በፊፋ ስታንዳርድ መሰረት እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የሳር ንጣፍ ስራ ተጀመረ፡፡
በዓለም-ዓቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) እንዲሁም በ World Athletics ስታንዳርዶች መሰረት በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የመጫወቻ ሜዳ ቅልቅል (Hybrid turf) ሳር ንጣፍ ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በአውሮፓ እና በአፍሪካ በሚገኙ ትልልቅ ስታዲየሞች ላይ ሰው ሰራሽ (Artificial turf ) እንዲሁም ቅልቅል (Hybrid turf ) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ የካበተ ልምድ ካለው የጣሊያኑ ሊሞንታ (Limonta Sport) ጋር የነበረው ንግግር በውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ኩባንያው በዛሬው ዕለት በስቴዲየሙ ተገኝቶ ዳታ የመልቀም ተግባር ጀምሯል፡፡
ስራውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንደገለፁት በስቴዲየሙ የሚነጠፈው የሳር አይነት ቅልቅል (Hybrid) ሆኖ አይነቱም carpet type እንደሚሰኝ ጠቅሰው ይህም ከ90 – 95 % የተፈጥሮ ሳር እንዲሁም ቀሪው ከ5–10 % ደግሞ አርቴፊሺያል እንደሚሆን ያብራሩ ሲሆን ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ ድርሳን ላይ አዲስ ገፅ የሚገልጥና ለስፖርት ቱሪዝም እንዲሁም ለውጪ ግንኙነታችንም ጭምር በጎ ፋይዳ እንደሚኖረው አያይዘው ጠቁመዋል፡፡
በስቴዲየሙ ግንባታ ላይ MNRC በዋና ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ZIAS International Designs PLC በአማካሪነት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

4 months ago