ወሳኙ የታሪክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ
************
ኢትዮጵያ በታሪኳ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። በጋራ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር ሐሳቦችን በነፃነት ማንሸራሸር እና የጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር የማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡
ለዘመናት የዘለቁ ፖለቲካዊ ቅራኔዎችን ለመፍታት፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ለጠንካራ የሀገር ግንባታ መሠረት ለመጣል ምክክር አማራጭ የሌለው ወሳኝ መንገድ ነው፡፡
በዚህ ረገድ፣ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት "የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል፡፡
ልዩነትን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የዚህ ሀገራዊ ጉባኤ ዋነኛ ግብ ነው፡፡ በምክክር ግጭትና መቃቃርን ተወግፍዶ የሐሳብ ልዕልና የሚነግሥበት እንዲሁም የጠመንጃ ድምፅ የሚሸነፍበት ሥርዓትን መገንባት ይቻላል፡፡
እውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም ሊመጣ የሚችለውም ተቀራርቦ በመወያየት እንጂ በመለያየት እና በፀብ ግንብ አይደለም፡፡ ምክክሩም ቅሬታ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ድምፃቸው የሚሰማበትና ለችግሮቻችን ዘላቂ መፍትሔ የምንፈልግበት ታሪካዊ መድረክ ነው፡፡
ዋናው የምክክር ጉባኤ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያሳትፍ በመሆኑ ለጉባኤው ስኬት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል። ለዚህ ምክክሩ ስኬትም የዜጎች ንቁ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው።
በአጠቃላይ፣ ሐምሌ 8 የሚጀመረው "የኢትዮጵያ ሕዝብ የምክክር ጉባኤ" የጥላቻና የግጭት ታሪክን ዘግተን፣ የሰላምና የአብሮነት አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ወርቃማ ዕድል ነው፡፡
ይህ ወሳኝ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምኅዳር የሚያሸጋግር የታሪክ ድልድይ ይሆናል፡፡
#ethiopianbroadcastingcorporation #national #dialogue #ethiopia

5 days ago