት ስሜት የሚደመቅበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#fifaworldcup2026 #vuvuzelaban #footballnews #fifa #stadiumrules

3 months ago
ኢራን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን በአሜሪካ ታደርጋለች - ፊፋ
****************
ኢራን የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን በአሜሪካ እንደምታከናውን የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በድጋሚ አረጋገጡ።
ኢንፋንቲኖ ይህንን ያስታወቁት በቫንኩቨር፣ ካናዳ መካሄድ የጀመረውን የፊፋ ጉባኤን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው።
በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ኢራን በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ስለመሳተፏ ጥርጣሬ ላይ ወድቆ ነበር።
ይሁን እንጂ ኢንፋንቲኖ ለጉባኤው በሰጡት መግለጫ፣ "በመጀመሪያ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢራን በ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ላይ በእርግጠኝነት ትሳተፋለች፤ ጨዋታዎቿንም በአሜሪካ ታደርጋለች" ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፊፋው ፕሬዚዳንት መግለጫ በኋላ ስለሁኔታው ተጠይቀው በሰጡት መልስ፣ “አዎ መጫወት ይችላሉ” ሲሉ መመለሳቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
ቀደም ሲል የኢራን ባለሥልጣናት የምድብ ጨዋታዎቻቸው ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፣ ጥያቄው በፊፋው ፕሬዚዳንት ጁሊያኒ ኢንፋንቲኖ ውድቅ ተደርጎ ነበር።
ባለፈው ሳምንት ደግሞ የጣሊያን ተወላጅ የሆኑት የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ፓውሎ ዛምፖሊ "ከዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ኢራን ተቀንሳ ጣሊያን ትተካ" የሚል ሐሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ የአሜሪካ መንግሥት ከዚህ ሐሳብ ራሱን ማራቁን የዘገበው ደግሞ ቲአርቲ ነው።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮም የኢራን እግር ኳስ ተጫዋቾች በአሜሪካ መልካም አቀባበል እንደሚደረግላቸው መግለጻቸው ይታወሳል።
#ebc #worldcup #iran #usa #fifa

ዓለም ዋንጫ ወደ ሀገሬ መጥቷል!
— ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆነ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ተቀየረ! ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ ብቸኛ መብት ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የ2026 የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ በነፃ (FTA - Free To Air) በቀጥታ ያስተላልፋል።
ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚካሄዱትን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው ያያሉ።
ከዓለም ዋንጫ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸውን የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከ 2029 ዓ.ም. ድረስ በብቸኝነት የማስተላለፍ መብትንም ተቆጣጥሯል።
ጨዋታዎቹን በጥልቅ ትንታኔ፣ በልዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶችና በደመቁ ስቱዲዮዎች ለማቅረብ ጣቢያው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
"ይህ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የስፖርት ወዳጆች ትልቅ ኩራት ነው። የግል ጣቢያዎች እንዲህ ባለ ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደራቸው ለኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን ኳስ ለማየት 'ሳተላይት' እና 'ክፍያ' ብሎ መጨነቅ ቀረ፤ ሀገሬ ቴሌቪዥን ዓለምን ወደ ቤታችን አምጥቶታል።"
የስፖርት ድግሱ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይደምቃል!
#getu #hagerietv #fifaworld Cup2026 #ethiopianmedia #sportnews #worldcupinethiopia #athletics2029 #breakingnews #ሀገሬቴሌቪዥን #ዓለምዋንጫ #ስፖርት #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

"ተጨዋቾቹ ይምጡ፤ አብዮታዊ ዘቡ ግን እዛው ይቆይ"
#ethiopia | አሜሪካ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ለሚሳተፈው የኢራን ብሔራዊ ቡድን ግልጽ የሆነ የ"ይለፍ" እና የ"ክልከላ" መስመር አስመረቀች። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርክ ሩቢዮ በሰጡት መግለጫ፣ ዋሽንግተን የኢራን ተጨዋቾች በዓለም ዋንጫው ላይ እንዳይሳተፉ የማገድ ፍላጎት እንደሌላት አስታውቀዋል።
ሚኒስትር ሩቢዮ እንደገለጹት፣ የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት ተጨዋቾቹ ሳይሆኑ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። "የእኛ ችግር ስፖርተኞቹ አይደሉም" ያሉት ሚኒስትሩ፣ የአብዮታዊ ዘቡ አባላት እንደ ጋዜጠኛ፣ አሰልጣኝ ወይም የቡድን አባላት ተመስለው ወደ አሜሪካ መግባት እንደማይችሉ በጠንካራ ቃላት አስገንዝበዋል።
ከሚኒስትሩ ጎን የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አስተዳደራቸው በፖለቲካዊ ምክንያቶች በስፖርተኞቹ ላይ ጫና ማሳደር እንደማይፈልግ ገልጸዋል። ይህ መግለጫ ባለፈው የካቲት 28 በአሜሪካ እና እስራኤል የጋራ ጥቃት የተከፈተባት ኢራን፣ በዓለም ዋንጫው ላይ ያላት ተሳትፎ አጠራጣሪ በሆነበት ወቅት የተሰጠ ነው።
ምንም እንኳን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ከፍተኛ ቢሆንም፣ የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ ፋቴሜህ ሞሃጀራኒ ሀገራቸው ለውድድሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቋን አረጋግጠዋል። የኢራን ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ቡድኑ በውድድሩ ላይ እንዲሳተፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ኢራን በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በምድብ ጨዋታዎቿ ከሚከተሉት ሀገራት ጋር ትፋለማለች፦
ቤልጂየም
ግብፅ
ኒውዚላንድ
ውድድሩ በፈረንጆቹ ሰኔ 11 የሚጀምር ሲሆን፣ የኢራን ብሔራዊ ቡድን አባላት ወደ አሜሪካ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የቪዛ እና የደህንነት ምርመራው ጥብቅ እንደሚሆን ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#worldcup2026 #usa #iran #football #internationalrelations #marcorubio #fifa

4 months ago
''ኢራንን አንተካም!" — ጣልያን
#ethiopia | ፊፋ ኢራንን ከዓለም ዋንጫ አስወግዶ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ ያቀረቡት ጥያቄ በራሷ በጣልያን መንግሥትና በስፖርት አመራሮቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።
የጣልያን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሉቺያኖ ቦንፊግልዮ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጠንከር ያለ ምላሽ፣ ጣልያን በሜዳ ላይ ባላሳየችው ውጤት በፖለቲካዊ መንገድ ወደ ዓለም ዋንጫ እንድትገባ የቀረበውን ሐሳብ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።
"ይሄ ከተፈጠረ እንደ ስድብ ነው የምወስደው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ማንኛውም ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ያለበት በችሎታውና በጠንካራ ሥራው መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አቋም ተጋርተዋል፦
"ይሄ አስፈላጊ አይደለም፤ ሜዳ ላይ ነው ማለፍ ያለብን" በማለት በጓሮ በር ወደ ውድድሩ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጂዮርጌቲ፦ ዜናው በግላቸው እንዳሳፈራቸው ገልጸው፣ "በዛ መንገድ ከሄድን አፍራለሁ" ሲሉ የሐሳቡን አሳፋሪነት ገልጸዋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ባለማለፉ ደጋፊዎቿ ቢያዝኑም፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ግን ከውጤት ይልቅ ለስፖርታዊ ጨዋነትና ለፍትሐዊ ውድድር ቅድሚያ በመስጠት ዓለም አቀፍ አድናቆትን እያገኙ ይገኛሉ።
ጣልያን "በችሎታችን ካላለፍን በሌላው ስንብት አንገባም" የሚል ጠንካራ መልዕክት ለዓለም አስተላልፋለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#italy #fifa #worldcup2026 #iran #footballnews #sportsmanship #fairplay #azzurri #lucianobonfiglio #andreaabodi #worldcupupdate

ኢራን በጣሊያን እንድትተካ የቀረበው አነጋጋሪ ጥያቄ
#fastmereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ኢራን በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ተሰርዞ በጣሊያን እንድትተካ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) ጥያቄ አቀረቡ።
ይህ ያልተጠበቀ ጥያቄ የቀረበው ልዩ መልዕክተኛው ፓኦሎ ዛምፖሊ ለፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል። ጥያቄው በዋናነት በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቅራኔ ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በሜሎኒ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ ትራምፕ በኢራን ጦርነት ዙሪያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን በሰነዘሩት ትችት ሳቢያ መሆኑ ተነግሯል።
ልዩ መልዕክተኛው ዛምፖሊ ጣሊያን አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያሸነፈች ታሪካዊ ሀገር በመሆኗ፣ በውድድሩ የመሳተፍ "ብቃት" አላት ሲሉ ተከራክረዋል። ጣሊያን ለማጣሪያው በቦስኒያ ሄርዞጎቪና ተሸንፋ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውጪ መሆኗ ይታወሳል።
ኢራን በበኩሏ ለውድድሩ ዝግጁ መሆኗንና እንደምትሳተፍ በይፋ አስታውቃለች። ከዚህ ቀደም ጨዋታዎቿ ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ለፊፋ ጥያቄ አቅርባ እንደነበር አይዘነጋም።
እስካሁን ፊፋም ሆነ የኋይት ሀውስ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ይፋዊ ምላሽ የለም። ይሁን እንጂ የፊፋ ህግ አንድ ሀገር ራሷን ካገለለች ሌላ ሀገር የመተካት ሙሉ ስልጣን ለማህበሩ ይሰጣል።

የኮንጎ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው
#ethiopia | የኮንጎ ሪፐብሊክ (ኮንጎ ብራዛቪል) ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FECOFOOT) ፕሬዝዳንት ዦን ጋይ ብሌዝ ማዮላስ (Jean-Guy Blaise Mayolas) በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የዕድሜ ልክ እስራት ፈረደባቸው።
ፕሬዝዳንቱ የተፈረደባቸው በሚከተሉት የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፈው በመገኘታቸው ነው፦
የገንዘብ ምዝበራ፦
ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (FIFA) ለኮንጎ እግር ኳስ እድገት የተላከ ከ1.1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለግል ጥቅም ማዋል፤
የኮቪድ-19 ፈንድ ስርቆት፦
ፊፋ በወረርሽኙ ወቅት ለሴቶች እግር ኳስ ልማት የመደበውን 500,000 ዶላር ለታለመለት ዓላማ አለማዋል፤
የሰነድ ማጭበርበር እና የጥቅም ግጭት፦ የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ለማጭበርበር የሀሰት ሰነዶችን መጠቀም እና ከቤተሰብ አባላት ጋር የተገናኙ የጥቅም ግጭቶች።
ባለፈው ሳምንት (መጋቢት 2026) በብራዛቪል የወንጀል ችሎት የተሰጠው ውሳኔ የሚከተሉትን አካቷል፦
ዦን ጋይ ብሌዝ ማዮላስ፦
በሌሉበት (In absentia) የዕድሜ ልክ እስራት፤
ሊዮኔል ማዮላስ (የፕሬዝዳንቱ ልጅ)፦
በተመሳሳይ ክስ የዕድሜ ልክ እስራት፤
ባጂ ሞምቦ ዋንቴቴ (የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ)፦ የ5 ዓመት እስራት፤
ራውል ካንዳ (የፌዴሬሽኑ ገንዘብ ያዥ)፦ የ5 ዓመት እስራት።
ማስታወሻ፦
ፕሬዝዳንቱ ማዮላስ ፍርዱ በሚሰጥበት ወቅት በችሎት ያልተገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ እንደማይታወቅና በፖሊስ እየታደኑ መሆኑ ተነግሯል።
ይህ ክስተት ፊፋ ቀደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ እና በኮንጎ እግር ኳስ ላይ የነበረውን የአስተዳደር ቀውስ ተከትሎ የመጣ ነው።

5 months ago
ኢራን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ ለማዛወር ከፊፋ ጋር እየተደራደረች ነው
#ethiopia | በፖለቲካዊ ውጥረትና በደህንነት ስጋት ምክንያት የኢራን እግር ኳስ ማህበር የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቹን በአሜሪካ ምትክ በሜክሲኮ ለማከናወን ጥያቄ ማቅረቡ ተሰማ። የኢራን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ እንደገለጹት፣ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለኢራን ብሔራዊ ቡድን በቂ የደህንነት ዋስትና ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቡድኑ ወደ አሜሪካ የመጓዝ ዕቅድ የለውም።
ፕሬዝዳንቱ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ትራምፕ ለቡድናችን ደህንነት ማረጋገጫ ባልሰጡበት ሁኔታ ወደ አሜሪካ መጓዝ አንችልም" ያሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጨዋታዎቹን ወደ ሜክሲኮ ለማዛወር ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ውሳኔ የተሰማው የኢራን ስፖርት ሚኒስትር አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አጠራጣሪ መሆኑን በገለጹ ማግስት ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ኢራን መሳተፍ እንደምትችል ቢገልጹም፣ "ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ባይመጡ ይሻላል" የሚል ይዘት ያለው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወሳል።
እንደ መጀመሪያው መርሃ ግብር ኢራን ሁለት የምድብ ጨዋታዎቿን በሎስ አንጀለስ፣ ቀሪውን አንድ ጨዋታ ደግሞ በሲያትል ለማከናወን ተመድባ ነበር። አሁን በቀረበው ጥያቄ ላይ ፊፋ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል::
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #worldcup2026 #fifa #iranfootball #mexico2026 #sportsnews #breakingnews #footballpolitics

🚨 የኢራን የአለም ዋንጫ ተሳትፎ አደጋ ላይ መውደቁ ተገለጸ!
#ethiopia | የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን መላው የእግር ኳስ አፍቃሪን የሚያስደነግጥ መግለጫ አውጥቷል። ሀገሪቱ በቀጣዩ የአለም ዋንጫ ላይ ላታካፍል እንደምትችል ፍንጭ ሰጥታለች።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ እንደገለጹት ከሆነ፣ በአሜሪካ ተፈጽሟል በተባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ሀገሪቱ በውድድሩ ላይ የመሳተፍ "ተስፋ የላትም" ብለዋል። ይህ ድንገተኛ መግለጫ በስፖርቱ ዓለም ትልቅ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ የሀገሪቱን የስፖርት መንፈስ ክፉኛ እንደጎዳው ተነግሯል።
ቀጣዩ እርምጃ ምንድነው?
* የባለስልጣናት ውሳኔ፦ ኢራን በውድድሩ ላይ ትሳተፍ ወይስ አትሳተፍ የሚለውን የመጨረሻ ውሳኔ የሀገሪቱ ከፍተኛ የስፖርት ባለስልጣናት በቅርቡ የሚወስኑ ይሆናል።
* የቤት ውስጥ ውድድሮች መቋረጥ፦ ከዚሁ ውሳኔ ጋር ተያይዞ በኢራን ውስጥ የሚካሄዱ ማናቸውም የእግር ኳስ ውድድሮች ለላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጡ ተወስኗል።
ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) እና በውድድሩ ድልድል ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #iran #worldcup #footballnews #breakingnews #iranfootball #fifa #mehditaj #sportsupdate

6 months ago
በፊፋ ስታንዳርድ መሰረት እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የሳር ንጣፍ ስራ ተጀመረ፡፡
በዓለም-ዓቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) እንዲሁም በ World Athletics ስታንዳርዶች መሰረት በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የመጫወቻ ሜዳ ቅልቅል (Hybrid turf) ሳር ንጣፍ ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በአውሮፓ እና በአፍሪካ በሚገኙ ትልልቅ ስታዲየሞች ላይ ሰው ሰራሽ (Artificial turf ) እንዲሁም ቅልቅል (Hybrid turf ) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ የካበተ ልምድ ካለው የጣሊያኑ ሊሞንታ (Limonta Sport) ጋር የነበረው ንግግር በውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ኩባንያው በዛሬው ዕለት በስቴዲየሙ ተገኝቶ ዳታ የመልቀም ተግባር ጀምሯል፡፡
ስራውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንደገለፁት በስቴዲየሙ የሚነጠፈው የሳር አይነት ቅልቅል (Hybrid) ሆኖ አይነቱም carpet type እንደሚሰኝ ጠቅሰው ይህም ከ90 – 95 % የተፈጥሮ ሳር እንዲሁም ቀሪው ከ5–10 % ደግሞ አርቴፊሺያል እንደሚሆን ያብራሩ ሲሆን ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ ድርሳን ላይ አዲስ ገፅ የሚገልጥና ለስፖርት ቱሪዝም እንዲሁም ለውጪ ግንኙነታችንም ጭምር በጎ ፋይዳ እንደሚኖረው አያይዘው ጠቁመዋል፡፡
በስቴዲየሙ ግንባታ ላይ MNRC በዋና ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ZIAS International Designs PLC በአማካሪነት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

"አንተ እውነተኛ አሸናፊ ነህ!" - ጂያኒ ኢንፋንቲኖ
#ethiopia | ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ንጉስ እና የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ 41ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በዛሬው ዕለት እያከበረ ይገኛል። ይህንን ተከትሎም የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ (FIFA) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ለተጫዋቹ የክብር መልእክት ልከዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ሮናልዶን "የጠንካራ ሥራ እና የተስፋ ያለመቁረጥ ተምሳሌት" ሲሉ አሞካሽተውታል።
የኢንፋንቲኖ መልእክት ዋና ዋና ነጥቦች፡
* ሪከርድ ሰባሪነቱ፡ "አንተ እውነተኛ አሸናፊ እና ታሪክ ሰሪ ነህ" ሲሉ የሮናልዶን ድል አድራጊነት መስክረዋል።
* አርአያነቱ፡ "ሁልጊዜም የተሻለ ለመሆን ስለምትጥር እና ትልቅ ህልም ያላቸውን ሁሉ ስለምታነሳሳ እናመሰግንሃለን" በማለት ለትውልድ ያለውን አስተዋጽኦ ገልጸዋል።
ኢንፋንቲኖ መልእክታቸውን የቋጩት ለሮናልዶ መልካም ልደትን በመመኘት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #cristianoronaldo #cr7 #fifa #gianniinfantino #footballlegend #sportnews #hbdcr7

🏆 የ2030 ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ፦ ስፔን ወይስ ሞሮኮ? ፍጥጫው በርትቷል!
#ethiopia | የ2030 ዓለም ዋንጫን በጋራ የሚያዘጋጁት ሀገራት በፍፃሜው ጨዋታ ቦታ ላይ መስማማት አልቻሉም። የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ራፋኤል ሉዛን ጨዋታው በስፔን እንደሚካሄድ በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
"ፍፃሜው ስፔን ውስጥ ይደረጋል!"
ፕሬዝዳንት ሉዛን ስፔን ውድድሩን የማዘጋጀት ብቃቷን ያረጋገጠች ሀገር መሆኗን ገልጸው፣ ሞሮኮን ግን በጠንካራ ቃላት ተችተዋል። ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በሞሮኮ በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የታዩ ክስተቶችን በማንሳት፣ "የዓለም እግር ኳስን ገጽታ ያበላሹ ነገሮችን ተመልክተናል" ሲሉ የሞሮኮን ብቃት ጥያቄ ውስጥ ከትተዋል።
የስታዲየሞች ክፍፍል፦
ለ2030 ዓለም ዋንጫ የተመደቡት ስታዲየሞች ብዛትም የስፔንን የበላይነት ያሳያል ተብሏል፦
* ስፔን፦ በ11 ስታዲየሞች (አብዛኛውን ጨዋታ ታስተናግዳለች)
* ሞሮኮ፦ በ6 ስታዲየሞች
* ፖርቹጋል፦ በ3 ስታዲየሞች
ሞሮኮ በበኩሏ ለፍፃሜው ጨዋታ የሚሆን እጅግ ግዙፍ እና ዘመናዊ ስታዲየም እየገነባች መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር በሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ እና ስፖርታዊ ግንኙነት ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#worldcup2030 #spain #morocco #portugal #fifa #footballnews #rafaelluzan #worldcupfinal #ethiopia #sportsnews

የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!
#ethiopia | "የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል።
የስታዲየሙ ገፅታዎች:
✅ ደረጃ: የፊፋ (FIFA) እና የካፍ (CAF) ስታንዳርድን ያሟላ።
✅ አቅም: ከ40,000 እስከ 45,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው።
✅ ዲዛይን: የወላይታን ህዝብ ታሪክ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የአካባቢውን ገፅታ ያካተተ ነው።
✅ ይዞታ: በ51 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ "ይህ ፕሮጀክት የህዝብ ነው፤ ከተባበርንና ካስተባበርን እውን ማድረግ ይቻላል" በማለት፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ የሚሆን ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት መላው ህዝብ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6
#wolaita #stadium #construction #ethiopia
#wolaitasodo #internationalstadium #ethiopia #development #sports #southethiopia

7 months ago
የሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ
ሥራዋ በኢትዮጵያ ቤተመንግሥት ሲኒማ ቤት እየታየ ነው
#ethiopia | መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉ ኢምባሲዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው 200 እንግዶች ዘጋቢ ፊልሙን በመመልከት ላይ ናቸው
***
ስለ ዳይሬክተሯ
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden and the Writer)
ሳራ ዶላታባዲ (Sara Dolatabadi)
የፊልም ዳይሬክተር፣ የምስል ጥበብ ባለሙያ (Visual Artist) እና ጸሐፊ
ሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ እና የመልቲሚዲያ ፊልም ሰሪ ናት። በልጅነቷ የኢራን እስላማዊ አብዮት እና የኢራን-ኢራቅ ጦርነት በህይወቷ ላይ ተፅእኖ አሳድሮባታል። እነዚህን ታሪካዊ ክስተቶች በልጅነት አይኖቿ ተመልክታለች። እነዚህ ትዝታዎች በምስል ጥበብ ባለሙያነቷ እና በፊልም ሰሪነቷ ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሲሆን፤ ስራዎቿ የግል ሕይወት (Microcosm) እና የፖለቲካው ዓለም (Macrocosm) የሚገናኙበት ነጥብ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።
ከቴህራን አዛድ የስነ-ጥበብ ዩኒቨርሲቲ (Azad Art University) ከተመረቀች በኋላ፣ ለአሥር አመታት በቶኪዮ፣ ፓሪስ እና ኒው ዮርክ በመስራት እና ስራዎቿን ለእይታ በማቅረብ አሳልፋለች። በኒው ዮርክ በሚገኘው ሃንተር ኮሌጅ (Hunter College) በስነ-ጥበብ የማስተርስ ዲግሪዋን (MFA) አግኝታለች። ለድህረ-ምረቃ መመረቂያ ጽሁፏ፣ ስለ ቤተሰቧ የሚያወሳ "Summer Light" (የበጋ ብርሃን) የተሰኘ አጭር ዶክመንተሪ ፊልም ዳይሬክት አድርጋ አዘጋጅታለች።
በመቀጠልም "An Owl, A Garden and the Writer" (ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ጸሐፊው) የተሰኘውን ዶክመንተሪ ፊልም የሰራች ሲሆን፤ ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ2023 በቪዥን ዱ ሪል (Vision du Réel) ፌስቲቫል ላይ ለእይታ በቅቷል። ይህ ፊልም በቡሳን የፊልም ፌስቲቫል (Busan Film Festival) እና በሴንተር ፖምፒዱ ኤክስትራ ፌስቲቫልን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች እና ፌስቲቫሎች ላይ ታይቷል።
በተጨማሪም ፊልሙ በዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doc Lisboa) "የመብት እና ነጻነት ሽልማት" (Rights and Freedom Award) እንዲሁም በ2024 በሞንትሪያል በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ ፊልም ፌስቲቫል ላይ "ምርጥ የቁም-ምስል ሽልማት" (Best Portrait Award) አሸንፏል።
በጋቦን ለሦስት ዓመታት በቆየችበት ጊዜ በሊብሬቪል (ሲሲባ) ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች ትምህርትን ለማስፋፋት የሚሠራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) ከመሰረቱት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ትኖራለች፣ ትሰራለችም።
***
ስለ ሀበሻ ቪው (habeshaview)
በ2015 (እ.ኤ.አ) የተመሰረተው ሀበሻ ቪው (habeshaview)፤ ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ቨርጂኒያ ያደረገ ሲሆን፣ በእንግሊዝ ለንደን እና በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉት። በተጨማሪም በኔዘርላንድ የዳታ ማዕከል (Data center) እና የቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አለው።
ሀበሻ ቪው ዘርፈ-ብዙ የሚዲያ፣ የመዝናኛ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የኦቲቲ (OTT) ፕላትፎርም እና አፕሊኬሽኖችን በማልማት ደረጃውን የጠበቀ የመመልከት ልምድን ያቀርባል።
የሚያቀርባቸው አገልግሎቶችም የቀጥታ የዜና ቻናሎችን፣ የመዝናኛ ጣቢያዎችን፣ እንደ ፍላጎት የሚታዘዙ ፊልሞችን (Video On Demand)፣ ጨዋታዎችን እና የኦዲዮ ቻናሎችን ያካትታሉ።
በተጨማሪም ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ የተለያዩ ስቱዲዮዎች የተገኙ ኦሪጂናል የሆኑ ፕሮግራሞችን በብዙ የቋንቋ አማራጮች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያለፉ ፕሮግራሞችን መልሶ የመመልከት (catch-up service) አማራጭ ጭምር ያቀርባል።
ሀበሻ ቪው ከዚህም በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፊልም አከፋፋይ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተሰሩ ጥራት ያላቸውን እና ኦሪጂናል ፊልሞችን በመምረጥ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎች እና የሲኒማ ቤቶች በማቅረብ ያስተዋውቃል።
በረጅም ጊዜ እቅዱም ከአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሌሎች ይዘቶችን በማሰራጨት በፓን-አፍሪካ የመዝናኛ እና የስትሪሚንግ ኢንዱስትሪ መሪ ለመሆን ራዕይ ሰንቋል።
***
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት
የሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ (habeshaview Technology and Multimedia) ተባባሪ መስራች እንደመሆኔ፣ ሞቅ ያለ ሰላምታዬን ሳቀርብላችሁ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።
የጉዞአችን ተካፋይ ስለሆናችሁ እጅግ ደስ ብሎኛል። ዛሬ አዲሱን የስራ ዘርፋችንን "ሀበሻ ቪው ሲኒማ" (habeshaview Cinema) በምናስጀምርበት በዚህ ወቅት፣ እንኳን ወደ ደማቁ የመዝናኛ፣ የባህል እና የፈጠራ ዓለማችን በሰላም መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ። ይህ በየወሩ የሚካሄድ የፊልም ክበብ፤ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ከተቀረው ዓለም የተውጣጡ ፊልሞችን ለእይታ የሚያቀርብ ነው።
ትዕግስት ከበደ
ተባባሪ መስራች፣
***
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden, & The Writer)
የፕሬስ ማስታወሻ እና ሽልማቶች
"እጅግ ዜማዊ እና ረቂቅ፣ ሆኖም ግን ጉልበት ያለው ስራ፤ እጅግ ታላቅ የሆነውን የፀሃፊውን ስብእና ሰብአዊ በሆነ መንገድ እያሳየን፣ ስላለፉት አስርት ዓመታት የኢራን ጨካኝ ስርዓት የሚያስተምረን ፊልም ነው።"
— ቢዝነስ ዶክ ዩሮፕ (BUSINESS DOC EUROPE)
ፌስቲቫሎች እና ሽልማቶች
ቪዥንስ ዱ ሪል 2023 (Visions du Réel): በርኒንግ ላይትስ ውድድር (የዓለም የመጀመሪያ እይታ)
ፖምፒዱ ሴንተር (Pompidou Centre): (የፈረንሳይ የመጀመሪያ እይታ)
ቡሳን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2023 (Busan IFF): (ዓለም አቀፍ የመጀመሪያ እይታ)
ዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doclisboa): የመብት እና ነጻነት ሽልማት አሸናፊ
ኦዛ (OZA) የዘመናዊ ዶክመንተሪ ፊልም ፌስቲቫል 2024: የዳኞች ልዩ ሽልማት
ፊፋ 2024 (FIFA): ምርጥ የቁም-ምስል (Portrait) ሽልማት
ካርሎቪ ቫሪ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2021: በሂደት ላይ ያሉ ስራዎች (Works in Progress) የድህረ-ምርት ልማት ሽልማት አሸናፊ
አይዲኤፍኤ ፎረም (IDFA Forum)
የአዘጋጆች መግለጫ [አሚር ናደሪ - ዋና አዘጋጅ (Executive Producer)]
ኢራናዊው ፊልም ሰሪ አሚር ናደሪ፤ "ቬጋስ፡ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ" (2008)፣ "ማንሃተን በቁጥሮች" (1993) እና "ዘ ረነር" (1985) በመሳሰሉ ፊልሞቹ ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2016 በቬኒስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለዘመናዊ ሲኒማ ፈጠራ እና እድገት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ለሚሰጠው "Jaeger-LeCoultre Glory to the Filmmaker" የተሰኘ ክቡር ሽልማት ባለቤት ሆኗል።
"[የፊልሙ ባለታሪክ] በዘመናችን ካሉ እጅግ ታዋቂ ኢራናውያን ደራሲያን አንዱ ነው። በስራዎቹ የሀገሩን ልብ እና ነፍስ መተረክ ችሏል። በፋርስ ቋንቋ ንጹህ እና ጠንካራ ድምጽ ያለው ይህ ደራሲ፤ በልብ ወለዶቹ እና በታሪኮቹ ውስጥ የህዝቡን ታሪክ መዝግቦ አስቀምጧል። ስለሆነም፣ በተለይም አሁን ካለው የዓለም እና የኢራን ሁኔታ አንጻር፣ የእሱን ህይወት እና ስራዎች መዝግቦ ማቅረብ (Document ማድረግ) ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።"
***
ሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ
በሀበሻ ቪው፤ ለኢትዮጵያ ስነ-ጥበብ፣ ባህል እና ተሰጥኦ ትልቅ ቦታ እና ክብር አለን። ተልዕኳችንም ይህንን የባህል ሀብት ከዘመናዊ እና ከላቀ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ ለክቡራን ደንበኞቻችን ልዩ እና ተመስጦን የሚፈጥር ልምድ ማቅረብ ነው።
በባህል እና በዘመናዊነት መካከል ድልድይ መሆን እንዳለብን እናምናለን፤ የፈጠራ ባለሙያዎቻችንን ድንቅ ተሰጥኦ ለዓለም ገበያ በማሳየት የኢትዮጵያን ስራዎች ለዓለም አቀፍ መድረክ ለማብቃት እንተጋለን።
እስካሁን ያደረግነው ጉዞ እጅግ አስደናቂ ነበር፤ ይህ ስኬትም ያለ እናንተ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሊታሰብ አይችልም ነበር። አሻራችንን እያሰፋን እና እያደግን ስንሄድ፣ ለዋና እሴቶቻችን ጸንተን እንቆማለን።
እነዚህም፦ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ እና ማልማት፣ የሀገር ውስጥ ተሰጥኦን ማሳደግ፣ እንዲሁም የቅርሶቻችንን እና የባህላችንን ተደራሽነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጎልበት ናቸው።

ሞሮኮ በሴኔጋል ላይ ክስ መሰረተች!
በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ሴኔጋል ሜዳ ጥላ መውጣቷን ተከትሎ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ወደ CAF እና FIFA በመውሰድ የህግ እርምጃ እንደሚጀምር አስታውቋል።
ምን ተፈጠረ?
ትላንት እሁድ ጥር 10/2018 ዓ.ም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ መጠናቀቂያ ላይ ለሞሮኮ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቶ ነበር። በዚህ ውሳኔ የተቆጡት የሴኔጋል ተጫዋቾች በቴክኒክ ዳይሬክተራቸው ፓፔ ቲያው ትዕዛዝ ለ15 ደቂቃ ያህል ሜዳ ጥለው ወጥተው ነበር።
የሞሮኮ ቅሬታ፦
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ፦
❌ የሴኔጋል ተጫዋቾች ሜዳ ጥለው መውጣታቸው በጨዋታው ሂደት እና በተጫዋቾች ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።
❌ ዳኛው የሰጡት የፍጹም ቅጣት ምት ትክክል ሆኖ ሳለ፣ የሴኔጋል ድርጊት ግን ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለውና ህግ የጣሰ ነው።
የጨዋታው ውጤት፦
ሴኔጋል ወደ ሜዳ ተመልሳ ብራሂም ዲያዝ የፍጹም ቅጣት ምቱን ስቶታል። ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቶ ሴኔጋል በፓፔ ጉዬ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ብታነሳም፣ ጉዳዩ አሁን ወደ ህግ መድረኩ ተሻግሯል።
ካፍ (CAF) በጉዳዩ ላይ ምርመራ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፣ የሴኔጋል አሰልጣኝ በድርጊታቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኩራት!
አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በካፍ ቴክኒካል ቡድን ውስጥ! 👏
* ጨዋታዎቹን የሚተነትኑት የካፍ ልሂቃን ውስጥ አብርሃም መብራቱ ይገኝበታል
#ethiopia | በሞሮኮ እየተካሄደ ባለው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2025) ላይ፤ ጨዋታዎችን በጥልቀት የሚገመግመው እና ምርጥ ተጫዋቾችን የሚመርጠው የካፍ የቴክኒክ ጥናት ቡድን (Technical Study Group - TSG) ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተካቷል።
የአብርሃም ሚና ምንድን ነው?
በአህጉሩ ካሉ ምርጥ የካፍ ኢንስትራክተሮች እና የቀድሞ ተጫዋቾች ጋር በመሆን፤ የቡድኖችን ቴክኒካዊ ብቃት መገምገም፣ የውድድሩን ታክቲካል ሂደት መተንተን እና ለፊፋ (FIFA) እና ለካፍ (CAF) ሪፖርት ማቅረብ ነው።
ትናንት አርሰን ቬንገር የጎበኙት እና ያደነቁት ይህንኑ የአብርሃም መብራቱ አባል የሆነበትን ቡድን ነው።
አብርሃም መብራቱ በተለያዩ ጊዜያት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር በመሆን አህጉራዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹⚽
#abrahammebratu #caf #tsg #afcon2025 #ethiopianpride #technicalstudygroup #ethiopia

የአደይ አበባ ስታድየም ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ::
ግዙፉና ዘመናዊው የአደይ አበባ ስታድየም ዋናው የመጫወቻ ሜዳ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) የተደረገለትን ጥብቅ ግምገማ በስኬት አጠናቋል።
እንደ መረጃው ከሆነ፣
የስታድየሙ መጫወቻ ሜዳ በፊፋ ባለሙያዎች የተደረጉለትን ልዩ ልዩ ቴክኒካዊ ቴስቶች በከፍተኛ ውጤት በማለፉ ነው ይህ ይፋዊ እውቅና የተሰጠው። ይህም ሜዳው ደረጃቸውን የጠበቁ ዓለም አቀፍ ግጥሚያዎችን ለማስተናገድ ሙሉ ብቃት እንዳለው ማረጋገጫ ሆኖታል።
ይህ ስኬት ለአገራችን እግር ኳስ እድገትና ለደጋፊዎቻችን ትልቅ ብሥራት ነው።
seledadotio

የአደይ አበባ ስታድየም የመጫወቻ ሜዳ የፊፋን ዓለም አቀፍ የጥራት እውቅና አገኘ
በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ የሚገኘው ግዙፉ ስታድየም ዋና የመጫወቻ ሜዳ፣ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) ተገምግሞ የብቃት እውቅና ማግኘቱ ተነግሯል።
ሜዳው ለዚህ ከፍተኛ እውቅና ሊበቃ የቻለው የፊፋን ጥብቅ መስፈርቶች እና ልዩ ልዩ ቴክኒካዊ ፍተሻዎችን በከፍተኛ ውጤት በማለፉ ነው።
በግምገማው ወቅት የሜዳው የሳር ጥራት፣ የኳስ ዝውውር ፍጥነት እና የመዝለል መጠን እንዲሁም የተጫዋቾችን ደህንነት የሚጠብቁ የብቃቶች በዝርዝር ተፈትሸው ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን ማሟላታቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪም የፊፋ ባለሙያዎች በሜዳው ላይ ባደረጉት ምርመራ፣ ሳሩ በማንኛውም የአየር ሁኔታ በተለይም በከባድ ዝናብ ወቅት ውሃን የማሳረግና የማፍሰስ ብቃቱ እጅግ አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ይህ የተሰጠው እውቅና ስታድየሙ ወደፊት የሚደረጉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያዎችን፣ የአፍሪካ ዋንጫንና ሌሎች ትልልቅ አህጉራዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችለውን መሠረታዊ መስፈርት ማሟላቱን የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ይህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የቤት ጨዋታዎቹን በሀገሩ ውስጥ እንዲያደርግ ለሚከናወነው ጥረት እንደ ትልቅ መነሻ ተደርጎ ተወስዷል።
ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ60,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም የሚኖረው የአደይ አበባ ስታድየም፣ ከእግር ኳስ በተጨማሪ ለአትሌቲክስና ለሌሎች ስፖርታዊ ኩነቶች ዘመናዊ መሳለጫዎችን የያዘ ይሆናል።
የሜዳው እውቅና አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ስታድየሙ ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ሲበቃ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የስፖርት ማዕከል በመሆን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

🏟️ የአደይ አበባ ስታዲየም ዓለም አቀፍ እውቅናን አገኘ!
#ethiopia | በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘውና የኢትዮጵያ ስፖርት አዲስ ተስፋ ተደርጎ የሚወሰደው የአደይ አበባ ስታዲየም፣ የመጫወቻ ሜዳው በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ተገምግሞ ብቃቱን ማረጋገጡ ተበሰረ።
✅ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ግምገማ
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የስታዲየሙ መጫወቻ ሜዳ በፊፋ የተቀመጡትን ጥብቅ መመዘኛዎች በከፍተኛ ውጤት ማለፍ ችሏል። ይህም ሜዳው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
🌟 የስታዲየሙ አስፈላጊነት
የአደይ አበባ ስታዲየም ሜዳ ይህንን እውቅና ማግኘቱ፦
* ኢትዮጵያ በሀገሯ ውስጥ የዓለም አቀፍና የአህጉራዊ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅሟን ያሳድጋል።
* ለብሔራዊ ቡድኑና ለክለቦች ጥራቱን የጠበቀና ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራ ይፈጥራል።
* የስታዲየሙ አጠቃላይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ሀገራችንን በስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ ያደርጋል።
ይህ እውቅና በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ስታዲየም ትልቅ ስኬት ሲሆን፣ ቀሪ ስራዎች ተጠናቀው ሜዳው ሙሉ በሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ የሚሆንበት ቀን በናፍቆት ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#አደይአበባስታዲየም #ኢትዮጵያ #እግርኳስ #ፊፋ #ስፖርት #አዲስአበባ #adeyabebastadium #ethiopia #fifa #football #sportnews

⚽ ፊፋ ለጨዋታ AI ልጠቀም ነው አለ
#ethiopia | የዓለም እግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ (FIFA)፣ በጨዋታዎች ወቅት ከፍተኛ ውዝግብ የሚነሳበትን የጨዋታ ውጪ ውሳኔ ይበልጥ ትክክለኛ ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence - AI) ቴክኖሎጂን በይፋ ሊጠቀም መሆኑን አስታወቀ።
🤖 "AI" በዓለም ዋንጫ ምን አዲስ ነገር ያመጣል?
በሚቀጥለው የዓለም ዋንጫ ላይ ተግባራዊ በሚደረገው በዚህ ቴክኖሎጂ፣ እያንዳንዱ ተሳታፊ ተጫዋች የራሱ የሆነ የ "AI" አምሳያ (Avatar) ይዘጋጅለታል። ይህም የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል፦
* ፈጣን ውሳኔ፦ በቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (VAR) ወቅት የሚባክነውን ጊዜ በመቀነስ፣ የጨዋታ ውጪ ውሳኔዎችን በሰከንዶች ውስጥ ለመለየት ያስችላል።
* ለተመልካች ግልጽነት፦ ተመልካቾች ውሳኔውን በቀጥታና በግልጽ እንዲመለከቱት በ "AI" አምሳያ ምስሎች የታገዘ ማብራሪያ ለስክሪኖች ይቀርባል።
* ከፍተኛ ጥራት፦ የተጫዋቾቹ የ "AI" አምሳያ ምስሎች በሜዳ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በትክክል በመተርጎም የሰው ዓይን ሊስታቸው የሚችሉ ስህተቶችን ያስቀራሉ።
🏟️ የወደፊቱ እግር ኳስ
ይህ የፊፋ ውሳኔ እግር ኳስን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለማጣጣም የሚያደርገው ጥረት አካል ሲሆን፣ በተለይም በታላላቅ ውድድሮች ላይ የሚፈጠሩ የዳኝነት ቅሬታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ተስፋ ተጥሎበታል።
የቴክኖሎጂው መተግበር ጨዋታውን ይበልጥ ፍትሃዊ እና ማራኪ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ፊፋ #እግርኳስ #ቴክኖሎጂ #ሰውሰራሽአስተውሎት #የዓለምዋንጫ #ai #fifa #worldcup #var #offsidetechnology

Comments