4 days ago
"ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ከአማራና ኦሮሞ ውህደት ውጭ ማየት አይቻልም"
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሀገሪቱን ለመቀየር ፖለቲካውንም ሆነ ኢኮኖሚውን ጎን ለጎን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ እንደነበር ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩም የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአማራና ከኦሮሞ ሕዝቦች ጥብቅ ውህደትና ትስስር ውጭ ሊታይ አይችልም። የዓድዋ ድልም የዚሁ ታሪካዊ አንድነት ትልቁ ማሳያ ነው፤ አብሮ የመኖር ባህልም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ እሴት እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ በሀገራችን ስልጣንን በኃይልና በሰው ግድያ ለመያዝ የመሞከር አጥፊ ባህል እንደነበር አውስተዋል። በዚህም የሰኔ 15ቱ ክስተት በለውጡ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸውን ሰዎች ያጣንበት የሕመም ጠባሳችን ነው ብለዋል።
ሆኖም ሕዝቡ ለውጡን በሙሉ ልብ የተቀበለ ሲሆን፣ በአንድነትና በትብብር አንዲት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በምርጫው ወቅት በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።
***
“የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች ለአጭር ጊዜ እፎይታ ተብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት መመለስ አይቻልም”
በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን ለአጭር ጊዜ እፎይታ ብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ መመለስ እንደማይቻል እና ጉዳዩ በሕግ አግባብ እና በሀገራዊ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የወልቃይትን ጉዳይ እንደ አብነት በማንሣት በትግራይም ሆነ በአማራ ክልል በኩል የሚነሡ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ዘላቂ መፍትሔው የሁለቱንም ሕዝቦች ጥቅም በማይጎዳ፣ በውይይት እና ሁለቱም አሸናፊ በሚሆኑበት ሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ካልሆነ መልሶ ለግጭት የሚዳርግ ቆይቶ የሚፈነዳ ቦምብ ይሆናል ብለዋል።
በሌላ በኩል ከውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በዚህም በፓርቲ ውስጥ የነበረውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሠራር ማስተካከል እና የክልሎችን ራስን የማስተዳደር መብት ማክበር ተችሏል ብለዋል ።
በተጨማሪም በመንግሥት ተቋማት አካታችነትን ማረጋገጥ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በካቢኔ እና በፖለቲካ ምኅዳር ማሳተፍ እንዲሁም አግላይ የነበሩ ትርክቶችን ማረቅም ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።
***
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል-
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሰኔ 15ቱን መጥፎ ክስተት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ታሪክን ማዛባት ለነገው ትውልድ የሚተርፍ እዳ ነው ብለዋል።
ለውጥን ለማምጣት በጽናት ሲሰሩ የነበሩ የለውጥ አበጋዞችን ያጣንበት፣ በፖለቲካው መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲሸረሸር ያደረገ እና የስልጣን ሽሚያ በሃይል የማስከበር መጥፎ ባህልን ያስቀጠለ አጋጣሚ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ስለ እለቱና ስለተፈጠረው ክስተት ሲያብራሩ፤ እለቱ ቅዳሜ ነበረ፤ መረጃውን እንደሰማሁ ለህዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ሚዲያዎች እንዲጠሩ አደረግኩ፤ ፋና እና ኢቢሲ በምሽቱ ፈጥነው አልደረሱም ነበር፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ግን እዚሁ 4 ኪሎ አቅራቢያ ስለነበር በፍጥነት ደረሰ ብለዋል።
መግለጫውን እኔ ቤት ሆኜ ለአሚኮ ሰጠሁ፤ በኋላ ግን 'ባህር ዳር ሆኖ መግለጫ ሰጠ' ተብሎ የሴራ ትንተና ተፈበረከበት በማለት አስታውሰዋል።
ይህ ክስተት ያስተማረን ትልቅ ሀቅም ታሪክን በትክክል አለማስቀመጥና ማዛባት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገውም ትውልድ እዳ ያተርፋል ሲሉ ተናግረዋል።
ገዳይም ሟችም በአንድ ላይ 'ጀግና' የሚደረግበት የታሪክ ስብራት ሊቆም እንደሚገባም በአፅንኦት አስገንዝበዋል።
***
"በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በዘመናት መካከል አብረው ሲኖሩ በብዙ መልኩ የተጋመዱ፣ የተሳሰሩ፣ የተጋቡ፣ የተዋለዱ በጋራ የኖሩ ናቸው''
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ethiopia #pmabiyahmed #currentaffairs #pmabiyahmed #amico #ethiopia #medemer #amharaandoromo #ethiopianunity

Comments