1 month ago
በጠቅላላ ምርጫው በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክር ቤት ወንበር ማሸነፋቸው የዴሞክራሲ ምህዳሩን መስፋት ያረጋገጠ ነው፡- የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
*******************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስኬት የተካሄደውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ በርካታ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክር ቤት ወንበሮችን ማሸነፋቸው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየሰፋ መመጣቱን በተግባር ያሳየ መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ።
ይህ ስኬት በክልል እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻለ የሀሳብ ብዝኃነት እንዲኖርና ጠንካራ የመንግሥት ተቋማትን የመገንባት ሂደትን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል።
በተገለጸው የምርጫ ውጤት መሠረት ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን ሲያገኝ፤ ኢዜማ 13፣ አብን 6፣ ነእፓ 3፣ መድረክ 3፣ አዴኃን 3፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 2 ወንበሮችን ያሸነፉ ሲሆን ሌሉች 10 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ የምክር ቤት ወንበር አግኝተዋል።
ለክልል ምክር ቤት በተደረገው ውድድርም ኢዜማ 73፣ ነእፓ 35፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት 34፣ ኦብነግ 20፣ ጉህዴን 14፣ መድረክ 11፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 6፣ ሕዳሴ ፓርቲ 5 እና ቤህነን 5 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል።
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሮ ነቢሃ መሀመድ ምርጫው የሕዝብ ድምፅ መንግሥት ለመመስረት ብቸኛው መንገድ መሆኑንና መንግሥት የሚመሰረተው በኃይል ሳይሆን በሐሳብ ብቻ መሆኑን ያስተማረ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አያይዘውም ፓርቲያቸው በሀገራዊ ጥቅም፣ በሉዓላዊነት፣ በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና በምግብ ዋስትና ዙሪያ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል የወሎ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ነጻነት ጣሰው ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እስከ ታችኛው መዋቅር ተቀራርቦ መሥራት ሀገር ለማሻገር ቁልፍ ሚና እንዳለው በመጥቀስ፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታና ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት ፓርቲያቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን በጥናት ለይቶ በማቅረብ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
#ethiopiaelections #democracy #politicalpluralism #nationalunity #ethiopianbroadcastingcorporation

የፓርቲዎች ታሪካዊ ፉክክር የታየበት ምርጫ
https://youtu.be/XkUbadQxi...
#ebc #ethiopia #democracy #democraticethiopia #politicalparties
1 month ago
ከመመካከር ቁም ነገር አለ፤ ካለመመካከር ምንም!
*****************
የሰው ልጅ የሥልጣኔ ማማ፣ የዕድገትና የመሻገር ምስጢር በመነጋገር፣ በመደማመጥ እና የሀሳብ ልዕልናን በማክበር ላይ የተመሠረተ ነው። ነገር ግን፣ ዛሬ ላይ ቆመን ራሳችንን በሐቅ ልንጠይቅ ይገባል፤ እ... ምን ቀረን፣ ካለመመካከር ውጪ? ለምንስ ተመካክረን አንሞክረውም? ወይስ ደግመን እንታኮስ?
ባለፉት ዘመናት የሃሳብ ልዩነቶችን በአግባቡ ማስተናገድ አቅቶን አሰቃቂ ዋጋ ስንከፍል ኖረናል።
የሃሳብ ልዩነትን በአግባቡ ማስተናገድ አቅቶን ዜጎች ከሀገር ተሰደዋል፣ በሃሳብ ልዩነት ብዙ ወጣቶች ሞተዋል፣ አንድ ትውልድ ረግፏል። አንዱን ገሎ ስልጣን ላይ መውጣት፣ የተለየ ሀሳብን ማጥፋት እና ስልጣንን ከጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ መፈለግ የፖለቲካችን ዋነኛ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል።
ይህ ሰው ወለድ ጭቆና እና ጠባብ የፖለቲካ እይታ፣ ሀገሪቱን ጽንፍ የያዙ ነጠላ ትርክቶች እንድትታመስና ሀገራዊ የጋራ ትርክት እንዳይኖረን በማድረግ እጅግ ውድ ዋጋ አስከፍሎናል።
እስኪ ቆም ብለን ወደ ሌሎች እንመልከት፤ አውሮፓውያን በምክንያታዊነት ዘመን (Period of Enlightenment) በጠረጴዛ ዙሪያ ሃሳቦቻቸውን ሞግተው፣ የሰላ የሃሳብ ፍጭት አድርገው፣ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ጠንካራ ሀገረ መንግሥታትን መገንባት ችለዋል። የፓርላማና የሊበራል አመለካከቶችን በማዳበር በማይናጋ መሠረት ላይ የቆመ የፖለቲካ ማህበረሰብ ፈጥረዋል።
ታዲያ እኛ ምን ያንሰናል? አባቶቻችን በባህላዊ እሴቶቻቸው ተመካክረው ታላላቅ ሥልጣኔዎችን በገነቡበት ሀገር፣ ዛሬ እኛ ለመመካከር ምጥ የሚይዘን ለምንድን ነው?
ላለፉት ዘመናት ውይይትን የሚጸየፉ እና የተለየ ሀሳብን የሚጠሉ መንግሥታት በነበሩበት ሀገር፣ ዛሬ የመመካከርን በሮች ወለል አድርጎ የከፈተ እና "የሀገራችንን ቀሪ ዕጣ ፈንታ በጋራ እንወስን" የሚል የለውጥ መንግሥት እና ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር ተፈጥሯል።
ስለሆነም፣ ይህ ትውልድ ከፊቱ ሁለት ግልጽና ወሳኝ ምርጫዎች ቀርበውለታል፡-
• ወደ ሀሳብ ጠረጴዛ መምጣት፣ መወያየት፣ በመነጋገር ውስጥ የሀሳብ ልዩነቶችን ማጥበብ፣ የጋራ አቋም መያዝና ብሔራዊ መግባባት ፈጥሮ ሀገርን ማዳን። ይህ አካሄድ የተሰበረውን ሀገረ መንግሥት ለመጠገንና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል ብቸኛው አማራጭ ነው።
• የጥፋት መንገድ፣ ውይይትን መግፋት፣ እንዳለፉት ጊዜያት እርስ በርስ መጠፋፋት፣ እየተታኮሱ መኖር እና የደም ዘመን እንዲቀጥል ማድረግ።
አሁን በተከፈተው የውይይት መድረክ ላይ አለመሳተፍ፣ ለመነጋገር ፈቃደኛ አለመሆን እና መመካከርን መጥላት አመፀኝነት ነው።
የሰላምን በር ዘግቶ የጥፋትን መንገድ መምረጥ የሀገርን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ታሪካዊ ስህተት ነው። ያልተመካከረ ውግዝ ነው፤ ያልተመካከረ አመፀኛ ነው!
እኛ ኢትዮጵያውያን የትናንት ገናና ታሪክ፣ ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር፣ በመከራም በደስታም አብሮ የመቆም ልምድ እና የዳበሩ ባህላዊ የዴሞክራሲ እሴቶች ያሉን ህዝቦች ነን። እነዚህን ነባር እሴቶች ተጠቅመን፣ ሁሉንም ህዝቦች በእኩልነት የሚያስተናግድ አሳታፊና አካታች የሆነ የመግባባት ዴሞክራሲ ማነጽ ይጠበቅብናል።
በመሆኑም፣ ዛሬ ላይ ዴሞክራሲ፣ መወያየት እና ብሔራዊ ምክክር ለኢትዮጵያውያን የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄ ነው። ሀገራችንን ጥቂቶች ብቻቸውን ሮጠው ሊያሻግሯት አይችሉም፤ ኢትዮጵያ የምትገነባውና የምትጸናው በሁሉም ልጆቿ የነቃ ትብብርና ተሳትፎ ብቻ ነው።
እጣ ፈንታችን በእጃችን ነው፤ ከመመካከር ብዙ ነገር አለ፣ ካለመመካከር ምንም! የተከፈተልንን የመመካከር ዕድል ተጠቅመን ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት በአንድነት እንነሳ!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #democracy #peace #statebuilding #ebc

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ልዩ የሚያደርገው አካታችነቱ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ ነው - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
*************************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አካታች እና ስኬታማ ለማድረግ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በቅርበት ሲሠራ መቆየቱን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ ገልጸዋል።
ድምጽ ከተሰጠ በኋላም ቦርዱ ላለፉት 20 ቀናት በርካታ ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ምክትል ሰብሳቢው አስታውቀዋል።
የዘንድሮውን ምርጫ ቀደም ካሉት ልዩ የሚያደርገው ዋነኛው ስኬት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና አካታችነቱ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ጠቅሰዋል።
ለዚህም እስከ ተፈናቃዮች ካምፕ፣ ወታደራዊ ሠፈሮች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ በመሄድ ሰፊ የመራጮች ምዝገባ መካሄዱን ገልጸዋል።
በምርጫው ሂደት ፓርቲዎች አማራጮቻቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበት ሰፊ የአየር ሰዓት ተደልድሎ 19 የፖሊሲ ክርክሮች በስኬት ተካሂደዋል።
ይህን ታሪካዊ ሂደት በነጻነት ለዓለም እንዲዘግቡም ለ1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥ እና ለ45 የውጭ ጋዜጠኞች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተገልጿል።
ምርጫው ከመጀመሩ በፊት በገለልተኛ ቡድን በተደረገ ግምገማ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል አስተማማኝ የጸጥታ ሁኔታ መኖሩን ቦርዱ አረጋግጦ ወደ ሥራ መግባቱ ተጠቁሟል።
በምርጫው ዕለት ያጋጠሙ እክሎችን ለመፍታት 663 አባላት ያሉት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ የተሳተፈ ሲሆን፣ አቤቱታ በቀረበባቸው ክልሎችም በማጣራት ውሳኔ ተሰጥቷል።
ምርጫውን ሊያዛቡ በሞከሩ ሕገ-ወጥ አካላት ላይም ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል።
በሂደቱ የዲጂታል ምዝገባ አጠቃቀም ችግሮች፣ የመረጃ ፍሰት ውስንነት፣ ረጃጅም ሰልፎች፣ የአንዳንድ አስፈጻሚዎች የብቃት እና የገለልተኝነት ክፍተት እንዲሁም የታችኛው መዋቅር አመራሮች ጣልቃ የመግባት ሙከራዎች በእጥረት ተነስተዋል።
ይሁንና ቦርዱ እነዚህን እክሎች በሕጋዊ መንገድ በመፍታት ስኬታማ ሥራ ማከናወኑን ምክትል ሰብሳቢው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድባቸው የተወሰነባቸው የምርጫ ክልሎች ውጤት በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ምክትል ሰብሳቢው አመላክተዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #democracy #ebc

The voting process and the entire turnout is indeed a testament to every Ethiopian, that we love democracy and we love also our country\
2 months ago
የቱለማ ገዳ ሥርዓት የ71ኛው ዙር የሥልጣን ሽግግር ነገ ይፈጸማል
********************
የቱለማ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት የ71ኛው ዙር የስልጣን ሽግግር 'ዳካ ኮራ' በተባለ ልዩ ስፍራ እየተካሄደ ይገኛል።
የሥልጣን ርክክቡ ማጠቃለያ በነገው ዕለት 'ዳካ ኮራ' በተባለ ልዩ ስፍራ የስልጣን ወይም የአለንጋ ሽግግር መርሐ ግብር የተለያዩ አካላት በተገኙበት ይካሄዳል።
የገዳ ሥርዓት ለብዙ ዘመናት የዘለቀ እና ዓለም ያደነቀው የማይዳሰስ ቅርስ ሲሆን፤ የማኅበረሰቡን ባህል፣ እሴትና ሥነ-ምግባር ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሻገር ረገድ ትልቅ ሚና እየተወጣ ነው።
ገዳ፤ ሰላም እና እርቅን የሚያሰፍን፣ የማኅበረሰቡን ተሳትፎ የሚያጠናክር፣ ማንነትን እና ባህልን የሚጠብቅ፣ እኩልነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግርን ለትውልድ የሚያስተምር ሥርዓት ነው።
የቱለማ ገዳ ሥርዓት የ71ኛውን ዙር የሥልጣን ሽግግር ከ'ገዳ ሜልባ' ወደ 'ገዳ ሙደና' ለማስተላለፍ የተለያዩ ባህላዊ ሥነ-ሥርዓቶች በ'ዳካ ኮራ' የባህል ስፍራ እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በዚህ ሥርዓት ላይ ሥልጣን ለሚረከቡት አካላት ቦኩ ወይም የሥልጣን ማሳያ የሆነው በትር እና አለንጋ ይረከባሉ።
በሥልጣን ሽግግሩ ባህላዊ ሥርዓት ላይ ግብዣዎች፣ ምርቃት፣ ባህላዊ ዜማዎች እና ውዝዋዜዎች የሚቀርቡ መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #geda #democracy

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ የተካሄደ ነው - የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት
*****************
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰብዓዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ በስኬት የተካሄደና የሰከነ የፖለቲካ ፉክክር የታየበት መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ገለጸ።
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ዳይሬክተር መስዑድ ገበየሁ እንደገለጹት፤ የዘንድሮው ምርጫ ሂደት ከሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አንጻር በጥሩ ሁኔታ የተከናወነና ስኬታማ ነበር።
አቶ መስዑድ እንዳሉት፣ በዘንድሮው ምርጫ ዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል።
በምርጫው የፉክክር ሂደት፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ ሃሳባቸውን ለህዝብ ሲያቀርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ የነበራቸው መናበብ አስደማሚ እንደነበር መታዘባቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ይህም ፖለቲካ ፓርቲዎች የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅሞች መከበር የሰከነ የፖለቲካ ምኅዳር በመፍጠር እየተሳተፉ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ አክለዋል።
በምርጫው ወቅት የተስተዋለው የምርጫ ጣቢያዎች አሠራርም ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ዜጎችን የመምረጥ መብት ያረጋገጠ ነበር ብለዋል።
በተለይ ለአካል ጉዳተኞች፣ መስማት ለተሳናቸው፣ ለነፍሰ ጡሮችና ጨቅላ ሕፃናት ለያዙ ወላጆች ምቹ ምኅዳር ተፈጥሮ እንደነበር በአብነት መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ethiopia #democracy #government #humanrights #ethiopiaprevails #ebc

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ታሪክ ተሰራ! ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ማለዳ ተነስተው ድምፃቸውን በመስጠት የአፍሪካን ዴሞክራሲ ከፍ አድርገዋል! ምርጫችን ሉዓላዊነታችን ነው።
#ethiopia #democracy #pmoethiopia #ebc
#ethiopia #democracy #pmoethiopia #ebc
2 months ago
Ethiopiau2019s 7th General Election proved that African democracy is self-reliant, peaceful, and validated by its own people. As African observers noted, this wasn't for show it's about absolute survival and building tomorrow's foundation.
#ethiopiaelection #africarising #panafrican #sovereignty #ethiopia #ebcdotstream ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
Ethiopia’s 7th General Election proved that African democracy is self-reliant, peaceful, and validated by its own people. As African observers noted, this wasn't for show it's about absolute survival and building tomorrow's foundation.
#ethiopiaelection #africarising #panafrican #sovereignty #ethiopia #ebcdotstream
2 months ago
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጠንካራ መሠረት መጣሉን የኦሮሚያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ
*************************
የኦሮሚያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በክልሉ የሚወዳደሩ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈው ምክር ቤቱ መግለጫውን ያወጣው፣ የፓርቲዎቹ መሪዎችና ተወካዮች በተገኙበት የምርጫውን አጠቃላይ ሂደት ገምግሞ ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በመግለጫው ምርጫው የሕዝብ ከፍተኛ ተሳትፎ የታየበትና የአስፈጻሚ አካላት ፍትሐዊነት የተረጋገጠበት መሆኑን አስታውቋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ አባላት በምርጫው ሂደት የታየው የሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቅም፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ በመግለጫው በተለይ ለምርጫው ሰላማዊነት የፀጥታ አካላት የተጫወቱትን ሚና ያደነቀ ሲሆን፣ ምርጫ ቦርድም ሂደቱን ከማስፈጸም ባለፈ የሚነሱ ቅሬታዎችን ከስር ከስር በመፍታት በኩል የነበረውን ጥረት አጉልቷል፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ ኅብረተሰቡ ምርጫውን ለማደናቀፍ የተሰማሩ ኃይሎችን በማምከን፣ ሥልጣን ማግኘት የሚቻለው በምርጫ ካርድ ብቻ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ሂደት እንደነበር በአፅንኦት ገልጿል፡፡
ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ያደረጉትን ከፍተኛ ርብርብ ያደነቀው ምክር ቤቱ፣ ሂደቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስልጡንነት እና መብቱን ለመጠቀም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያመላከተ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዘሃራ መሀመድ #የምርጫውጤት #ኢትዮጵያ #oromiajointcouncil #ethiopianelection #democracy #ethiopia

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር መፃኢ እድል እና ለዲሞክራሲ ግንባታ ያለው ፋይዳ የጎላ እንደሆነ መራጮች ገለጹ
*********************
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ የተሄደ ሲሆን የዜጎችን የፖለቲካ ንቃትና የዲሞክራሲ ፍላጎት በግልጽ ያሳየ ክስተት ነበር።
በምርጫው ሂደት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ዜጎች እንደገለጹት መምረጥ ማለት ተራ ተግባር ሳይሆን የሀገርን መፃኢ እድል የመወሰንና የዲሞክራሲ መሰረትን የማጠናከር ወሳኝ ሂደት ነው ብለዋል።
ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ የወጡት ያለምንም አስገዳጅነትና በራሳቸው ተነሳሽነት መሆኑን ገልፀው ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ይሆነኛል የሚሉትን እና ለሀገር እድገት ይሰራል የሚሉትን አካል በነፃነት ለመሰየም መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ምርጫው ለሀገር ገንባታ ትልቅ መድረክ ነው የምርጫ ሂደት ኢትዮጵያ ወደተሻለ የዲሞክራሲ ምህዳር ለማሸጋገርና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገርን ለመገንባት የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው ብለዋል።
ምርጫ ዜጎች በመረጡት መሪ የመተዳደር መብታቸውን በማስጠበቅ ለሀገራዊ አንድነትና ለዘላቂ ሰላም መሰረት ሆኖ ያገለግላል።
በቢታኒያ ሲሳይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #election #democracy

IGAD Congratulates Ethiopia on Peaceful and Orderly 7th General Election
#ethiopia #igad #ethiopianelection #democracy #stabilityandprogress
2 months ago
የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አደነቁ
**************
የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቀዋል።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለእጩዎች እና ለሲቪል ማኅበራት ለምርጫው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ለአፍሪካ ኅብረት እና ለኢጋድ የምርጫ ታዛቢነት ሚና እውቅና ሰጥተዋል።
#ebc #ethiopia #democracy #peace #democraticrights

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavoted #democracy #fanatelevision

በሀረሪ ክልል ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች እየተለጠፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በሚገኙ ሦስት የምርጫ ክልሎች በተቋቋሙ 294 የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች እየተለጠፉ ነው።
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም በክልሉ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤቶች ለሕዝብ እይታ ግልጽ በሆኑ ቦታዎች እየተለጠፉ ሲሆን÷ መራጩ ሕዝብም ውጤቶቹን እየተመለከተ ይገኛል።
በተሾመ ኃይሉ

u12edu1204u1295u1295 u1215u12ddu1265 u121bu1308u120du1308u120d u1218u1273u12f0u120d u1290u12cdu1293 u1270u1218u122bu132eu127d u12ebu12a8u1260u122bu127du1201u1295 u12a0u12adu1265u122bu127du1201 u1208u12f4u121eu12adu122bu1232 u1225u122du12d3u1275 u12cbu130b u12e8u12a8u1348u1208u12cdu1295 u12edu1204u1295u1295 u1215u12ddu1265 u1260u1295u133du1215u1293 u1208u121bu1308u120du1308u120d u12ebu1265u1243u127du1201 - u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) #nebe #ethiopia #democracy #ebcdotstream ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #nebe #ethiopia #democracy #ebcdotstream
2 months ago
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው
#ኢትዮጵያ #ምርጫ2018 #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavotes #democracy #fanatelevision
2 months ago
የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው
#ethiopia | ''የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።''
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)
#pmabiyahmed #ethiopianelection #democracy #ethiopianpeople #abiyahmed #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ከኃይል እርምጃ ወደ ሰላማዊ ምርጫ ከተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች አንደበት
********************
ብቸኛ የሥልጣን ምንጭ የሕዝብ ድምጽ ሊሆን እንደሚገባ የሰላም አማራጭን የተቀበሉ መራጮች ተናግረዋል።
የኃይል አማራጭን በመጠቀም በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው በምርጫ ሂደቱ ሲሳተፉ ታይተዋል።
ከኃይል አማራጭ ይልቅ ሰላምን በማስቀደም ድምፃቸውን ይወክለኛል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ መስጠታቸውን ነው የተናገሩት።
ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው መንግሥት ለመመሥረት የሚያግዝ እና የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በምርጫው ሊሳተፍ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
#ebc #ethiopia #ebcdotstream #democracy

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ ነው - የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ
#ethiopia | የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን የሚመሩት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋ።
አሁሩ ኬንያታ በመራጮች ማዕከላት የተመለከቱትን ሁኔታ ሲገልጹ፣ የድምፅ አሰጣጡ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ቀኑን ሙሉ በተመሳሳይ መንፈስ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
"ድምፅ መስጠት ዜጎች የሚወክሏቸውን መሪዎች እና ተወካዮች በነፃነት የሚመርጡበት መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብት ነው" ያሉት ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ እውነተኛ ውክልና፣ አካታችነት እና ሕዝቦች የራሳቸውን መሪዎች የመምረጥ አቅም እንዲጠናከር እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የምርጫ ሂደቶች ፈተናዎች እንዳሉ ቢገልጹም፣ ከእያንዳንዱ ምርጫ በኋላ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ባህል ለመገንባት ዕድል እንዳለ ጠቅሰዋል።
"ኢትዮጵያ የዚህች ታላቅ አህጉር ዋና ከተማ ናት፤ በዚህች ሀገር የሚገኝ ስኬት በመላው አፍሪካ ውስጥ ይንጸባረቃል" ሲሉ የተናገሩት ኬንያታ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸው የምርጫው ሂደት በሥርዓት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #ethiopia #ebcdotstream #democracy #africanunion

A thriving democracy requires absolute transparency. For this general election, more than 1,800 journalists have been licensed to report on the ground.
#ethiopiae #democracy #transparency #ebc
2 months ago
Defining Moment for Ethiopia #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavotes #democracy #fanatelevision #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል
2 months ago
Tomorrow, the eyes of the world turn to Ethiopia as over 54 million citizens cast their votes to make their voices heard.
#ethiopia #ebc #democracy #ethiopiavotes
2 months ago
Pour l’intégrité électorale
#election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavotes #democracy #fanatelevision #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል
Sponsored by
Surafel
2 months ago
Ethiopia's 7th General Election, A Pivotal Moment for Democracy
#ethiopiavotes #democracy #ebc #ebcdotstream
2 months ago
2 months ago
እያንዳንዱ ወጣት በምርጫው በንቃት እንዲሳተፍ ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እያንዳንዱ ወጣት በነገው ዕለት በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት እንዲሳተፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጥሪ አቀረበ፡፡
ፌዴሬሽኑ ምርጫውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በርካታ ወጣቶች በእጩነት፣ በምርጫ ታዛቢነት እንዲሁም በመራጭነት በመመዝገብ በንቃት መሳተፋቸውን አስታውቋል፡፡
ከአጠቃላይ መራጮች ውስጥ ከ15 ሚሊየን በላይ ወጣቶች መሆናቸውን የገለጸው ፌዴሬሽኑ፥ ከተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች በእጩነት ከቀረቡት ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ ወጣቶች ናቸው ብሏል፡፡
32 ሺህ 500 ታዛቢዎችን ማሰማራቱንና 20 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራቱን አመልክቷል፡፡
ምርጫ ወጣቱ የራሱን ዕጣ በራሱ የሚወስንበት በመሆኑ ሁሉም ወጣት በነገው እለት ድምፅ እንዲሰጥ ፌዴሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
በቤተልሄም መኳንንት
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያትመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavotes #democracy #fanatelevision

Comments