3 months ago
''ኢራንን አንተካም!" — ጣልያን
#ethiopia | ፊፋ ኢራንን ከዓለም ዋንጫ አስወግዶ በምትኳ ጣልያንን እንዲያስገባ ያቀረቡት ጥያቄ በራሷ በጣልያን መንግሥትና በስፖርት አመራሮቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው።
የጣልያን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሉቺያኖ ቦንፊግልዮ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጠንከር ያለ ምላሽ፣ ጣልያን በሜዳ ላይ ባላሳየችው ውጤት በፖለቲካዊ መንገድ ወደ ዓለም ዋንጫ እንድትገባ የቀረበውን ሐሳብ እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።
"ይሄ ከተፈጠረ እንደ ስድብ ነው የምወስደው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ማንኛውም ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማለፍ ያለበት በችሎታውና በጠንካራ ሥራው መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አቋም ተጋርተዋል፦
"ይሄ አስፈላጊ አይደለም፤ ሜዳ ላይ ነው ማለፍ ያለብን" በማለት በጓሮ በር ወደ ውድድሩ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጂዮርጌቲ፦ ዜናው በግላቸው እንዳሳፈራቸው ገልጸው፣ "በዛ መንገድ ከሄድን አፍራለሁ" ሲሉ የሐሳቡን አሳፋሪነት ገልጸዋል።
ምንም እንኳን የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለ2026ቱ ዓለም ዋንጫ ባለማለፉ ደጋፊዎቿ ቢያዝኑም፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ግን ከውጤት ይልቅ ለስፖርታዊ ጨዋነትና ለፍትሐዊ ውድድር ቅድሚያ በመስጠት ዓለም አቀፍ አድናቆትን እያገኙ ይገኛሉ።
ጣልያን "በችሎታችን ካላለፍን በሌላው ስንብት አንገባም" የሚል ጠንካራ መልዕክት ለዓለም አስተላልፋለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#italy #fifa #worldcup2026 #iran #footballnews #sportsmanship #fairplay #azzurri #lucianobonfiglio #andreaabodi #worldcupupdate

4 months ago
🇮🇹 የጣልያን እግር ኳስ መርዶ
አዙሪዎቹ ለ16 ዓመታት ከዓለም ዋንጫ ተለዩ
#ethiopia | በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ስሟ በወርቅ የተጻፈው ጣልያን፣ ዛሬ የቀራት የትዝታ ማዕበል ብቻ ሆኗል።
እነ ማልዲኒ፣ ፒርሎ፣ ቡፎንና ባጂዮን ያፈራው የጣልያን ማህፀን፣ ዛሬ በታሪኩ አስከፊ የሚባለውን የውድቀት ዘመን እያሳለፈ ይገኛል።
ጣልያን ከ2018 እና ከ2022 በመቀጠል፣ አሁን ደግሞ ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆናለች። ይህም ለአንድ ትልቅ ሀገር ለ16 ዓመታት (አራት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች) ከመድረኩ መራቅ በታሪክ የመጀመሪያዋ ያደርጋታል።
በትናንትናው ወሳኝ የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ፣ በፊፋ 71ኛ ደረጃ ላይ በምትገኘው ቦስኒያ ሄርዞጎቪና በመለያ ምት 4 ለ 1 ተሸንፋ ተሰናብታለች።
ሞይስ ኬን ጣልያንን መሪ ቢያደርግም፣ የባስቶኒ ቀይ ካርድና የቦስኒያ የአቻነት ግብ ጨዋታውን ወደ መለያ ምት ወስዶታል።
የጣልያን የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ትዝታ በ2014 ብራዚል ላይ ሱዋሬዝ ቺሊኒን የነከሰበትና ጣልያን በኡራጓይ ተሸንፋ ከምድብ የቀረችበት መራራ ምሽት ሆኖ ቀርቷል።
ከ2006ቱ ድል በኋላ ጣልያን በዓለም ዋንጫ መድረክ አንድም ስኬታማ ጉዞ ማድረግ አልቻለችም።
ጂናሮ ጋቱሶ የሉቺያኖ ስፓሌቲን መንበር ተረክቦ ሊታደጋት ቢሞክርም፣ እሱም እንደ ማንቺኒና ኮንቴ ሁሉ የአዙሪዎቹን ክብር ሳይመልስ አንገቱን ደፍቶ ወጥቷል።
ኩራሳኦና ጆርዳን ወደ አሜሪካ ሲያመሩ፣ አዙሪዎቹ ግን አሁንም ቤታቸው እንዲቀሩ ተፈርዶባቸዋል።
#getu #italyfootball #azzurri #worldcup2026 #gattuso #footballnews #worldcupqualifiers #italyvsbosnia #footballhistory #ጣልያን #እግርኳስ #ዓለምዋንጫ #መርዶ #ትዝታ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments