ሞሮኮ በሴኔጋል ላይ ክስ መሰረተች!
በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ሴኔጋል ሜዳ ጥላ መውጣቷን ተከትሎ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ወደ CAF እና FIFA በመውሰድ የህግ እርምጃ እንደሚጀምር አስታውቋል።
ምን ተፈጠረ?
ትላንት እሁድ ጥር 10/2018 ዓ.ም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ መጠናቀቂያ ላይ ለሞሮኮ የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጥቶ ነበር። በዚህ ውሳኔ የተቆጡት የሴኔጋል ተጫዋቾች በቴክኒክ ዳይሬክተራቸው ፓፔ ቲያው ትዕዛዝ ለ15 ደቂቃ ያህል ሜዳ ጥለው ወጥተው ነበር።
የሞሮኮ ቅሬታ፦
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ፦
❌ የሴኔጋል ተጫዋቾች ሜዳ ጥለው መውጣታቸው በጨዋታው ሂደት እና በተጫዋቾች ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።
❌ ዳኛው የሰጡት የፍጹም ቅጣት ምት ትክክል ሆኖ ሳለ፣ የሴኔጋል ድርጊት ግን ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለውና ህግ የጣሰ ነው።
የጨዋታው ውጤት፦
ሴኔጋል ወደ ሜዳ ተመልሳ ብራሂም ዲያዝ የፍጹም ቅጣት ምቱን ስቶታል። ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቶ ሴኔጋል በፓፔ ጉዬ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ብታነሳም፣ ጉዳዩ አሁን ወደ ህግ መድረኩ ተሻግሯል።
ካፍ (CAF) በጉዳዩ ላይ ምርመራ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፣ የሴኔጋል አሰልጣኝ በድርጊታቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።

7 months ago