2 months ago
ስዊዲን በቱኒዚያ ላይ የ 5 ለ 1 ድል ቀዳጀች
#ethiopia | በምድብ ስድስት የተደለደለችው ስዊዲን በባለሜዳነት ብልጫ የታጀበ አስደናቂ ጨዋታ በማሳየት ሰሜን አፍሪካዊቷን ቱኒዚያን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።
ይህ ውጤት ስዊዲን በምድብ ጨዋታዋ ጠንካራ እና ስኬታማ ጅማሮ እንድታደርግ አስችሏታል።
በሞንቴሪ ስታዲየም በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ያሲን አያሪ ሁለት ግቦችን በማግባት ደምቆ ሲያመሽ፣ አሌክሳንደር ኢሳቅ፣ ቪክቶር ዮኬሬስ እና ሳቨንበርግ ቀሪዎቹን የድል ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል።
በሌላ በኩል ለቱኒዚያ ብቸኛዋን ማፅናኛ ግብ ያስቆጠረው ረቂቅ የተባለው ተጫዋች ነው።
#football #sportnews #sweden #tunisia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በቆጂ : አትሌት ማሞ ሐጫሉ እና ማህሌት ካሳሁን የድል አክሊል ደፉ
#ethiopia | ለአምስተኛ ጊዜ መነሻና መድረሻውን በቆጂ ስታዲየም ባደረገው የ12 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወንዶች ዘርፍ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ክለብ ተወካይ የሆነው ማሞ ሐጫሉ አንደኛ በመሆን አሸንፏል።
በዚሁ ምድብ አማን ቃዲ እና አልዬ ቃሲም ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች ምድብ በተደረገው ፉክክር የአሰላ አትሌቲክስ ክለብ አትሌት ማህሌት ካሳሁን ቀዳሚነቱን ስትይዝ፤ ኪያ ፍስሃ እና ድርቤ ኢርኮ በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።
የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር አካል በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ ዕድሜያቸው ከ11 እና ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በሁለቱም ጾታ ያደረጉት ተሳትፎ ለውድድሩ የተለየ ድምቀት ሰጥቶት አርፍዷል።
በስፍራው ተገኝተው የክብር እንግዳ የነበሩት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ መኪዩ ሙሐመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ እንደገና አበበ ዶክተር፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ እና የበቆጂ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ብርሃኔ ነገሰ ሲሆኑ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ታድመውታል።
በስድስት ከተሞች ላይ የሚካሄደው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ውድድር ቀጣይ መርሃ ግብሩን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ የሚያደርግ ሲሆን የፍጻሜው ውድድር ደግሞ ሐምሌ 12 ቀን በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
#bekoji #athletics #ethiotelecom #greatethiopianrun #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን የወንዶች ምድብ አትሌት ጌታቸው ማስረሻ ድል ቀናው
#ethiopia | በአዲስ አበባ በተከናወነው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች መካከል በተደረገው ፉክክር የሸገር ሲቲ ተወካይ የሆነው አትሌት ጌታቸው ማስረሻ አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኗል።
የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አትሌት ባለይልኝ ተሻገር የሁለተኛነት ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ የተወዳደረው አትሌት በላይ ጥላሁን ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ፈጽሟል።
#ethiopia #athletics #halfmarathon #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የኢትዮጵያ አትሌቶች በሞስኮ የደመቀ ድል አስመዘገቡ
#ethiopia | በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በተካሄደው የ2026 የዝናሜንስኪ ሜሞሪያል የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ከፍተኛ የበላይነት በመቀዳጀት አራት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ሁለት የነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አበርክተዋል።
በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ፉክክር አትሌት ብርቄ ኃይሎም አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ስታሸንፍ ሳሮን በርሔ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በተመሳሳይ በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ፈንታዬ ጫኔ፣ ቤተልሄም ኦላና እና ሰላማዊት ሻምበል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የሀገራቸውን የበላይነት አስመስክረዋል።
በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የመስመር ውድድር አትሌት እዮብ ስመኝ የሩሲያ አትሌቶችን አስከራሪ ፉክክር በመስበር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን ሽመልስ ንጉሴ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ የወጣበት ነበር።
በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ዲንቃ ፍቃዱ ቀዳሚ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ሂርኮ ኃይሉ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በተጨማሪም በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ብርቱካን ገዳሙ የብር ሜዳሊያ ያስገኘች ሲሆን በ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ሀብታም ገበየሁ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን ፈጽማለች።
#ethiopianathletics #znamenskymemorial2026 #ethiopianpride #runningchampions #greenflood #moscow2026 #athletics #running #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
አትሌት አበባ አረጋዊ በኦታዋ ማራቶን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጻፈች
#ethiopia | በአንድ ወቅት በ1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ በነበራት ተደጋጋሚ ስኬት የርቀቱ ልዩ ባለሙያ በመባል የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አበባ አረጋዊ የ2026 የኦታዋ ማራቶንን በሴቶች ዘርፍ በአንደኝነት አጠናቃለች።
በዚሁ ውድድር ላይ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ኩፍቱ ታሂር በ2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ ቤቲ ቺፕኮሪር ደግሞ በ2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መሰረት በለጠ 4ኛ፣ መስከረም አሰፋ 5ኛ፣ መሰረት ደከቦ 7ኛ እንዲሁም ታደለች በቀለ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ፈጽመዋል።
በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ የትውልድ ሀገሯን ኢትዮጵያን ወክላ በ1,500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያገኘችውና በ2013 የሞስኮ አለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈችው አበባ አረጋዊ በ2014 የቤት ውስጥ አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደግሞ ስዊድንን ወክላ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።
የሁለት ጊዜ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊዋ አትሌት አበባ አረጋዊ ከዚህ የድል ጉዞዋ በኋላ በሰጠችው አስተያየት ለኦታዋ ማራቶን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓንና በማሸነፏም ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ገልጻለች።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ስዊድናዊቷ አትሌት አበባ አረጋዊ የኦታዋ ማራቶንን ለማሸነፍ የፈጀባት ጊዜ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ባለቤቷ አትሌት የማነ ፀጋይም በ2014 እና በ2018 የካናዳን የቦታው ሪከርድ በመስበር ማሸነፉ ይታወሳል።
ይህ አጋጣሚ ባልና ሚስቱ የኦታዋ ማራቶንን በተለያዩ አመታት በማሸነፍ አዲስ ታሪክ በጋራ እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።
✍️ በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል
#marathon #ottawamarathon #athletics #running #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
)

3 months ago
የጀግናዋ አትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ
#ethiopia | በበርካታ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ስታደርግ የቆየችው ዝነኛዋ አትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር ተፈጽሟል።
በመጋቢት ወር 1982 ዓ.ም በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የተወለደችው አትሌቷ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሩጫው ዓለም በመግባት ስኬታማ ጉዞ ስታደርግ ቆይታለች።
በ2003 ዓ.ም የመከላከያ መቻል ስፖርት ክለብን በመቀላቀል በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በ10 ኪሎ ሜትር፣ በሀገር አቋራጭ እንዲሁም በማራቶን ውድድሮች በርካታ ድሎችን ለሀገሯና ለክለቧ አስመዝግባለች።
አትሌት የብርጓል መለሰ እ.ኤ.አ በ2015 በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ፣ በ2013 በዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በሂውስተን፣ በሻንጋይ፣ በፕራግ እና በሊዝበን ማራቶኖች አንደኛ በመውጣት ታላቅ ውጤት ያስመዘገበች ጀግና ነበረች።
አትሌቷ በካናዳ ለሚካሄደው የኦታዋ ማራቶን ዝግጅት እያደረገች በነበረበት ወቅት በደረሰባት ድንገተኛ የጤና እክል ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
በዛሬው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የጦር ኃይሎች መኮንኖች፣ አትሌቶችና ቤተሰቦቿ በተገኙበት በመከላከያ የክብር ዘብ የታጀበ ሽኝት ተደርጎላታል።
አትሌት የብርጓል በትዳር አጋሯ አትሌት ወሰን ዘለቀና በሁለት ሕፃናት ልጆቿ እንዲሁም በሥራ ባልደረቦቿ ዘንድ በትሕትናዋና በአርአያነቷ የምትታወስ ታላቅ ስፖርተኛ ነበረች።
Getu Temesgen ( ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ በጀግናዋ አትሌት ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦ፤ ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እንመኛለን።
#athletics #ethiopianathletes #yebrgualmelese #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ዓለም ዋንጫ ወደ ሀገሬ መጥቷል!
— ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆነ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ተቀየረ! ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ ብቸኛ መብት ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የ2026 የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ በነፃ (FTA - Free To Air) በቀጥታ ያስተላልፋል።
ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚካሄዱትን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው ያያሉ።
ከዓለም ዋንጫ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸውን የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከ 2029 ዓ.ም. ድረስ በብቸኝነት የማስተላለፍ መብትንም ተቆጣጥሯል።
ጨዋታዎቹን በጥልቅ ትንታኔ፣ በልዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶችና በደመቁ ስቱዲዮዎች ለማቅረብ ጣቢያው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
"ይህ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የስፖርት ወዳጆች ትልቅ ኩራት ነው። የግል ጣቢያዎች እንዲህ ባለ ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደራቸው ለኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን ኳስ ለማየት 'ሳተላይት' እና 'ክፍያ' ብሎ መጨነቅ ቀረ፤ ሀገሬ ቴሌቪዥን ዓለምን ወደ ቤታችን አምጥቶታል።"
የስፖርት ድግሱ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይደምቃል!
#getu #hagerietv #fifaworld Cup2026 #ethiopianmedia #sportnews #worldcupinethiopia #athletics2029 #breakingnews #ሀገሬቴሌቪዥን #ዓለምዋንጫ #ስፖርት #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ኢራንን በጣልያን ለመተካት እየታሰበ ነወ ተባለ
#ethiopia | በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ዋዜማ፣ የእግር ኳሱን ዓለም የሚያነጋግር አዲስ ውዝግብ ተነስቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መልዕክተኛ የሆኑት ፓኦሎ ዛምፖሊ፣ ፊፋ ኢራንን ከውድድሩ ውጪ አድርጎ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ መጠየቃቸው ታውቋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በሜዳ ላይ በነበረው የማጣሪያ ጨዋታ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ባይችልም፣ ዛምፖሊ ግን ፊፋ በኢራን ላይ የቅጣት እርምጃ እንዲወስድና ለጣልያን ድንገተኛ ዕድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። ጥያቄው በዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች የታጀበ እንደሆነ ቢገለጽም፣ በስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ግን ግርምትን ፈጥሯል።
ለጣልያን ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ቢመስልም፣ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ግን ከሳምንት በፊት በሰጡት ማረጋገጫ ኢራን በውድድሩ ላይ እንደምትሳተፍ በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።
ፊፋ እስካሁን ድረስ በፖለቲካዊ ምክንያቶች ቡድኖችን ከመተካት ይልቅ በሜዳ ላይ ለተመዘገበ ውጤት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ይታወቃል።
ኢራን በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንድትታገድና ጣልያን እንድትተካ የቀረበ ጥያቄ።
ቡድኑ በማጣሪያው ወድቆ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በደብዳቤ የመግባት ዕድል እየተፈለገለት ነው።
ፕሬዝዳንት ኢንፋንቲኖ የኢራንን ተሳትፎ አስቀድመው አረጋግጠዋል።
ይህ ያልተጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በፊፋ ውሳኔ ላይ ለውጥ ያመጣ ይሆን ወይስ ኢራን በለመደችው መልኩ ጉዞዋን ትቀጥላለች? የሚለው ጉዳይ የብዙዎች መጠባበቂያ ሆኗል። ሆኖም የኳስ ወዳጆች እንደሚሉት "የሜዳ ውጤት በደብዳቤ አይቀየርም"።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbc
#fifa2026 #worldcup #italy #iran #gianniinfantino #footballnews #trumpenvoy #worldcupupdate #sportnews

🇪🇹 ኢትዮጵያ አልተቻለችም
📌ዋልያዎቹ ወደ ምድብ ድልድሉ በክብር ተሻግረዋል!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ተግዳሮት በድል ወጥተዋል። ከሳኦ ቶሜ ጋር በተደረገው የመልስ ጨዋታ ዋልያዎቹ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋንና ወሳኝዋን የማሸነፊያ ግብ ከመረብ ያሳረፈው ቸርነት ጉግሣ ነው። በዚህም ውጤት መሰረት ኢትዮጵያ የደርሶ መልስ ጨዋታውን በድምር 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማጠናቀቅ በቀጥታ ወደ ምድብ ድልድሉ ተቀላቅላለች።
አሁን ላይ ሙሉ ትኩረት የሚሆነው በ2027 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ሲሆን፣ የቡድኖቹ የዕጣ ድልድልም በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
እንኳን ደስ አላችሁ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #walyas #afcon2027 #ethiopianfootball #chernetgugsa #sportnews #ዋልያዎቹ #ኢትዮጵያ

5 months ago
🔴 የኦልድ ትራፎርድ የህልም ፕሮጀክት በፈተና ውስጥ!
#ethiopia | የማንችስተር ዩናይትድ አዲሱ የስታዲየም ግንባታ እቅድ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና በመሬት ይዞታ ውዝግብ ምክንያት እንቅፋት እየገጠመው መሆኑ ተሰማ። 100 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም እንዲኖረው ታስቦ የታቀደው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ አሁን ላይ ካለበት መዘግየት አኳያ ወጪው ከአምስት ጣራ ሊነካ እንደሚችል ተገምቷል።
ወቅታዊ የሆኑ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የዋጋ ንረት፦ ቀድሞ በ 2 ቢሊዮን ፓውንድ ይጠናቀቃል ተብሎ የታሰበው ግንባታ፣ አሁን ባለው ሁኔታ እስከ 3 ቢሊዮን ፓውንድ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተነግሯል።
* የመሬት ግብግብ፦ ለግንባታው በሚፈለገው መሬት ላይ ክለቡ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ሲያቀርብ፣ የመሬቱ ባለቤቶች ግን እስከ 400 ሚሊዮን ፓውንድ በመጠየቃቸው ድርድሩ ቆሟል።
* የጊዜ ገደብ ስጋት፦ ግንባታው በአፋጣኝ የማይጀመር ከሆነ፣ ሂደቱ እስከ አስር ዓመታት ሊራዘም እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።
* የአመራር ጫና፦ ሰር ጂም ራትክሊፍ በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት እና በሂደቱ ላይ ያላቸው አቋም በፕሮጀክቱ ቀጣይነት ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል እየተነገረ ነው።
ይህ "የሰሜኑ ኦልድ ትራፎርድ" ተብሎ የሚጠራው ታላቅ ተስፋ፣ በፋይናንስ እና በዲፕሎማሲያዊ ድርድሮች መካከል ሆኖ ቀጣይ እጣ ፈንታው በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #manchesterunited #oldtrafford #stadiumconstruction #sirjimratcliffe #footballnews #mufc #stadiumproject #sportnews

ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የጥገኝነት ጥሪ አቀረቡ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ላይ ለሚገኙት የኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
የክስ መነሻው ምንድን ነው?
የኢራን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በሀገሪቱ ይፋዊ ቴሌቪዥን በ"ሀገር ክህደት" ወንጀል መከሰሳቸው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል። ተጫዋቾቹ ወደ ሀገራቸው ቢመለሱ ከፍተኛ ስቃይ አልፎ ተርፎም የሞት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።
የትራምፕ አቋም
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
* ለአውስትራሊያ የቀረበ ጥሪ፦ በአሁኑ ወቅት ተጫዋቾቹን ይዛ የምትገኘው አውስትራሊያ በምንም መልኩ አሳልፋ እንዳትሰጥ እና ጥገኝነት እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል።
* የአሜሪካ አማራጭ፦ አውስትራሊያ ይህንን የማታደርግ ከሆነ፣ ተጫዋቾቹ ወደ አሜሪካ እንዲመጡና አስተማማኝ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ሀሳብ አቅርበዋል።
ይህ እርምጃ በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ሊያከርረው እንደሚችል እየተገመተ ይገኛል። በተለይም በስፖርተኞች ሰብአዊ መብት ዙሪያ ትልቅ ክርክር ቀስቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #trump #iran #womensfootball #asylum #usa #humanrights #politicalnews #ethiopia #sportnews

የአልሜሪያው አሰልጣኝ ግብዣ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ
#ethiopia | የፖርቹጋሉ ድንቅ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ የስፔኑን ክለብ አልሜሪያ 25 በመቶ ድርሻ መግዛቱን ተከትሎ፣ በሜዳ ላይ ስለሚኖረው ተሳትፎ አዳዲስ ወሬዎች እየተሰሙ ነው። የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ሩቢ፣ ሮናልዶን እንደ ባለቤት ብቻ ሳይሆን እንደ ተጫዋችም ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን በይፋ ገልጸዋል።
"ውሳኔው የራሱ ነው"
አሰልጣኝ ሩቢ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት፣ ሮናልዶ ወደ አልሜሪያ መጥቶ ቢጫወት ለክለቡ ትልቅ ኩራት እንደሚሆን ተናግረዋል። "ሮናልዶ ለአልሜሪያ ቢጫወት ድንቅ ነበር" ያሉት አሰልጣኙ፣ ጉዳዩ ግን በቀጥታ ከሮናልዶ ፍላጎት ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።
"ይህ ጥያቄ እሱ ራሱ መመለስ ያለበት ነው፤ ምክንያቱም አልሜሪያ የራሱ ክለብ ነው" ሲሉ አሰልጣኙ የሮናልዶን ባለቤትነት አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ለተጫዋች-ባለቤቱ ክፍት የሆነ በር
ሮናልዶ አሁንም በከፍተኛ የእግር ኳስ እርከን ላይ መቆየት እንደሚችል የሚታመን ሲሆን፣ አሰልጣኝ ሩቢም የኮከቡን መምጣት በደስታ እንደሚቀበሉት ገልጸዋል።
* የአሰልጣኙ ቁርጠኝነት፦ "ሮናልዶ መጫወቱን መቀጠል ከፈለገ እጃችንን ከፍተን እንቀበለዋለን።"
* ስለ አሰልጣኞች ስምምነት፦ "አሰልጣኙ ማንም ቢሆን ሮናልዶን ለማሰለፍ ጥርጣሬ ይኖረዋል ብዬ አላስብም" በማለት በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
ይህ የሮናልዶ "ባለቤት እና ተጫዋች" የመሆን ዕድል ከተሳካ፣ በስፔን ላሊጋ (ወይም በክለቡ አሁናዊ ሊግ) አዲስ ታሪክ ሊጻፍ ይችላል። "አለቃው" ወደ ሜዳ ገብቶ ለራሱ ክለብ ጎል ሲያስቆጥር ማየት ለደጋፊዎች ትልቅ ጉጉትን ፈጥሯል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #tikvah #cristianoronaldo #almeria #cr7 #footballnews #laliga #ronaldo #ethiopia #sportnews

ቅሬታ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ
"ላባችን ሳይደርቅ ክፍያችን ይፈጸምልን!" 🏃♂️⚖️
#ethiopia | በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር በድምቀት ቢጠናቀቅም፣ ከጀርባው ግን የባለሙያዎች እሮሮና ምሬት ሰፍኖ ይገኛል። ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ50 በላይ ዳኞችና የፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች ላለፉት 10 ቀናት አበላቸው ሳይከፈላቸው ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
📌 ዋና ዋና ቅሬታዎች፦
የክፍያ መዘግየት፦
ውድድሩ ካለቀ 10 ቀናት ቢቆጠሩም፣ በህጉ መሠረት መከፈል የነበረበት አበል እስካሁን አልተከፈለንም ብለዋል።
ማህበራዊ ቀውስ፦
"በቀን 900 ብር አበል እየተሰጠን፣ በዚህ የኑሮ ውድነት መኝታና ምግብ ችለን፣ አንድ መኝታ ላይ ሁለት እየተኛን ስራችንን ብንሰራም አበላችንን በመከልከላችን ለከፍተኛ ችግርና ለብድር ተጋልጠናል" ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል።
የሚኒስቴሩ ድጋፍና የፌዴሬሽኑ ዝምታ፦ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለውድድሩ አስፈላጊውን ፈሰስ ቀደም ብሎ ቢያደርግም፣ ፌዴሬሽኑ ለምን ክፍያውን እንዳዘገየው ግልጽ እንዳልሆነ ተገልጿል።
🚨 የመረጃ መውጣትና የፌዴሬሽኑ ድንገተኛ ሩጫ፦
ይህ መረጃ ለሚዲያ መድረሱ ከተሰማ በኋላ፣ ፌዴሬሽኑ "መረጃው ቀድሞን እንዳይወጣ" በሚል ስጋት ለዳኞቹ በአካውንታቸው ክፍያውን ለመፈጸም ሩጫ መጀመሩን የሀትሪክ ስፖርት ዘገባ አመልክቷል።
🔇 የተቋሙ ምላሽ፦
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት፣ "ከሚዲያ የሚደወል ስልክ አታንሱ" በሚል መመሪያ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ይህ የህዝብን የመረጃ ባለቤትነት የሚክድ አሰራር በስፖርቱ አመራር ላይ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ያሳያል።
#ethiopianathletics #athleticsfederation #adama #fairpay #sportnews #hattricksport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
ከቂም ይልቅ ለሙያ ክብር
አቶ ዱቤ ጅሎ ወደ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መጡ! 🇪🇹🏆
#ethiopia | በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ ያልተጠበቀና ብዙዎችን ያስገረመ ታላቅ ሹመት ተሰምቷል።
ለረጅም ጊዜ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋር የከረረ የሃሳብ ልዩነትና ትችት ውስጥ የነበሩት አንጋፋው ባለሙያ አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኮሚቴው አዲሱ የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
ለምን ይሄ ሹመት ትልቅ ትርጉም አለው?
🤝 ቂምን ወደ ጎን ማለፍ፦ ዶክተር አሸብር ሲሰነዘርባቸው የነበረውን ጠንካራ ትችት ወደ ጎን በመተው፣ የአቶ ዱቤን የአትሌቲክስ እውቀት ለሀገር ጥቅም ለማዋል መወሰናቸው ከበርካቶች አድናቆትን አትርፎላቸዋል።
🏃♂️ የልምድ ተራራ፦
አቶ ዱቤ ጅሎ በአትሌትነት፣ በፌዴሬሽን ኃላፊነት፣ በቴክኒክ ዳይሬክተርነትና በስፖርት ኮሚሽነርነት ያለፉ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ "ምርጥ የቴክኒክ ዳይሬክተር" ተብለው የተጠሩ የዘርፉ ቁንጮ ባለሙያ ናቸው።
🔄 ከፌዴሬሽኑ ወደ ኦሎምፒክ፦
በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ "ላገልግል" ብለው ቢጠይቁም በፕሬዝዳንቱ ኮማንደር ስለሺ ስህን በኩል በሩ ተዘግቶባቸው የቆዩት አቶ ዱቤ፣ አሁን በኦሎምፒክ ኮሚቴ በኩል የሙያ ማገልገያ እድላቸውን አግኝተዋል።
💡 የታዛቢዎች አስተያየት፦
ይህ ውሳኔ "ዘመናዊ አመራር ቂም አይይዝም" የሚል መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ በተለይ በአትሌቲክሱ ያለውን የቴክኒክ ክፍተት ለመሙላት፣ ከአለም አቀፍ ግንኙነትና ከስልጠና ጥራት አኳያ አቶ ዱቤ ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል ተብሎ ይታመናል።
በጋዜጠኛ #ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት)
የተገኘው ይህ መረጃ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት አመራር ላይ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት እንደሚችል ይጠበቃል።
የስፖርት ቤተሰቡ ሆይ፤ ይህን ያልተጠበቀ ሹመት እንዴት አያችሁት? ከቂም ይልቅ ለሙያ ቅድሚያ መስጠቱ በሌሎችም ዘንድ ሊለመድ ይገባል? አስተያየታችሁን አጋሩን። 👇
#ethiopianolympics #dubejilo #drashebir #athleticsethiopia #sportnews #breakingnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

"አንተ እውነተኛ አሸናፊ ነህ!" - ጂያኒ ኢንፋንቲኖ
#ethiopia | ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ንጉስ እና የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ 41ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በዛሬው ዕለት እያከበረ ይገኛል። ይህንን ተከትሎም የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ (FIFA) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ለተጫዋቹ የክብር መልእክት ልከዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ሮናልዶን "የጠንካራ ሥራ እና የተስፋ ያለመቁረጥ ተምሳሌት" ሲሉ አሞካሽተውታል።
የኢንፋንቲኖ መልእክት ዋና ዋና ነጥቦች፡
* ሪከርድ ሰባሪነቱ፡ "አንተ እውነተኛ አሸናፊ እና ታሪክ ሰሪ ነህ" ሲሉ የሮናልዶን ድል አድራጊነት መስክረዋል።
* አርአያነቱ፡ "ሁልጊዜም የተሻለ ለመሆን ስለምትጥር እና ትልቅ ህልም ያላቸውን ሁሉ ስለምታነሳሳ እናመሰግንሃለን" በማለት ለትውልድ ያለውን አስተዋጽኦ ገልጸዋል።
ኢንፋንቲኖ መልእክታቸውን የቋጩት ለሮናልዶ መልካም ልደትን በመመኘት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #cristianoronaldo #cr7 #fifa #gianniinfantino #footballlegend #sportnews #hbdcr7

⚡️ ባካሪ ሳኛ በአድዋ ድል መታሰቢያ!
#ethiopia | የቀድሞው የፈረንሳይ እና የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ (የአርሰናል እና የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች) ባካሪ ሳኛ አዲስ አበባን እየጎበኘ ነው።
የጉብኝቱ ዋና ዋና ኩነቶች:
ቦታ: የአድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት የአፍሪካን የድል ታሪክ ተመልክቷል።
አድናቆት: በመታሰቢያው ውስጥ የሚገኘውን ዘመናዊ ጂምናዚየም (Fit_corner) ጎብኝቶ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን በመግለጽ አድናቆቱን ሰጥቷል።
ሳኛ በሜዳ ላይ ባሳየው ዲሲፕሊን እና አመራርነት እንዲሁም በማህበራዊ ተሳትፎው የሚታወቅ ተወዳጅ ስፖርተኛ ነው።
#bacarysagna #adwamuseum #addisababa #sportnews

"አሁን ላይ የዓለማችን ምርጡ ቡድን አርሰናል ነው!"
- ፔፕ ጋርዲዮላ 🗣️⚽
#ethiopia | የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ለተቀናቃኛቸው አርሰናል ያላቸውን አድናቆት ገለጹ!
ነገ ከዎልቭስ ጋር ለሚኖራቸው ጨዋታ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ "አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊግ፣ በፕሪሚየር ሊግ፣ በኤፍ ኤ ዋንጫ እና በካራባኦ ዋንጫ እያሳየ ያለው ብቃት አሁን ላይ የዓለማችን ምርጡ ቡድን ያስብለዋል" ሲሉ ተደምጠዋል።
ሲቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዩናይትድ እና በቦዶ ግሊምት መሸነፉ ይታወሳል።
ፔፕ አክለውም "አርሰናል አንድ እድል እንደሚሰጠን ተስፋ አደርጋለሁ" በማለት የዋንጫው ፉክክር እንዳልተጠናቀቀ ጠቁመዋል።
የፔፕ ንግግር ከልብ ነው ወይስ የተለመደው 'Mind Game' (የስነ-ልቦና ጨዋታ)? 🤔
#arsenal #mancity #pepguardiola #premierleague #sportnews

7 months ago
🏟️ የአደይ አበባ ስታዲየም ዓለም አቀፍ እውቅናን አገኘ!
#ethiopia | በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘውና የኢትዮጵያ ስፖርት አዲስ ተስፋ ተደርጎ የሚወሰደው የአደይ አበባ ስታዲየም፣ የመጫወቻ ሜዳው በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ተገምግሞ ብቃቱን ማረጋገጡ ተበሰረ።
✅ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ግምገማ
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የስታዲየሙ መጫወቻ ሜዳ በፊፋ የተቀመጡትን ጥብቅ መመዘኛዎች በከፍተኛ ውጤት ማለፍ ችሏል። ይህም ሜዳው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ደረጃ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
🌟 የስታዲየሙ አስፈላጊነት
የአደይ አበባ ስታዲየም ሜዳ ይህንን እውቅና ማግኘቱ፦
* ኢትዮጵያ በሀገሯ ውስጥ የዓለም አቀፍና የአህጉራዊ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅሟን ያሳድጋል።
* ለብሔራዊ ቡድኑና ለክለቦች ጥራቱን የጠበቀና ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራ ይፈጥራል።
* የስታዲየሙ አጠቃላይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ሀገራችንን በስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ ያደርጋል።
ይህ እውቅና በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ስታዲየም ትልቅ ስኬት ሲሆን፣ ቀሪ ስራዎች ተጠናቀው ሜዳው ሙሉ በሙሉ ለጨዋታ ዝግጁ የሚሆንበት ቀን በናፍቆት ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#አደይአበባስታዲየም #ኢትዮጵያ #እግርኳስ #ፊፋ #ስፖርት #አዲስአበባ #adeyabebastadium #ethiopia #fifa #football #sportnews

🏆 የአፍሪካ ዋንጫ፡ አስተናጋጇ ሞሮኮ እና ሴኔጋል ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ! ⚽️
#ethiopia | በአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ትልልቅ ቡድኖች ድል አስመዝግበዋል።
🇲🇦 ሞሮኮ 2 - 0 ካሜሩን 🇨🇲
አስተናጋጇ ሞሮኮ ካሜሩንን በመርታት ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፋለች።
ጎል አስቆጣሪዎች፡ ብራሂም ዲያዝ እና ኢስማኤል ሳባሪ።
የኮከቡ ብቃት፡ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ብራሂም ዲያዝ በውድድሩ 5ኛ ግቡን በማስቆጠር ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።
ቀጣይ ተጋጣሚ፡ ሞሮኮ በግማሽ ፍጻሜው ከአልጄሪያ እና ናይጄሪያ አሸናፊ ጋር ትገናኛለች።
🇸🇳 ሴኔጋል 1 - 0 ማሊ 🇲🇱
ሴኔጋል በጠባብ ውጤት ማሊን በማሸነፍ ጉዞዋን ቀጥላለች።
ወሳኝ ክስተት፡ የማሊው ኢቭ ቢሱማ በ45ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መወገዱ ለማሊ ፈተና ሆኖ ነበር።
ጎል አስቆጣሪ፡ ኢልማን ኒዳየ የሴኔጋልን የማለፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ቀጣይ ተጋጣሚ፡ ሴኔጋል በግማሽ ፍጻሜው ከግብጽ እና ኮትዲቯር አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
የዘንድሮውን ዋንጫ ማን የሚያነሳው ይመስላችኋል? ግምታችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ! 👇
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#afcon2025 #morocco #senegal #football #africacupofnations #sportnews

⚽️ አርሰናል እና ሊቨርፑል ነጥብ ተጋሩ!
FT: አርሰናል 0-0 ሊቨርፑል
#ethiopia | በጉጉት የተጠበቀው የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በኤምሬትስ ስታዲየም ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የጨዋታው አንኳር ነጥቦች፡-
ያመለጠው ዕድል፡ የሊጉ መሪ አርሰናል፤ የማንችስተር ሲቲን ነጥብ መጣል ተከትሎ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 8 የማስፋት ወርቃማ ዕድል አምክኗል።
የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ፡ መድፈኞቹ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ፍፁም ብልጫ ቢወስዱም የሊቨርፑልን መረብ መድፈር ተስኗቸዋል።
ደረጃ ሰንጠረዥ፡
1️⃣ አርሰናል፡ 49 ነጥብ (አሁንም መሪ)
4️⃣ ሊቨርፑል፡ 35 ነጥብ (ከአርሰናል በ14 ነጥብ ዝቅ ብሎ)
ይህ ውጤት ለማን ይጠቅማል? አርሰናል ዋንጫውን ለማንሳት ይህ ነጥብ መጣል ዋጋ ያስከፍለው ይሆን? ሀሳቦን ያጋሩን! 👇
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#arsenal #liverpool #premierleague #emirates #draw #ethiopia #sportnews

Comments