1 month ago
አቶ ዳዊት ገበየሁ እና አቶ ገደኖ ካዋይታ ተፈረደባቸው።
⚫ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን የተለገሰ 6,594 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ተሸጦ ለግል ጥቅም ውሏል ፤ 3,702,466.67 ብር ነው ተሽጦ የተበላው።
የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ዳዊት ገበየሁ እና የግብርና መምሪያ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ የነበሩት አቶ ገደኖ ካዋይታ ላይ የፍርድ ውሳኔ ማሳለፉን የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሀባ ቀውያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ " የመንግስትን የሥራ ኃላፊነት በማይመች አኳኋን መምራት እና የሙስና ወንጀል " ጥፋተኛ መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አሳውቀዋል።
ተከሳሾቹ በ2014 ዓ.ም በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲሆን ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተለገሰውን 6,594 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸው በማስረጃ መረጋገጡን አቶ ሙሀባ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ተከሳሾች ለግል ጥቅማቸው ያዋሉት ሀብት ግምቱ ብር 3,702,466.67 (ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሁለት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ስልስት ብር ከስልስ ሰባት ሳንቲም) መሆኑን ጠቅሰው ፤ የተገኘው ጥቅምና በህዝብ ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲሁም የወንጀሉ ዓላማ ከባድ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ግምት ውስጥ ማስገባቱን ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፣ ፍርድ ቤቱ በመመሪያው መሠረት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ15 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50,000 ብር መቀጮ እንዲቀጡ መነሻ ቅጣት ወስኖ ነበር።
ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ ፦
- ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌላቸው፣
- የቤተሰብ አስተዳዳሪና ለረዥም ጊዜያት ያገለገሉ በመሆናቸው፤
- በተለይ 1ኛ ተከሳሽ "እምርታ" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ የነበሩ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው ሦስት የቅጣት ማቅለያዎች መያዛቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤት የሚከተለውን የመጨረሻ ውሳኔ ማስተላለፉን አቶ ሙሀባ ቀውያ ገልጸዋል።
1ኛ ተከሳሽ አቶ ዳዊት ገበየሁ ፦ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ከሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሚቆጠር በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 20,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ፤
2ኛ ተከሳሽ አቶ ገደኖ ካዋይታ ፦ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ከመስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚቆጠር በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 20,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል።
በተጨማሪም ተከሳሾቹ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉትን ብር 3,702,466.67 ለመንግስት በጋራ እንዲመልሱ መወሰኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
አቶ ዳዊት ገበየሁ በዚሁ ፍ/ቤት በሌላ የወንጀል መዝገብ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5,000 ብር መቀጮ ተፈርዶባቸው የነበረ መሆኑን አቶ ሙሀባ ገልጸው፤ ሁለቱም የወንጀል ቅጣቶች ተደምረው ተከሳሹ በአጠቃላይ በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በ25,000 ብር የገንዘብ መቀጮ የሚቀጡ መሆኑን አስታውቀዋል።
tikvahethiopia

2 months ago
የብርሃን ጉዞ ወደ ገጠር
* የሶላር ሚኒግሪድ ፕሮጀክቶች በደቡብ ኢትዮጵያ ስኬት እያስመዘገቡ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከብሔራዊ የኃይል ቋት (Grid) የራቁ የገጠር አካባቢዎችን በአማራጭ የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረው የተቀናጀ የልማት ሥራ ውጤታማ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለፁ።
በደቡብ ኦሞ ዞን (ሳላማጎ፣ ሐመር፣ ኦሞራቴና ዳሰነች) እንዲሁም በጋሞ ዞን (ጋርዳ ማርታ) የሶላር ሚኒግሪድ ማመንጫዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
በአጠቃላይ 2,325 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ከ20 ሺህ በላይ የገጠር አባወራዎችን የብርሃን ተጠቃሚ አድርገዋል።
ይህ ኃይል ከመኖሪያ ቤት ብርሃን ባለፈ ለመጠጥ ውሃ፣ ለጤና ተቋማትና ለመስኖ ልማት እንዲውል ከተቋሙ ጋር በትብብር እንደሚሠራ ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሌሎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ። ይህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 የያዘችውን የኃይል ተደራሽነት ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
#getu #eeu #solarenergy #ruralelectrification #southethiopia #greenenergy #developmentnews #worldbank #energyaccess #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ሶላር #ልማት #ደቡብኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የሰብአዊነት ጥሪ
ለኮንሶ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!
#ethiopia | የጥንካሬና የታታሪነት ተምሳሌት የሆነው የኮንሶ ሕዝብ፣ በሰገን ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ምክንያት አስቸጋሪ መከራ ውስጥ ይገኛል።
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በሸራ ተጠልለው የነበሩ ወገኖች፣ በደረሰው ከባድ ዝናብና ጎርፍ መጠለያቸው በሙሉ ተወስዶባቸዋል።
በዚህ የክረምት ዝናብ ወቅት መጠለያ ማጣት የሕፃናትና የእናቶችን ሕይወት ለከፋ አደጋ አጋልጧል።
ኮንሶ ሁልጊዜም ለችግሮች አገር በቀል መፍትሔ በማምጣት የሚታወቅ ድንቅ ሕዝብ ነው። ዛሬ ግን ይህ የታታሪ ሕዝብ ልጆች የእኛን እጅ ይሻሉ።
የክልሉና የዞኑ መንግሥታት ዘላቂ ማቋቋሚያ ሥራ ቢጀምሩም፣ ወቅቱ አጣዳፊ በመሆኑ የእኛ ድጋፍ ወሳኝ ነው።
በሰገን ዙሪያ ወረዳ የመልሶ ማቋቋሚያ ስም በተከፈተው የባንክ አካውንት አቅማችን የፈቀደውን በማድረግ ከወገኖቻችን ጎን እንቁም፦
🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000418082438
🔹 አድራሻ፦ የሰገን ዙሪያ ወረዳ የመልሶ ማቋቋሚያ
መከራን በጋራ ማለፍ ባህላችን ነው!
የቻልነውን በማበርከት፣ ካልቻልን ደግሞ ይህን መረጃ ሼር (Share) በማድረግ ለወገኖቻችን ድምፅ እንሁን።
ለጀግናው፤ ለታታሪው የኮንሶ ሕዝብ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ
5,000.00 ( አምስት ሺህ ብር ) ድጋፍ አድርገናል።
እንመጣለን - ኾንሶ ኻኖ
#getu #savekonso #segenzuria #floodrelief #humanitariancall #ethiopiahelp #konsopeople #supportethiopia #emergencyaid #ኮንሶ #ሰገንዙሪያ #ሰብአዊነት #ድረሱልን #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

አስቸኳኪ የድረሱልን ጥሪ
በኮንሶ የሰገን ወንዝ የፈጠረው "የሞት ድልድይ" እና የነዋሪዎች ሰቆቃ!
#ethiopia | በኮንሶ ዞን የሰገን ወንዝ ሞልቶ ዳር እስከ ዳር በመትረፍረፉ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በሞትና በሕይወት መካከል የሚገኝ አስከፊ መከራን እያስተናገደ ይገኛል።
ነዋሪዎቹ ለዕለት ጉርሳቸውና ለልጆቻቸው ምግብ ፍለጋ ሲሉ ብቻ ወንዙን ለመሻገር የማይታሰብ አደጋ ውስጥ ይገባሉ።
ነዋሪዎቹ በወንዙ ግራና ቀኝ በተተከሉ እንጨቶች ላይ ገመድ አስረው በመንጠልጠልና በኃይለኛ ሞገድ እየተመቱ ለመሻገር ይገደዳሉ።
አንዲት ትንሽ ስህተት ወይም የገመድ መበጠስ በቀጥታ ወደ ግርማዊው የሰገን ወንዝ ውሃ በመግባት ሕይወትን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ አማራጭ የለውም።
የአካባቢው ነዋሪዎች እርሻና መተዳደሪያቸው በወንዙ ማዶ በመሆኑ፣ ይህን "የሞት ድልድይ" ሳይወዱ በግድ በየቀኑ ለመጠቀም ይገደዳሉ።
ይህ ችግር ከዞኑ አቅም በላይ በመሆኑ፣ የክልልና የፌዴራል መንግሥታት የወገኖቻቸውን ሰቆቃ ተመልክተው አስቸኳይ ድልድይ በመገንባት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጡ ጥሪ ይቀርባል።
ወገኖቻችን በገመድ ተንጠልጥለው ወደ ወንዝ የሚገቡበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል!
#getu #konso #segenriver #bridgerequest #humanitariancrisis #ethiopianews #safetyfirst #infrastructure #southernethiopia #ኮንሶ #ሰገንወንዝ #ድልድይ #ሰቆቃ #ድረሱልን #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የሲሲአርዲኤ (CCRDA) የ53 ዓመታት የልህቀት አሻራ
የሲአርዲኤ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ለውጥና ልማት ላይ የሚሰራ አንጋፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት (ኮንሶርትየም) ሲሆን፣ ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመናት በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ አሻራ አሳርፏል።
እ.አ.አ በ1973 በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረሃብ ወቅት፣ የእርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለማከናወን በልበ ቀናዎች የተመሰረተ ተቋም ነው።
ዛሬ ላይ የ53 ዓመታት የልህቀት እና የለውጥ ጉዞን አስቆጥሯል።
ራዕይ፦
ድህነት ተወግዶ ማየት።
ተልዕኮ፦
ማህበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ከአባላት ጋር በትጋት መስራት።
በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባላቱም በሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በሚከተሉት ዘርፎች ይሰማራሉ፦
ሰብዓዊ ድጋፍ እና ጤና
ልጆች፣ ወጣቶች እና ስነ-ፆታ
አካባቢ ጥበቃ እና የውሃ ንፅህና
ኤች አይ ቪ መከላከል
መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ
ሲሲአርዲኤ አባላቱ ተሞክሮ የሚለዋወጡባቸው መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በፖሊሲ ውትወታ (Advocacy) እና በሀብት ማሰባሰብ ረገድ የአባላቱን ተፅዕኖ የማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
𝐅𝐚𝐜𝐞𝐛𝐨𝐨𝐤: https://web.facebook.com/c...
𝐋𝐢𝐧𝐤𝐞𝐝𝐈𝐧: www.linkedin.com/in/ccrda-...
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦: https://t.me/ccrda_et
𝐘𝐨𝐮𝐓𝐮𝐛𝐞: https://www.youtube.com/@c...
𝐗 (𝐓𝐰𝐢𝐭𝐭𝐞𝐫): https://x.com/CCRDA454972
𝐖𝐞𝐛𝐬𝐢𝐭𝐞: https://ccrdaeth.org/
#ccrda #ሲሲአርዲኤ #ethiopia #ngos #civilsociety #development #socialjustice #53yearsofservice #impact #humanitarianaid #policyadvocacy #communitydevelopment #ethiodevelopment

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አዱኛ አዛዥ፣ በመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
አመራሯ በኮንሶ አካባቢ የነበራቸውን የመስክ የሥራ ግዳጅ አጠናቅቀው ወደ አርባ ምንጭ በመመለስ ላይ ሳሉ፣ በጋርዱላ ዞን (ሆልቴና ሽላሌ አካባቢ) ባልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱባቸው ድንገተኛ ተኩስ በአራት ጥይቶች ተመትተው ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገው ነበር።
ወዲያውኑ ወደ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢወሰዱም፣ ለሰዓታት የፈጀ የሕክምና ባለሙያዎች ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ መጋቢት 10 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ወይዘሮ አዱኛ ቀደም ሲል የጎፋ ዞን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በመሆን ያገለገሉና በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ያገለገሉ አመራር ነበሩ።
የክልሉ መንግሥት ድርጊቱን በጽኑ በማውገዝ፣ ይህን "እኩይ ተግባር" የፈጸሙ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ በትኩረት እንደሚሠራና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ዩቲዩብ ተመልካቾችን የሚያስቆጣ አዲስ አሰራር ይፋ አደረገ፤ ማለፍ የማይቻሉ ማስታወቂያዎች
ከዚህ ቀደም ተመልካቾች ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ 'Skip' በማድረግ የሚያልፏቸው ማስታወቂያዎች በአዲሱ አሰራር መሰረት ሙሉ 30 ሰከንድ እንዲታዩ ይገደዳሉ።
ጎግል ይህን ለውጥ ያመጣው ሰዎች በቲቪ ፕሮግራሞችን በሚከታተሉበት ወቅት ያላቸው ባህሪ ከመደበኛው የቴሌቪዥን ስርጭት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ነው ብሏል።
ኩባንያው አዲሱን አሰራር በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ መሆኑን ገልጾ የ6 ሰከንድ፣ የ15 ሰከንድ እና አዲሱን የ30 ሰከንድ ማስታወቂያ እንደ አስፈላጊነቱ እያፈራረቀ እንደሚጠቀም አስታውቋል።
ይህ ለውጥ ተግባራዊ የተደረገው በቅርብ ዓመታት ውስጥ የዩቲዩብ የቲቪ ተመልካቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ ነው።
ይህ አሰራር ተመልካቾች ማስታወቂያ የሌለበትን 'YouTube Premium' የተባለውን የሚከፈልበት አገልግሎት እንዲጠቀሙ ለማበረታታት የታለመ መሆኑም ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅት ለውጡ በስማርት ቲቪዎች፣ በጌም ኮንሶሎች እና በሌሎች የቲቪ መተግበሪያዎች ላይ ብቻ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
seledadotio

በቀጣይ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ የሚኖርባቸው አካባቢዎች ይፋ ተደረጉ‼️
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በቀጣይ 10 ቀናት ከመካከለኛ እስከ ከባድ የዝናብ መጠን የሚኖርባቸውን አካባቢዎች ይፋ በማድረግ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ።
ኢንስቲትዩቱ በመግለጫው፤
📌ጋሞ
📌ወላይታ፣
📌ጎፋ፣
📌ጌዴዮ፣
📌ባስኬቶ፣
📌አሪ፣
📌ኮንሶ፣
📌ቡርጂ፣
📌 አሌ፣
📌ጋርዱላ፣ ኮሬ
እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የዝናብ መጠን ያገኛሉ።
ይህ የዝናብ መጠን ለግብርና ሥራ አወንታዊ ጎኖች ያሉት ቢሆንም፤ የአፈር መሸርሸር፣ በሰብል ማሳ ላይ ውሃ መተኛት፣ የሰብል በሽታና ተባይ እንዲሁም የአረም መከሰት ሊያስከትል እንደሚችል መግለጫው አመልክቷል።
በመሆኑም አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎችን እንዲያከናውኑ፣ የሰብል በሽታና አረም እንዳይስፋፋ መከላከል ላይ እንዲተጉና ማሳዎችን በቅርበት እንዲከታተሉ ኢንስቲትዩቱ ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል።

4 months ago
ቱሪዝም ልጇን አጣች!
"ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
#ethiopia | የጋቶ ወንዝን እንደተሻገራችሁ የምታገኟት የኮንሶዎች መንደር ፍጨጫ ትባላለች፡፡ ከፍተኛ የአሸዋ ምርት የሚገኝበትን ካይሌ ወንዝ እንዳለፋችሁ ካራት ከተማ ትገባላችሁ፡፡
ዘሪሁንን የተዋወቅሁት ካረት፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ነበር።
ዱሮ ዱሮ የኮንሶ ብሔረሰብ የሚኖረው በ49 የተከለሉ አምባ መንደሮች ውስጥ ነበር፡፡ አሁን ሰባቱ አምባ መንደራት ፈርሰው 42ቱ ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 12ቱ መንደሮች የላይኛውና የታችኛው ዶከቱ፣ ታራ፣ ጋሞሌ፣ ቡሶ፣ ኦላንታ፣ መጨሎ፣ መጨቄ፣ ጎጫ፣ ሁሉሜ፣ ቡርኩዳና ቡርጆ የጥበቃ ከለላ ድንበር "ሦስቱ የጎሳ መሪዎች የሚያስተዳድሯቸው ‹‹የተቀደሱ ደኖች››፤ ጋሞሌ አምባ መንደር የሚገኘው ‹‹ሙራ ካላ››፣ በላይኛው ዶካቱ ‹‹ሙራ ባማሌ››፣ በፋሻ ‹‹ሙራ ቁፋ›› እንዲሁም ኩሬ ሃርዳ ዶከቱ፣ ሃርዳ መጨቄ፣ ሃርደ ዱራይቴና ሀርዳ ቡሶ (ጥንታዊ ባሕላዊ ኩሬዎች) የላቀ ዓለም አቀፍ ቅርስ እንዳላቸው ታምኖ በዩኔስኮ ተመዝግበዋል፡፡
ነፍሱ ይማርና ከኃይለመለኮት አግዘው ጋር
ኮንሶ አምባ መንደር በተደጋጋሚ ለሥራ ስንጓዝ ከሠራዊት ኮንሶ ጋር ዘሪሁን ግርማን አናጣውም ነበር።
የኮንሶ ልጅ፤ ዘሪሁን መምህራን ( እናቱና አባቱ ) መኖሪያ ቤት ከረት ከተማ፣ ኮንሶ ተስተናግደናል። ቤተሰቦቹ ከኮንሶ ወደ አርባምንጭ ተጉዘው መኖር እንደጀመሩ ነግሮኝ ነበር።
ዘሪሁን - ከዚህ በታች የላከልኝ መልዕክት ለአገርና ለሕዝብ አጋርቼለት ነበር።
"ዘሪሁን ግርማ #zerihun Girma ነኝ። የባህል የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ጋዜጠኛ እና አማካሪ ከአስር /10/ አመታት በላይ በሬዲዮ ዘርፍ በዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም፣ በደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 እና በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያን ባህል ቱሪዝም እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍን ሳስተዋውቅ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ኘሮግራሞችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ።
ነገር ግን የብዙ ወዳጆቼ እና የሬዲዮ አድማጮቼ ጥያቄ ያለኝን ልምድ እና ስለኢትዮጵያ በጉዞ ያወኳቸውን በምስል ማሳየት እችል ዘንድ በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንድመጣ ነበር።
ይሁንና ፈጣሪ የፈቀደው ነውና የሚሆነው አሁን ጊዜው ደርሷል።
ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
ውብ ሀገር
በኢሳት ቴሌቪዥን ከቅዳሜ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓም - ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ ይቀርብ ነበር።
ዘርሁን ግርማ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አርበኛ ነበር። በድንገተኝ ሞት አጣነው።
የሀገራችን የሆስፕታሊትና ቱሪዝም አምባሳደር የሆነው ወንድማችን ዘሪሁን ግርማ በድንገተኝ ሞት ተለየን።
ዘሪሁን ግርማ የቱሪዝም ሞተር፣ ተጓዥ ጋዜጠኛ፣ የውብ ሀገሬ ቲሌቪዥን ፕሮግራም መሥራች፣ የቱሪዝም ባለሙያወች ድምፅ ነበር።
#ኮዞባቱ ኾራ አታ ኾንሶ ሰኔ 20-21/2017ዓ.ም በዓል አዘጋጅ ነበር።
ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው፣ በሀገሩ የሚኮራ፣ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ፣ ብዙ የሠራ፤ የታተረ የውብ ሀገር ጋዜጠኛ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አሳዝኖናል።
የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር በጋዜጠኛ ዘሪሁን ህልፈት መግለጫ አውጥቷል።
"...ቱሪዝም ልጇን አጣች፣ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው በሀገሩ የሚኮራው በሬድዮ እና በቲቪ የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ብዙ ለመስራት ብዙ ለመሮጥ ሀገሩን በሰፊው ለማስተዋወቅ የውብ ሀገር ብሎ የጀመረው የማህበራችን መስራች እና አባል ወንድማችን ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አዝነናል"
ዘሪሁን
ከሐያት 49 ወደ አርባምንጭ ከለሊቱ 7:00 ሰዓት አስከሬኑ በክብር ተሸኝቷል።
ዘሪሁን ግርማ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ እግዚአብሔር ያጽናችሁ።
ነፍስ ይማር።

በ202 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
አባት አርበኛና የዕድሜ ባለጸጋ ጋኖ ጋዳቾ በ202 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ጥር 13/2018 ዓ/ም በጮርሶ ወረዳ በቢሻ ቀበሌ ተፈጽሟል።
የአባተ አርቤኛ ጋኖ ጋዳቾ ሰባት ልጆችና 362 የልጅ ልጆች ነበሯቸዉ፡፡፡
በ17ኛ ዓመቱ ማለትም በ1878 የጎጃም ንጉሤ ካዋ ከሞ በነገሰበት ዘመን አቶ ጋኖ ገዴቾ እስከ ጎጃም መዘመታቸው ይነገራል ።
የአባታቸው ውክልና በ 1914 በመውሰድ የይርጋ ጨፌ፣ የወናጎና አከባቢዎች እስከ ያበሎ፣ሀገርማሪያ፤ቡርጅ ፣ኮንሶ፤ጉጂ፣በቦራና በጌዴኦ መካከል የዘመኑን ግብር በማሰባሰብ ለ13 ዓመት ህዝብን ያገለገሉ አርበኛ አባት መሆናቸውን የታሪክ አዋቂዎች ከሟቹ አንድበት መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡
አርበኛ ጋኖ ገዴቾ በአከባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ ያላቸው፣ አስታራቂና መካሪ አባት እንደነበሩ ተጠቅሰዋል፡፡
ስርአተ ቀብሩ የወራዳ አመራሮች የባህል አባቶች ወዳጅ ዘመጆች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በጌዴኦ ባህላዊ ሥርዓተ ቀብራቸው በጮርሶ ወሬዳ ብሻ ቀበሌ ተፈጽሟል፡፡
ጌዴኦ ቴሌቪዥን

6 months ago
የአራት ወር ህፃን ላይ የፈላ ውሃ በመድፋት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን በካራት ከተማ ሚሊኒየም ሰፈር በአቶ ኩሲያ ካላሌ መኖርያ ቤት ግቢ ውስጥ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።
ሊባን ኤርሚያስ የተባለች የ4 ወር ዕድሜ ያላት ህፃን በእናቷ ወይዘሮ ካይሎቴ አማሬ ታቅፋ እያለ ተከሳሽ የፈላ ውሃ በብረት ድስት በማድረግ እናት በታቀፈቻት ልጅ ፣በእናትየው እና በሌላ በ3 ዓመት ከ5 ወር ልጅ ላይ በመድፋት ጉዳት ማድረሷ ተገልፆል፡
በዚህም የአራት ወር እድሜ ያለት ህፃን ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ የ3 ዓመት ከ5 ወር ህፃን እና ወላጅ እናት በህክምና ህይዉታቸው ማትረፍ ተችሏል ሲሉ በኮንሶ ዞን የቀና ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገመቹ ገለገሎ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል በወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 27/1 58/1/ሀ እና 539/1 ጠቅሶ ክስ መሰርቷል፡፡ተከሳሽ የወንጀሉን ድርጊት አምና ተበዳይ ስለምትሰድባትና ስለምታንቋሽሻት ወንጀሉን የፈፀመች መሆኗን ገልፃ ችሎቱም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰማ በኋላ በክስ አንድ በወንጀል ህግ አንቀጽ 58/1/ለ እና 540 ስር እና በክስ 2 እና 3 በወንጄል ህግ አንቀጽ 58/1/ለ እና 555/ሀ እንድትከላከል ብይን ሰጥቷል።
ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ለችሎት የገለፀች በመሆኑ ችሎቱም እንዲትከላከል ብይን በሰጠበት የህግ አንቀጽ ስር ጥፋተኛ በማድረግ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን በኮንሶ ዞን የቀና ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገመቹ ገለገሎ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡#dagu

ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ለችሎት የገለፀች በመሆኑ ችሎቱም እንዲትከላከል ብይን በሰጠበት የህግ አንቀጽ ስር ጥፋተኛ በማድረግ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን በኮንሶ ዞን የቀና ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገመቹ ገለገሎ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

ቱሪስቱን ገንዘብ የጠየቀው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ
ቻይናዩን የሳይክል ተጓዥ መንገድ ላይ አስቁሞ ፓስፖርቱን የጠየቀው ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። ከኮንሶ ወደ ያቤሎ በሳይክል እየቀረጸ እየተጓዘ የነበረ ቻይናዊ ቦረና ዞን ኤልወያ ወረዳ ላይ በሞተር ሳይክል በመከታተል ገንዘብ ሲጠይቁት በቪዲዮ ላይ ይታያል።

ኢጋድ ጋዜጠኞችን ሊሸልም ነው
ከዕዝራ እጅጉ( ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | 3ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ኅዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ።እሁድ ከ10 ሰዓት ጀምሮ የውድድሩ አሸናፊዎች ይታወቃሉ።
በኢትዮጵያ መንግሥትና ኢጋድ ትብብር በተዘጋጀው በዚህ ሽልማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የተሻለ የይዘት ሥራ ያከናወኑ የሚድያ ባለሙያዎች ዕውቅና ያገኛሉ።
የዘንድሮው ሽልማት Story Telling for Climate Action -for a Secure, Resilient and Stable Region በሚል ርዕሰ የሚካሄድ ይሆናል።
ሦስተኛውን የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ የዝግጅት ሂደት አስመልክቶም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው እና በኢትዮጵያ የኢጋድ ተጠሪ አበባው ቢሆነኝ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ የኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶችን ዕውቅና የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በሚዲያ አዋርድ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።
የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።
ውድድሩበቴሌቪዥን፣ሬዲዮ፣ህትመት፣ዲጂታል ሚዲያ እና ሴቶች ዘርፍን ጨምሮ በስምንት ዘርፎች ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል።
400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ናቸው።
ተወዳጅ ሚድያ የኢጋድ የሚድያ አዋርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 3 ዓመት በፊት
በጅቡቲ ሲካሄድ አሸናፊ ከነበሩት የፎቶ ባለሙያዎች አንዱ መስፍን ሰሎሞን ያነጋገረ ሲሆን መስፍን የቦረናን ድርቅ በምስል በማስቀረቱ ነበር ዕውቅናውን ያገኘው።
መስፍን ይህ ዓይነት ውድድር በሙያው እንዲበረታ እንዳገዘው ገልጾ ያገኘው የዋንጫ እና የ1000 ዶላር ሽልማትም ትልቅ ትርጉም እንዳለው ነግሮናል። መስፍን፣ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገለ ባለሙያ ሲሆን ሦስተኛው የኢጋድ የሚድያ አዋርድ ኢትዮጵያ መዘጋጀቱ ለባለሙያዎች አይን ከፋች በመሆን ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብሎናል።
ኮሰን ብርሃኑ የሚዲያ ባለሙያ ሲሆን በዘርፉም ከስምንት አመት በላይ ሠርቷል። በ2007 ዓ.ም የማስተርስ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒሸርሲቲ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት በከፍተኛ ነጥብና የጥናት ውጤት እንደተመረቀ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ተቀላቀለ።
ከድርቅ ጋር ተያይዞ በቦረና፣ በሶማሌ ክልልና ኮንሶ በመገኘት ድርቁ የፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በማሳየት ለችግሩ መንግስትና ህዝብ እንዲረባረብ ያደረጉ ዘገባዎችንም ሰርቷል። በኮንሶ አካባቢ በሰራው የድርቅ ዘገባ በመጀመሪያው የኢጋድ ሚዲያ አዋርድ በመወዳደር አሸንፏል ፤ የእውቅና ሰርተፍኬትና የብር ሽልማት አግኝቶበታል።
የኢጋድ ሽልማት ዋና ዓላማም በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት ማድረግና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ዘንድሮ በሚካሄደው የሽልማት ሥነስርዓት 2000 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እና የአፍሪካ ህብረት የተባባሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች የዓለምአቀፍ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም ጋዜጠኞች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
የኢጋድ ሚድያ ዓመታዊ ሽልማት ከድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጥንስስ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው።አንደኛው ውድድር ጅቡቲ ሁለተኛውን የኢጋድ የሚድያ ሽልማት ደግሞ ኬንያ ማስተናገዳቸው ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ የሚታደሙ የሚድያ ባለሙያዎችን በመጋበዝና የማህበራዊ ሚድያ ዘገባዎችን በማከናወን ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ተግባሩን እየተወጣ ነው። ተወዳጅ ሚድያ እንደሚታወቀው የሚድያ ባለሙያዎችን ሕይወት በአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ (መዝገበ አእምሮ) እያወጣ እንደሆነ ይታወቃል።

7 months ago
የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ አገልግሎት ፕሮጀክት በምስራቅ አፍሪካ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግቦ ተጠናቀቀ
በምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ለመደገፍ “የመሬት፤ የአፈርእና የሰብል መረጃ አገልግሎቶች" የተሰኘው ፕሮጀከት ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በሩዋንዳ ሲሰራበት የቆየውን ቁልፍ ውጤቶችና የተገኙ ልምዶችን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በአውሮፓ ህብረት በዴቨሎፕመንት ስማርት ኢኖቬሽ ስር የሚገኘው የግብርና ምርምር ፕሮግራም፣ በኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በISRIC በጋራ የጎንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ይህ ፕሮጀከት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በሩዋንዳ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።
ይህ ፕሮግራም ዐላማ በሀገራዊ የምርምር ተቋማት ውስጥ ዘላቂነት ያላቸውን የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ ማዕከላትን በማቋቋም ሀገራዊ የግብርና እውቀትና ፈጠራ ሥርዓቶችን በማጠናከር ላይ ነው። እነዚህ የመረጃ ማዕከላት ባለፉት አራት ዓመታት የተሰበሰበው መረጃ በማቀናበርና በማስተሳሰር፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን የሚያጎለብቱ ሲሆን መረጃው ለባለድርሻ አካላት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆን ያስችላሉ።
የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ ማዕከላቱ የተነደፉት በአገር አቀፍ፣ በክልልና በአካባቢ ደረጃ ያሉ የግብርና ባለድርሻ አካላትን ለማገልገል ሲሆን፣ የአየር ንብረት ተስማሚ የግብርና ልምዶችን ለመደገፍ፣ የገጠር ለውጥን ለማስፋፋት እንዲሁም የምግብ ሥርዓት ጥንካሬን ለማጠናከር የተቀናጀ መረጃን ያቀርባሉ ተብሏል።
"የፈጠርናቸው አጋርነቶች፣ ያስተዋወቅናቸው ፈጠራዎች እና ያካፈልነው ዕውቀት ሊቀጥሉ የሚገባቸው መልካም ሁኔታዎች ናቸው። ለሁሉም የገንዘብ ደጋፊዎች እና ለሀገር ውስጥ አጋሮቻችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ።" ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አበራ ደሬሳ ናቸው፡፡
የአምስት ዓመት የሥራ መርሃግብር በሶስት ብሔራዊ የግብርና ምርምር ተቋማት ውስጥ የመሬት፣ የአፈር እና የሰብል መረጃን የሚያቀናጁ ማዕከላትን በተሳካ ሁኔታ ገንብቶ አስፍሯል — እነዚህም የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የኬንያ ግብርናና እንስሳት እርባታ ምርምር ድርጅት እና የሩዋንዳ ግብርናና የእንስሳት ሀብት ልማት ቦርድ (በሶስቱ አጋር ሀገራት ውስጥ ይገኛሉ።
ቁልፍ የፕሮጀከቱ ውጤቶች:
. ማዕከል ማቋቋም: የተበታተነውን የምርምር መረጃ ወደ አንድ ለማሰባሰብ እና ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ የተቀናጁ የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ ማዕከላት ተዘርግተዋል።
አቅም ግንባታ: ልዩ ሥልጠና በመስጠት የአካባቢው ሠራተኞች እነዚህን ውስብስብ የሆኑ የመረጃ ሥርዓቶች በራሳቸው የማስተዳደር እና የማስቀጠል ሙሉ ብቃት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በተጠቃሚዎች ላይ የተገኘው ለውጥ: የመሬት አስተዳደርን ለማሻሻል እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚስማማ ግብርናን ለመተግበር እንዲቻል መረጃውን መጠቀም የሚችሉ የመጨረሻ ተጠቃሚዎችን፣ የአገር ውስጥ ገበሬዎችን ጨምሮ፣ በማሳተፍ ሥልጠና ተሰጥቷል፡።
"የቴክኒክ እና የአደረጃጀት ውጤቶቹ ሙሉ በሙሉ በብሔራዊ የምርምር ተቋማት እጅ ገብተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ፣ የእነዚህ መረጃ ሥርዓቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ ነው” ሲሉ NISRIC ከፍተኛ ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አንድሬ ኮይማን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ የተተገበረው በዋገንገን ዩኒቨርሲቲ እና ምርምር በሚመራውና ከISRIC፣ ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምርተቋም ፤ ከኬንያ ግብርና እና እንስሳት ምርምር ድርጅት ፡ ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ፣ ከሩዋንዳ ግብርናና እንስሳት ሀብት ልማት ቦርድ ፣ ከዓለም አግሮፎረስትሪ ፣ ከዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት (እና ከጀርመን ኤሮስፔስ ማዕከል ጋር በመተባበር በሚሰራ ኮንሶርሺየም ነው።
የመሬት፣ የአፈርና የሰብል መረጃ አገልግሎቶች ህብረት በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ብሔራዊ የግብርና እውቀት እና ፈጠራ ሥርዓቶች ውጤታማነትን ለማሳደግ የወሰኑ መሪ ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ የምርምር ድርጅቶች ጥምረት ነው፡፡
በአውሮፓ ህብረት እና በኔዘርላንድስ በጋራ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ይህ ፕሮጀከት የገጠር ለውጥን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚስማማ ግብርናን ለመደገፍ ዘላቂነት ያላቸውንና ለሁሉም ክፍት የሆኑ ዲጂታል መረጃ ማዕከላትን በማልማት፣ በመሞከር እና በማስተላለፍ ላይ ያተኩራል ተብሏል።

8 months ago
የግሌዘር ቤተሰቦች ዩናይትድን ሊሸጡ ይችላሉ !
#ethiopia | የማንችስተር ዩናይትድ ከፍተኛ ድርሻ ባለቤት የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ማንችስተር ዩናይትድን ሊሸጡ እንደሚችሉ ተገልጿል።
የግሌዘር ቤተሰቦች የተሻለ ገንዘብ ለማግኘት ከ 2027 በፊት ማንችስተር ዩናይትድን ለመሸጥ ሊያስቡ እንደሚችሉ ተነግሯል።
የግሌዘር ቤተሰቦች ከሰር ጂም ራትክሊፍ ጋር ባላቸው ስምምነት መሰረት ከ 2027 በኋላ ከሸጡ የተሻለ ገንዘብ ማግኘት አይችሉም።
ከ የካቲት 2027 በኋላ ክለቡ ባለበት እዳ እና በሚኖረው የማርኬት ለውጥ ምክንያት የሚያገኙትን ገንዘብ ያሳንሰዋል ተብሏል።
ዩናይትድን ማን ሊገዛው ይችላል ?
ማንችስተር ዩናይትድን ይገዛሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል ኳታራዊው ሼህ ጃሲም ቢን ሀማድ አል ታሃኒ አንዱ ናቸው።
የኳታር ባንክ ሊቀመንበር ሼህ ጃሲም ከዚህ በፊት ክለቡን ለመግዛት ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንዳልተሳካላቸው አይዘነጋም።
በተጨማሪም የዩናይትድ አረብ ኤምሬትሱ ኮንሶርሽያ እና የሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች ለመግዛት ይንቀሳቀሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#ts #sport #gtmc

በቺሊ በስህተት የወር ደሞዙ 330 እጥፍ የገባለት ሰራተኛ ስራ ለቀቀ
አንድ ሰራተኛ በስህተት የወር ደሞዙን 330 እጥፍ የሚያህል ገንዘብ ወደ ሂሳቡ ገብቶለታል። እሱም ወዲያውኑ ስራውን ለቆ የኃላፊውን የስልክ ጥሪዎች መመለስ አቆመ። በኋላም ቀጣሪው ገንዘቡን ለማስመለስ ፍርድ ቤት ሲሄድ፣ ፍርድ ቤቱ ለሰራተኛው ወሰነ።
ክስተቱ የተፈጸመው በቺሊ ሲሆን፣ በግንቦት 2022 በደመወዝ ክፍያ ላይ በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ወደ ሰራተኛው የባንክ ሂሳብ በግምት የ127 ሺህ ፓውንድ ተቀማጭ ተደርጓል።
ነገር ግን፣ በዳን ኮንሶርሲዮ ኢንዱስትሪያል ደ አሊሜንቶስ ደ ቺሊ በሚባለው የምግብ አምራች ድርጅት ውስጥ የአስተዳደር ረዳት የነበረው ወርሃዊ ደሞዙ 386 ፓውንድ ብቻ ነበር።
መጀመሪያ ላይ ሰውየው ሙሉውን ገንዘብ እንደሚመልስ ለኩባንያው አረጋግጦ ነበር። ሆኖም፣ ከሶስት ቀናት በኋላ ስራውን ለቀቀ።
ኩባንያውም በኋላ በስርቆት ወንጀል ከሰሰው።
ከሶስት ዓመታት የህግ ሂደት በኋላ፣ ዳኛው ክስተቱ ስርቆት ሳይሆን ያልተፈቀደ ደረሰኝ መሆኑን በመወሰን የወንጀል ክስ ተብሎ መታየት የለበትም የሚል ውሳኔ አስተላለፉ።
ፍርድ ቤቱ ሰውየውን ከወንጀል ክስ ነፃ ቢያደርገውም፣ ኩባንያው ገንዘቡን በሲቪል ፍርድ ቤት በኩል ለማስመለስ መሞከሩን እንደሚቀጥል ተናግሯል።
ኩባንያው ለዲያሪዮ ፊናንሲየሮ ለተባለው ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ፣ “ይህንን ውሳኔ ለማስመለስ (ለመከለስ) ሁሉንም ህጋዊ እርምጃዎች እንወስዳለን” ብሏል።

የአዲስ አበባን ሙት ወንዞች “መዘዘኛም” – “ገላግሌም” ይሏቸዋል፡፡
‘እዳ’ እንጂ ‘እሴት’ ያልሆኑትን የውሃ ገጾች ወደ ተፈጥሮ ማንነታቸው እንደሚመለሱ በፕሮጀክቱ ታቅዷል። Back to their Origin
====================
(ተቀናበረ: በጋዜጠኛና የሕብረተሰብ ጤናሻምፒዮን አምባሳደር እሸቱ ገለቱ)
-----------+
Rivers back to their Origin ማለት ነው። የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ወንዞች "ሙት" ናቸው።
‘እዳ እንጂ እሴት ሆነው አልቆዩም’፡፡ ኑሮ በደከመባቸው የአዲስ አበባ ሰፈሮች እነኚህ የተዘነጉ ወንዞችን “ገላግሌ” ይሏቸዋል፤ የተነወረ አቋራጭ አማራጭ ቢሆንም የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን ነዋሪው በዘፈቀደ ይጥልባቸዋል፡፡
ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ግቡ የሞት ቀጣና የሆኑትን የውሃ ገጾች ከብክለት ወደ ተፈጥሮ ማንነታቸው መመለስ (Back to origin) ነው፡፡
በዚህም ንፁህና ውብ ድባብን መፍጠርና በከተሞቹ ውስጥ በሙት ወንዞቹ መዘዝ መለያየቱን እንደ ድልድይ ሆነው መቀራረብን (Connectivity) መፍጠር ነው፡፡
የወንዝ ዳር ልማቱ ከተማዋ በዋና ቀዶ ሕክምና አልፋ ዳግም ተውባ ከትንሳኤዋ የምትገናኝበት (It's a Major City Surgery) ነው ተብሎለታል፡፡
አንዳንዶቹ እንደውም ለስም እንጂ የወንዝነትን ባህሪም አያሟሉም፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ አመቱን ሙሉ በቋታቸው ውሃ ዝር የሚልባቸው ስላይደሉ፡፡
ይሁንና በዙሪያቸው አይደለም ቁጭ ተብሎ ሊታረፍባቸው ቀርቶ፣ በአጠገባቸው ሲታለፍ እንኳ አፍንጫ የሚሰነፍጥ ሽታ መመንጫ ሆነዋል፡፡
ይህ ከሀገራዊው የቆሻሻ አወጋገድ አለመሰልጠን ጋር ተያይዞ ሙት የሆኑት የውሃ ገጾቹ ለነዋሪውም የዘርፈ ብዙ እዳ መዘዝ ሆነው ዘልቀዋል፡፡
ጉንፋንና አስም አለርጂን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት ላይ ከሚያሳድሩት የጤና ችግሮች ባሻገር ሌሎች የውሃ ወለድ የሆድና ቆዳ አጥቂ በሽታዎችም እንዲባባሱ ምንጮች ሆነዋል፡፡
ወደ ውሃ ገጹ የሚለቀቁት መርዛማ ኬሚካሎች፣ የሽንት ቤቶች ፍሳሾች፣ የእንስሳት በድን የሚጣልባቸው፣ በአጠቃላይ ከየማዕዘናቱ ወደውሃ ገጹ መአት ግሳንግስ ቆሻሻዎች ይጣሉበታል፡፡
የተፋሰሱ መስመሮች በአግባቡ ባለመያዛቸውም ጭር ያሉ አስፈሪ ስፍራዎች ናቸው፡፡ አሮጌ ቄራና እሪ በከንቱን ለአብነት ብናነሳ የዝርፊያ፣ የማጅራት መምቻና የሴቶች ጥቃት የሚፈፀምባቸው የሰዎች ደህንነት ስጋቶችም ሆነው ቆይተዋል፡፡
ሌላው በክረምት ዝናብን ተከትሎ ጎርፍ ተንደርድሮ የሚያልፍባቸው መሆኑ በተፋሰሱ አጠገብ ቤቶች እየተናዱ በየአመቱ የሞት ቀጣናም መሆኑ ሌላው የአዲስ አበባ ክፉ ገጽ ሆኖ ይታወቃል፡፡
የከተማዋ የማይሟሙና በአፈርም የማይበሰብሱ ፕላስቲኮች ጎማዎችም የሚሞጀርባቸውና ከመርዘኛ ኬሚካሎች ጋር ተዳምሮ ከወንዞቹ ውሃን ያሉ የቤት እንስሳትም ፌስታልና ፕላስቲክ አብረው እየዋጡ የሚሞቱበትም ሆነዋል፡፡
ለሕብረተሰብ ጤና ማበልፀግና ጤና ኮምዩኒኬሽን ባለኝ ልምድ መሰረት የወንዝ ዳር ልማቱ የጤና ፋይዳውን ጨምሮ የሚያሳድረውን ከላይ የተዘረዘሩትን ዘግናኝ ደረቅ መራር ሀቆችን የሚቀይር መሆኑን በቅርቡ ጉብኝቴ መገንዘብ ችያለሁ፡፡
ታላቅ ፋይዳ ቢኖረውም በጠቀሜታው ልክ ግን የተዘመረለት አልመሰለኝም፤ ልብንና ቀልብ የማይገዙ የፖለቲካዊ መሪ ቃል እየተለጠፈባቸው የሚቀርቡት ገለጻዎች በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ታላቅ ጠቀሜታ ሳያደበዝዘው አልቀረም፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ መድህን ሊሆን የሚችል ልማትን፤ ለምን በፖለቲካ ቅብ ቅኝት አይቼ ማህበረ - ኢኮኖሚያዊና የውበት ጥበብ ገጾቹን ለምን አወሳስበዋለሁ አስብሎኛል፡፡
የፖለቲካው አስተዳደር ከዚህ ስራ ጋር ግን ሞገሱን ይውሰድ የሚያስብለው ነጥብ አጠቃላይ የከተማዋን መልክዐ ምድርና የተፋሰሱን ባህሪ አገናዝቦ ሁሉን ባቀናጀ የአካቶ ጥያቄ አመላለስ ዘይቤ በምልዑ ሁኔታ (Integrated approach & Comprehensive design) የፕሮጀክት ሳይቱ መደዘኑ ነው፡፡
ከፖለቲካው አውድ አርቄውና ከውዳሴ ከንቱ መነጽር ውጪ ልየው ያስባለኝም የልማት ፋይዳው በላሽቶ የቆየ አያያዝን ማርሽን 360 ዲግሪ ማርሽ የሚቀይር መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡
የወንዝ ዳሩ ልማት አሁን ላይ ይሸፍናል ተብሎ ከተነገረለት 42 ኪሎ ሜትር መካከል 23ቱን ኪሎ ሜትር ርዝመት በሸፈነው መልክዓ ምድር ላይ የተሰራውን ድንቅ ስራ ዞሬ መቃኘቴ ነው፡፡
አዲስ አበባ በማህፀኗ ያቀፈቻቸው ወንዞቿና ገባሮቻቸው ከነተፋሰሳቸው ቀኑን ሙሉ አልበቃ ብሎ ዞረን ማየት የቻልነው ከፊል ገጹን ነው፡፡
አንድ የተረዳሁት ነገር በምን ያህል ደረጃ የወንዞቹ ተፋሰስ የአዲስ አበባን ክፍለ ከተሞች በሙሉ አስተሳስሮና አቆራኝቶ የሚያገናኝ መሆኑን ነው፡፡
በወንዝ ዳር ልማቱ በዝርዝር ከጎበኘኋቸው መካከል የወንዝ መጠበቂያ የአረንጓዴ ገጽና የጋቢዮን ግንብ፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች፣ የመተላለፊያ መንገድና ድልድዮችን የመሰሉ መሰረተ ልማቶች፣ የወንዞቹን ውሃ ማከሚያ ቋት ተቋማትንና የቢዝነስ ማዕከላትን ካተተና በዳርቻዎቹ አቅራቢያ የተፈናቀሉት በጋራ መልሶ ግንባታ እንዲሰፍሩ ማመቻቸትም (repurposed housing) ይጠቀሳል፡፡
የወንዝ ዳር ልማቱ መልክዓ ምድር በተቻለ መጠን ከእንጦጦ ፓርኩ ጋር እንዲናበብ፣ እስከ ፒኮክ መናፈሻ ድረስ ሲዘልቅም ዲዛየኖቹ ከአካባቢው ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ፣ እንደ ኮንሶ ባህላዊ የዳገት እርከን ልምድንም እንዲያዋድዱ፣ የወንዝ ውሃ ማጣሪያ ነጥብን እንዲያካትት፣ በአንዳንድ ቦታ ውሃ ፍሰት ጠብቆ እንዲወርድ አስቻይ የውሃ መከተሪያ (Check dam) እንዲኖር ተደርጓል፡፡
እንደ መዝናኛም አማራጭ ከወንዙ ዳርቻው እልፍ ብለው በተገኙ ትርፍ ሳብ ያሉ መሬቶችም ላይ የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችንና አነስተኛ እጥር ስታዲየምን ማዘጋጀት፣ በዙሪያው ካፌ፣ ወንዙም ላይ ተወዛዋዥ የቡና መጠጫ ልዩ ቤቶችና የወንዝ ዳር ሙዚየም እየተሰራ ነው፡፡
በድምሩም 21 የውሃ ማጣሪያና ማከሚያ ኩሬዎች፣ አገናኝ ድልድዮች እና ኮሪደሮች የተገነቡ ሲሆን የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችና የታክሲ መጫኛና ማውረጃ መናኸሪያዎች፣ በእግር ሽርሽር የሚባልባቸው መረማመጃዎችም አብረው እንደተሰሩ በጉብኝታችን ታዝበናል፡፡
ቀጨኔ፣ ቡልቡላ፣ ቀበና፣ አምባሳደር፣ እሪ በከንቱ፣ ጎርደሜ እያልን ከአዲስ አበባ የተለያዩ ማዕዘናት የሚመነጩ ወንዞችን መጥቀስ ሲቻል፣ ያየነው የወንዝ ዳር ልማት ሽፋንም 1 ሺህ 37 ሄክታር እንደሚደርስ የተሰጠን መግለጫ ያመለክታል፡፡
ለወጣቶች ትኩረት ሰጥቷል በተባለው የልማት ስራው 18 ሺህ ያህል የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት አባላት በግንባታ ኮንትራቱ ስራ መሳተፋቸው ይነገራል፡፡
በትይዩ ከስራው ይልቅ አጋጣሚውን ለግል ጥቅም ተጠቅመዋል የተባሉም ከ40 በላይ አመራሮች መባረራቸውንና ከ45 በላይ ኮንትራክተሮችም ውል ባለማክበራቸው መሰናበታቸው ተጠቅሷል፡፡
ፕሮጄክቱ የዛሬ 5 አመት እንደተጀመረ፤ግን ያኔ በውጭ ድጋፍ ከእንጦጦ እስከ አቃቂ ያለው መልክዐ ምድር ተካቶ የወንዝ ዳሩ ልማት ሲወጠን ከ10 አመት በላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

9 months ago
በወላይታ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ከኮንሶ ወደ ሞጆ በሬ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኤፍኤስአር የጭነት ተሽከርካሪ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ ሜንታ ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው በወረዳው ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ሌሊት 7፡30 ገደማ ሲሆን፥ የአሽከርካሪውና የረዳቱ ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡
በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ 17 በሬዎች በሙሉ መሞታቸውን ገልጸው፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ነው ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ የገለጹት።
Seledadotio

በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ
ከኮንሶ ወደ ሞጆ በሬ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኤፍኤስአር የጭነት ተሽከርካሪ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ ሜንታ ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው በወረዳው ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ሌሊት 7፡30 ገደማ ሲሆን፥ የአሽከርካሪውና የረዳቱ ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡
በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ 17 በሬዎች በሙሉ መሞታቸውን ገልጸው፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ነው ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ የገለጹት።
FMC

11 months ago
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ
#ethiopia I 58ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት መደበኛ ጉባኤ ሞጆ በሚገኘው የኮንሶላታ አባቶች ገዳም የሱባኤ ማዕከል ከሀምሌ 1 እስከ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ጉባኤው ሐዋርያዊ መልዕክት በማስተላለፍ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ተጠናቋል።
በጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉት ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ረዳት ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ መርሃክርስቶስ የሀዋሳ ሀገረስብከት ጳጳስ ከቀድሞ ጳጳሳት (በጡረታ ላይ የሚገኙ) ጋር በበርካታ ብፁዓን ጳጳሳት ተሳታፊነት የተካሄደው ጉባኤ በወቅታዊ ሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት ጉባኤው ላይ መገኘት ካልቻሉት ከብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ በስተቀር የ12ቱ ሀገረስብከቶች ጳጳሳት ተገኝተዋል።
በጉባኤው አዲስ የተሾሙት የቅድስት መንበር ሊቀጳጳስ ብሪያን ኡዳግዌ በመገኘት የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮን 14ኛን የአብሮነት መልዕክት ለብፁዓን ጳጳሳት አስተላልፈዋል።
ሊቀጳጳስ ብሪያን ወደኢትዮጵያ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ በጋራ ለመስራት ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል።
የቤተክርስቲያንን ኃላፊነትን ለመጋራት፣ ለተግዳሮቶች አዳዲስ የመፍትሔ ሀሳብ ለመስጠትና ለዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች አዳዲስ ጳጳስት መሾም ጉባኤውን የበለጠ እንደሚያጠክረው የገለጹልን የጳጳሳት ጉባኤ የተግባቦት እና ህዝብ ግንኙነት ተወካይ እና የባህር ዳር ደሴ ሀገረስብከት ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ናቸው።
ጉባኤው በተለያዩ የቤተክርስቲያን ተልዕኮ፣ መዋቅር፣ ተቋማት፣ ስብከተ ወንጌል፣ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መወያየቱን አክለው ገልጸዋል። እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን ያማከሉ ውሳኔዎች እና ምክሮችን ማሳለፍ ችሏል።
ቤተክርስቲያን እንደእናት ልጆቿ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የዘወትር ምኞቷ እና ጭንቀቷ መሆኑን የገለጹት ብፁዓን ጳጳሳት ሀገራችን ባለችበት አሁናዊ ሁኔታ ግን ከምንግዜውም በበለጠ አንድ በመሆን ድምጻችን እንዲሰማ እንሻለን ብለዋል።
ለዚሁም ማሳያ ይሆን ዘንድ ሐዋርያት ተጨንቀው በር ዘግተው በነበሩበት ወቅት ክርስቶስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” እንዳለው፤ ብፁዓን ጳጳሳትም ይሄንኑ በሐዋርያዊ መልዕክታቸው ገልጸዋል።
በመልዕክታቸውም ሁሉም የእግዚአብሔር ቤተሰብ ለሰላም ሊጸልይ፣ ሊጾም እና ሊሰራ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአንድ አባት ጥላ ስር ሆና 23 ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩ የተለያዩ የሊጡርጊያ አይነት ያላቸው ቤተክርስቲያናት ባለሀብት ናት።
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የምስራቅ እና የላቲን ሥርዓቶች የሚተገበሩ ሲሆን ከ13ቱ ሰበካዎች ዘጠኙ በላቲን ሥርዓት ቀሪ አራቱ ደግሞ በምስራቅ ሥርዓት የሚተዳደሩ ናቸው።
ብፁዓን ጳጳሳት በኢትዮጵያ ስለሚተገበሩ የሉጡርጊያ አይነቶች የተወያዩ ሲሆን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የሚጠበቁት በቅድስት መንበር የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ክላውዲዮ ጉጁሬቲ ጋር ስለሚኖራቸው ቆይታ ተወያይተዋል።
የቤተክርስቲያን ዋና ተልዕኮ የሆነው የሐዋርያዊ አገልግሎት በጠቅላይ ጽ/ቤት በተሻለ መንገድ ለማጠናከር በአዲስ መልኩ ለመስራት የታሰበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ዘርፉን የሚያሰተባብሩ ብቁ የሆኑ ካህንም በቅርቡ ለመምረጥ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸው በሲኖዶሳዊ አብሮ የመጓዝ መንፈስ ከምዕመናን ጋር ስብከተ ወንጌል መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።
የቤተክርስቲያን ተቋማት የሆኑት የጤና ጣቢያዎች፣ የትምህርት ተቋማት እና የካቶሊክ ጽህፈትቤቶቻችን አስተዳደራዊ እና የአፈጻጸም ጉዳዮች ላይ በሰፊው በመመካከር በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምክረ ሀሳቦች እና ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።
ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤያቸው መደምደሚያ በሞጆ በሚገኘው የኮንሶላታ አባቶች ገዳም የሱባኤ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂደዋል። “ውዳሴ ለአንተ” (ላውዳቶ ሲ) የተሰኘው የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ የጻፉት ሐዋርያዊ ማነቃቂያ መሰረት በየአመቱ በጉባኤያቸው ማጠናቀቂያ የሚያድርጉት የችግኝ ተከላ መርሃግብር በዘንድሮ በተለየ ሁኔታ ከህፃናት፣ ከምዕመናን እና ከገዳማውያን ጋር በህብረት ተክለዋል።
በመርሃግብሩ ብፁዓን ጳጳሳት በህፃናት ዝማሬ ታጅበው ምድርን መንከባከብ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን በማስተማር ልዩ ቆይታ አድርገዋል። ህፃናቱም ችግኞቹን ከጳጳሳት ጋር በመትከላቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።

58ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
#ethiopia I የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 58ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን ሞጆ በሚገኘው የኮንሶላታ ልዑካን የሱባኤ ማዕከል ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምረዋል።
ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤው አጀንዳቸው የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ በማተኮር ሐዋርያዊ እና ማህበራዊ ልማት አገልግሎቶች፣ ወቅታዊ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ሌሎችም የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመመወያየት አቀጣጫ እና መመሪያዎችን እንደሚሰጡ የጉባኤው ጠቅላይ ጸኃፊ ክቡር አባ ከተማ አስፋው ገልጸዋል።
ጉባኤው እስከ ሀምሌ 4 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል