2 days ago
ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ
*ሊዮ 14ኛ በቀጣይ ጉብኝት የሚያደርጉባቸውን ሦስት ሀገራት ታውቀዋል።
#ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኅዳር ወር በደቡብ አሜሪካ አገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።
ፖፕ ሊዮ 14ኛ በኡሩጉዋይ፣ አርጀንቲና እና ፔሩ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቋል።
ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ በኋላ ወደ ደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዟቸው ይሆናል።
በዚህም ከኅዳር 6 እስከ 17 ባሉት 12 ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ከተሞችን የሚሸፍን ጉብኝት ይሆናል ተብሏል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቀድሞ ስማቸው ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት በፔሩ አገር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በምስዮናዊነት እና በጳጳስነት ያገለገሉ ሲሆን የዚያች አገር ሙሉ ዜግነትም እንዳላቸው ተገልጿል።
ፖፕ ሊዮ ረጅሙን የጉዞ ጊዜ በፔሩ የሚያሳልፉ ሲሆን ሊማ ቺክላዮና ኩስኮ ከተሞችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የትውልድ አገራቸው አርጀንቲናን በ12 ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነታቸው ወቅት መጎብኘት አልቻሉም ነበር።
አሁን የሊዮ 14ኛ የአርጀንቲና ጉብኝት በአገሪቱ ዜጎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #popeleo #vatican #peru #argentina #uruguay

7 days ago
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጉ ዘንድ ግብዣ እና የጸሎት ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት ባሳለፍነው ሰኔ ወር በቅድስት መንበር ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ ጋር ባደረጉት የካርዲናሎች ጉባኤ ለቅዱስነታቸው የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው በየአመቱ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚደረገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞ የአፍሪካ ቀንድ ዋና ማዕከል ወደሆነችው ኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደቀረበላቸው በመግለጽ ምዕመናን ለዚህ ምኞት መሳካት እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የዘመናት የታሪክ ባለቤት የሆነች፣ የአማኞች ሀገር፣ የአፍሪካ ማዕከል እና በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2027 ለሚዘጋጀው 32ኛው የአየር ንብረት ጉባኤ (COP32) በአዘጋጅነት የተመረጠች ሀገር በመሆኗ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛ በቀጣይ ዓመት ለሚኖራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን ማካተት እንዲቻል ጥሪ አቅርበዋል።
ከሐምሌ 11-19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኬንያ ናይሮቢ በተካሔደው 21ኛው የምስራቅ አፍሪካ የጳጳሳት ጉባኤም ይህ ጥሪ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሌዎ 14ኛ መቅረቡ ተገልጿል።
ይህም ታላቅ እና የዘመናት የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ምኞት ምላሽ ይገኝ ዘንድ መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል #ethiopia #getutemesgen #getunews #catholic #popeleo

Comments