1 day ago
የCPJ የ2026 ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊዎች ተገለጹ
#ethiopia | የጋዜጠኞችን ጥበቃ ኮሚቴ (CPJ) ለ36ኛ ጊዜ የሚያዘጋጀውን ዓመታዊ International Press Freedom Awards (IPFA) የ2026 ተሸላሚ ጋዜጠኞችን ይፋ አድርጓል።
የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ኅዳር 19 ቀን 2026 በኒውዮርክ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በድፍረታቸውና በሙያዊ ተግባራቸው ይሸለማሉ።
በዚህ ዓመት ከተሸለሙት መካከል ከሊባኖስ፣ ከኤርትራ፣ ከሀንጋሪ፣ ከኮሎምቢያ እና ከሚያንማር የመጡ ጋዜጠኞች ይገኛሉ።
ክርስቲና አሲ – ሊባኖስ
የAFP ፎቶ ጋዜጠኛ ክርስቲና አሲ በጥቅምት 2023 በእስራኤል–ሊባኖስ ድንበር ዘገባ ስትሰራ በደረሰባት ጥቃት ቀኝ እግሯን አጥታለች፤ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ኢሳም አብዳላህም በዚያው ጥቃት ተገድሏል።
CPJ እንደሚለው፣ በዚህ ጉዳይ እስካሁን ተጠያቂ የሆነ አካል የለም። አሲ ከዚያ በኋላ ለጋዜጠኞች ደኅንነትና ለፍትሕ ድምፅ ሆና እየሠራች ነው።
"ኤርትራ 16"
CPJ በዚህ ዓመት ለ25 ዓመታት ያለ ፍርድ ታስረው የቆዩትን "ኤርትራ 16" የተባሉ 16 ጋዜጠኞች በጋራ ሸልሟል።
እነዚህ ጋዜጠኞች በ2001 የግል ሚዲያዎች ከተዘጉ በኋላ ታስረው ሲሆን፣ እስካሁን ክስ አልቀረበባቸውም፣ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም። የጤናቸውና የሕይወታቸው ሁኔታ እንኳን በግልፅ አይታወቅም።
ሳቦልች ፓንዪ – ሀንጋሪ
የምርመራ ጋዜጠኛው ሳቦልች ፓንዪ የሩሲያ ተፅዕኖ፣ ሙስናና የፖለቲካ ሥልጣን ላይ በሠራቸው ዘገባዎች የሚታወቅ ሲሆን፣ በ2026 የሀንጋሪ ምርጫ ዋዜማ ከባድ ጫናና የስለላ ክስ ተጋፍጦበታል።
ኤስቴፋኒ ሮድሪጌዝ – ኮሎምቢያ
በአሜሪካ የስፓኒሽ ቋንቋ ሚዲያ Nashville Noticias ዘጋቢ የሆነችው ኤስቴፋኒ ሮድሪጌዝ በ2026 በICE ተይዛ ታስራ ነበር።
CPJ ጉዳዩ በስደተኞች ጉዳይ ላይ በምታደርገው ዘገባ ምክንያት በጋዜጠኞች ላይ የሚደረግ ጫናን የሚያሳይ ነው ብሏል።
ሳይ ዛው ታይክ – ሚያንማር
የMyanmar Now ፎቶ ጋዜጠኛ ሳይ ዛው ታይክ በ2023 የCyclone Mocha ጉዳትን ሲዘግብ ተይዞ 20 ዓመት ከባድ እስራት ተፈርዶበታል።
CPJ እንደሚለው ሚያንማር በዓለም ላይ ጋዜጠኞችን በእስር ከሚያቆዩ አገራት መካከል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የGwen Ifill የፕሬስ ነፃነት ሽልማት
የ2026 Gwen Ifill Press Freedom Award የኤል ሳልቫዶር ጋዜጠኛና El Faro መስራች ካርሎስ ዳዳ ተሸላሚ ሆኗል።
ዳዳ ለዓመታት በሙስና፣ በወንጀለኛ ቡድኖች፣ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በመንግሥት አሰራር ላይ የምርመራ ዘገባዎችን በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከመንግሥታዊ ጫና የተነሳ በስደት እየኖረ ነው።
CPJ እንደገለጸው፣ የ2026 ተሸላሚዎች የተመረጡት ከፍተኛ አደጋና ጫና ውስጥ ሆነው ለሕዝብ እውነታን ለማድረስ ባሳዩት ድፍረትና ቁርጠኝነት መሠረት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ
*ሊዮ 14ኛ በቀጣይ ጉብኝት የሚያደርጉባቸውን ሦስት ሀገራት ታውቀዋል።
#ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኅዳር ወር በደቡብ አሜሪካ አገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።
ፖፕ ሊዮ 14ኛ በኡሩጉዋይ፣ አርጀንቲና እና ፔሩ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቋል።
ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ በኋላ ወደ ደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዟቸው ይሆናል።
በዚህም ከኅዳር 6 እስከ 17 ባሉት 12 ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ከተሞችን የሚሸፍን ጉብኝት ይሆናል ተብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቀድሞ ስማቸው ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት በፔሩ አገር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በምስዮናዊነት እና በጳጳስነት ያገለገሉ ሲሆን የዚያች አገር ሙሉ ዜግነትም እንዳላቸው ተገልጿል።
ፖፕ ሊዮ ረጅሙን የጉዞ ጊዜ በፔሩ የሚያሳልፉ ሲሆን ሊማ ቺክላዮና ኩስኮ ከተሞችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የትውልድ አገራቸው አርጀንቲናን በ12 ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነታቸው ወቅት መጎብኘት አልቻሉም ነበር።
አሁን የሊዮ 14ኛ የአርጀንቲና ጉብኝት በአገሪቱ ዜጎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #popeleo #vatican #peru #argentina #uruguay

4 days ago
የአረንጓዴ ዐሻራ የሰባት ዓመታት ሰባት አንኳር ስኬቶች
*************
አረንጓዴ ዐሻራ በኢትዮጵያ ምድር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ ሀገራችንን ከአፈር መሸርሸር እና ከበረሃማነት የመታደግ ሀገራዊ ራዕይ ብቻ ሳይሆን፤ የምድርን ሕይወት የሚያድስ፣ የዜጎችን ሥነ-ልቦናዊ አስተሳሰብ የሚቀርጽ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም የሚገነባ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሆኖ ዘልቋል።
ይህ ሀገራዊ የሕልውና ጥረት ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትራቴጂዎች ጋር ተናብቦ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያስመዘገባቸው ሰባት ዋና ዋና ተጨባጭ ስኬቶች እንደሚከተለው ተተንትነዋል።
1. የችግኝ ብዛትን ከጽድቀት ምጣኔ ጋር ያጣመረ አዲስ ታሪካዊ ሽግግር
ባለፉት ሰባት ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የተከላው ዋና ትኩረት ወደ ጥራት እና ድኅረ-ተከላ እንክብካቤ በማደጉ የችግኞች ጽድቀት ምጣኔ ከ80 በመቶ በላይ ማደግ ችሏል።
ይህም ቀደም ሲል የነበረውን "መተከል እንጂ አለመጽደቅ" የሚል የብክነት ታሪክን በመቀየር በቆላ እና በደጋ አካባቢዎች የተጎዱ መሬቶች በፍጥነት አረንጓዴ እንዲለብሱ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ሚዛን እንዲጠበቅ አድርጓል።
2. ከአካባቢ ጥበቃ ወደ የምግብ ዋስትና የተደረገ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር
አረንጓዴ ዐሻራ ከተፈጥሮ የደን ዛፎች ባሻገር እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ አፕል እና ቡና ያሉ ፍሬያማ ተክሎችን በስፋት አካትቷል።
ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ፕሮጀክቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እና አባወራዎችን የገበያ ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ብሎም የሀገራችን የግብርና ምርት የወጪ ንግድ የሚያሳድግ የኢኮኖሚ ሞተር አድርጎታል።
ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ማሻሻል ግብ ጋር በማስተሳሰር ዘላቂነቱ የተረጋገጠ የልማት ምሰሶ እንዲሆን አስችሎታል።
3. የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እና የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ
በመላ ሀገራችን የተቋቋሙት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች ለብዙ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለሴቶች አዲስ እና ዘላቂ የገቢ ምንጭ ሆነዋል።
ችግኝ ማፍላት፣ መንከባከብ እና ለገበያ ማቅረብ በራሱ አዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጅማሮ በጠንካራ መሠረት ላይ አኑሮታል።
ችግኞች ከተተከሉ በኋላ የሚደረገው ጥበቃ እና ክብካቤም በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ቋሚ የሥራ ዘርፍ መሆን ችሏል።
4. የውኃ ሀብት እና የታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ዋስትና
በስፋት የተከናወነው የደን ልማት እና የአፈር ጥበቃ ሥራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች በደለል እንዳይሞሉ የመከላከል ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል።
በተጨማሪም የከርሰ ምድር ውኃ መጠን እንዲያገግም እና የደረቁ የምንጭ ውኃዎች መልሰው እንዲፈልቁ በማድረግ አስተማማኝ የውኃ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
ይህ ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የመጠበቅ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን የውኃ ምንጭ ለሆነችላቸው የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ትልቅ ትሩፋት ነው።
5. አረንጓዴ ዲፕሎማሲ እና የቀጣናዊ ትሥሥር ማጠናከሪያ
ኢትዮጵያ ያዘጋጀቻቸውን ችግኞች እንደ ጂቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ላሉት ጎረቤት ሀገራት በማጋራት፣ የምሥራቅ አፍሪካን እና የአፍሪካ ቀንድን የቀጣና አየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮት በጋራ የመከላከል መሪነት ሚናዋን በተግባር አሳይታለች።
ይህም አረንጓዴ ዐሻራን የድንበር ተሻጋሪ ዲፕሎማሲ፣ የቀጠናው ሰላም እና የጋራ ልማት መሣሪያ አድርጎታል።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ በመከተል የአረንጓዴ ልማትን በሀገሮቻቸው እያስፋፉ ይገኛሉ።
ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ባመጣቻቸው ተጨባጭ ስኬቶች “ዘላቂ የደን ልማት አያያዝ እና አጠቃቀም” በሚል ዘርፍ ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) ከፍተኛ እውቅናን አግኝታለች።
6. የከተሞች ሥነ-ምኅዳር መታደስ እና የኮሪደር ልማት ውበት
አረንጓዴ ዐሻራ በገጠር ተራራዎች ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ወደ ከተሞች በመግባት የዘመናዊ ፓርኮች ግንባታ፣ የከተማ አረንጓዴ ልማት እና አሁን ላይ በስፋት እየተተገበረ ላለው የኮሪደር ልማት ዋነኛ አካል ሆኗል።
ይህም የከተሞችን የአየር ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ከመጨመሩም በላይ፣ የሥነ-ሕይወት ስብጥርን ወደ ነበረበት በመመለስ እና ለዜጎች ምቹ የመዝናኛ እና የኑሮ አካባቢን በመፍጠር የከተሞቻችንን ገጽታ ሙሉ በሙሉ በመለወጥ ላይ ይገኛል።
7. ሕዝባዊ ንቅናቄ እና የዜግነት አገልግሎት ባህል ግንባታ
በአንድ ጀምበር በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ችግኝ የመተከል ልምዳቸው፣ የአካባቢ ጥበቃን ከዘመቻነት አውጥቶ የባህል እና የዜግነት ግዴታ አካል አድርጎታል።
ይህም የሕዝባዊ ወንድማማችነትን ያጠናከረ እና የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤን በማሳደግ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር እጅግ ግዙፍ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ስኬት ነው።
በአጠቃላይ አረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተፈጥሮ ሀብታችንን ከመመለስ አልፎ ሀገራዊ አንድነትን ያጠናከረ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ አቅማችንን የገነባ እና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አቅራቢ ሀገር ያደረገ አንጸባራቂ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #climateaction #greendiplomacy #greeneconomy

5 days ago
የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏
በምጽዋትና በስገድት የምትጋደለው እናቱ ዮስቴና ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ወደ በረኃ ሄደች።
በዚያ ያገኘችው ባሕታዊም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሰች፡፡ የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ከዚህች የተባረከች ሴት ጋር ተጋባ። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች፣ በሕግ ተወስና በጾም፣ በጸሎት፣ የምትተጋ ነበረች።
ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔር አንጸው አሳደጉት። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።
አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅ ሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል።
እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡ ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። የቅዱስ ማቴዎስንና የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ሲያነብ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ ሰጠው፡፡
የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ሲያነብም ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ ሰጠውና ቃል ኪዳን ገባለት። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶች ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክት ሁሉ እየተደሰቱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያምን “ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል” አሉት። ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው በሰላም ተለየች።
ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Sponsored by
Surafel

አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል።

6 days ago
እንኳን ለቅዱስ መርቆርዮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏
የመጀመሪያ ስሙ ፒሉ-ፓዴር ሲሆን ቤተሰቦቹ አረማውያን ሲሆኑ ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የተመለሱ ናቸው፡፡ ፊታቸው የውሻ የሆነ፣ የአውሬነት ጸባይ ያላቸው በእግዚአብሔር ኃይል የሚታዘዙት ሁለት አገልጋዮች የነበሩት አባቱ ወደ መርዶሳውያን ሀገር ተማርኮ ቢሔድም ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት በዚያ ሹመት አጊቷል፡፡ ልጃቸው ቅዱስ መርቆርዮስን የወለዱት ግን በሮም ነው፡፡ ወላጆቹ ሲያርፉም የአባቱን ስልጣን ተረክቧል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ሁሉ ዘንድ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካቸው ከሚነገርላቸው ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያም በአማላጅነቱ የሚታወቀው ታላቁ ሰማዕት ነው፡፡ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጉሙ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያም በበርካቶች ዘንድ በፈጣን ተራዲኢነቱ ይታወቃል፡፡
የዓለም ክብራቸውን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ከጣሉና በተጋድሏቸው ከሚታወቁ ሰማዕታትም አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ የአባቱን ስልጣን ወርሶ በንጉሱ ስር በመርዶሳውያን አገር ላይ ተሾመ፡፡ መርቆሬዎስ በመኰንንነት በተሾመም ጊዜ የውሻ ፊት ያላቸው የአባቱ አገልጋዮች አብረውት ነበሩ፤ ለመዋጋትም ሲወጣም እግዚአብሔር የአውሬነት ተፈጥሯቸውን ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ የድል አድራጊነት ኃይሉ ዜናም በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በጦሩ መካከል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ “እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ” አለው፤ ከዚያም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና “ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው” አለው፡፡
ቅዱስ መርቆሬዎስ በድሉ ውስጥ ትልቅ ድርሻ በወሰደበት ውጊያም ጦርነቱ በንጉሱ ዳኪዮስ ወገን አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ መርቆሬዎስም ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት “ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት ረሳህ” አለው፡፡ ንጉሡ ግን ከጦርነቱም በኋላ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ በዚህ ያዘነው ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን አልተገኘም፡፡ ንጉሡም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣውና “ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?” አለው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ “ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፤ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም” አለው፡፡ ከዚህ በኋላ ሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ በክርስትናው ተፈተነ፤ ውለታው ተረስቶ ንጉሡ በልዩ ልዩ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡ ይሁንና ስለ መርቆሬዎስ ብለው የሀገሩ ሰዎች እንዳይነሡበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡
በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፤ በየወሩ በ25ኛው ቀንም መታሰቢያው ነው፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፤ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ ዛሬም የገዳማውያንን ጸሎት ይሰማል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

"ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ከአማራና ኦሮሞ ውህደት ውጭ ማየት አይቻልም"
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሀገሪቱን ለመቀየር ፖለቲካውንም ሆነ ኢኮኖሚውን ጎን ለጎን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ እንደነበር ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩም የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአማራና ከኦሮሞ ሕዝቦች ጥብቅ ውህደትና ትስስር ውጭ ሊታይ አይችልም። የዓድዋ ድልም የዚሁ ታሪካዊ አንድነት ትልቁ ማሳያ ነው፤ አብሮ የመኖር ባህልም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ እሴት እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ በሀገራችን ስልጣንን በኃይልና በሰው ግድያ ለመያዝ የመሞከር አጥፊ ባህል እንደነበር አውስተዋል። በዚህም የሰኔ 15ቱ ክስተት በለውጡ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸውን ሰዎች ያጣንበት የሕመም ጠባሳችን ነው ብለዋል።
ሆኖም ሕዝቡ ለውጡን በሙሉ ልብ የተቀበለ ሲሆን፣ በአንድነትና በትብብር አንዲት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በምርጫው ወቅት በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።
***
“የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች ለአጭር ጊዜ እፎይታ ተብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት መመለስ አይቻልም”
በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን ለአጭር ጊዜ እፎይታ ብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ መመለስ እንደማይቻል እና ጉዳዩ በሕግ አግባብ እና በሀገራዊ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የወልቃይትን ጉዳይ እንደ አብነት በማንሣት በትግራይም ሆነ በአማራ ክልል በኩል የሚነሡ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ዘላቂ መፍትሔው የሁለቱንም ሕዝቦች ጥቅም በማይጎዳ፣ በውይይት እና ሁለቱም አሸናፊ በሚሆኑበት ሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ካልሆነ መልሶ ለግጭት የሚዳርግ ቆይቶ የሚፈነዳ ቦምብ ይሆናል ብለዋል።
በሌላ በኩል ከውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በዚህም በፓርቲ ውስጥ የነበረውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሠራር ማስተካከል እና የክልሎችን ራስን የማስተዳደር መብት ማክበር ተችሏል ብለዋል ።
በተጨማሪም በመንግሥት ተቋማት አካታችነትን ማረጋገጥ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በካቢኔ እና በፖለቲካ ምኅዳር ማሳተፍ እንዲሁም አግላይ የነበሩ ትርክቶችን ማረቅም ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።
***
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል-
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሰኔ 15ቱን መጥፎ ክስተት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ታሪክን ማዛባት ለነገው ትውልድ የሚተርፍ እዳ ነው ብለዋል።
ለውጥን ለማምጣት በጽናት ሲሰሩ የነበሩ የለውጥ አበጋዞችን ያጣንበት፣ በፖለቲካው መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲሸረሸር ያደረገ እና የስልጣን ሽሚያ በሃይል የማስከበር መጥፎ ባህልን ያስቀጠለ አጋጣሚ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ስለ እለቱና ስለተፈጠረው ክስተት ሲያብራሩ፤ እለቱ ቅዳሜ ነበረ፤ መረጃውን እንደሰማሁ ለህዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ሚዲያዎች እንዲጠሩ አደረግኩ፤ ፋና እና ኢቢሲ በምሽቱ ፈጥነው አልደረሱም ነበር፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ግን እዚሁ 4 ኪሎ አቅራቢያ ስለነበር በፍጥነት ደረሰ ብለዋል።
መግለጫውን እኔ ቤት ሆኜ ለአሚኮ ሰጠሁ፤ በኋላ ግን 'ባህር ዳር ሆኖ መግለጫ ሰጠ' ተብሎ የሴራ ትንተና ተፈበረከበት በማለት አስታውሰዋል።
ይህ ክስተት ያስተማረን ትልቅ ሀቅም ታሪክን በትክክል አለማስቀመጥና ማዛባት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገውም ትውልድ እዳ ያተርፋል ሲሉ ተናግረዋል።
ገዳይም ሟችም በአንድ ላይ 'ጀግና' የሚደረግበት የታሪክ ስብራት ሊቆም እንደሚገባም በአፅንኦት አስገንዝበዋል።
***
"በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በዘመናት መካከል አብረው ሲኖሩ በብዙ መልኩ የተጋመዱ፣ የተሳሰሩ፣ የተጋቡ፣ የተዋለዱ በጋራ የኖሩ ናቸው''
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ethiopia #pmabiyahmed #currentaffairs #pmabiyahmed #amico #ethiopia #medemer #amharaandoromo #ethiopianunity

10 days ago
ታላቁ ሩጫ በአዲስ አበባ!
የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ኅዳር 13 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ይካሔዳል።
የውድድሩን ቲሸርት በቴሌብር ሱፐርአፕ በቀላሉ መግዛት ይችላሉ፤ አሁኑኑ ቲሸርትዎን በመግዛት ለዚህ ታላቅ ሩጫዝግጁ ይሁኑ!
በቴሌብር ሱፐርአፕ
https://bit.ly/telebirr_Su... ስንሳተፍ እንዲህ ነን!
#ደንበኛ_ስንሆን_እንዲህ_ነን #ስንመዘገብ_እንዲህ_ነን #ስንጭን_እንዲህ_ነን #ስናስጀምር_እንዲህ_ነን

23 days ago
ሀገር በምክክር እና በጋራ መግባባት ላይ ስትመሠረት ዘላቂ ሰላምና ጥንካሬ ታገኛለች
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተጻፈው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ላይ ሀገር በምክክር እና በጋራ መግባባት ላይ ስትመሠረት ዘላቂ ሰላምና ጥንካሬ እንደምታገኝ በሰፊው ተብራርቷል።
መጽሐፉ የኢትዮጵያን ዘመናት ያስቆጠሩ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ስብራቶች ለመጠገን ቁልፍ መፍትሔው ንግግርና ብሔራዊ ምክክር መሆኑን ያስረዳል።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ጉድለት በዋና ዋና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀምጦ በሰለጠነ መንገድ የመመካከር ባህል ማነስ ነው።
ይህንን ክፍተት ተንተርሶ የተጻፈውና የመደመር ፍልስፍናን ወደ ተግባራዊ የመንግሥት መዋቅር የሚያሸጋግረው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ፣ ሀገር ሊጸና የሚችለው በምክክርና በጋራ መግባባት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
መጽሐፉ እንደሚያስረዳው፣ ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፣ በውይይት ጎልብተው፣ አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት ታላቅ ምኅዳር ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ ሕዝብ በሰፊው ተመካክሮ የጋራ መግባባት ላይ ያልደረሰባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ።
በዚህም የተነሣ በየዘመናቱ ቅሬታዎች፣ ኩርፊያዎች፣ አብዮቶችና ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሲከሰቱ ኖረዋል።
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያብራራው፣ ሀገራዊ ምክክር እነዚህን የዘመናት ስብራቶች ለመጠገንና አዲስ የሰላም ምዕራፍ ለመክፈት ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው።
መጽሐፉ የፖለቲካ ባህላችንን ከጠብመንጃና ከኃይል አማራጭ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ንግግር መቀየር እንዳለብን ያሳስባል።
የተግባባንባቸውን ጉዳዮች በሕግና በሥርዓት አጽንቶ መጓዝ፣ ያልተግባባንባቸውን ደግሞ ለቀጣይ ምክክሮች አቆይቶ በሂደት መፍታት የሰለጠነ ማኅበረሰብ መገለጫ ነው።
ምክክር በሌለበት ምኅዳር ውስጥ ነገሮች በተናጠል ስለሚቀርቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና ሁለንተናዊ ዕይታን እንደሚያጠፋ መጽሐፉ ያስጠነቅቃል።
ኢትዮጵያ በታላላቅ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ የውስጥ አንድነትና የጋራ አቋም ሊኖራት የሚችለው ዜጎችና የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ መድረክ ላይ ሲመክሩ ብቻ ነው።
እንደ ሀገር በአንድነት ካልቆምን የትኛውም ዓይነት የልማትም ሆነ የዲፕሎማሲ ሥራ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል መጽሐፉ በምክንያት ያስረዳል።
ምክክሩም የትኛውም ዜጋ ሳይገለል የራሱን ሐሳብ አዋጥቶ የጋራ ሀገር የሚገነባበትን ዕድል ይሰጣል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያስረዳው፣ የሀገር ጽናት የሚለካው በኃይል ሳይሆን በውስጥ መግባባት ጥልቀት ነው።
ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት፣ የተግባባንበትን የጋራ ትርክት በማስፋትና ያልተስማማንበትን በሂደት በማጥበብ ብቻ ጠንካራና የማይናወጥ ሀገረ መንግሥት መገንባት ይቻላል።

24 days ago
የድኅረ-እውነት ፈተና፦ እውነት ዋጋ ባጣበት ዘመን ኢትዮጵያን ማዳን
**********************
በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕዝብ አስተያየት አወቃቀር እና የፖለቲካ ንግግሮች ምኅዳር በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጧል።
ለዚህም ዋነኛው ማሳያ፥ ተጨባጭ እና ሳይንሳዊ ሐቆች ለሕዝባዊ ውሳኔዎች መሠረት መሆን ሲገባቸው፣ ከእውነት ይልቅ ለሰዎች ስሜት እና ቀድሞ ለተነገሩ የግል እምነቶች የሚቀርቡ የማሳመን ሙከራዎች ከፍተኛውን ተፅዕኖ መፍጠራቸው ነው።
ምሁራን ይህን ጽንሰ-ሐሳብ "ድኅረ-እውነት" (post-truth) በማለት ይገልጹታል። ይህ ጽንሰ-ሐሳብ ሰዎች እውነትን ስለመቃወማቸው ሳይሆን፣ እውነት ራሱ ዋጋ ቢስ ወደሚሆንበት እና ከጉዳይ ወደማይቆጠርበት ደረጃ መድረሱን የሚያሳይ ነው።
ጀርመናዊው ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ ይህን ሀሳብ ሲገልጽ፣ "ተጨባጭ የሆኑ ፍፁማዊ እውነታዎች የሉም፤ ያለው የሰው ልጅ የሥልጣን ፍላጎት የሚፈጥረው ትርጓሜ ብቻ ነው" ይላል።
ዛሬ ላይ እውነታን ከፈጠራ የመለየት አቅም ማጣት ማኅበረሰብን ወደ አጠቃላይ አምባገነናዊነት እና ትርምስ እየመራው ይገኛል።
የድኅረ-እውነት ፖለቲካ መፈጠር እና መስፋፋት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዴሞክራሲያዊ ተቋማት፣ በሕዝብ አመኔታ እና በብሔራዊ ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ውድቀቶችን አስከትሏል።
እ.አ.አ በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ እና በእንግሊዝ የ‘ብሬግዚት' ውሳኔ ወቅት፣ ፖለቲከኞች የሕዝቡን የኢኮኖሚ ስጋት እና ብሔራዊ ስሜት የሚቀሰቅሱ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የምርጫውን ውጤት መለወጥ ችለዋል።
በተመሳሳይ እ.አ.አ በ2017 በሚያንማር በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ የጥላቻ እና የሐሰት ዘገባዎች በሀገሪቱ ለተፈጸመው አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋነኛ መንስኤ እንደነበሩ የተባበሩት መንግሥታት መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለዚህ የመረጃ ሥነ-ምህዳር መዛባት ግንባር ቀደም መደላድል የፈጠሩት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ ያሉት የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ናቸው።
የነዚህ መድረኮች የውሳኔ ሰጪ ስልተ-ቀመሮች (Algorithms) የተገነቡት የመረጃን እውነትነት ለማረጋገጥ ሳይሆን፣ የተጠቃሚዎችን ቀልብ በመሳብ መድረኩ ላይ ረጅም ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማድረግ ነው።
በዚህም የተነሳ ስሜት ቀስቃሽ፣ ጽንፈኛ እና አስደንጋጭ የሐሰት መረጃዎች በፍጥነት ይሰራጫሉ።
በተጨማሪም ተጠቃሚዎች የራሳቸውን አመለካከት ብቻ ከሚያስተጋቡ ሰዎች ጋር እንዲገናኙ በማድረግ፣ "Echo Chambers" ውስጥ እንዲዘፈቁ እና ከተቃራኒ እውነታዎች እንዲገለሉ ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ፈተና እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ
በኢትዮጵያ ያለው የድኅረ-እውነት ፈተና ከምዕራባውያን ሀገራት በተለየ መልኩ እጅግ አደገኛ እና የሰዎች ሕይወት ላይ አደጋ የሚፈጥር እየሆነ ነው።
በጥቂት ጽንፈኞች የሚነዙ ስሜት ቀስቃሽ የፈጠራ ትርክቶች ሀገራችንን ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈሏት፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት እንደ ጦር መሣሪያ ያገለገለው የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምስክር ነው።
መንግሥት መረጃ የማጣራት ሥራ ቢሠራም፣ የቴክኖሎጂው ፍጥነት ለቁጥጥር ፈተና ሲሆን አስተውለናል።
በአሁኑ ወቅትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተፈበረኩ እና ከሃይማኖት እንዲሁም ከብሔር ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ የሤራ ትንተናዎች ማኅበራዊ ሚዲያውን አጥለቅልቀውታል።
ይህ የመረጃ መዛባት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተካሄደ ካለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንጻር ሲታይ አሳሳቢ ነው።
ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ ሊሆን እና የዘመናት ቁስሎቻችንን ሊያክም የሚችለው፣ በሐሰተኛ ትርክቶች ያልተመረዘ፣ ለእውነት እና ለምክንያታዊነት የቆመ የሕዝብ ተሳትፎ ሲኖር ነው።
ነገር ግን የድኅረ-እውነት ፖለቲካ አራማጆች የሕዝቡን ስሜት በመኮርኮር፣ መተማመንን ለማሳጣት እና ልዩነቶችን ለማስፋት የሐሰት መረጃን በስፋት እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
በመሆኑም እውነተኛ ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ የምክክር ሂደቱ ከሐሰተኛ የመረጃ ዘመቻዎች ሊጠበቅ ይገባል።
አሁን እያንዳንዱ ዜጋ ሀገሩን ከዚህ ፈተና የማዳን ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። ማንኛውንም መረጃ ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት "መረጃው ከየት መጣ? ምንጩስ ታማኝ ነው ወይ?" ብለን መጠየቅ ዘመኑ የሚጠይቀው ዋነኛ የዜግነት ግዴታችን ነው።
ስሜትን ከሚኮረኩሩ እና ሀገርን ወደ ግጭት ከሚመሩ የሐሰት ትርክቶች ራሳችንን በማራቅ፣ ሀገራችንን ከድኅረ-እውነት አደጋ በጋራ እንታደግ!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #posttruth #disinformation #factcheck #socialmedia #ebc

26 days ago
ለዘመናት የተከማቹ መዋቅራዊ ስብራቶች ማከሚያ - ሀገራዊ ምክክር
******************
(የዕለቱ መልዕክት)
የምናካሂደው ሀገራዊ ምክክር የአንድ ወቅት ስህተቶች ማረሚያ አይደለም፤ ይህ መድረክ ለዘመናት፣ በትውልዶች ቅብብሎሽ ውስጥ ሳይፈቱ ተከማችተው እዚህ የደረሱትን ስብራቶች በጠረጴዛ ዙሪያ አምጥቶ መልክ የመስጠት፣ የቆዩ አንዳንዴም የተዛቡ ትርክቶችን የማቃናት የታሪክ አጋጣሚ ነው።
ዛሬ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ትልቁ ፈተናም የችግሮች መኖር ሳይሆን ችግሮቹን የምንመለከትበት መነጽር በመሆኑ እውነታውን በጥቅሉ መረዳት ያስፈልጋል።
የምክክሩ ዓላማም ለዘመናት የተከማቹትን አብረን ተወያይተን መልክ ለመስጠት እና አዲስ ማኅበራዊ ውል መሥራት ነው።
አሁን ያለንበት ወቅት “ይህንን ችግር ማን አመጣው?” በሚል ጣት የመቀሳሰር ጨዋታ ውስጥ የምንገባበት ጊዜም አይደለም። ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባው እውነታ ቢኖር አሁን የምንወያይባቸው ፈተናዎች የታሪክ ውጤቶች መሆናቸውን ነው።
ትናንትን መለወጥ ባንችልም፣ ነገን ግን ዛሬ በምናደርገው ምክክር መቅረጽ እንችላለን። ለዚህ ደግሞ ልብን ማስፋት፣ ሌላውን ለማዳመጥ መዘጋጀት እና ሁሉን አቀፍ የሆነ አካሄድን በቅንነት መቀበል ቀዳሚው ተግባር ነው።
ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወይም ችግሮች ሲነሡ “ማን ጀመረው፣ ለምን ጀመረው፣ እንዴት ተጀመረ?” የሚለው ጥያቄ እና ሒደቱን የመፍታት ቁርጠኝነት አሁን ባለው ትውልድ ላይ ብቻ እንደተጫነ ሸክም ተደርጎ ባይወሰድ ይመረጣል።
ያም ሆኖ፣ “አሁን ያለው ትውልድ መክሮ፣ ዘክሮ እና ተነጋግሮ መፍታት አለበት” የሚለውን እምነት በመያዝ ምክክሩን መቀጠል እና መደገፍ ይገባል።
ስለ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት “እንዴት ይሆናል?” ብለው ለሚጠይቁ ወገኖችም የሚሰጠው ምላሽ ግልጽ ነው፤ ሒደቱ በዕቅድ፣ በዕውቀት እና በዝግጅት እየተመራ በመሆኑ ምንም የሚፈጠር ችግር የለም።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ከሕዝብ የመጡ ሐሳቦችን (አጀንዳዎችን) አቀናብሮ በማቅረቡ፣ ተመካካሪዎችም ሆኑ መላው ማኅበረሰብ በትህትና የሚማርበት፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉዳዮች በውይይት አሻሽሎ በጋራ የሚሰበሰብበት እና የሚያጸድቅበት እንጂ መደናገጥ የሚፈጠርበት መድረክ አይሆንም።
ምክንያቱም ምክክሩ ያለውን የሚያሻሽል፣ የነበሩ መልካም ጅማሮዎችን የሚያጠናክር እንጂ የሚያጎድል ባለመሆኑ ነው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ እና ዜጎቿ በልዩነቶቻቸው ውስጥ ውበት አግኝተው በጋራ የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን ማድረግ የምንችለው እኛው ራሳችን ነን።
ዓለም የእኛን የመነጋገር እና የመደመጥ አቅም፣ ልዩነቶቻችንን አቻችለን በጋራ መኖር የምንችል ሕዝቦች መሆናችንን በጉጉት እየተመለከተ ነው።
ለዘመናት የተከማቹትን ችግሮች ለመፍታት ልባችንን እናስፋ፤ አዲሱን ማኅበራዊ ውል በጋራ እንጻፍ።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #nationaldialogue #endc #hope

27 days ago
ከፖለቲካ ሽኩቻ የላቀው የጋራ ተቋማችንን እናክብር
****************
የአንድ ሀገር ጥንካሬ ከሚገለጽባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ዜጎች በጋራ የሚግባቡባቸው እና በኩራት የሚጠሯቸው ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚውን እና የክብር ማማውን ስፍራ ይይዛል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንመለከት፣ በሠለጠኑ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የሠራዊት አባላትን ማክበር ከፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የላቀ ብሔራዊ መግባባት የተገነባበት ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ በፓርቲዎች መካከል የጎላ ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነት ቢኖርም፣ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ፉክክር ውጪ የማድረግ ብሔራዊ ስምምነት አለ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በሚተቹበት ወቅት እንኳ በጦር ግንባር የተሰማሩትን ወታደሮች እንደ ጀግና በመቁጠር ውዳሴ እና ክብር ያቀርባሉ።
በዩናይትድ ኪንግደም "የጦር ኃይሎች ቃል ኪዳን" (Armed Forces Covenant) የተሰኘው ብሔራዊ ሰነድ የሠራዊት አባላት ልዩ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋል።
ካናዳ ለአርበኞች ልዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ስታቋቁም፣ ፈረንሳይ ደግሞ ሠራዊቷን የሀገሯ የክብር እና የአጋርነት ብሔራዊ ተምሳሌት በማድረግ በትልቅ ማዕረግ ትዘክራለች።
ወደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በባሕርይው እጅግ ሕዝባዊ የሆነ፣ ከሀገር አልፎ ለዓለም የሰላም ዘብ በመሆን ደሙን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር በኮሪያ ልሳነ ምድር በቃኘው ሻለቃ አማካኝነት "አንድም ወታደር አልተማረከም፤ የሞተ ጓዱንም ጥሎ አልመጣም" የሚል የዓለምን አስደናቂ ሪከርድ ያስመዘገበ ጀግና ነው።
በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በአብዬ፣ በዳርፉር እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት አፍሪካውያን ወንድሞቹን ከእልቂት የታደገ፣ የራሱን ሬሽን እያካፈለ የውጭ ሀገር ዜጎችን ያኖረ የሰብአዊነት ተምሳሌት ነው።
ይህ ሠራዊት በሀገር ውስጥም ቢሆን ጦር መሣሪያውን አስቀምጦ በክረምት የገበሬውን ማሳ ሲያርስ እና በመኸር ሲያጭድ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ከነፍስ አድን ሥራ እስከ አንበጣ መንጋ ማባረር ድረስ ከሕዝቡ ጎን የቆመ ታላቅ አለኝታ ነው።
ነገር ግን አለመታደል ሆኖ፣ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል በሚደረጉ ፍልሚያዎች ውስጥ የከፉ ምኞቶች ሰለባ ሲሆን ይስተዋላል።
አንዳንዴም የፖለቲካ ልዩነትን እና የሀገርን የፀጥታ ምሰሶ መለየት ያቃታቸው አካላት ሠራዊቱን የማንቋሸሽ አዝማሚያ ያሳያሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ማክበር እና ለሀገር ሕልውና የሚከፍለውን ዋጋ ማወቅ የአንድ ማኅበረሰብ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገርን ጠብቆ የሚያኖርን ኃይል እንደ "ገዳይ" መፈረጅ እና ተቋማዊ ክብሩን አለማወቅ የሲቪል-ወታደራዊ ግንኙነትን አለመረዳት እና ያለመሠልጠን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት እና ፖሊሲ አውጪዎችን በጥብቅ መተቸት የዴሞክራሲ አካል ነው። ነገር ግን ለሀገር ሕልውና አጥንቱን የሚከሰክሰውን ሠራዊት ከተቋማዊ ትችት ነፃ አድርጎ በጀግንነት መዘከር ይገባል።
በመሠረቱ ሠራዊቱ ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት የመካስ የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት አድርጋ ከሠራችባቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል የፀጥታ ተቋማት ግንባታ ዋነኛው የሆነውም ለዚሁ ነው።
ሠራዊታችን ከፖለቲካ ልዩነቶቻችን በላይ የሆነ የጋራ የብረት አጥራችን እና የሕልውናችን ምሰሶ በመሆኑ ዘወትር ክብር እና ሞገስ ይገባዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #endf #nationalpride #standwithourtroops

28 days ago
ለቀጣናው ዋስትና እየሆነች ያለች ሀገር
የኢትዮጵያ የፀጥታና የደኅንነት ተቋማት ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና ሰብአዊ አቅምን በማስተባበር በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የጎላ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት እና በፌደራል ፖሊስ የተገነባው ይህ አስተማማኝ አቅም ቀጣናዊ የሽብር አደጋዎችን እና ሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመከላከል ረገድ ለአፍሪካ ቀንድ የማይተካ የደኅንነት ዋስትና ሆኗል።
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጡ፣ በተለዋዋጭ የደኅንነት ምኅዳር እና በተለያዩ የድንበር ተሻጋሪ አደጋዎች የተከበበ ነው።
በእነዚህ ፈተናዎች መካከል ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብሯን እና የሕዝቦቿን ሰላም ለማስጠበቅ የገነባቻቸው የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት፤ በማንኛውም ዓይነት የውስጥም ሆነ የውጭ ሤራ የማትበገር ጽኑ ሀገር መሆኗን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
ተቋማቱ በሰው ኃይልና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አቅም በመገንባታቸው ተልዕኳቸውን በብቃት እየተወጡ ይገኛሉ።
ባለፉት ሀገራዊ የለውጥ ዓመታት ውስጥ መንግሥት ከተገበራቸው የሪፎርም አምዶች አንዱ ጠንካራና ገለልተኛ የፀጥታና የደኅንነት ተቋማትን መገንባት ነበር።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቴክኖሎጂ፣ በመረጃና በሳይበር ሥርዓት የዘመነ አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል።
ሰራዊቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ለቀጣናው ሀገራት መከታና የሰላም ምሰሶ አድርጓታል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በበኩሉ የቀጣናውን የፀጥታ ሁኔታ በጥልቀት በመተንተን አሸባሪ ቡድኖችና አደገኛ አውታረ መረቦችን ቀድሞ በመምታት ሀገራዊና ቀጣናዊ ሰላምን በማስጠበቅ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስልታዊ ድሮኖችን በመታጠቅ የአየር ክልሉን ፍፁም የማይደፈር አድርጎታል።
የኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ደግሞ ኢትዮጵያ በግፍ ወደ ተነጠቀችው የባህር በር ለመመለስና የኢትዮጵያን የወደፊት የኢኮኖሚና የደኅንነት ጥቅም ለመጠበቅ በንቃት ራሱን አደራጅቶ ለተልእኮ እየተዘጋጀ ይገኛል።
በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ ለዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች፣ ለሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያና የሰዎች ዝውውር ተጋላጭ ነው።
የኢትዮጵያ የፀጥታ ተቋማት መረጃዎችን በወቅቱ በመለዋወጥ እና በማክሸፍ በቀጣናው ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀርተዋል።
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አሰራሮች ምንም ዓይነት የስጋት ደረጃ እንደሌለባቸው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ያረጋገጠው፣ ተቋማቱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን አሳይቷል።
አዳዲስ ጦርነቶች በሳይበር ሥርዓት እና በፈጣን መረጃ ልውውጥ ላይ በተመሰረቱበት በዚህ ዘመን፣ የሀገሪቱ የሳይበር ደኅንነት ተቋማት ሀገራዊና ቀጣናዊ መሠረተ ልማቶችን ከአደጋ በመጠበቅ አስተማማኝ ዋስትና ሆነዋል።
የኢትዮጵያ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሰላምና ልማት ከማረጋገጥ ባለፈ ለቀጣናው አፍሪካ ቀንድ የሰላምና መረጋጋት ትልቅ ዋስትና ናቸው።
ተቋማቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በሰለጠነ የሰው ኃይል እና በብቃት በመታገዛቸው ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የፖለቲካና የደኅንነት አጋርነት አጠናክረው የሚያስቀጥሉ ናቸው፡፡

1 month ago
ከጊዜያዊ እርካታ ወደ ዘላቂ ከፍታ፡ የማይሻረው የትውልድ አሻራ
***********************
( የዕለቱ መልዕክት)
ዛሬ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የልማትና የኢኮኖሚ ምዕራፍ በተጨባጭ የሚዳሰሱ ፍሬዎችን እያሳየ ይገኛል። በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ ጥቂት ሀገራት ተርታ ቀዳሚ መሆን መቻሏ በየከተሞች የተገነቡ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻዎችና በየአካባቢው የሚታዩት ሜጋ ፕሮጀክቶች ሀገራችንያላትን ተፈጥሯዊ ጸጋና የመስራት ብቃት በተግባር ያሳዩ ናቸው።
ይሁንና ይህ ስኬት ገና የመንገዳችን ጅማሮ እንጂ ፍጻሜያችን አይደለም። ከትናንት የድህነት ልካችን አንጻር የተሻለ ቦታ ላይ መድረሳችን እውነት ቢሆንም ከሚጠበቅብን ግዙፍ ሀገራዊ ስራ ውስጥ ገና አንድ በመቶዉን ብቻ እንዳከናወንን መገንዘብ ይገባል።
ለአንድ ሀገር ትልቁ ስነ-ልቦናዊ አደጋና በሽታ በትንሽ ስኬት መርካት ነው። በትናንሽ ስኬቶች መታወር ወደፊት እንዳንራመድ አግዶ በነበርንበት እንድንቆም ያደርገናል። በመሆኑም አሁን የተጀመሩት ስራዎች ለቀጣዩ ትልቅ ምዕራፍ እንደ ማበረታቻ ምልክት እንጂ እንደ መጨረሻ ማረፊያ ሊወሰዱ አይገባም።
ሀገርን መገንባት ለእለት ፍጆታ የሚደረግ ጊዜያዊ ሩጫ ሊሆን አይገባም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደሚሉት ሰው በሀገሩ ላይ የሚገነባውና የሚያለማው ለዕለት ፍጆታ ብቻ መሆን የለበትም፤ የምንሠራው ሥራ የሚዘልቅ፣ የሚሻገርና ለልጆቻችን የሚወረስ መሆን አለበት።
በመሆኑም ዛሬ የምንተክለውና የምንገነባው ማናቸውም መሰረተ ልማት በጥራት ላይ የተመሰረተ ለነገው ትውልድ የሚሻገርና የአካባቢውን ባህላዊና ስነ-ልቦናዊ እሴት የጠበቀ “የማይፈርስ አሻራ” ሊሆን ይገባል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን አሁን ያለችበት ቦታ የሚመጥናት አይደለም። ወደሚገባት ታላቅ ከፍታ ለመድረስ የጋራ እይታ፣ የተገለጠ ራዕይ እና የማየት ብቃት ያስፈልገናል። በተለይም በምግብ ራስን መቻል፣ በበጋ ስንዴ ማምረት እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ማስፋፋት የህልውና ጉዳዮች እንጂ ምርጫዎች ሊሆኑ አይችሉም።
ይህን ልማት የሚሸከም ጤናማ ማኅበራዊ ስነ-ምኅዳር መፍጠር ግን ቀዳሚው የቤት ስራ ነው። በተለይም የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ አካባቢዎች ማኅበረሰብ ታማኝነትን፣ አስተማማኝ ሰላምን፣ ጽዳትና አረንጓዴነትን እንደ መርህ ሊይዟቸው ይገባል።
የአንድ ቀን የሌብነትና የክፋት ተግባር የአመታትን በጎ ስም በአንድ ጀንበር ያጠለሸዋል። ቱሪስት ንብረቱ ቢጠፋበት እንኳን ተፈልጎ የሚመለስበት የታማኞች ምድር መሆን ቀጣይ ኢንቨስትመንትን የሚስብ ትልቁ ሀብታችን ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የሕዝቦች አንድነትና ትብብር ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ብሔረሰቦች ውብ ስብስብ ነች። አንዱ ብሔር ከሌላው እንደማይበልጥና ሁሉም እኩል መሆናቸውን አምኖ መቀበል የስልጣኔ መጀመሪያ ነው።
"እኔ እበልጣለሁ፣ ከእኔ ውጪ" የሚለው የትዕቢት ስሜት፣ አካባቢያዊና ብሔር ተኮር ሽኩቻዎች እንዲሁም የፖለቲከኞች የከፋፍለህ ግዛ አጀንዳዎች ለዘመናት በድህነት አቆይተውናል። መበላለጥ መለካት ያለበት በብሄርስም ሳይሆን በተግባርና በስራ ብቻ ነው። አንዱ አካባቢ ሲለማ ሌላው የሚደሰትበት፣ የትም ቦታ የሚመጣን ሰራተኛና ባለሀብት እንደ እራስ ወገን አቅፎ የሚያስተናግድ ሰፊ ልቦና ሲኖረን የሀገራችን ብልጽግና ይፈጥናል።
የሀገር ዕድገትና ትውልድን ማሻገር በተግባር እንጂ በባዶ ንግግርና በልመና አይመጣም። ዓለም አቀፋዊ እውነታው የሚያሳየንም አስቀድመው የተዘጋጁ ሀገራት ጥቅማቸውን እንደሚያስከብሩና ያልተዘጋጁት ደግሞ ሳይነኩ የሚንኮታኮቱ መሆኑን ነዉ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳመለከቱትም አሁን ያለው ትውልድ በታሪክ አጋጣሚ የድህነትን መጥፎ አሻራ ተሸክሞ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ድህነት ወደሚቀጥለው ትውልድ እንዳይሻገር ራሳችንን ክደን፣ ለልጆቻችን ዘላቂ መሠረት የመጣል ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን።
ፈተናዎችና ወደ ኋላ የሚስቡ እጆች ቢኖሩም በመልካም እሳቤና በትጋት የሚሰሩ ኃይሎች ማሸነፋቸው አይቀሬ ነው።
በማንኛውም መመዘኛ እየወደቀ ካለ ሀገር ይልቅ እያደገ ካለ ሀገር ጋር መጓዝ ይመረጣል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ማደግ የጀመረች እና ከፍተኛ ሥራ የምትሻ በመሆኗ የምናፈስሰው ላብና የምናሳየው አንድነት ነገ ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ ሀገር ያጸናል።
ስንሰራም ሆነ ስንተባበር ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ በሚሻገር አሻራ ላይ ይሁን።

የሸገር ወንዞች ሲፈውሱ፡- ከብክለት ወደ ሕዝብ መዝናኛነት
********************
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያስመዘገበችው ግዙፍ የከተማ ገጽታ ለውጥ ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባሻገር የከተማዋን ነዋሪዎች አኗኗር፣ ማኅበራዊ መስተጋብርና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የቀየረ ጥልቅ ስትራቴጂካዊ ሽግግር ነው።
ለረጅም ዘመናት አዲስ አበባ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ማደግ፣ በኮንክሪት ሕንጻዎች መበራከትና በአረንጓዴ ሥፍራዎች መመናመን ትታወቅ የነበረች ቢሆንም በቅርቡ የተከናወኑት የተቀናጁ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ግን ከተማዋን ወደ አዲስ የዕድገትና የውበት ምዕራፍ አሸጋግረዋታል።
ይህ ዘመናዊ ለውጥ በተለይም ቀደም ሲል የብክለት፣ የቸልተኝነትና የከተማዋ የጀርባ ገጽታ መገለጫ የነበሩትን የውሃ አካላትና ተፋሰሶች ወደ ሕያው፣ ማራኪና ሥነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ ወደላቸው የሕዝብ መጠቀሚያዎች በመለወጥ ረገድ ያተመዘገበው ስኬት የከተማዋን ታሪክና ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።
ይህ ዓይነቱ ትራንስፎርሜሽን የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ጥራት ከማሻሻሉም በላይ አዲስ አበባ በዓለም አቀፍና በአህጉራዊ መድረኮች ያላትን የላቀ አቋምና የቱሪስት መዳረሻነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገው ይገኛል።
ለዚህም በዋና ማሳያነት የሚጠቀሰው ከእንጦጦ ጋራ ተነስቶ እስከ ቀበና የሚዘልቀው የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ነው። ይህ ሰፊ ኮሪደር ቀደም ሲል ለደህንነት አስጊና በቆሻሻ መጣያነት ያገለግል የነበረ አካባቢን ወደ ዘመናዊ የሕዝብ መዝናኛ፣ የእግር ጉዞ መንገዶችና የአረንጓዴ ልማት ማዕከልነት እንዴት መቀየር እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ታላቅ ስኬት ነው።
በእንጦጦ እና በቀበና ተፋሰስ መካከል በተገነቡት ዘመናዊ የሕዝብ መጠቀሚያ ሥፍራዎች ውስጥ የሚገኙት ውብ የእግር ጉዞ መስመሮች፣ የተፈጥሮን ሚዛን የጠበቁ የአትክልትና የዛፍ ዝርያዎች እንዲሁም ለዕረፍትና ለንባብ የተዘጋጁ ምቹ መቀመጫዎች ተፈጥሮንና ዘመናዊነትን በአንድ ጥላ ሥር ያቀናጁ ናቸው።
ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ከከተማዋ የዕለት ተዕለት ጫጫታና ውጥረት ወጥተው ንጹህ አየር የሚተነፍሱበት አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነታቸውን የሚያድሱበት ሰላማዊ ምኅዳር ተፈጥሯል።
ይህ መሠረተ ልማት በከተማ ፕላን ውስጥ ለሰዎች ቅድሚያ የመስጠትን መርህ ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ወንዞች የከተማዋ የጀርባ አጥንትና የውበት መገለጫ መሆን እንደሚችሉ ያስመሰከረ አብነት ነው።
የዚህ የገጽታ መቀየር ዘላቂ ፋይዳ በዋናነት በሦስት ታላላቅ ዘርፎች ጎልቶ ይታያል። የመጀመሪያውና ግዙፉ ተጽዕኖ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ የታየው አስደናቂ መነቃቃት ነው። አዲስ አበባ ቀደም ሲል የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና የትራንዚት መንገደኞች ጊዜያዊ ማረፊያ ብቻ ሆና የምትታወቅበትን የቆየ ገጽታ በመቀየር አሁን ላይ ጎብኚዎች ቀናትን አሳልፈው የሚዝናኑባትና የሚጎበኟት እውነተኛ የመዳረሻ ከተማ እየሆነች ነው።
የወንዝ ዳርቻዎቹ ውበት፣ ማራኪ የውሃ ፏፏቴዎችና በምሽት በደማቅና ውብ መብራቶች የሚዋቡት ፓርኮች ለምሽት ቱሪዝም አዲስ በር ከፍተዋል። ይህም የፎቶግራፍ አፍቃሪዎችንና ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን የሚስቡ በርካታ ማራኪ ቦታዎችን በመፍጠር የከተማዋን ዓለም አቀፍ ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ገንብቶታል።
ሁለተኛው ከኢኮኖሚ ዕድገትና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር የተያያዘ ነው። በእነዚህ የተገነቡ የሕዝብ መጠቀሚያዎች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ተቋማት፣ ባህላዊ የምግብና የመጠጥ አቅራቢዎች እንዲሁም የዕደ-ጥበብ ውጤቶች መሸጫዎች ለበርካታ ዜጎች ዘላቂ የገቢ ምንጭና የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል። ይህ ሁኔታ የከተማዋን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ በማነቃቃት የቱሪዝም ኢኮኖሚው በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ እንዲደርስ አድርጓል።
ሶስተኛውና ትልቁ ስኬት የአካባቢ ጥበቃና የስነ-ምህዳር ሚዛንን ከመጠበቅ አንጻር የተመዘገበው ዘላቂ ውጤት ነው። ወንዞችን ከኢንዱስትሪና ከቤት ውስጥ ብክለት መታደግ መቻሉ፣ በዳርቻዎቻቸው ላይ የተተከሉ አረንጓዴ ተክሎችና ዛፎች የከተማዋን የካርቦን ልቀትን ለመቀነስና ብዝሃ ሕይወትን መልሶ ለማደስ ያላቸው ሚና ወደር የለውም።
በአጠቃላይ ሲታይ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተመዘገበው የወንዝ ዳርቻ ልማትና የውበት ስራ ከተማዋን ይበልጥ ለኑሮ ተስማሚ፣ ለዐይን ማራኪና በኢኮኖሚ ረገድ እራሷን የቻለች ማዕከል እያደረጋት ይገኛል።
ይህ ዓይነቱ የተቀናጀ የልማት አካሄድ አዲስ አበባ በአፍሪካ አህጉር ያላትን ተወዳዳሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገር ታላቅ የታሪክና የውበት ዐሻራ ነው።
በበረከት ሽመልስ
#addisababa #riversidedevelopment #greenlegacy #tourismethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

የነገው የኢኮኖሚ ሞተሮች፤ ከተመራቂነት ማዕረግ በስተጀርባ ያለው የሥራ ፈጠራ ጥሪ
*******************
ይህ ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉበት ጊዜ ነው። ነገር ግን ከምርቃቱ ድምቀት በስተጀርባ እያንዳንዱ ተመራቂ “ቀጣዩ ምዕራፍ ምንድን ነው?” የሚል ከባድ ጥያቄ በውስጡ ይዟል። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የቀድሞው የተለመደው የቅጥር ፈላጊነት አስተሳሰብ ተለውጦ ወደ ሥራ ፈጣሪነት መሸጋገር የሕልውና ጉዳይ ሆኗል።
የሀገራችን ተጨባጭ እውነታ እንደሚያሳየው ከነበረብን የቆየ ተደራራቢ ችግር እና የሥራ አጥ ፍላጎት አንጻር የሥራ ፈጠራ ጉዳይ የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳይሆን፣ የረዥም ጊዜና ከፍተኛ ርብርብ የሚጠይቅ አጀንዳ ነው።
መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ለ15 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የገለጸ ሲሆን፣ ይህም በአማካይ በየዓመቱ ለ4 ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ተስፋን የሰነቀ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ ይህ አሃዝ የሚያሳየው ትልቁ እውነት ገበያው አሁንም ምን ያህል ሰፊና ተለዋዋጭ መሆኑን እንዲሁም አዳዲስ ተመራቂዎችን የሚጠብቃቸውን ዕድልና ኃላፊነት ነው።
ለአዲሱ ተመራቂ ትውልድ ትልቁ መልካም ዜና የሥራ ገበያው መዋቅር ከባህላዊው አሠራር ወጥቶ ወደ ዘመናዊና አማራጭ መንገዶች እየተቀየረ መሆኑ ነው። ለምሳሌ በ2017 በጀት ዓመት ከተፈጠረው የ5 ሚሊዮን የሥራ ዕድል ውስጥ በሀገር ውስጥ ከተሰማሩት 4.4 ሚሊዮን ዜጎች በተጨማሪ፣ በውጭ ሀገር የሥራ አማራጮች 503 ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
ከሁሉም በላይ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረው የውጭ ሀገር የርቀት ሥራ 57 ሺህ ዜጎች መሳተፍ መቻላቸው፣ ለአሁኑ ተመራቂ ወጣት አዲስ የሥራ ዓለም መከፈቱን ያበስራል። ይህ ስኬት ቴክኖሎጂን የታጠቀ፣ ክህሎቱን ያዳበረና በዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደር የሚችል ወጣት ሳይሰደድ በሀገሩ ተቀምጦ የዓለም ገበያን መቆጣጠር እንደሚችል ማሳያ ነው።
ውጤቱ ሊመዘገብ የቻለው የግል ዘርፉን እንደ ዋና የልማት አጋር በመመልከት፣ የብድርና የፋይናንስ ማነቆዎችን በመፍታት ልዩ የድጋፍ ማዕቀፍ በመፈጠሩ ነው። አሁን ወደ ገበያው የሚገቡ ተመራቂዎች ይህንን የተመቻቸ ምኅዳር በመጠቀም የራሳቸውን የፈጠራ ሐሳብ ወደ ንግድ የመቀየር ትልቅ ዕድል አላቸው።
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዓመታት ፈጣንና ፍትሓዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ በምታደርገው ጥረት በተለይም በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን ማሳደ፣ በአምራች ኢንዱስትሪው ረገድ ሰፊ መነቃቃትን መፍጠር እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፉን ይበልጥ ማዘመን ላይ በትኩረት እየሠራች ትገኛለች።
እነዚህን ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተያዘው ብሔራዊ ዕቅድ ለአዳዲስ ተመራቂዎች ሰፊ የሥራ ዕድል፣ አዳዲስ የገበያ አማራጮችንና ሰፊ የፈጠራ ሜዳን ይዞ የሚመጣ በመሆኑ ትልቅ ተስፋን የሚሰነቅ ነው።
በዚህም በየዓመቱ ለ3 ሚሊዮን ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በታቀደው ብሔራዊ ራዕይ ውስጥ፣ የተመራቂዎች ሚና የነገውን ተስፋ የሚወስን ነው።
የዲጂታል ምኅዳሩ መስፋፋት፣ የክህሎትና የብቃት ማደግ እንዲሁም የፋይናንስ አቅርቦቶች መመቻቸት ተመራቂዎች የሥራ ፈላጊነት ሰለባ ሳይሆኑ ራሳቸውን ችለውና ለሌሎችም ተርፈው የኢኮኖሚው ዋና ሞተር እንዲሆኑ በር ከፍቷል።
ስለዚህ የዘንድሮ ተመራቂዎች ማዕረጋቸውንና ዕውቀታቸውን ይዘው ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ ማሰብ ያለባቸው፣ መንግሥትና የግሉ ዘርፍ ባዘጋጁት የኢኮኖሚ መነሻ ላይ ቆመው በራሳቸው የፈጠራ ጥረት የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ እውን ማድረግ ላይ መሆን አለበት።

የሥልጣን መያዣው መንገድ በምርጫ ብቻ መሆን እንዳለበት ሕዝቡ በተግባር አሳይቷል፡- የኢዜማ መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት
**********************
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ከኢቲቪ ወቅታዊ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የድህረ ምርጫ ወቅታዊ ሁኔታዎችንና የፓርቲያቸውን የቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መሪው በምርጫው ወቅት የታየውን ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ያደነቁ ሲሆን፣ ሕዝቡ በተለያዩ ተግዳሮቶች ሳይበግረው ረጅም ሰዓት ተሰልፎ መምረጡ ከሰላማዊ አማራጭ ውጪ በጠመንጃ ሥልጣን የመያዝ አባዜ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ውስጥ ሙሉ በሙሉ መወገድ እንዳለበት ያሳየበት ግልጽ መልዕክት ነው ብለዋል፡፡
ኢዜማ ወደ ምርጫው የገባው የኢትዮጵያን ተጨባጭ የፖለቲካ ምኅዳር በጥልቀት ገምግሞ መሆኑን የገለጹት አቶ እዮብ፣ ፓርቲው አስቀድሞ ካስቀመጠው ግብ አንጻር የአሁኑ ተሳትፎው ከሞላ ጎደል ስኬታማ እንደነበርና ምርጫ ሲደርስ ብቻ የሚደናገጥ ሳይሆን ራሱን ወዲያውኑ ለቀጣዩ ምርጫ ማዘጋጀት መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
ኢዜማ በክልልና በፌደራል ምክር ቤቶች በድምሩ 86 ወንበሮች ማግኘቱን የጠቀሱት መሪው፣ እነዚህን ወንበሮች በመጠቀም አማራጭ ፖሊሲዎችን ወደፊት ለመግፋትና መንግሥትን ለመጠየቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩበት አረጋግጠዋል፡፡
አያይዘውም አሁን ለተመረጠው መንግሥት የተሰጠው ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጠ ሕዝባዊ አደራ እንጂ እንደፈለጉ የሚፈነጩበት ሥልጣን አለመሆኑን አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የምርጫ ሥርዓት ተቀይሮ የአንድም ዜጋ ድምፅ እንዳይባክን የሚያደርግ “የተመጣጣኝ ውክልና ሥርዓት” ሊተገበር እንደሚገባ ፓርቲያቸው በፅኑ እንደሚያምንና ኢትዮጵያ ውስጥ ከፖለቲካና ከዘውግ ወገንተኝነት የጸዱ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ገለልተኛ ተቋማትን (Institutions) ለመገንባት የገዥው ፓርቲ ቀዳሚ ኃላፊነት ቢሆንም የሁላችንም የጋራ ርብርብ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
የባሕር በር ጉዳይን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት አቶ እዮብ መሳፍንት፣ የባሕር በር ጥያቄ የቅንጦት ሳይሆን ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ላላት ሀገር የልማት፣ የዕድገትና የደኅንነት ዋስትና መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ብሔራዊ ጥቅም ከፊት ሆኖ ከሚያራምድ ከማንኛውም አካልና ከመንግሥት ጋር በትብብር ለመሥራት ፓርቲያቸው ዝግጁ መሆኑን በድፍረት ተናግረዋል፡፡
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopianelection #ezema #peacefulpolitics #nationalinterest #ethiopianbroadcastingcorporation

2 months ago
የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር እመርታ
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዓለማችን በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ፈጣን ግስጋሴ ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት በውል በመገንዘብ፣ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚዋን ከመሠረቱ የሚቀይር ታሪካዊ የዲጂታል ሽግግር እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት ዓመታት ሀገራችን ያለባትን ዘላቂ የቢሮክራሲ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቅረፍ ዲጂታላይዜሽንን እንደ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ በመውሰድ በቁርጠኝነት እየሠራችበት ነው።
ይህ ጉዞ የሀገርን የልማት ምሰሶ በጠንካራ መሠረት ላይ የሚያጸና የመንግሥት የረጅም ጊዜ ራዕይ ማሳያ ነው።
በአንድ ወቅት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ሩቅ ሕልም ይታይ የነበረ ቢሆንም በ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ በተከናወኑት መሠረታዊ ሥራዎች ዛሬ ውጤት መገኘት ችሏል።
አሁን ደግሞ የሀገራችንን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ በትግበራ ላይ መዋሉ የሂደቱን ቀጣይነት ያረጋግጣል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በየተቋመት ጥቅም ላይ መዋል ለሚሰጠው አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
የ“ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምም ለጠቅላላው የዲጂታል ሥነ ምኅዳር ግንባታው መሠረት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
እስከ 90 ሚሊዮን ዜጎችን በሥርዓቱ ውስጥ ለማቀፍ የታቀደው ይህ ግዙፍ መርሐ ግብር ለባንክ፣ ለፋይናንስ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ ነው።
የሀገርን የሰው ኃይል በዕውቀት ሳያደራጁ ዘላቂ ስኬትን ማሰብ ስለማይቻል፣ ከዚህ መሠረት ጋር ተያይዞ በ“ኢትዮ ኮደርስ” ኢኒሼቲቭ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና መጀመሩ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚረከቡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተጣለ ታላቅ መሠረት ነው።
ይህ የዲጂታል መሠረት የዜጎችን እንግልት ወደሚቀንስ የሲቪል ሰርቪስ ዝማኔ በተግባር ተሻግሯል።
የአገልግሎት አሰጣጥን በዘመናዊ መልክ ለመቅረጽ በሁሉም አካባቢዎች እየተገነባ የሚገኘው “የመሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተንዛዛ ቢሮክራሲን በማስቀረት የመንግሥትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
ይህ ዓይነቱ የተቀናጀ አሠራር ሙስና እና ብክነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል አስተማማኝ ተቋማዊ አቅም እየፈጠረ ይገኛል።
በፋይናንስ ዘርፍም ቢሆን በዲጂታል የተከናወነው የግብይት ዋጋ 16 ትሪሊዮን ብር መድረሱ የዲጂታል ኢኮኖሚው ምን ያህል ውጤታማ እና ተደራሽ እየሆነ ለመምጣቱ ማሳያ ነው።
ይህ ስኬት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን በተግባር አረጋግጧል።
ለወደፊቱም መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ፕላትፎርሞች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ የሀገራችንን የነገ ገጽታ በእጅጉ የሚቀይር ነው።
መንግሥት የሳይበር ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የስታርትአፕ ሥነ ምኅዳርን በማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግር ሂደቱን አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ እያደረገው ይገኛል።
ይህ ታሪካዊ ጉዞ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያቀልል፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ እና የኢኮኖሚ ልማታችንን ከሕልም ወደ እውነት የለወጠ የጋራ ብሔራዊ ስኬታችን በመሆኑ ሁሉም አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #ai #technology

ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና የሕግ የበላይነት!!
መግቢያ፤
በማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና የፕሬስ ነጻነት የሉዓላዊነትና የነጻነት መገለጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። በተለይም በመገናኛ ብዙኃን የሚሠሩ ጋዜጠኞች የማኅበረሰቡን ድምፅ በማስተጋባት፣ የመንግሥትን አሠራር በመታዘብና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ የጎላ ሚና አላቸው።
ይሁን እንጂ የፕሬስ ነጻነትና የብሔራዊ ደኅንነት ሚዛን፣ እንዲሁም በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች የሚወሰዱ እርምጃዎች ከሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎች ጋር ያላቸው መጣጣም በተደጋጋሚ ለክርክር የሚዳርግ ጉዳይ ነው።
ይህ ጽሑፍ ማንነትንና ሃይማኖትን ማእከል ባደረጉ ግድያዎችና ማፈናቀሎች ዙሪያ በሠራቻቸው ቪዲዮዎች ከሰሞኑን በቁጥጥር ስር የዋለችውንና ለ10 ቀናት ፍርድ ቤት ያልቀረበችውን የጋዜጠኛ ሣልሳዊት ባይነሳኝ ጉዳይ መነሻ በማድረግ- የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችን መሠረት በማድረግ ሙግታዊ ትንታኔ ያቀርባል።
1. ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሕገ-መንግሥታዊና ዓለም አቀፋዊ መሠረቶች፤
የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት በአንቀጽ ፳፱ (29) ላይ ማንኛውም ሰው ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት የፈለገውን ሐሳብ የመያዝ፣ የመግለጽና መረጃ የመሰብሰብ እንዲሁም የማሰራጨት መብት እንዳለው በግልጽ ይደነግጋል። ይህ መብት በተለይ የፕሬስ ነጻነትንና የሚዲያ ተቋማትን ሥራ የሚመለከት ሲሆን ሳንሱር በሕግ የተከለከለ መሆኑንም ያረጋግጣል።
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ተቀብላ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ለምሳሌ፤
የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀጽ 19፤
የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር (ACHPR) አንቀጽ 9፤
እነዚህ ሰነዶች ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት የሰብአዊ መብቶች ሁሉ መሠረት መሆኑን ያስገነዝባሉ። ከንድፈ-ሐሳብ አንጻር እንደ John Stuart Mill ያሉ ምሁራን፤ "የሐሳብ የገበያ ቦታ" (Marketplace of Ideas) በሚለው እሳቤያቸው፤ እውነት ሊገኝ የሚችለው ሐሳቦች በነጻነት ሲንሸራሸሩና ክርክር ሲደረግባቸው ብቻ እንደሆነ ይከራከራሉ።
በመሆኑም ጋዜጠኞች በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ አስከፊ እውነታዎችን (እንደ ማፈናቀልና ግድያ ያሉ) ይፋ ማድረጋቸው የሙያዊ ኃላፊነትና የሕዝብን መረጃ የማግኘት መብት የማክበር ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል።
2. የፍጹምነት ወሰን እና የብሔራዊ ደኅንነት ሚዛን፤
ምንም እንኳን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መሠረታዊ ቢሆንም ፍጹም (Absolute) አይደለም። የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 29(6) እንዲሁም የ-ICCPR አንቀጽ 19(3) መብቱ ገደብ ሊጣልበት የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ያስቀምጣሉ።
እነዚህም የሌሎችን መብትና ክብር ለመጠበቅ፤
ብሔራዊ ደኅንነትን፣ የሕዝብን ሰላምና ጸጥታን እንዲሁም የሕዝብን ጤና ወይም ሥነ-ምግባር ለመጠበቅ ሲባል ነው።
የሙግት ነጥብ፡- በሀገሪቱ ስሱ የሆኑ የማንነትና የሃይማኖት ጉዳዮችን ይፋዊ የቪዲዮ ምስሎችንና ጽሑፎችን ማጋራት በአንድ በኩል ግልጽነትንና እውነትን ማውጣትን የሚያበረታታ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ይዘቶቹ የጥላቻ ንግግርን (Hate Speech) የሚያነሳሱ፣ ወይም ግጭትን የሚቀሰቅሱ ከሆኑ በሕግ ሊጠየቁ የሚችሉበት ዕድል አለ።
ሆኖም ግን ይህ ገደብ ሥራ ላይ ሊውል የሚችለው በሕግ የተደነገገ (Prescribed by Law) አስፈላጊ (Necessary) እና ተመጣጣኝ (Proportional) በሆነ መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ምሁራን ይከራከራሉ። ጋዜጠኛን ማሰር የመጨረሻ አማራጭ (Ultima Ratio) መሆን ያለበት እንጂ የዜጎችን የመረጃ ፍሰት መግቻ መሣሪያ መሆን የለበትም።
3. የ48 ሰዓት ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ እና የሕግ የበላይነት መሸርሸር፤
የዚህ ጉዳይ ዋነኛውና አሳሳቢው ሕጋዊ ጥሰት የሚጀምረው ጋዜጠኛዋ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ከተፈጸመው የአያያዝ ሂደት ነው። የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፲፱ (፫) በግልጽ እንደሚያስቀምጠው፦
"የተያዙ ሰዎች በቁጥጥር ስር በዋሉ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ይህ ጊዜ ተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት ከሚያስፈልገው ተገቢ ጊዜን አይጨምርም ነፃነታቸውን እንዳያጡ ለመከላከል ወዲያውኑ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው።"
ይህ ድንጋጌ የፓርላማ ሕግ ሳይሆን፣ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ (Supreme Law) ነው። ጋዜጠኛዋ ላለፉት 10 ቀናት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ መቅረቷ ይህንን ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት በግልጽ የጣሰ ድርጊት ነው።
ምሁራዊና ተጠየቃዊ ትንታኔ (Theoretic and Philosophical Perspective)፤
ሐቤስ ኮርፐስ (Habeas Corpus)፦ ይህ መርህ በሕግ ታሪክ ውስጥ ግብረ-ገብነትንና ፍትሕን ለማስፈን ከተቀረጹ ትልልቅ መርሆዎች አንዱ ነው። ትርጉሙም "አካሉን ይዘህ ቅረብ" ማለት ሲሆን አስፈጻሚው አካል (የጸጥታ ኃይሉ) አንድን ዜጋ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለረጅም ጊዜ አፍኖ እንዳያቆይ የሚከላከል የነጻነት ጋሻ ነው።
የሥልጣን ክፍፍል መርህ (Separation of Powers)፦ በቻርለስ ደ ሞንቴስኪው (Montesquieu) ፍልስፍና መሠረት፣ የሕግ አስፈጻሚው አካል (ፖሊስ/ጸጥታ) ሰዎችን የመያዝ ሥልጣን ቢኖረውም የእስሩን ሕጋዊነት የመመርመርና የመወሰን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ የሕግ ተርጓሚው (የፍርድ ቤት) ብቻ ነው።
ፖሊስ አንድን ዜጋ ለ10 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይልክ ሲያቆይ ራሱን በሕግ ተርጓሚነት ቦታ ላይ እየሰየመ መሆኑን ያሳያል። ይህ ደግሞ ወደ አምባገንነትና ወደ ሕግ አልባነት (Arbitrary Detention) የሚወስድ አደገኛ መንገድ ነው።
የጸጥታ ኃይሎች የሚዲያ ይዘቱ "የሀገር ደኅንነትን ይነካል" የሚል እምነት ቢኖራቸው እንኳ ያንን እምነታቸውንና ያሏቸውን ማስረጃዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ለገለልተኛ ዳኛ አቅርበው የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ (Remand) መጠየቅ ነበረባቸው። ይህ ሳይሆን መቅረቱ የእስሩን ሕጋዊነት ሙሉ በሙሉ ጥያቄ ውስጥ የሚጥለውና የመንግሥትን ሕግ የማክበር ግዴታ (Duty to Respect) የሚሸረሽር ነው።
መደምደሚያ፤
ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም ይልቁንም የማኅበረሰብን ሕመም የሚያሳይ መስተዋት ነው። በማንነትና በሃይማኖት ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችንና መፈናቀሎችን ወደ አደባባይ ማውጣት፣ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስገድድ የሕዝብ ድምፅ ሊሆን ይችላል።
የይዘቱ አግባብነትና ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚወድቅ ቢሆን እንኳ ሊፈታ የሚገባው በሕገ-መንግሥታዊና በሕጋዊ ሥርዓቶች መዋቅር ውስጥ ብቻ ነው።
አንድን ጋዜጠኛ ለ10 ቀናት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰር ሕገ-መንግሥቱን መጣስ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገሪቱ የዲሞክራሲ ምኅዳር ላይ የፍርሃት ጥላ (Chilling Effect) የሚያሳድር ድርጊት ነው።
መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር መጀመሪያ ራሱ በሕግ መገዛት አለበት። ስለሆነም ጋዜጠኛዋ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ልትቀርብ ወይም ሕገ-መንግሥታዊ መብቷ ተከብሮ በአፋጣኝ ልትፈታ ይገባል።
ሕግን ለመጠበቅ በሚደረግ ጉዞ ውስጥ ሕግን መጣስ፣ ራሱ ሌላ የሕግ መፍረስን የሚወልድ በመሆኑ ሥርዓቱ ሊታረም ይገባዋል።
(በፍቅር ለይኩን)፤

🇪🇹 A milestone. A movement. A shared responsibility.
#june 16/2026
ELiDA Ethiopia proudly celebrates the establishment of the National Anti-Technology Facilitated Gender-Based Violence (Anti-TFGBV) Network.
We extend our sincere gratitude to government institutions, civil society organizations, media, social media influencers, justice actors, academia, and development partners who have united behind one clear message: online violence must end.
Together, we are building a stronger movement for safer digital spaces, survivor-centered responses, effective laws, accountability, and justice.
This is not just a network—it is a national commitment to ensure that every woman and girl can participate, lead, and thrive online without fear.
🇪🇹 ታሪካዊ ምዕራፍ። ታላቅ ንቅናቄ። የጋራ ኃላፊነት።
ኤሊዳ ኢትዮጵያ (ELiDA Ethiopia) ብሔራዊ የፀረ-TFGBV (ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት) መረብ መመስረቱን በኩራት ያበስራል።
«የኢንተርኔት ጥቃት ሊቆም ይገባል!» በሚለው አንድ ግልጽ ዓላማ ሥር ለተሰለፋችሁ፦
ለመንግሥትና ለፍትህ ተቋማት፣
ለሲቪል ማኅበረሰብ እና ለልማት አጋሮች፣
ለሚዲያ፣ ለማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ለአካዳሚዎች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በጋራ በመሆን፦ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ምኅዳር፣ ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ ምላሽ፣ ጠንካራ ሕጎች እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት እንገነባለን።
ይህ ዝም ብሎ መረብ አይደለም፤ እያንዳንዱ ሴት እና ሴት ልጅ ያለ ፍርሃት በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንዲሳተፉ፣ እንዲመሩ እና እንዲበለጽጉ የተገባ ብሔራዊ ቃል ኪዳን ነው!
#የፀረTFGBVመረብ #tfgbvይብቃ #tfgbv #elidaethiopia ! #antitfgbvnetwork #endtfgbv #digitalsafety #technology #የቴክኖሎጂ_ጥቃት_ይቆም #ዲጂታል_ደኅንነት
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር Ethiopian Civil Society Organizations Council Ethio telecom Sustainable Technology Solutions-STS Christian Aid Institute for Peace and Security Studies UN Trust Fund to End Violence against Women Ethiopian Women Development Organization - EWDO የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ የመንግሥት ሰራተኞች

የመደመር አንቀጽ
ሀገራዊ ምክክር፡- በሀገራችን የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፣ በውይይትና በምክክር ጎልብተው፣ አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ሁሉም ስለ ሀገር የሚያገባው አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር ነው። በውይይትና በምክክር ወደ መግባባት የሚደረስበት መንገድ ነው።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ከገጠሙን እጥረቶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በሀገረ መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፣ ያልተግባባባቸውን ደግሞ ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም። በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይሄን የዘመናት ስብራት የሚጠግን ነው::
የመደመር መንግሥት
ገጽ 384

ወሳኙ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ
************
ኢትዮጵያ በታሪኳ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። በጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር ሐሳቦችን በነፃነት ማንሸራሸር እና የጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር የማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡
ለዘመናት የዘለቁ ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለመፍታት፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ለጠንካራ የሀገር ግንባታ መሠረት ለመጣል ምክክር አማራጭ የሌለው ወሳኝ መንገድ ነው፡፡
በዚህ ረገድ፣ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት "የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል፡፡
ልዩነትን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የዚህ ሀገራዊ ጉባኤ ዋነኛ ግብ ነው፡፡ በምክክር ግጭትና መቃቃርን ተወግፍዶ የሐሳብ ልዕልና የሚነግሥበት እንዲሁም የጠመንጃ ድምፅ የሚሸነፍበት ሥርዓትን መገንባት ይቻላል፡፡
እውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለውም ተቀራርቦ በመወያየት እንጂ በመለያየት እና በፀብ ግንብ አይደለም፡፡ ምክክሩም ቅሬታ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ድምፃቸው የሚሰማበትና ለችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ የምንፈልግበት ታሪካዊ መድረክ ነው፡፡
ዋናው የምክክር ጉባኤ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ በመሆኑ ለጉባኤው ስኬት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል። ለዚህ ምክክሩ ስኬትም የዜጎች ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው።
በአጠቃላይ፣ ሐምሌ 8 የሚጀመረው "የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" የጥላቻና የግጭት ታሪክን ዘግተን፣ የሰላምና የአብሮነት አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ወርቃማ ዕድል ነው፡፡
ይህ ወሳኝ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምኅዳር የሚያሸጋግር የታሪክ ድልድይ ይሆናል፡፡
#ethiopianbroadcastingcorporation #national #dialogue #ethiopia

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏
ልጇን ይዛ ወደ ግብፅ ተሰደደች
የአዳም ተስፋው እውን ሊሆን አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ብስራት በድንግል ማሕጸን አደረ፡፡ የማይቻለውን ቻለችው፣ የማይወሰነውንም ወሰነችው፡፡ ሰማይና ምድርን የፈረጠረውን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በሰማይ ዙፋኑ ሳይጎድል ማኅጸኗን ዓለም አድርጎ ተቀመጠ፡፡ በመጨረሻም በታሕሳስ 29 ቀን በበረት ተወለደ፤ በጨርቅ ተጠቀለለ፣ ሰውና መላዕክት በአንድ ላይ አመሰገኑት፤ ሰብዓ ሰገልም ገበሩለት፡፡ ጌታችን 2 ዓመት ሲሞላው ንጉስ ሔሮድስ ንጉስ መወለዱን ከሰብዓ ሰገል ሲሰማ ሊገድለው ተነሳ። የእግዚአብሔር መልአክም ለዮሴፍ በሕልም ተገልጾ “ተነስተህ እናቱንና ብላቴናውን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ” ብሎ ነገረው፡፡ ይህ የእመቤታችን ስደትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ለማሰብም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ወርኀ ጽጌ፣ ዘመነ ጽጌ የአበባ ዘመን እየተባለ ይታሰባል፡፡
እመቤታችንም ከዮሴፍ ጋር ልጇን ይዛ ወደ ግብፅ ተሰደደች፡፡ እድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ጋር ወደ ግብፅ በተሰደደችበት ጊዜ ብዙ መከራ ገጥሟታል፡፡ ልጇን ከሞት ለማዳን ብዙ ችግር አይታለች፡፡ የቀን ሐሩር፣ የሌሊት ቊር እየተፈራረቀባት፣ እሾሁ እየወጋት፣ እንቅፋቱ እየመታት፣ መውጫና መግቢያው በማይታወቅ በረሃ ውስጥ ብዙ ተሰቃይታለች፡፡ ሕፃኑን ልጇን ለመግደል ባለ ኃይሉ ይጥር የነበረው ሄሮድስ አራት ወታደሮቹን ከእነጭፍሮቻቸው ሸልሞ እመቤታችንን ከነልጇ ይዘው ከመጡ የበለጠ ሹመትና ሽልማት እንደሚሰጣቸው ነግሮ ላካቸው፡፡ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ ይህንን ሰምቶ ሲነግራቸው ቅድስት ድንግል ማያርም ምርር ብላ አልቅሳለች፡፡ የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ወይም ትርጓሜ እንደሚነግረን በግብፅ በርሃ ሲጓዙም እመቤታችን ወደ ትዕማን ቤት ሄደች፡፡ ይሁንና ያቺ ሴትና አገልጋዩዋ በእመቤታችንና በዮሴፍ ላይ ተዘባበቱ፡፡
በእናቱ እቀፍ የነበረውን ጌታችንንም አገልጋይዋ ኮቲባ ከእናቱ እቅፍ ነጥቃ መሬት ላይ ጣለችው፡፡ ጌታም ትዕማንንና ኮቲባን አጥፍቷቸው በቤቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇና ከዮሴፍ እንዲሁም አብራት ወደ ስደት ከመጣችው ሰሎሜ ጋር ለስድስት ወር ያህል ከተቀመጡ በኋላ ጉዟቸውን ዱር ለዱር አደረጉ፡፡ ይህም እመቤታችን ልጇን እንዳይገሉባት ነበር፡፡
ነገር ግን በስቅለት ዕለት በግራውና በቀኙ የተሰቀሉት ወንበዴዎች ጥጦስና ዳክርስ አገኟቸው፡፡ የጌታን ልብስ ገፈውም ቁመው ሲማከሩ እመቤታችን ልጇን የሚገድሉባት መስሏት አለቀሰች፡፡ ሆኖም ግን ጥጦስ ካደረበት ፍቅርና ርኅራኄ የተነሳ “እነዚህ ሰዎች አሳዘኑኝ! ወደዚህ ቦታ የመጡት ያለ ምክንያት አይሆንምና አንቀማቸው እንተውላቸው” ብሎ ልብሳቸውን መልሶላቸው ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ ረዳቸው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደት 42 ወራት አሳልፋለች፡፡
በየዓመቱ ኅዳር 6 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ፣ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በሄሮድስ ምክንያት የደረሰባቸው ስደትና መከራ አልፎ ደብረ ቁስቋም በተባለች ቦታ ያረፉበት ነው፡፡ በማቴዎስ 2÷20 እንደተጻፈው “ሄሮድስም በሞተ ጊዜ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ በግብፅ ሀገር ለዮሴፍ በሕልም ታየው፡፡ የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡” አረጋዊው ዮሴፍም ሰሎሜ እያገዘችው የሚያገለግላትን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከተወደደ ልጇ ጋር ይዞ ከስደት ተመልሰዋል፡፡ ገዳማውያን ይሕን የስደቷን ጊዜ በጾምና ጸሎት ያስቡታል፤ በረከትም ያገኙበታል፡፡ ከበረከታቸው እንሳተፍ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

የዲጂታል ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ - ከስትራቴጂ ወደ ስኬት
***********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዛሬ ዓለማችን በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ፈጣን ግስጋሴ ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት በውል በመገንዘብ፣ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚዋን ከመሠረቱ የሚቀይር ታሪካዊ የዲጂታል ሽግግር እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት ሀገራችን ያለባትን ዘላቂ የቢሮክራሲ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቅረፍ ዲጂታላይዜሽንን እንደ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ በመውሰድ እየሠራችበት ትገኛለች።
ይህ ጉዞ የሀገርን የልማት ምሰሶ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያጸና የመንግሥት የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለን እናምናለን።
በአንድ ወቅት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ሩቅ ሕልም ይታይ እንደነበር አይዘነጋም፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑት መሠረታዊ ሥራዎች ግን ዛሬ ላይ ሊሻር በማይችል እውነታ ላይ የቆመ መሠረት ተጥሏል።
መንግሥት ያደረጋቸው ሰፊ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያዎች “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችለዋል።
አሁን ደግሞ የሀገራችንን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉ የሂደቱን ቀጣይነት ያረጋግጣል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ለችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች መበልጸግ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ የሚበረታታ እርምጃ ነው።
በዚህ ዘመናዊ የታሪክ እጥፋት ውስጥ የ“ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እና የ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ ሚና እጅግ የላቀ ነው።
የዲጂታል መታወቂያ ለኢኮኖሚው ግንባታ ልክ እንደ ቤት መሠረት ነው። እስከ 90 ሚሊዮን ዜጎችን በሥርዓቱ ውስጥ ለማቀፍ የታቀደው ይህ ግዙፍ መርሐ ግብር ለባንክ፣ ለፋይናንስ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ ነው።
“የቆጠሩት እህል አያልቅም” እንደሚባለው የሀገርን የሰው ኃይል በዕውቀት ሳያደራጁ ዘላቂ ስኬትን ማሰብ አይቻልም። በመሆኑም በ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚረከቡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተጣለ ታላቅ መሠረት ነው።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በሁሉም አካባቢዎች እየተገነባ ያለው “የመሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የተንዛዛ ቢሮክራሲን እና የዜጎችን እንግልት በማስቀረት የመንግሥትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ሙስና እና ብክነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል አስተማማኝ ተቋማዊ አቅም ይፈጥራል።
በፋይናንስ ዘርፍም ቢሆን በ2017 በጀት ዓመት ብቻ በዲጂታል የተከናወነው የግብይት ዋጋ 16 ትሪሊዮን ብር መድረሱ የዲጂታል ኢኮኖሚው ምን ያህል ውጤታማ እና ተደራሽ እየሆነ ለመምጣቱ ሕያው ማሳያ ነው።
ይህ ስኬት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን በተግባር አረጋግጧል።
ለወደፊቱም መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ፕላትፎርሞች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ የሀገራችንን የነገ ገጽታ በእጅጉ የሚቀይር ነው።
መንግሥት የሳይበር ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የስታርትአፕ ሥነ ምኅዳርን በማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግር ሂደቱን አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ እያደረገው ይገኛል።
በአጠቃላይ ይህ ታሪካዊ ጉዞ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያቀልል፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ እና የኢኮኖሚ ልማታችንን ከሕልም ወደ እውነት የለወጠ የጋራ ብሔራዊ ስኬታችን በመሆኑ ሁሉም አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #5millioncoders #success #𝐃𝐢𝐠𝐢𝐭𝐚𝐥𝐄𝐜𝐨𝐧𝐨𝐦𝐲

ጠመንጃን በውይይት የመተካት ታሪካዊ ዕድል፦ ሀገራዊ ምክክር እና የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ
**********************
ኢትዮጵያ በታሪኳ አካታች የተባለለትን ሀገራዊ ምክክር እያካሄደች ትገኛለች።
ባለፉት ዓመታት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ አጀንዳ ሲያሰባስብ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሁን ወደ ዋናው እና የማጠቃለያው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው።
ይህ ሂደት በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ትልቅ አጋጣሚ የሚታይ ወርቃማ ዕድል ነው።
ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ፣ ኢትዮጵያን ለዘመናት ሲፈታተናት ከኖረው የግጭት አዙሪት አውጥቶ አዲስ ብሩህ ጊዜ የሚያመጣላት ነው።
በበርካታ ጩኸት እና ወከባ መካከል ታሪካዊ ምርጫ በማካሄድ ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር የገለጹት ኢትዮጵያውያን፣ የምክክሩን ሂደትም በውጤታማነት እንደሚያጠናቅቁት አይጠረጠርም።
በአንድ ሀገር ታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነት ሲገነግን እና ሥር የሰደዱ ታሪካዊ ቅሬታዎች ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የሀገር ሕልውና ፈተና ላይ ይወድቃል። ይህም የተለያዩ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ያስከትላል።
እነዚህን ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች በመቀልበስ ሀገራዊ ሕልውናን ጠብቆ ለማቆየት የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም የተለመደ ነው።
ከእነዚህ አማራጮች መካከል በርካታ ሀገራት ከከፋ ብሔራዊ የመበታተን አደጋ ራሳቸውን የታደጉበት ዋነኛው ስትራቴጂያዊ መፍትሔ ሀገራዊ ምክክር ነው።
የሀገራዊ ምክክር መድረክ የፖለቲካ ልሂቃን ጊዜያዊ ስምምነት ሳይሆን የአንድን ሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያገለግል የሕልውና ዋስትና ነው።
የሀገራዊ ምክክር ዋነኛው እና ቀዳሚው አስፈላጊነት፣ የኃይል አማራጭን ሙሉ በሙሉ በመግታት የሀሳብ የበላይነትን ማረጋገጥ መቻሉ ላይ ነው።
በተለይም የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ፍላጎቶቻቸውን በኃይል ወይም በጦርነት ለማስፈጸም በሚሞክሩበት በአሁኑ ወቅት፣ ምክክሩ ጠመንጃን አስቀምጦ በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት የመደማመጥ ዕድልን ይፈጥራል።
ይህ ሂደት ማኅበረሰቦችን ከአውዳሚ ጦርነት አውጥቶ፣ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት አዲስ የፖለቲካ ባህልና ሥነ-ልቦና ለመቅረጽ ትልቅ አጋጣሚ ነው።
ምክክሩ ሁሉም ድምጹን የሚያሰማበት አካታች መድረክ መሆኑም ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ጽኑ መሠረት ነው።
ሀገራዊ ቀውሶች የሚፈጠሩት በዜጎች እና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ሲሻክር ወይም ነባር የሕግ እና የፖለቲካ መዋቅሮች ሁሉንም እኩል ማስተናገድ ሲያቅታቸው ነው።
ሀገራዊ ምክክር ዜጎች በወል እሴቶቻቸው፣ በሀገራዊ አርማዎቻቸው እና በወደፊት የጋራ ዕጣ ፈንታቸው ላይ ተወያይተው አዲስ ማኅበራዊ ውል እንዲቀርጹ ዕድል ይሰጣል።
በተለይ በዚህ የዲጂታል ሚዲያ ዘመን የተዛቡ ትርክቶች እና ጽንፍ የያዙ የፖለቲካ አመለካከቶች በማኅበረሰቦች መካከል ጥርጣሬን እና ጥላቻን የመዝራት አቅም አላቸው።
ሀገራዊ ምክክር በዚህ መልኩ የተቃረኑ የፖለቲካ ኃይሎች እና የኅብረተሰብ ክፍሎች ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲደማመጡ ያደርጋል።
ይህም ለዘመናት የዘለቁ ታሪካዊ ቁርሾዎችን ለመፈወስ፣ የጋራ እውነትን ለመፈለግ እና በጥርጣሬ የተሞላውን ምኅዳር ወደ መተማመን ለመቀየር የሚረዳ ፍቱን መድኃኒት ነው።
በአግባቡ ከተጠቀሙበት፣ ምክክር ለሀገር ያለው አስፈላጊነት ከሰላም መድረክነት የላቀ ነው።
ምክክር ሀገርን ከትርምስ አውጥቶ በጽኑ መሠረት ላይ መልሶ የመገንቢያ ሁነኛ መሳሪያ ነው።
ማረጋገጥ የሚያሻን ሂደቱ ሁሉን አቀፍ እንዲሁም ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የጸዳ፣ ገለልተኛ መሆኑን ብቻ ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconcensus #sustainablepeace #ebc

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ የተካሄደ ነው - የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት
*****************
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ በስኬት የተካሄደና የሰከነ የፖለቲካ ፉክክር የታየበት መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ገለጸ።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ዳይሬክተር መስዑድ ገበየሁ እንደገለጹት፤ የዘንድሮው ምርጫ ሂደት ከሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አንጻር በጥሩ ሁኔታ የተከናወነና ስኬታማ ነበር።
አቶ መስዑድ እንዳሉት፣ በዘንድሮው ምርጫ ዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።
በምርጫው የፉክክር ሂደት፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ ሃሳባቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ የነበራቸው መናበብ አስደማሚ እንደነበር መታዘባቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ይህም ፖለቲካ ፓርቲዎች የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅሞች መከበር የሰከነ የፖለቲካ ምኅዳር በመፍጠር እየተሳተፉ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ አክለዋል።
በምርጫው ወቅት የተስተዋለው የምርጫ ጣቢያዎች አሠራርም ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ዜጎችን የመምረጥ መብት ያረጋገጠ ነበር ብለዋል።
በተለይ ለአካል ጉዳተኞች፣ መስማት ለተሳናቸው፣ ለነፍሰ ጡሮችና ጨቅላ ሕፃናት ለያዙ ወላጆች ምቹ ምኅዳር ተፈጥሮ እንደነበር በአብነት መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ethiopia #democracy #government #humanrights #ethiopiaprevails #ebc

የኢትዮጵያ ስልታዊ ዲፕሎማሲ፦ ከውስጥ ጽናት እስከ ዓለም አቀፍ ከፍታ
********************
(የዕለቱ መልእክት)
ዲፕሎማሲ በዓለም አቀፍ መድረክ የሀገር ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ሳያስደፍሩ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚቀመር ረቂቅ የፖለቲካ ጥበብ ነው።
ዓለም በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ሽኩቻዎች በታመሰችበት በዚህ ዘመን የውጭ ግንኙነት መርሆዎችን እንደየአካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች እያስተካከሉ ጥቅምን ማስከበር የህልውና ጉዳይ ነው።
ባለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ምኅዳር ያጋጠሙትን ፈተናዎች የተሻገረው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ "የውስጥ ጥንካሬ ለውጭ ዲፕሎማሲ ስኬት መሠረት ነው" የሚል ጽኑ እምነትን ሰንቆ ስልታዊና ጥልቀት ባለው የሪፎርም መነጽር በመመራቱ ነው።
በዚህም የተመዘገቡት ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ኢትዮጵያ ካጋጠሟት ፈተናዎች አንጻር ሲመዘኑ እጅግ አስደማሚ ናቸው። እነዚህ ድሎች ሊመዘገቡ የቻሉት ቀደም ሲል የነበረውን በጥቂት ሀገራት ላይ ብቻ ያተኮረ የውጭ ፖሊሲ በመለወጥ፣ በአዲስ መልክ የተቀረጸ ገቢራዊ የሆነ የብዝኃነት ፖሊሲን በተግባር በመተርጎም ነው።
ኢትዮጵያ በምሥራቅ (እንደ ቻይና እና ሩሲያ) እና በምዕራብ (እንደ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት) ኃይሎች መካከል በአንዱ ወገን ብቻ ሳትጠለል፣ ከሁሉም ጋር ያላትን ግንኙነት በማመጣጠን ብሔራዊ ጥቅሟን የማስከበር ስልታዊ ሚዛኗን ጠብቃለች። ይህንን ፖሊሲ ተከትሎ በተደረገ ከፍተኛ ጥረትም የስትራቴጂካዊ አማራጭ ስኬት የሆነውና በአንድ ወገን ፖለቲካዊ ጫና ውስጥ እንዳትወድቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዋስትና የሚሰጣት የብሪክስ ሙሉ አባል መሆን ተችሏል።
ከተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጋር የተሠራው ስኬታማ የሚዲያ ሥራና ሕዝባዊ ንቅናቄም የሀገርን ገጽታ በአዎንታዊ መልኩ ከመገንባቱ ባለፈ፣ የሕዝብ ዲፕሎማሲ (Citizen Diplomacy) ምን ያህል አቅም እንዳለው ያሳየ ክስተት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ጦርነትን የመከላከያ ጋሻ፣ ሰላምን የማስፈኛ ድልድይ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን የማፋጠኛ ሞተር ሆኖ ያገለገለው በተለይ ከብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ጋር በተያያዙ ትልልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ነው። ለአብነትም ታላቁን የሕዳሴ ግድብ በስኬት ማጠናቀቅ የዲፕሎማሲያችን ትልቅ ድል ነው።
የዚህ አዲስ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ሌላኛው አንጸባራቂ ስኬት፣ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ያገኘው ዕውቅና እና አክብሮት ነው። ምርጫው በዲፕሎማሲያዊ መድረክ የኢትዮጵያን የውስጥ ዴሞክራሲያዊ ብስለትና የፖለቲካ መረጋጋት በተግባር ያስመሰከረ ታላቅ ሁነት ሆኗል።
ምርጫው በሰላማዊና ሥልጣኔ በተሞላበት መንገድ መጠናቀቁ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና አጋር ሀገራት ለኢትዮጵያ የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊ ምርጫ ያላቸውን አመለካከት በአዎንታዊ መልኩ እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል። ይህም የሀገራችንን የዲፕሎማሲ የሞራል የበላይነት ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው ስኬት አስተማማኝ መሠረት ጥሏል።
ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የመስጠት ፖሊሲ እና የባሕር በር ለማግኘት የተጀመሩት ስትራቴጂካዊ ጥረቶችም ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ አድምቀውታል።
ይሁንና የወደፊቱ የዲፕሎማሲ ስኬታችን ቀጣይነት እንዲኖረው የውጭ ፖሊሲያችን ይበልጥ በብሔራዊ ጥቅም ላይ ያተኮረ፣ በዕውቀት የሚመራ እና ጠንካራ የውስጥ ሰላምን መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል። የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ይህ በጽናትና በብልሃት የተገኘው የዲፕሎማሲ ስኬት ሁልጊዜም የንቃትና የጥንካሬ መገለጫችን ሆኖ ሊቀጥል ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል መልእክት
Ethiopian Broadcasting Corporation #diplomacy #ethiopia #ኢትዮጵያ

በነገሥታት ፊት የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ።
በምጽዋትና በስገድት የምትጋደለው እናቱ ዮስቴና ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ወደ በረኃ ሄደች። በዚያ ያገኘችው ባሕታዊም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሰች፡፡ የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ከዚህች የተባረከች ሴት ጋር ተጋባ። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች፣ በሕግ ተወስና በጾም፣ በጸሎት፣ የምትተጋ ነበረች። ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔር አንጸው አሳደጉት። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።
አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል።
እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡ ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። የቅዱስ ማቴዎስንና የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ሲያነብ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ ሰጠው፡፡
የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ሲያነብም ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ ሰጠውና ቃል ኪዳን ገባለት። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶች ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክት ሁሉ እየተደሰቱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያምን “ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል” አሉት። ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው በሰላም ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ገዳም ስትገባ የተቀደሰ ልጅ እንደምትወልድ ተነግሯት የተመለሰችው እናቱ ዮስቲና ትባላለች። ልጅም ሲወልዱ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔርም አንጸው አሳደጉት።
በቤተ ክርስቲያንም የሰማውን “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የምትል ጸሎት እጅጉን ቢወዳት ሌሊቱን ሙሉ በቤቱ እየጸለያት የሚጋደል ሆነ። አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ ጓደኞቹን “ዝናም ይዘንማልና ወደቤት እንግባ” አላቸው። ቃሉን ሊሰሙት ባይወዱ በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ኃይለኛ ዝናም ዘነመ። ገና በአዳጊነት እድሜውም ብዙ ተአምራት ያደርግ ነበር፡፡
በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል። እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ ጌታችን ተገለጠለት። አቡነ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡
ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ ስለማንበቡ፣ ስለተጋድሎው፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። ከሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትንና ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የብርሃን ሠረገላም ሰጠው፣ መታሰቢያውን የሚያደርጉትን እንደሚምርለትም፣ ቃል ኪዳን ገባለት። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ስትለይም ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፤ ገዳማቸውን እንደግፍ ከበረከታቸውም እንካፈል፡፡

Comments