ሀገር በምክክር እና በጋራ መግባባት ላይ ስትመሠረት ዘላቂ ሰላምና ጥንካሬ ታገኛለች
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተጻፈው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ላይ ሀገር በምክክር እና በጋራ መግባባት ላይ ስትመሠረት ዘላቂ ሰላምና ጥንካሬ እንደምታገኝ በሰፊው ተብራርቷል።
መጽሐፉ የኢትዮጵያን ዘመናት ያስቆጠሩ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ስብራቶች ለመጠገን ቁልፍ መፍትሔው ንግግርና ብሔራዊ ምክክር መሆኑን ያስረዳል።
በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቁ ጉድለት በዋና ዋና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀምጦ በሰለጠነ መንገድ የመመካከር ባህል ማነስ ነው።
ይህንን ክፍተት ተንተርሶ የተጻፈውና የመደመር ፍልስፍናን ወደ ተግባራዊ የመንግሥት መዋቅር የሚያሸጋግረው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ፣ ሀገር ሊጸና የሚችለው በምክክርና በጋራ መግባባት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
መጽሐፉ እንደሚያስረዳው፣ ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፣ በውይይት ጎልብተው፣ አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት ታላቅ ምኅዳር ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ ሕዝብ በሰፊው ተመካክሮ የጋራ መግባባት ላይ ያልደረሰባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ።
በዚህም የተነሣ በየዘመናቱ ቅሬታዎች፣ ኩርፊያዎች፣ አብዮቶችና ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሲከሰቱ ኖረዋል።
የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያብራራው፣ ሀገራዊ ምክክር እነዚህን የዘመናት ስብራቶች ለመጠገንና አዲስ የሰላም ምዕራፍ ለመክፈት ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው።
መጽሐፉ የፖለቲካ ባህላችንን ከጠብመንጃና ከኃይል አማራጭ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ንግግር መቀየር እንዳለብን ያሳስባል።
የተግባባንባቸውን ጉዳዮች በሕግና በሥርዓት አጽንቶ መጓዝ፣ ያልተግባባንባቸውን ደግሞ ለቀጣይ ምክክሮች አቆይቶ በሂደት መፍታት የሰለጠነ ማኅበረሰብ መገለጫ ነው።
ምክክር በሌለበት ምኅዳር ውስጥ ነገሮች በተናጠል ስለሚቀርቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርና ሁለንተናዊ ዕይታን እንደሚያጠፋ መጽሐፉ ያስጠነቅቃል።
ኢትዮጵያ በታላላቅ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ የውስጥ አንድነትና የጋራ አቋም ሊኖራት የሚችለው ዜጎችና የፖለቲካ ኃይሎች በጋራ መድረክ ላይ ሲመክሩ ብቻ ነው።
እንደ ሀገር በአንድነት ካልቆምን የትኛውም ዓይነት የልማትም ሆነ የዲፕሎማሲ ሥራ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል መጽሐፉ በምክንያት ያስረዳል።
ምክክሩም የትኛውም ዜጋ ሳይገለል የራሱን ሐሳብ አዋጥቶ የጋራ ሀገር የሚገነባበትን ዕድል ይሰጣል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ እንደሚያስረዳው፣ የሀገር ጽናት የሚለካው በኃይል ሳይሆን በውስጥ መግባባት ጥልቀት ነው።
ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት፣ የተግባባንበትን የጋራ ትርክት በማስፋትና ያልተስማማንበትን በሂደት በማጥበብ ብቻ ጠንካራና የማይናወጥ ሀገረ መንግሥት መገንባት ይቻላል።

23 days ago