3 days ago
የዲጂታል ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ - ከስትራቴጂ ወደ ስኬት
***********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዛሬ ዓለማችን በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ፈጣን ግስጋሴ ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት በውል በመገንዘብ፣ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚዋን ከመሠረቱ የሚቀይር ታሪካዊ የዲጂታል ሽግግር እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት ሀገራችን ያለባትን ዘላቂ የቢሮክራሲ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቅረፍ ዲጂታላይዜሽንን እንደ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ በመውሰድ እየሠራችበት ትገኛለች።
ይህ ጉዞ የሀገርን የልማት ምሰሶ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያጸና የመንግሥት የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለን እናምናለን።
በአንድ ወቅት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ሩቅ ሕልም ይታይ እንደነበር አይዘነጋም፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑት መሠረታዊ ሥራዎች ግን ዛሬ ላይ ሊሻር በማይችል እውነታ ላይ የቆመ መሠረት ተጥሏል።
መንግሥት ያደረጋቸው ሰፊ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያዎች “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችለዋል።
አሁን ደግሞ የሀገራችንን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉ የሂደቱን ቀጣይነት ያረጋግጣል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ለችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች መበልጸግ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ የሚበረታታ እርምጃ ነው።
በዚህ ዘመናዊ የታሪክ እጥፋት ውስጥ የ“ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እና የ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ ሚና እጅግ የላቀ ነው።
የዲጂታል መታወቂያ ለኢኮኖሚው ግንባታ ልክ እንደ ቤት መሠረት ነው። እስከ 90 ሚሊዮን ዜጎችን በሥርዓቱ ውስጥ ለማቀፍ የታቀደው ይህ ግዙፍ መርሐ ግብር ለባንክ፣ ለፋይናንስ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ ነው።
“የቆጠሩት እህል አያልቅም” እንደሚባለው የሀገርን የሰው ኃይል በዕውቀት ሳያደራጁ ዘላቂ ስኬትን ማሰብ አይቻልም። በመሆኑም በ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚረከቡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተጣለ ታላቅ መሠረት ነው።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በሁሉም አካባቢዎች እየተገነባ ያለው “የመሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የተንዛዛ ቢሮክራሲን እና የዜጎችን እንግልት በማስቀረት የመንግሥትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ሙስና እና ብክነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል አስተማማኝ ተቋማዊ አቅም ይፈጥራል።
በፋይናንስ ዘርፍም ቢሆን በ2017 በጀት ዓመት ብቻ በዲጂታል የተከናወነው የግብይት ዋጋ 16 ትሪሊዮን ብር መድረሱ የዲጂታል ኢኮኖሚው ምን ያህል ውጤታማ እና ተደራሽ እየሆነ ለመምጣቱ ሕያው ማሳያ ነው።
ይህ ስኬት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን በተግባር አረጋግጧል።
ለወደፊቱም መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ፕላትፎርሞች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ የሀገራችንን የነገ ገጽታ በእጅጉ የሚቀይር ነው።
መንግሥት የሳይበር ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የስታርትአፕ ሥነ ምኅዳርን በማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግር ሂደቱን አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ እያደረገው ይገኛል።
በአጠቃላይ ይህ ታሪካዊ ጉዞ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያቀልል፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ እና የኢኮኖሚ ልማታችንን ከሕልም ወደ እውነት የለወጠ የጋራ ብሔራዊ ስኬታችን በመሆኑ ሁሉም አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #5millioncoders #success #𝐃𝐢𝐠𝐢𝐭𝐚𝐥𝐄𝐜𝐨𝐧𝐨𝐦𝐲

Comments