Logo
Getu Temesgen
የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በይፋ ተጀመረ!
#ethiopia | ​"የወላይታን ባህልና ታሪክ የያዘ፣ ከ40 እስከ 45 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ግዙፍ ስታዲየም" ​በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና በወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ አማካኝነት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለታል።

​የስታዲየሙ ገፅታዎች:

✅ ደረጃ: የፊፋ (FIFA) እና የካፍ (CAF) ስታንዳርድን ያሟላ።

✅ አቅም: ከ40,000 እስከ 45,000 በላይ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም አለው።

✅ ዲዛይን: የወላይታን ህዝብ ታሪክ፣ ባህላዊ እሴቶች እና የአካባቢውን ገፅታ ያካተተ ነው።

✅ ይዞታ: በ51 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።

​ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፤ "ይህ ፕሮጀክት የህዝብ ነው፤ ከተባበርንና ካስተባበርን እውን ማድረግ ይቻላል" በማለት፤ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ የሚሆን ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል።

​የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!" በማለት መላው ህዝብ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ዎጌታ ኤፍ ኤም 96.6
​#wolaita #stadium #construction #ethiopia
​#wolaitasodo #internationalstadium #ethiopia #development #sports #southethiopia

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.