ፊፋ በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ የግጥሚያ ማስተካከል አልተፈጸመም ሲል አስታወቀ
#ethiopia | የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር ወቅት የግጥሚያ ማስተካከል (Match-fixing) ተፈጽሟል የሚሉ ወሬዎችን በድጋሚ በማስተባበል፣ በውድድሩ ሙሉ ጊዜ ከውርርድ ወይም ከግጥሚያ ማጭበርበር ጋር የተያያዘ ማንኛውም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ አልተገኘም ብሏል።
ፊፋ እንደገለጸው፣ በውድድሩ 104 ጨዋታዎች በሙሉ የስፖርት ታማኝነትን የሚከታተል ልዩ ቡድን ከዓለም አቀፍ የውርርድ ቁጥጥር ተቋማት ጋር በመተባበር ቁጥጥር ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉም የግጥሚያ ውጤት መቀየር ወይም ሕገ-ወጥ የውርርድ እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ አልተገኘም ብሏል።
ይህ መግለጫ የወጣው በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ በተፈጠሩ የዳኝነት ውሳኔዎችና የVAR አጠቃቀም ዙሪያ የተነሱ ክርክሮች ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተስፋፉ የ“ውድድሩ ተስተካክሏል” የሚሉ ውንጀላዎችን ተከትሎ ነው።
ቀደም ሲልም የፊፋ የዳኝነት ኃላፊ ፒየርሉጂ ኮሊና የዳኞችን ታማኝነት የሚጠራጠሩ ያልተደገፉ ክሶች በስፖርቱ ውስጥ ቦታ የላቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

14 days ago