1 month ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምዕራብ አባያ ወረዳ ያደረጉት የገጠር ኮሪደር ጉብኝት
#ruralcorridor #pmabiyahmed #southethiopia
#ethiopia #medemer
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች፣ የነገ የሀብት ምንጭ ናቸው፦ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
******************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
ተከላውን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ኦቾሎ ላንቴ ቀበሌ ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፥ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች፣ የነገ የሀብት ምንጭና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ መሆናቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ መርሐ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በተለይም ክልሉ ለናዳ እና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በተራራማ አካባቢዎች የአረንጓዴ ልማት ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ በበኩላቸው፥ ባለፉት 8 ዓመታት የክልሉን የደን ሽፋን ከነበረበት 19 በመቶ፣ ወደ 24.5 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል።
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ንቅናቄ የሚከናወነው የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ፣ ችግኝ ከመትከል ያለፈ የተስፋ ምልክት መሆኑ ተገልጿል።
በተመስገን ተስፋዬ
#ethiopia #climateaction #environmentalprotection #greenlegacy #southethiopia #ebc

2 months ago
የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በዲላ ከተማ በደመቀ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ
#ethiopia | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቡኖ ማላ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በሚገኘው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በይፋ ተከፍቷል።
ይህ ታላቅ መድረክ የጌዴኦን የቡናና የሥጋ ምርት ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የዲላን የኢንቨስትመንት ሳቢነት ለማሳደግ እንዲሁም በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለዓለም ማህበረሰብ በሰፊው ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
ትናንት በተከናወነው የዝግጅቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌደራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጌዴኦ ዞንና የዲላ ከተማ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ኤክስፖው ዛሬም በተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ጎብኚዎች መጎብኘቱን የሚቀጥል ሲሆን፣ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ እና የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማካተት እስከ አመሻሹ ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል።
#bunomalaexpo #dilla #gedeo #southethiopia #coffeeexpo #tourismethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኅብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ
*****************
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአምስት ከተሞች የሚገኙ ከ180 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግዙፍ የውኃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እየሆኑ ነው።
በክልሉ በ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡና ከአምስት በላይ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ምረቃ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በተገኙበት፣ በዛሬው ዕለት በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የተገነባው የብዝሃ ቀበሌ ንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ብቻውን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ከ31 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰሞኑን የተመረቁትን ጨምሮ በክልሉ ግንባታቸው በተከታታይ እየተመረቁ የሚገኙት እነዚህ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከ180 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጌዴኦ ዞን የጨለለቅቱ ከተማ፣ በወላይታ ዞን የሆቢቻ ወረዳ ብዝሀ-ቀበሌ፣ በጋሞ ዞን የዘፍነ ከተማ፣ በደቡብ ኦሞ ዞን የቀያፈር ከተማ እና በኮሬ ዞን የኬሌ ከተማ የሚገኙ ናቸው።
በትናንትናው ዕለት በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ የምረቃ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን፣ ዛሬ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳም ተካሂዷል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ቀሪ ከተሞች የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ እንደሚካሄድ ታውቋል።
እነዚህ የንፁህ መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች "የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት" አካል ሲሆኑ፣ ግንባታቸውም በፌዴራል፣ በክልልና በዞን መንግሥት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተከናወነ ነው።
ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸው በክልሉ በተለይም በገጠር እና በከፊል የከተማ አካባቢዎች የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውኃ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰው በምረቃው ወቅት ተገልጿል።
በትዕግስቱ ቡቼ
#ethiopia #southethiopia #waterinfrastructure #development #cleanwater #ethiopianbroadcastingcorporation

Sponsored by
Surafel
4 months ago
🍎 "አፕሎቹ" ታሪክ ጻፉ
ጋሞ ጨንቻ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
#ethiopia | ለጋሞ ዞንና ለጨንቻ ከተማ ህዝብ ልዩና ታሪካዊ ቀን! በ2011 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደገው ጋሞ ጨንቻ፣ ዛሬ በጅማ ስታዲየም ባሳየው ድንቅ ብቃት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሸጋገሩን አረጋግጧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ "ተግቶ መስራትና ብሩህ ተስፋን አርቆ መመልከት ውጤቱ ይሄው ነው" በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ እንደገለጹት፣ ጨንቻ ከአርባምንጭ ከተማ ቀጥሎ ዞኑን በፕሪሚየር ሊግ የሚወክል ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሊጉ የሚገኙት ወላይታ ዲቻና አርባምንጭ ከተማ የውስጥ ችግሮቻቸውን ቀርፈው ውጤታማ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
"አፕሎቹ" ለአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ።
#getu #gamochencha #applochu #ethiopianpremier League #promotion #gamozone #southethiopia #footballnews #ethiopiadecides #ጋሞጨንቻ #አፕሎቹ #ፕሪሚየርሊግ #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የብርሃን ጉዞ ወደ ገጠር
* የሶላር ሚኒግሪድ ፕሮጀክቶች በደቡብ ኢትዮጵያ ስኬት እያስመዘገቡ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከብሔራዊ የኃይል ቋት (Grid) የራቁ የገጠር አካባቢዎችን በአማራጭ የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረው የተቀናጀ የልማት ሥራ ውጤታማ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለፁ።
በደቡብ ኦሞ ዞን (ሳላማጎ፣ ሐመር፣ ኦሞራቴና ዳሰነች) እንዲሁም በጋሞ ዞን (ጋርዳ ማርታ) የሶላር ሚኒግሪድ ማመንጫዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
በአጠቃላይ 2,325 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ከ20 ሺህ በላይ የገጠር አባወራዎችን የብርሃን ተጠቃሚ አድርገዋል።
ይህ ኃይል ከመኖሪያ ቤት ብርሃን ባለፈ ለመጠጥ ውሃ፣ ለጤና ተቋማትና ለመስኖ ልማት እንዲውል ከተቋሙ ጋር በትብብር እንደሚሠራ ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሌሎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ። ይህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 የያዘችውን የኃይል ተደራሽነት ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
#getu #eeu #solarenergy #ruralelectrification #southethiopia #greenenergy #developmentnews #worldbank #energyaccess #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ሶላር #ልማት #ደቡብኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ
#ethiopia | የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ወ/ሮ አዱኛ አዛዥ፣ የተሰጣቸውን የመንግስት የስራ ተልዕኮ አጠናቅቀው በመመለስ ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
ኃላፊዋ ጥቃቱ ከደረሰባቸው በኋላ በህክምና ማዕከል እርዳታ ሲደረግላቸው የቆየ ቢሆንም፣ ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም። ወ/ሮ አዱኛ በቀድሞው የጋሞ ጎፋ ዞን፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ እንዲሁም አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ ወዲህ በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ላይ ሀገርንና ህዝብን በቅንነት ያገለገሉ ብርቱ አመራር እንደነበሩ ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በባለስልጣኗ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፤ ድርጊቱን ያልተገቡ ፍላጎቶችን በጉልበትና በጦር መሳሪያ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ኋላቀር ቡድኖች የፈጸሙት የጥፋት ተግባር ሲል ኮንኖታል።
በመሆኑም የክልሉ መንግስት እንዲህ አይነት እኩይ ተግባራትን አምርሮ እንደሚታገል አሳውቆ፣ በጥቃቱ ተሳታፊ የሆኑና የተባበሩ አካላትን ለይቶ ለህግ ለማቅረብና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። ፍትህ እስኪሰፍንም ድረስ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ዜና #ደቡብ_ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ #ወቅታዊ_መረጃ #southethiopia #ethiopiannews

አስቸኳይ የሰብዓዊነት ጥሪ፦
ለጋሞ ወገኖቻችን በጋራ እንድረስላቸው!
#ethiopia | ውድ ኢትዮጵያውያን፣ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ (ማዞ ዶይሳ) እና አካባቢው በደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ወገኖቻችን በከፍተኛ ሰቆቃ ውስጥ ይገኛሉ። ሰው ለማትረፍ ሲሉ ሕይወታቸውን ላጡና ለጠፉ ወገኖች ቤተሰቦች ድጋፋችንን የምናሳይበት ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው።
🙌 ከቦታው የቀረበ ምስጋና
ድምፃዊ Bujustar ከአደጋው ቀጠና ባስተላለፈው መልእክት፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ላሳያችሁት አጋርነት ምስጋናቸውን እንዲህ ገልጸዋል፦
"በማህበራዊ ሚዲያ እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ እና ሽፋን ለጌጡ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) እና ለሌሎችም ልባዊ ምስጋናችንን አቅርብልን ብለዋል።"
ይህ ምስጋና የእርስዎ ሚዲያ ለተጎዱ ወገኖች ድምፅ በመሆን እያደረገ ያለውን የማይተካ ሚና የሚያረጋግጥ ነው።
የወቅታዊ ጉዳት መረጃ (በፖሊስ የተረጋገጠ)
የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም ቡሔ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ሰዓት ዋናው ርብርብ በቀሪ አስክሬኖች ፍለጋ ላይ ነው፦
* የተገኙ አስክሬኖች፦ 64
* የጠፉ ሰዎች ቁጥር፦ 128 (ፍለጋው በከባድ ሁኔታ ቀጥሏል)
* ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት፦ ዳጮ ባባ ወረዳ (59 አስክሬኖች ተገኝተዋል)
ሌሎች አካባቢዎች፦
በቦንኬ እና በከምባ ዙሪያ ወረዳዎች 5 አስክሬኖች ተገኝተዋል።
📢 ለተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች የቀረበ ጥሪ
የሚዲያ ሽፋን ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ በአስቸኳይ ይደረግ ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ፦
በአደጋው የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመደገፍና የተደቀነውን ስጋት በጋራ ለመወጣት የሚከተሉት የባንክ አካውንቶች በይፋ ተከፍተዋል፦
የጋሞ ልማት ማህበር
(Gamo Development Association)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦
1000021467174
የጋሞ ዞን አደጋ ስጋት
(Gamo Zone Disaster Risk Management)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦
1000321312865
#ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው ! #ጋሞ #ደቡብኢትዮጵያ #ጎርፍአደጋ #ትኩረትለጋሞ #ጌጡተመስገን #ኢትዮጵያ #gamo #southethiopia #floodemergency #ethiopianews #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

የ64 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል፤ 128 የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ላይ ነን
#ethiopia | በጋሞ ዞን የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር እና የፍለጋ ሂደትበጋሞ ዞን በሦስት ወረዳዎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ዙሪያ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የቅርብ ጊዜውን መረጃ ይፋ አድርጓል። እንደ ዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም ቡሔ ገለጻ፣ በአሁኑ ሰዓት ትኩረቱ በቀሪ አስክሬኖች ፍለጋ ላይ ሆኗል።
የአደጋው ዝርዝር መረጃ
* የተገኙ አስክሬኖች፦ 64
* የጠፉ ሰዎች ቁጥር፦ 128 (ፍለጋው እንደቀጠለ ነው)
* ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ወረዳ፦
ዳጮ ባባ ወረዳ (59 አስክሬኖች ተገኝተዋል)
* ሌሎች ወረዳዎች፦ በቦንኬ እና በከምባ ዙሪያ ወረዳዎች 5 አስክሬኖች ተገኝተዋል።
ኢንስፔክተር አብረሀም ቡሔ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች እንዳሉ ጠቁመው፣ ኅብረተሰቡ የተሳሳቱ ቁጥሮችን ከመቀበል እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን (South Ethiopia Regional State Police Commission) ይፋዊ ገጾችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ አደጋው ከተከሰተ ጊዜ አንጻር አሁን ላይ የነፍስ አድን (Rescue) ሥራው ተስፋ የሚጣልበት ባለመሆኑ፣ ዋናው ትኩረት የቀሪ አስክሬኖችን ፍለጋ በማጠናከር ላይ ሆኗል።
በዚህ አሰቃቂ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦችና ለመላው የጋሞ ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን። አሁንም ፍለጋ ላይ ላሉ ወገኖች ድካማቸው እንዲሳካና ወገኖቻችን በክብር እንዲያርፉ ምኞታችን ነው።
#ጋሞ #ደቡብኢትዮጵያ #ጎርፍአደጋ #ወቅታዊመረጃ #ኢትዮጵያ #gamo #southethiopia #floodemergency #ethiopianews #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

6 months ago
የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!
#ethiopia | "የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል።
የስታዲየሙ ገፅታዎች:
✅ ደረጃ: የፊፋ (FIFA) እና የካፍ (CAF) ስታንዳርድን ያሟላ።
✅ አቅም: ከ40,000 እስከ 45,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው።
✅ ዲዛይን: የወላይታን ህዝብ ታሪክ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የአካባቢውን ገፅታ ያካተተ ነው።
✅ ይዞታ: በ51 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ "ይህ ፕሮጀክት የህዝብ ነው፤ ከተባበርንና ካስተባበርን እውን ማድረግ ይቻላል" በማለት፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ የሚሆን ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት መላው ህዝብ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6
#wolaita #stadium #construction #ethiopia
#wolaitasodo #internationalstadium #ethiopia #development #sports #southethiopia

Comments