1 month ago
የለንደን ማራቶን ነገ ይካሄዳል
* ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ተዘጋጅተዋል
#ethiopia | ነገ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠውና በጉጉት የሚጠበቀው የለንደን ማራቶን ይካሄዳል። የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ክብራቸውን ለማስጠበቅና አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ወደ ለንደን አምርተዋል።
በሴቶች
ያለፈው ዓመት ሻምፒዮን እና በለንደን ማራቶን (ሴቶች ብቻ በሚሳተፉበት) የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት (2:15:50)! ትግስት ባደረገቻቸው ያለፉት 6 ማራቶኖች ከ2ኛ ደረጃ ዝቅ ብላ አታውቅም። ነገም ክብሯን እንደምታስጠብቅ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባታል።
በወንዶች
የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ ለ5ኛ ጊዜ በለንደን ይሳተፋል። ከዚህ ቀደም በተሳተፈባቸው 4ቱም ውድድሮች እስከ 6ኛ ባለው ደረጃ ማጠናቀቁ ለነገው ድል ትልቅ መተማመኛ ሆኖታል።
በ10 ሺህ ሜትር ዝነኛው ዮሚፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ 42 ኪሎ ሜትር (ማራቶን) የሚሮጥበት ታሪካዊ መድረክ ይሆናል። ዮሚፍ በማራቶን ምን ዓይነት አስገራሚ ውጤት ይይዝ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።
ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ፣ ዩጋንዳውያኑ ጃኮብ ኪፕሊሞ እና ጆሽዋ ቼፕቴጋይ ለኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቀናቃኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ለንደን ማራቶን ለኢትዮጵያውያን የድል አውድማ ነው። ትግስት አሰፋ በለንደን ጎዳናዎች ላይ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት እንደምትስብ ጥርጥር የለኝም። ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ ወደ ማራቶን ያደረገው ሽግግር ለሀገራችን አትሌቲክስ አዲስ ተስፋ ነው። ይህንን ታላቅ ውድድር በሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ መመልከት መቻላችን ደግሞ ድሉን ከቤታችን ሆነን እንድንጋራ ያደርገናል።
ድል ለኢትዮጵያ አትሌቶች!
#getu #londonmarathon2026 #ethiopianathletes #tigistassefa #tamirattola #yomifkejelcha #athleticsnews #worldrecord #hagerietv #ለንደንማራቶን #ኢትዮጵያ #ትግስትአሰፋ #ታምራትቶላ #ዮሚፍቀጀልቻ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ዓለም ዋንጫ ወደ ሀገሬ መጥቷል!
— ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆነ
#Ethiopia | የኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ተቀየረ! ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ ብቸኛ መብት ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የ2026 የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ በነፃ (FTA - Free To Air) በቀጥታ ያስተላልፋል።
ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚካሄዱትን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው ያያሉ።
ከዓለም ዋንጫ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸውን የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከ 2029 ዓ.ም. ድረስ በብቸኝነት የማስተላለፍ መብትንም ተቆጣጥሯል።
ጨዋታዎቹን በጥልቅ ትንታኔ፣ በልዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶችና በደመቁ ስቱዲዮዎች ለማቅረብ ጣቢያው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
"ይህ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የስፖርት ወዳጆች ትልቅ ኩራት ነው። የግል ጣቢያዎች እንዲህ ባለ ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደራቸው ለኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን ኳስ ለማየት 'ሳተላይት' እና 'ክፍያ' ብሎ መጨነቅ ቀረ፤ ሀገሬ ቴሌቪዥን ዓለምን ወደ ቤታችን አምጥቶታል።"
የስፖርት ድግሱ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይደምቃል!
#getu #hagerietv #fifaworld Cup2026 #ethiopianmedia #sportnews #worldcupinethiopia #athletics2029 #breakingnews #ሀገሬቴሌቪዥን #ዓለምዋንጫ #ስፖርት #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
የእስር ቤት ጥበቃ ሰራተኛው ዴኒስ ኦሜዲ በአፍሪካ ዋንጫ
#ethiopia | ዴኒስ ኦሜዲ ይባላል የቀድሞ የኪታራ ኤፍሲ አጥቂ እና ለዩጋንዳ ክሬንስ ቁልፍ ተጫዋች የነበረ ነው፡፡በወቅቱም የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል።
አጥቂው ዩጋንዳ ለ2025 የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ በመርዳት እና የ2024ቱን የስታንቢክ ኡጋንዳ ዋንጫ ከኪታራ ኤፍሲ ጋር በማሸነፍ ያሳየው አስደናቂ ብቃት ከፍተኛውን ሽልማት አስገኝቶለታል።
ዴኒስ ኦሜዲ ያስቆጠራት ምርጥ ቄንጠኛ ጎል በ2024 የፊፋ ፖሽካሽ የአመቱ ምርጥ ጎል በመባል እጩ እንደነበረች የሚታወስ ነው::
ታዲያ ይህ አጥቂ ከሀገሩ ዩጋንዳ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ሞሮኮ ላይ ከትሟል፡፡በምድብ ሶስት ላይ የምትገኘው ዩጋንዳ ትናንት ምሽት ከቱኒዝያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 3ለ1 መሸነፏ ይታወሳል፡፡
ብቸኛዋን አንድ ጎል ለዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በ90 ደቂቃ ጭማሪ ያስቆጠረው አጥቂው ዴኒስ ኦሜዲ ሲሆን ይህም ተጨዋች በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውም ለሀገሩ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
ዴኒስ ኦሜዲ የትርፍ ጊዜ እግር ኳስ ተጨዋች እንደነበር ብዙ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን እንዲሁም ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ በነርሲንግ ዲፕሎማውን እንዳገኘ ታውቋል፡፡
ሌላው የዴኒስ ኦሜዲ አስገራሚ የህይወት ጉዞ ሲቀጥል ወደ አፍሪካ ዋንጫ ከማቅናቱ በፊት የህይወት መንገዱ ተቀይሮ የእስር ቤት ጥበቃ ሰራተኛ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ተገልጿል።
31 ዓመቱ ላይ የሚገኘው ዴኒስ ኦሜዲ ከስድስት አመታት በኋላ ዩጋንዳን በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ወክሎ ሞሮኮ ከትሟል፡፡
ዩጋንዳ በምድቡ የሁለተኛ ዙር ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ ከታንዛኒያ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡
#hagerietv

6 months ago
“የግድያ ማስፈራሪያ ደርሶብኝ ነበር” ሩኒ
#ethiopia | እንግሊዛዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ዋይን ሩኒ የልጅነት ክለቡን ኤቨርተንን ለቆ ወደ ወደ ኦልድትራፎርድ ባቀናበት ወቅት የግድያ ማስፈራሪያ ዛቻዎች ይደርሱት እንደነበር ተናግሯል፡፡
እ.ኤ.አ 2004 በ27 ሚሊዮን ፓውንድ ከኤቨርተን ማንችስተር ዩናይትድን በተቀላቀለበት ወቅት የመርሲሳይዱ ክለብ ደጋፊዎች የማስፈራሪያ እና የግድያ ዛቻ ይልኩበኝ ነበር ሲል ገልጿል፡፡
የቤተሰቦቹ ቤት ላይ ሳይቀር የማስፈራሪያ ጽሁፎች ጭምር ተፅፈው እንደነበር የተናገረው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪካዊ ተጨዋች እንደዚህ አይነት ነገር ሲገጥማቸው ተጨዋቾች በአዕምሮ ጠንካራ መሆን አለባቸው ሲል ለቢቢሲ ስፖርት በሰጠው ቃል ገልጿል።

Sponsored by
Surafel
9 months ago
የፔንታጎን ስያሜ ወደ ጦር ሚንስቴር ሊቀየር ነው
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገሪቱን መከላከያ ሚንስትር ስያሜ የጦር ሚንስቴር ወደሚል ሊቀይሩት እንደሆነ ተሰምቷል።
ይሁን እንጂ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በአሜሪካ ኮንግረስ በኩል ተቀባይነት ማግኘት እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን የፔንታገን ሁለተኛ ስያሜ አድርገው የመጠቀም ስልጣን እንዳላቸው ተገልጿል።
የጦር ወይም የጦርነት ሚንስቴር የሚለው ስያሜ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 1947 ድረስ የተቋሙ ስያሜ ሆኖ ሲያገለግል እንደነበረ ይታወሳል።
ስያሜው የተቀየረው ከዛ በፊት የተለያዩ የነበሩት የአሜሪካ ጦር፣ ባህር ሀይል እና አየር ሀይል በአንድ አደረጃጀት ስር እንዲመሩ የሚያስችለው ውሳኔ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ሀሪ ትሩማን መፈረሙን ተከትሎ እንደነበር አስታውሶ የዘገው ሮይተርስ ነው ። #hagerietv

11 months ago
በሚቀጥሉት ቀናት ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተጠቆመ
#ethiopia | በሚቀጥሉት ቀናት በምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በመጪዎቹ የነሃሴ የመጀመሪያዎቹ አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህም የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና የሚኖረው ቢሆንም፤ ተያያዥ ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች መተግበር ይገባል ተብሏል፡፡ #hagerietv

የዝውውር ገበያውን ክብረወሰን የሰበረችው ኦሊቪያ ስሚዝ
#ethiopia | በናኦሚ ግርማ ተይዞ የነበረውን የሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች የዝውውር ክፍያ ክብረ ወሰን ለአርሰናል በፈረመችው አጥቂ ኦሊቪያ ስሚዝ ተሰብሯል፡፡
ካናዳዊቷ አጥቂ ኦሊቪያ ስሚዝ በሴቶች እግርኳስ ታሪክ ክብረወሰን የሆነውን የናኦሚ ግርማ የ900 ሺህ ፓውንድ ዝውውር እንደሰበረችው ታውቋል፡፡
ናኦሚ ባሳለፍነው ጥር ከአሜሪካው ክለብ ሳን ዲዬጎ ቼልሲን መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ ሌላኛውን ክብረውሰን የሰበረችው ኦሊቪያ ስሚዝ 1 ሚሊዮን ፓውንድ በሆነ ዋጋ ከሊቨርፑል አርስናልን በመቀላቀል ነው ያሻሻለችው፡፡
በዚህም በሴቶች የእግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛውን ክፍያ በማግኘት ወደ ሌላ ክለብ የተዘዋወረች ተጫዋች ለመሆን ችላለች።የ20 ዓመቷ ወጣት ስሚዝ ከሻምፒየንስ ሊጉ ባለቤት አርስናል ጋር የአራት ዓመት ኮንትራት ፈርማለች።
ኦሊቪያ ስሚዝ ከአንድ አመት በፊት ከፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሊቨርፑል መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡
ተጨዋቿ ከመርሲሳይዱ ክለብ ጋር ቀሪ የሁለት ዓመት ውል ቢኖራትም ሊቨርፑል የቀረበለትን ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ ውድቅ ማድረግ እንዳልቻለ ታውቋል፡፡
ስሚዝ በመጀመሪያ የውድድር ዘመን ለሊቨርፑል በተሰለፈችባቸው ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ማስቆጠር ስትችል እንዲሁም ለሀገሯ ካናዳ 18 ጨዋታዎችን በማድረግ አራት ግቦችን ማስቆጠር ችላለች፡፡ #hagerietv

ኤስሚላን የራስሙስ ሆይሉንድን ሁኔታ ጠይቋል
#ethiopia | የጣልያን ሴሪአው ክለብ ኤሲሚላን በማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ ጊዝያትን ማሳለፍ የተሳነው ዴንማሪካዊው አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድን ማሰፈረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ክለቡን መጠይቁ ተዘግቧል፡፡
እኤአ በ2023 ከጣልያኑ ክለብ አታላንታ 72 ሚሊዮን ፓውንድ በሚጠጋ የዝውውር ዋጋ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ራስሙስ ሆይሉንድ በመጀመርያው የውድድር አመት የኦልድትራፎርድ ቆይታው ትልቅ ተስፋን የሰጠ እንቅስቃሴን ማደረግ ችሎ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ሆይሉንድ በ2023/24 የውድድር ዘመን በ43 ጨዋታዎች 16 ጎሎችን አስቆጥሮ 2 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ ማቀበሉ የሚታወስ ነው፡፡
የ22 አመቱ ሆይሉንድ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር አጀማመሩ ጥሩ እንደነበር ቢታወስም አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ወደ ክለቡ ከመጡ ወዲህ ደካማ የተባለ ጉዞን ያሳለፈበት ሆኗል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር አመት ባጠቃላይ 10 ጎሎችን ብቻ ያስቆጠረው ሆይሉንድ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸው ጎሎች 4 ብቻ መሆናቸው ተጨዋቹ በቀጣይ የኦልድትራፎርድ ቆይታው ትልቅ ጥያቄ እንዲነሳበት ያደረገ ሆኗል፡፡
የጣልያኑ ክለብ ኢንተርሚላን ሆይሉንድን ማስፈረም ፍላጎት ካላቸው ክለቦች መካከል ቀዳሚው እንደነበር ቢገለጸም ሌሎች አጥቂዎችን መመልከት መጀመሩን ተከትሎ በተቀናቃኙ ኤስሚላን አይን አርፎበታል፡፡
በአሰልጣኝ ማስሚላኖ አሌግሪ የሚመራው ኤስሚላን ስለተጨዋቹ ሁኔታ ማንችስተር ዩናይትድን ማናገራቸው ተዘግቧል፡፡
በማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም በተጨዋቹ በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም ነገር ግን ክለቡ ትክክለኛ ዋጋ ከቀረበለት አጥቂውን ለመሸጥ አይኑን እንደማያሽ በመዘገብ ላይ ይገኛል፡፡ #hagerietv

Comments