3 months ago
ኢራን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቿን ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ ለማዛወር ከፊፋ ጋር እየተደራደረች ነው
#ethiopia | በፖለቲካዊ ውጥረትና በደህንነት ስጋት ምክንያት የኢራን እግር ኳስ ማህበር የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎቹን በአሜሪካ ምትክ በሜክሲኮ ለማከናወን ጥያቄ ማቅረቡ ተሰማ። የኢራን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ እንደገለጹት፣ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለኢራን ብሔራዊ ቡድን በቂ የደህንነት ዋስትና ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቡድኑ ወደ አሜሪካ የመጓዝ ዕቅድ የለውም።
ፕሬዝዳንቱ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ትራምፕ ለቡድናችን ደህንነት ማረጋገጫ ባልሰጡበት ሁኔታ ወደ አሜሪካ መጓዝ አንችልም" ያሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ጨዋታዎቹን ወደ ሜክሲኮ ለማዛወር ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ውሳኔ የተሰማው የኢራን ስፖርት ሚኒስትር አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አጠራጣሪ መሆኑን በገለጹ ማግስት ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ኢራን መሳተፍ እንደምትችል ቢገልጹም፣ "ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ባይመጡ ይሻላል" የሚል ይዘት ያለው ማስጠንቀቂያ መስጠታቸው ይታወሳል።
እንደ መጀመሪያው መርሃ ግብር ኢራን ሁለት የምድብ ጨዋታዎቿን በሎስ አንጀለስ፣ ቀሪውን አንድ ጨዋታ ደግሞ በሲያትል ለማከናወን ተመድባ ነበር። አሁን በቀረበው ጥያቄ ላይ ፊፋ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል::
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #worldcup2026 #fifa #iranfootball #mexico2026 #sportsnews #breakingnews #footballpolitics