Logo
Getu Temesgen
🇪🇹 የኢትዮጵያ ኩራት!
አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በካፍ ቴክኒካል ቡድን ውስጥ! 👏

* ​ጨዋታዎቹን የሚተነትኑት የካፍ ልሂቃን ውስጥ አብርሃም መብራቱ ይገኝበታል
#ethiopia | ​በሞሮኮ እየተካሄደ ባለው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2025) ላይ፤ ጨዋታዎችን በጥልቀት የሚገመግመው እና ምርጥ ተጫዋቾችን የሚመርጠው የካፍ የቴክኒክ ጥናት ቡድን (Technical Study Group - TSG) ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተካቷል።

​የአብርሃም ሚና ምንድን ነው?
በአህጉሩ ካሉ ምርጥ የካፍ ኢንስትራክተሮች እና የቀድሞ ተጫዋቾች ጋር በመሆን፤ የቡድኖችን ቴክኒካዊ ብቃት መገምገም፣ የውድድሩን ታክቲካል ሂደት መተንተን እና ለፊፋ (FIFA) እና ለካፍ (CAF) ሪፖርት ማቅረብ ነው።

​ትናንት አርሰን ቬንገር የጎበኙት እና ያደነቁት ይህንኑ የአብርሃም መብራቱ አባል የሆነበትን ቡድን ነው።

​አብርሃም መብራቱ በተለያዩ ጊዜያት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር በመሆን አህጉራዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

​እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹⚽

​#abrahammebratu #caf #tsg #afcon2025 #ethiopianpride #technicalstudygroup #ethiopia

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.