ከፖለቲካ ሽኩቻ የላቀው የጋራ ተቋማችንን እናክብር
****************
የአንድ ሀገር ጥንካሬ ከሚገለጽባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ዜጎች በጋራ የሚግባቡባቸው እና በኩራት የሚጠሯቸው ጠንካራ ብሔራዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።
ከእነዚህ ተቋማት መካከል ደግሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚውን እና የክብር ማማውን ስፍራ ይይዛል።
የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ስንመለከት፣ በሠለጠኑ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት የሠራዊት አባላትን ማክበር ከፖለቲካዊ ሽኩቻዎች የላቀ ብሔራዊ መግባባት የተገነባበት ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።
በአሜሪካ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ በፓርቲዎች መካከል የጎላ ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነት ቢኖርም፣ ሠራዊቱን ከፖለቲካ ፉክክር ውጪ የማድረግ ብሔራዊ ስምምነት አለ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግሥትን ፖሊሲ በሚተቹበት ወቅት እንኳ በጦር ግንባር የተሰማሩትን ወታደሮች እንደ ጀግና በመቁጠር ውዳሴ እና ክብር ያቀርባሉ።
በዩናይትድ ኪንግደም "የጦር ኃይሎች ቃል ኪዳን" (Armed Forces Covenant) የተሰኘው ብሔራዊ ሰነድ የሠራዊት አባላት ልዩ ክብር እንዲያገኙ ያደርጋል።
ካናዳ ለአርበኞች ልዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ስታቋቁም፣ ፈረንሳይ ደግሞ ሠራዊቷን የሀገሯ የክብር እና የአጋርነት ብሔራዊ ተምሳሌት በማድረግ በትልቅ ማዕረግ ትዘክራለች።
ወደ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ስንመጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በባሕርይው እጅግ ሕዝባዊ የሆነ፣ ከሀገር አልፎ ለዓለም የሰላም ዘብ በመሆን ደሙን የገበረ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር በኮሪያ ልሳነ ምድር በቃኘው ሻለቃ አማካኝነት "አንድም ወታደር አልተማረከም፤ የሞተ ጓዱንም ጥሎ አልመጣም" የሚል የዓለምን አስደናቂ ሪከርድ ያስመዘገበ ጀግና ነው።
በኮንጎ፣ በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ፣ በላይቤሪያ፣ በአብዬ፣ በዳርፉር እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በመሰማራት አፍሪካውያን ወንድሞቹን ከእልቂት የታደገ፣ የራሱን ሬሽን እያካፈለ የውጭ ሀገር ዜጎችን ያኖረ የሰብአዊነት ተምሳሌት ነው።
ይህ ሠራዊት በሀገር ውስጥም ቢሆን ጦር መሣሪያውን አስቀምጦ በክረምት የገበሬውን ማሳ ሲያርስ እና በመኸር ሲያጭድ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ከነፍስ አድን ሥራ እስከ አንበጣ መንጋ ማባረር ድረስ ከሕዝቡ ጎን የቆመ ታላቅ አለኝታ ነው።
ነገር ግን አለመታደል ሆኖ፣ የሀገራችን መከላከያ ሠራዊት በፖለቲካ ኃይሎች መካከል በሚደረጉ ፍልሚያዎች ውስጥ የከፉ ምኞቶች ሰለባ ሲሆን ይስተዋላል።
አንዳንዴም የፖለቲካ ልዩነትን እና የሀገርን የፀጥታ ምሰሶ መለየት ያቃታቸው አካላት ሠራዊቱን የማንቋሸሽ አዝማሚያ ያሳያሉ።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ማክበር እና ለሀገር ሕልውና የሚከፍለውን ዋጋ ማወቅ የአንድ ማኅበረሰብ የሥልጣኔ መገለጫ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፣ ሀገርን ጠብቆ የሚያኖርን ኃይል እንደ "ገዳይ" መፈረጅ እና ተቋማዊ ክብሩን አለማወቅ የሲቪል-ወታደራዊ ግንኙነትን አለመረዳት እና ያለመሠልጠን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግሥት እና ፖሊሲ አውጪዎችን በጥብቅ መተቸት የዴሞክራሲ አካል ነው። ነገር ግን ለሀገር ሕልውና አጥንቱን የሚከሰክሰውን ሠራዊት ከተቋማዊ ትችት ነፃ አድርጎ በጀግንነት መዘከር ይገባል።
በመሠረቱ ሠራዊቱ ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታ ሲኖርበት፣ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ የሠራዊቱን መሥዋዕትነት የመካስ የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ትኩረት አድርጋ ከሠራችባቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል የፀጥታ ተቋማት ግንባታ ዋነኛው የሆነውም ለዚሁ ነው።
ሠራዊታችን ከፖለቲካ ልዩነቶቻችን በላይ የሆነ የጋራ የብረት አጥራችን እና የሕልውናችን ምሰሶ በመሆኑ ዘወትር ክብር እና ሞገስ ይገባዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #endf #nationalpride #standwithourtroops

26 days ago