1 day ago
ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ
*ሊዮ 14ኛ በቀጣይ ጉብኝት የሚያደርጉባቸውን ሦስት ሀገራት ታውቀዋል።
#ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኅዳር ወር በደቡብ አሜሪካ አገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።
ፖፕ ሊዮ 14ኛ በኡሩጉዋይ፣ አርጀንቲና እና ፔሩ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቋል።
ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ በኋላ ወደ ደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዟቸው ይሆናል።
በዚህም ከኅዳር 6 እስከ 17 ባሉት 12 ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ከተሞችን የሚሸፍን ጉብኝት ይሆናል ተብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቀድሞ ስማቸው ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት በፔሩ አገር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በምስዮናዊነት እና በጳጳስነት ያገለገሉ ሲሆን የዚያች አገር ሙሉ ዜግነትም እንዳላቸው ተገልጿል።
ፖፕ ሊዮ ረጅሙን የጉዞ ጊዜ በፔሩ የሚያሳልፉ ሲሆን ሊማ ቺክላዮና ኩስኮ ከተሞችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የትውልድ አገራቸው አርጀንቲናን በ12 ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነታቸው ወቅት መጎብኘት አልቻሉም ነበር።
አሁን የሊዮ 14ኛ የአርጀንቲና ጉብኝት በአገሪቱ ዜጎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #popeleo #vatican #peru #argentina #uruguay

18 days ago
ስፔን የ23ኛው ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በመጠናቀቁ አሸናፊውን ለመለየት 30 ደቂቃ ተጨምሯል።
በጭማሪው ክፍለ ጊዜ 106ኛው ደቂቃ ላይ ፌራን ቶሬስ ያስቆጠራት ግብ ስፔንን አሸናፊ አድርጋለች።
በዚህም ስፔን ከ16 ዓመታት በኋላ ውድድሩን አሸንፋ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
#worldcup #fifaworldcup #fifaworldcup2026 #argentina #spain #finalmatch #football #sports

ስፔን 1-0 አርጀንቲና
*********
እየተካሄደ ባለው የ23ኛው ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ስፔን 106ኛው ደቂቃ ላይ በፌራን ቶሬስ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ 1 ለ 0 መምራት ጀምራለች።

አርጀንቲና 0 - 0 ስፔን :- የመደበኛ ሰዓት ውጤት
*****************
በአርጀንቲና እና በስፔን መካከል እየተደረገ የሚገኘው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ መደበኛው የ90 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ አሸናፊ ባለመገኘቱ፣ አሸናፊውን ለመለየት ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።
ኤንዞ ፈርናንዴዝ ፓብሎ ኩባርሲ ላይ በሰራው ጥፋት 90+3 ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

Sponsored by
Surafel
22 days ago
አርጀንቲና ወደ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
***************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝና አርጀንቲና መካከል የተካሄደው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በአርጀንቲና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለአርጀንቲና የአሸናፊነት ግቦቹን በ85ኛው ደቂቃ ኤንዞ ፈርናንዴዝ እንዲሁም በጭማሪ ሰዓት (90+3) ላውታሮ ማርቲኔዝ ከመረብ አሳርፈዋል። ለእንግሊዝ ብቸኛዋን ግብ በ55ኛው ደቂቃ አንቶኒ ጎርደን አስቆጥሯል።
የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና ለዋንጫው ክብሯን ለማስጠበቅ የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸናፊዎቹ ፈረንሳይና እንግሊዝ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ሌሊት 3ኛ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ የሚጫወቱ ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports

99'- 🏴 England 1-2 Argentina 🇦🇷
አርጀንቲና በአለቀ ሰዓት እንግሊዝን 2 ለ 1 በመርታት ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
#አትላንታ — በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ዘመናት ከሚታወሱት እጅግ አስገራሚና አስደናቂ ጨዋታዎች መካከል አንዱ በዛሬው ዕለት በአትላንታ ስታዲየም ተመዝግቧል።
የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና እስከ ጨዋታው ማጠናቀቂያ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ስትመራ ብትቆይም፣ በአስደናቂ ብቃትና መነሳሳት ባስቆጠረቻቸው ሁለት ፈጣን ግቦች እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ መድረሷን አረጋግጣለች።
በዚህም መሠረት አርጀንቲና በተከታታይ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ማለፍ የቻለች ሲሆን፣ ዋንጫውን በድጋሚ ለማንሳትና የበላይነቷን ለማስጠበቅ በታላቁ የፍፃሜ ፍልሚያ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
ጨዋታው ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ እጅግ ማራኪና ታክቲካዊ ጥንቃቄ የበዛበት የነበረ ቢሆንም፣ በሁለተኛው አጋማሽ የእንግሊዙ ተቀይሮ የገባ ኮከብ አንቶኒ ጎርደን ባስቆጠራት አስደናቂ ግብ 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር።
እንግሊዝ እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ ውጤቱን አስጠብቃ በመጓዝ ወደ ፍፃሜው ለመድረስ እጅግ ተቃርባ የነበረ ቢሆንም፣ የአርጀንቲናውያን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ጨዋታውን በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ ገልብጦታል።
የቼልሲው አማካይ ኢንዞ ፈርናንዴዝ የአርጀንቲናን ተስፋ ያለመለመችውን ወሳኝ ግብ ከመረብ አሳርፏል። ለዚህች ግብ መገኘት ደግሞ ታላቁ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ድንቅ የሆነ የኳስ አመቻችቶ ማቀበል (Assist) ሥራ ሰርቷል።
የአሸናፊነቷ ግብ (90+')፦ ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ያመራል ተብሎ በሚጠበቅበት በአለቀ ሰዓት፣ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ እንግሊዝን ሙሉ በሙሉ ያስደነገጠችውንና ለአርጀንቲና የፍፃሜ ትኬት የቆረጠችውን ድንቅ የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ይህን አስገራሚና ድራማዊ ጨዋታ ተከትሎ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ስፖርት ሚዲያዎች ዘገባዎቻቸውን አውጥተዋል፦
"አርጀንቲናዎች ፈፅሞ እጅ እንደማይሰጡ በድጋሚ አሳይተዋል። ሜሲና የቡድን አጋሮቹ በመጨረሻዎቹ አምስት ደቂቃዎች የፈጠሩት ተአምር የዓለም ዋንጫን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው፤ እንግሊዝ በሰራችው ጥቂት መዘናጋት ዋጋ ከፍላለች።"
— ESPN
"ሊዮኔል ሜሲ ግብ ባያስቆጥርም ጨዋታውን የመቆጣጠርና የመምራት ብቃቱ አሁንም ወደር የለሽ መሆኑን አስመስክሯል። ለኢንዞ ፈርናንዴዝ ያቀበላት ኳስ የአርጀንቲናን የሞተ ተስፋ ቀስቅሳለች። አርጀንቲና አሁን አይኗን በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ክብር ላይ ጥላለች።"
- BBC Sport
"የእንግሊዝ የልብ ስብራት! አንቶኒ ጎርደን በእንግሊዝ ደጋፊዎች ዘንድ ጀግና ለመሆን ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተውት ነበር። ነገር ግን ላውታሮ ማርቲኔዝ በአስገራሚ አጨራረስ የእንግሊዝን ህልም አክስሟል።"
— Sky Sports*
በአትላንታው ስታዲየም የታየው ይህ አስደናቂ ፍልሚያ ለአርጀንቲና ደጋፊዎች ታላቅ ደስታን ሲያበረክት፣ ለእንግሊዞች ግን እጅግ ልብ ሰባሪ ሽንፈት ሆኖ አልፏል።
አርጀንቲና ዋንጫውን በተከታታይ ለማንሳት ከስፔን ጋር የምታደርገው የፍፃሜ ጨዋታ ሌላው በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ መድረክ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

እንግሊዝ 0 - 0 አርጀንቲና :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
28 days ago
ፈረንሳይና አርጀንቲና በቅጣት ምቶች እኩል ሪከርድ አላቸው
#ethiopia | በመጨረሻዎቹ ሶስት የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድሮች (2018፣ 2022 እና 2026) ፈረንሳይና አርጀንቲና እያንዳንዳቸው 8 የፍፁም ቅጣት ምቶች ተሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በተጠቀሱት ሦስት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የፍፁም ቅጣት ምት እንዳገኙ ያሳያል።
በ2026 የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ከሞሮኮ ጋር በተደረገው ጨዋታም ፈረንሳይ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝታ ቢሆንም፣ ኪሊያን ምባፔ ወደ ግብ መቀየር አልቻለም።
#fifaworldcup #france #argentina #mbappe #messi #getu

30 days ago
"ጨዋታው ተጭበርብሯል፤ ዓለም ሁሉ አይቶታል!"
— አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን
* የግብፅ–አርጀንቲና ጨዋታ በዳኝነት ውሳኔዎች መነጋገሪያ ሆነ
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የ16 ዙር ማጣሪያ አርጀንቲና ግብፅን 3 ለ 2 በሆነ አስደናቂ ውጤት አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ ብታልፍም፣ ከውጤቱ በላይ በሜዳ ላይ የታዩት የዳኝነት ውሳኔዎችና ውዝግቦች የዓለም ስፖርት ሚዲያዎችን እያናወጡ ይገኛሉ።
ከ2 ጎል መሪነት እስከ መጨረሻው ደቂቃ "ንፁህ ቀውስ" (Pure Chaos)
ግብፅ በመጀመሪያው ክፍለ ጨዋታ "እንደ ፒራሚድ ፀንታ" ድንቅ የመከላከል ብቃት በማሳየት አርጀንቲናን በከባድ ሁኔታ ፈትና ነበር። ሆኖም አርጀንቲና ከሁለት ጎሎች መመራት በኋላ ተስፋ ሳትቆርጥ ባሳየችው አስደናቂ የመመለስ ብቃት ጨዋታውን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሲል በነበረው ከፍተኛ ውጥረት ዳኛው በስምንት ደቂቃ ውስጥ ብቻ 5 የቢጫ ካርዶችን ለመምዘዝ ተገዷል።
"ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው፤ ሜሲ እንዲቆይ ይፈልጋሉ!" — የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ቁጣ
ከጨዋታው በኋላ የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን በሰጡት እጅግ ቅሬታ የተሞላበትና ያልተጠበቀ መግለጫ ፊፋንና የዳኝነት ቡድኑን በኃይለኛ ቃላት ወርፈዋል፦
*ስለ ቪአይአር (VAR) ውሳኔዎች፦
"በመሐመድ ሳላህ ላይ የተሰራው ጥፋት (የፍጹም ቅጣት ምት) በVAR ሳይታይ ቀርቷል፤
ሁለተኛው ጎላችንም ባልታወቀ ምክንያት ተሰርዟል።
ማክ አሊስተር ማሊያ ሲጎትት እያየን VAR አልተፈተሸም።"
ስለ ፈረንሳዩ ዳኛ ምደባ፦
"አርጀንቲና በ2022 ፈረንሳይን ማሸነፏን ተከትሎ በነበረው ሁኔታ የዚህን ፈረንሳዊ ዳኛ መመደብ ቀድመን ተቃውመን ነበር።"
"እውነቱን ለመናገር ጨዋታው በግልጽ የተጭበረበረ ነበር። ሁሉም ነገር ስለ ገንዘብ ነው። ሊዮኔል ሜሲ በውድድሩ ውስጥ እንዲቆይ ይፈልጋሉ። አርጀንቲና እንድታሸንፍ ይህን ያህል የሚፈልጉ ከሆነ ሌላውን ቡድን ለምን ለውድድር ይጠሩታል?"
የአሰልጣኙ ሆሳም ሀሰን ውሳኔ፦
"ከደረሰብን ኢፍትሃዊነት የተነሳ ከእንግዲህ አንድም ደቂቃ የዚህን ዓለም ዋንጫ ጨዋታ አልመለከትም!"
የእግር ኳስ ተንታኞች፦
የግብፅን አስደናቂ ተጋድሎና የአርጀንቲናን እስከ መጨረሻው የመታገል መንፈስ እያደነቁ ቢሆንም፣ የዳኝነት ውሳኔዎቹ ግን ጨዋታውን መበላሸታቸውን ይስማማሉ።
የፊፋ (FIFA) ምላሽ፦
እስካሁን ድረስ ፊፋ በአሰልጣኙ ክስ ላይ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም፤ ክሶቹም በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም።
የእናንተስ አስተያየት ምንድነው?
የአፍሪካ እግር ኳስ አፍቃሪያን!
በግብፅ ላይ የተፈጸመው የዳኝነት ውሳኔ ትክክል ነበር ወይስ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እንዳሉት አድልዎ ተፈጥሯል?
**ሀሳባችሁን በኮሜንት መስጫው ላይ ያካፍሉን!
አለባቸው ደሳለኝ ከለንደን 🇬🇧
**#fifaworldcup #egypt #argentina #hossamhassan #mohamedsalah #messi #africa #footballnews **

1 month ago
ግብፅ አርጀንቲናን መርታ የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቀቀች
*******************
እየተካሄደ በሚገኘው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ግብፅ አርጀንቲናን 1 ለ 0 በመምራት የመጀመሪያ አጋማሽ አጠናቅቃለች፡፡
በጥሎ ማለፍ ጨዋታው ግብፅን መሪ ያደረገችውን ግብ ያሲር ኢብራሂም በ15ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በጨዋታው 21ኛው ደቂቃ ላይ አርጀንቲና ያገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
#ebc #argentina #egypt #football #sports #roundof16 #knockout

አርጀንቲና ኬፕቨርዴን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
*********
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ32 ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር አፍሪካዊቷን ደሴት ኬፕቨርዴን የገጠመችው አርጀንቲና 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን የ16 ሀገራት ጥሎ ማለፍ ዙር ተቀላቅላለች።
ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ዳንኤል ዱዋርቴ ደግሞ ለኬፕቨርዴ 1 አቻ በተጠናቀቀው መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
አሸናፊውን ለመለየት በተጨመሩት 90 ደቂቃዎች፤ የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩት ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ዲኔይ ቦርገስ(በራሱ መረብ ላይ) ሲሆን የኬፕ ቨሮዴን ግብ ሲድኒ ካብራል ከመረብ አሳርፏል።
ሻምፒዮኗ አርጀንቲና በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ግብፅን የምትገጥም ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup #argentina #caboverde #lionelmessi #football #sports

ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
**************************
የ“አልበ ሰልስቴ”ዎቹ ወርቃማ ትውልድ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ለሌላ የዓለም ሻምፒዮንነት የጀመረውን መንገድ በአስገራሚ ሁኔታ እየተጓዘ ነው። የ48 ዓመቱ ሰው በሊዮኔል ሜሲ ዙሪያ የተገነባውን ቡድን በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ስኬታማነት እያመላለሰው ነው።
ከ2018ቱ ዓለም ዋንጫ በኋላ ስካሎኒ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን አሰልጣኝነት ሲረከብ በዓለም እግር ኳስ በጉልህ የሚጠራ ስም አልነበረውም። ሆኖም አሰልጣኙ የጎላ የአሰልጣኝነት ልምድ ሳይኖረው የኳታሩን ዓለም ዋንጫ ጨምሮ ሁለት የኮፓ አሜሪካ ክብሮችን አሳክቷል። የፋይናሊዝማ ዋንጫም የስኬቱ አካል ነው።
ያኔ ከስምንት ዓመታት በፊት ስካሎኒ የሆርጌ ሳምፓውሊን መንበር ሲረከብ ታላቁን ማራዶና ጨምሮ ብዙዎች በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱት። ልምዱ ታላቋን የእግር ኳስ ሀገር በአሰልጣኝነት ለመምራት ብቁ አይደለም የሚለው የጥርጣሬው መነሻ ነበር።
ማራዶና ኃይለ ቃላትን ጭምር ተጠቅሞ ስካሎኒን የተቸው ጄራርዶ ማርቲኖ ወደ ቀድሞ አሰልጣኝነታቸው መመለሳቸውን በመሻትም ጭምር ነው።
የቀድሞ የዲፖርቲቮ ላካሮኛ እና ላዚዮ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድንም ቢሆን ከሰባት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ውጭ ኣላሸነፈም። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር አብረው የተጫወቱበት የ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ በተጫዋችነት ትልቁ ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው።
የአሰልጣኝነት ትልቁ ልምዱ ግን በ2018 ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ በተሰናበተው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የሆርጌ ሳምፖሊ ረዳት ሆኖ ሲሰራ ይጀምራል። የሳምፖሊ መሰናበት ደግሞ ለስካሎኒ አዲስ ዕድል ይዞለት መጣ።
“አልበ ሰልስቴ”ዎቹን በዋና አሰልጣኝነት የመምራት ዕድል። በዚህም ጊዜያዊ አሰልጣኝ በኋላም ዋና አሰልጣኝ ሆኖ በቅርብ ዓመታት ከታዩ ውብ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱን አሳየ።
“ስካሎኒታ” አሁን በተጫዋችነት ዘመኑ ያላገኘውን ክብር በአሰልጣኝነት ተቀዳጅቷል። ስካሎኒ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ካደረጋቸው 99 ጨዋታዎች 72 አሸንፏል፣ በ18 አቻ ተለያይቷል፣ በ9 ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፏል። ከ2019 – 2022 የተጓዘበት በ36 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውም የመንገዱ አካል ነው።
ነገ ሚያሚ ላይ የሚደረገው የ32ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለሊዮኔል ስካሎኒ 100ኛ መርኃ ግብር ሆኖ ይመዘገባል። አርጀንቲና ሲሆን አስከ ሻምፒዮንነት ካልሆነ ግን እስከ ፍፃሜ ትጓዛለች ተብላ በምትጠበቅበት በዚህ ዓለም ዋንጫ መሃል ስለ 100ኛ ጨዋታው ተጠይቆ፤ ያኔ 100ኛ ጨዋታው ላይ እደርሳለሁ ብሎ አስቦ እንዳልነበር ነው የተናገረው።
ሆኖም ይህ በህይወቱ አስቦት የማያውቀው ደረጃ ቢሆንም ዋነኛ ትኩረቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ለተከታታይ የዓለም ሻምፒዮንነት ማብቃት መሆኑን ገልጿል።
ይህን በዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ምሳሌ የሆነ ታሪካዊ ቡድንን መምራት እና ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ግን አልሸሸገም።
ትሁቱ ሰው የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእግር ኳስ ክስተት ሜሲንም ሆነ ብሔራዊ ቡድኑን ውጤታማ በሚያደርግ አግባብ በእርሱ ዙሪያ የገነባው ቡድን ለስኬታማነቱ በምክኒያትነት የሚጠቀስ ዋነኛ ጉዳይ ነው።
የዓለም ዋንጫውን ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ከኪሊያን ምባፔ ጋር በስድስት ግቦች እየመራ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የዘመኑን ውጤታማ ጊዜያት በስካሎኒ አሰልጣኝነት ስር ነው ያሳለፈው።
በ74 ጨዋታዎች 58 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል። በ128 ጨዋታዎች 65 ግቦች ካስቆጠረበት የቀደመው ጊዜ ጋር ተነፃፅሮ በጨዋታዎች ብዛት ሲሳላ በእጅጉ ያነሰ ነው።
በመጀመሪያው 0.51 በሁለተኛው ደግሞ 0.78 በአማካይ በየጨዋታው ያስቆጠራቸው ግቦች ናቸው። ይህ ቁጥር ስካሎኒ በሜሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ቡድን ለመገንባቱ ጉልህ ማሳያ ነው።
የአሰልጣኙ ውል በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ያበቃል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌደሬሽንም የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ለማራዘም እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።
የ48 ዓመቱ ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን የዓለም ዋንጫው ክስተት ከሆነችው ኬፕቨርዴ ጋር ነገ ሌሊት 7፡00 ሰዓት በሚያሚው ሃርድ ሮክ ስታዲየም ያደርጋል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #messi #argentina #football

2 months ago
ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ከፍተኛውን የግብ ማግባት ክብረ ወሰን ላይ ደረሰ
#ethiopia | የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ ከአልጄሪያ ጋር ባደረገችው ፍልሚያ የ38 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ ሦስት ግቦችን በአስደናቂ ሁኔታ አስቆጥሯል።
በዚህም ስኬቱ ሜሲ በፊፋ የዓለም ዋንጫ ታሪክ ከፍተኛውን የግብ ማግባት ክብረ ወሰን እኩል መጋራት ችሏል።
ይህ ታሪካዊ የምሽት ስኬት አርጀንቲና በውድድሩ የመጀመሪያዋን ድል እንድትቀዳጅ ከመርዳቱም በላይ ሜሲ በስፖርቱ ዓለም ያለውን የማይበገር አቅም በድጋሚ ያሳየበት ሆኗል።
#argentina #worldcup2026 #messi #footballnews #algeria #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments