1 month ago
የ Zadok Perth International Ministry, Ethiopia ትምህርቶችና ስብከቶች! ✨
#ethiopia | በአውስትራሊያ "በወንጌል ለአለም ቤተክርስትያን" አገልጋይ በሆነው ተመስገን ነጋሽ የሚዘጋጁ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች በተለያዩ አማራጮች ወደ እናንተ እየቀረቡ ይገኛሉ።
ፕሮግራሞቹን የሚከታተሉባቸው መንገዶች፦
በGMM TV, Ethio- Sat
ዘወትር ቅዳሜ፦ ከቀኑ 10:30 - 11:00 ሰዓት
በድጋሚ ረቡዕ፦ ጠዋት 2:00 - 2:30 ሰዓት
በማህበራዊ ሚዲያ፦
YouTube: በየሳምንቱ ቅዳሜ አዳዲስ ቪዲዮዎች ይለቀቃሉ Zadok Perth YouTube
Facebook: Zadok Perth Facebook
TikTok: Zadok Perth TikTok
እነዚህን መንፈሳዊ ይዘቶች በመከታተል፣ ሰብስክራይብ በማድረግና ለሌሎች በማጋራት (Share) የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ እጋብዛችኋለሁ። ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻቸው zadokperthgmail.com ማግኘት ትችላላችሁ።
ቃሉን በመስማት ህይወታችንን እናድስ! 🙏📖
👉YouTube https://youtube.com/zadok...
👉Facebook https://www.facebook.com/s...
👉TikTok https://www.tiktok.com/@za...
#zadokperth #temesgennegash #gmmtv #spiritualgrowth #gospelfortheworld #australiaministry #ethiopiangospel #zadokperthinternational #የወንጌልለአለም #ስብከት #መንፈሳዊትምህርት

5 months ago
🇪🇹 የኢትዮጵያ ኩራት!
አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በካፍ ቴክኒካል ቡድን ውስጥ! 👏
* ጨዋታዎቹን የሚተነትኑት የካፍ ልሂቃን ውስጥ አብርሃም መብራቱ ይገኝበታል
#ethiopia | በሞሮኮ እየተካሄደ ባለው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON 2025) ላይ፤ ጨዋታዎችን በጥልቀት የሚገመግመው እና ምርጥ ተጫዋቾችን የሚመርጠው የካፍ የቴክኒክ ጥናት ቡድን (Technical Study Group - TSG) ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተካቷል።
የአብርሃም ሚና ምንድን ነው?
በአህጉሩ ካሉ ምርጥ የካፍ ኢንስትራክተሮች እና የቀድሞ ተጫዋቾች ጋር በመሆን፤ የቡድኖችን ቴክኒካዊ ብቃት መገምገም፣ የውድድሩን ታክቲካል ሂደት መተንተን እና ለፊፋ (FIFA) እና ለካፍ (CAF) ሪፖርት ማቅረብ ነው።
ትናንት አርሰን ቬንገር የጎበኙት እና ያደነቁት ይህንኑ የአብርሃም መብራቱ አባል የሆነበትን ቡድን ነው።
አብርሃም መብራቱ በተለያዩ ጊዜያት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር በመሆን አህጉራዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
እንኳን ደስ አለን! 🇪🇹⚽
#abrahammebratu #caf #tsg #afcon2025 #ethiopianpride #technicalstudygroup #ethiopia

7 months ago
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የባህል ስፖርቶች ኮንፌደሬሽን አባልነት አገኘች
👉ፕሬዝደንቷ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌደሬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ባስታወቀው መሰረት፣ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ስትጠይቀው የቆየው በአፍሪካ የባህል ስፖርቶችና ጨዋታዎች ኮንፌደሬሽን (ATSGC) የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።
ጥያቄው ተቀባይነት ያገኘው ከኖቬምበር 6 ጀምሮ በዚምባቡዌ ሃረሬ እየተካሄደ ባለው የኮንፌደሬሽኑ ጉባኤ ላይ ሲሆን፣ አባልነቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ልምድ በመለዋወጥ የሀገር ውስጥ ባህላዊ ስፖርቶችን ለማሳደግና ተወዳዳሪነትን ለመጨመር ትልቅ እድል ይፈጥራል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ በትላንትናው እለት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል። ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርቶች ማደግ ላቅ ያለ አስተዋፅኦና ተደማጭነትን እንደሚጨምር ተጠቁሟል። ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2026 የሚካሄደውን አህጉራዊ የባህላዊ ስፖርቶች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅም ስለመመረጧ የተሰማ ሲሆን፣ ይህም ለሀገሪቱ ተጨማሪ እድል ይዞ ይመጣል።
በሌላ በኩል፣ በአሁኑ ወቅት የውድድር ህግና ደንብ ወጥቶላቸው በፌደሬሽን ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት 11 ያህል ባህላዊ ስፖርቶች ሲሆኑ፣ የአፋር ክልል ባህላዊ ጨዋታ የሆነው ኮይሶ ጥናቱ ተጠናቆ 12ኛ የባህል ስፖርት ሆኖ ለመቀላቀል ዝግጅት ላይ እንደሆነም ተገልጿል።

8 months ago
#እንኳን_ደሰ_አላችሁ !
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (ATSGC) ያቀረበው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ።
የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (African traditional sports and games confederation) ያቀረበው የአባልነት ጥያቄ በዛሬው ዕለት ተቀባይነት አገኝቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በመግለፅ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለውም በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገኙ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የውበት፣ የማንነት፣ የኩራት እና የጀግንነት ተምሳሌታዊ መገለጫ የሆኑ ብርቅዬ ባህላዊ ስፖርቶቻችንን በሀገር አቀፍ፤ በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ለማስተዋወቅ ብሎም ተዘውታሪ ለማድረግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አመርቂ ውጤቶችን ያስመዘገቡ ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አያይዘውም ፌዴሬሽኑ በ2018 ዓ.ም ለመከወን ከያዛቸው እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን በአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (African traditional sports and games confederation) አባል የመሆን እቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በአመቱ የመጀመሪያ ወር ላይ ልናሳካ ችለናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግንኙነቶችን በመፍጠር ባህላዊ ስፖርቶቻችንን ለማስተዋወቅ እና የባህል ልውውጦችን ለማድረግ ጉልህ ሚናን ይጫወታል ብለዋል።
በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ወቅት ልዩ የሆነ ትኩረትን በመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን የ2026 African traditional sports and multi event festival ለማዘጋጀት መጠነ ሠፊ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ህይወት ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በፌዴሬሽኑ በኩል ለሚሰሩ በርካታ ስራዎች ፈር የቀደደ ታሪካዊ ጅማሮ በመሆኑ ሁላችንም የዚህ ጅማሮ አካል በመሆን ባህላዊ ስፖርቶቻችንን በማሳደግ፣ በማስተዋውቅ፣ በመጠበቅ እና በማልማት ሀላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Comments