16 days ago
በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይፋዊ የዲጂታል ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነው
📌ተቋማቱ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
#ethiopia | በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ይፋዊ የገቢ ማሰባሰቢያ የመክፈቻ ፕሮግራም በቅርቡ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ሁለቱ ተቋማትም አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በይፋ ተፈራርመዋል።
ይህ ልዩ መርሃ-ግብር ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ግልጽነት ባለው እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደገፉ ዲጂታል የለጋሽነት መፍትሄዎች አማካኝነት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰብአዊ እና ማህበረሰባዊ እገዛዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ያለመ ስትራቴጂካዊ የገቢ ማሰባሰብ አጋርነት መጀመሩን አብስረዋል።
በዕለቱም አይራብ ዶኔሽን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ለጋሾች በቴሌብር ሱፐር አፕ እና በአይራብ ዶኔሽን ድረ-ገጽ አማካኝነት በቀላሉና በአስተማማኝ ሁኔታ መዋጮ ማድረግ የሚችሉበትን ምቹ ዲጂታል አሰራር በጉልህ የሚያሳይ ይሆናል።
የአይራብ ቴክ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (AYRAB TECH SOLUTION PLC) መስራች አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እና የጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር መሌቻ ሎጄ ህዝቡ እና የሚመለከተው አካል ሁሉ በዚህ ሰብአዊ ስራ ላይ ከጎናቸው እንዲሆንና አጋርነቱን እንዲያጠናክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጃታኒ አሊ ፋውንዴሽን በአርቆ አሳቢው ሻለቃ ጃታኒ አሊ ማስታወሻነት የተመሰረተ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ ራሱን እንዲችል፣ ጠንካራ የሆነ ማህበረሰብ እንዲገነባ እና ዘላቂ ልማት እንዲፈጠር በትምህርት፣ በውሃ፣ በጤና እና በማህበረሰብ አቅም ግንባታ ላይ በትጋት እየሰራ ነው።
ዛሬ የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚና በተለያዩ ሀገር የሃላፊነት ቦታዎች የሚያገለግሉ ብዙ ግለሰቦች ሻለቃ ጃታኒ አሊ በተቋቋመው ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ይህም የፋውንዴሽኑ ትውልድ የሚቀይር ራዕይ ህያው ማስረጃ ነው።
የእርስዎ ድጋፍ አንድ ልጅ እንዲማር፣ አንድ ቤተሰብ ተስፋ እንዲያገኝ እና አንድ ማህበረሰብ በራሱ እግር እንዲቆም ያግዛል።
ዛሬ ይቀላቀሉ ፣ ይደግፉ ፣ዘላቂ ለውጥ ይፍጠሩ። ሲሉ ጥሪያቸውንም አስተላልፈዋል።
እንዲሁም: በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ በሚገኘው አይራብ(AYRAB) አፕ ላይ እና በአይራብ ዶኔሽን ( https://donate.ayrabtech.c... ) ሊንክ በመግባት በቀላሉ በሃገር ውስጥም ይሁን ከሃገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮዽያ ወዳጆች በቀላሉ የፈለጉትን እና የቻሉትን ያህል መለገስ የሚችሉ መሆኑን አሳውቀዋል።
ይህንን ትልቅ ሰብአዊ እቅድ በይፋ ለመጀመር በሚሰናዳው በዚሁ ደማቅ መርሃ-ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የቢዝነስ መሪዎች፣ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ የኢትዮጵያ ስብዕናዎች እና ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia #ayrabdonation #jatanialifoundation #digitalfundraising #techforgood #humanitarianaid #telebirr #addisababa #socialimpact #ethiopiannews

1 month ago
"አግዙት አግዙት፤ አለበለዚያ እኔ አሳክመዋለሁ!"
#ethiopia | ድጋፋችን ለበረከት በቀለ (ፍልፍሉ)፦ የሳቅ ምንጫችንን በጋራ እናግዘው
የብዙዎቻችንን ቤት በሳቅና በደስታ ሲሞላ የቆየው ተወዳጁ ኮሜዲያን በረከት በቀለ (ፍልፍሉ) ባጋጠመው ድንገተኛ የጤና እክል (ስትሮክ) ምክንያት የሁላችንንም ድጋፍና ጸሎት ይሻል።
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ (የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)፦ "አግዙት አግዙት፤ አለበለዚያ እኔ አሳክመዋለሁ!" በማለት አስተላልፈዋል።
በረከት አሁን ካለበት የጤና እክል አገግሞ ወደ ስራውና ወደ መድረኩ እንዲመለስ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በቴሌብር የቻልነውን ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንቁም።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት፦
1000374461315
በረከት በቀለ
ቴሌብር
+251920659123
በረከት "... ቤቴ ገብቼ እያገገምኩ ነው። ...በቅርቡ ሥራዬ ላይ እንገናኛለን።
🙏 ምስጋናዬ ከልብ ይድረሳቸው
መላው በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን
አክሰን የስትሮክ እና የጀርባ አጥንት ማዕከል
(Axon Stroke and Spine Center)
አባይ ቴሌቪዥን
ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ (የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)፦
መምህር የማርያምወርቅ ተሻገር
አዶናይ ማዳ
ሠሎሞን ከበረ (ታምኮን ሶልሽን) ሌሎችም ... ከልብ ❤ አመሰግናለሁ።
ጸሎታችሁና ድጋፋችሁ አይለየው።
#getu #bereketbekele #filfilu #supportfilfilu #ethiopiancomedy #humanitarianaid #staystrong #በረከትበቀለ #ፍልፍሉ #አፋልጉኝ #ድጋፍ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago
አስቸኳይ የእርዳታ ተማጽኖ
ለጀግናው ብስክሌተኛ ሀይላይ አርአያ ደራሽ እንሁን! 🚴♂️🙏
#ethiopia | ሀገሩን በብስክሌት ስፖርት ለብዙ ዓመታት በክብር ያስጠራው፣ በፅናቱ ለብዙዎች አርአያ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል ሀይላይ አርአያ፣ በአሁኑ ሰዓት በከባድ የጤና ችግር ምክንያት በሆስፒታል አልጋ ላይ ይገኛል።
ከዚህ በፊት ታክሞ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ህመሙ በአጣዳፊ ሁኔታ በማገርሸቱ ጀግናው የእያንዳንዳችንን ድጋፍ ይፈልጋል።
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
(CBE)፦ 1000365329854
ሀይላይ አርአያ ገ/ማርያም
(HAILAY ARAYA G/MARIAM)
ለተጨማሪ መረጃ
+251-915-815264
"ጀግና ሲወድቅ አይታይም" የሚለውን አባባል በተግባር ቀይረን፣ ይህን ጀግና በጋራ እናንሳው።
ዛሬ የምናደርገው ትንሽ ድጋፍ ለሀይላይ የነገ ህይወቱ ትንሳኤ ነው።
እባካችሁ ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን።
#getu #helphailayaraya #ethiopianhero #cyclingethiopia #humanitarianaid #sportscommunity #addisababa #ethiopia #supportourheroes #ርዳታ #ለሀይላይአርአያ #ጀግናሲወድቅአይታይም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ለታዳጊ በእምነት እሱባለው ደራሽ እንሁን! 🙏
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሥር በሚገኘው የአዲስ ሕይወት ትምህርት ቤት የ5ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው በእምነት እሱባለው፣ ባጋጠማት ድንገተኛ የአንጎል ደም ስር መበጠስና የደም መርጋት ምክንያት በከባድ ሕመም ላይ ትገኛለች።
ወላጅ እናቷ ወይዘሮ የዝና አያሌው ሕክምናውን በግላቸው ለመሸፈን ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው፣ ለልጃቸው ሕይወት መዳን የእናንተን እርዳታና ጸሎት ይሻሉ።
💰 እርዳታ ለማድረግ፦
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000635435325 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የአካውንቱ ስም፦ የዝና አያሌው (Yezina Ayalew)
ለተጨማሪ መረጃ፦ 0920515114 (በለካዱ ኤርጋቡስ ለሜሳ)
"ዛሬ ለታዳጊ በእምነት የምናደርገው ጥቂት እርዳታ፣ ነገ ለእሷ ትልቅ ተስፋና ትንሳኤ ይሆናል።"
እባካችሁ ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን። በዓሉ የደስታና የፈውስ ይሁንልን!
#getu #humanitarianaid #helpbeemnet #addisababa #ethiopia #healthappeal #unityforlife #charityethiopia #እርዳታ #ለበእምነትእሱባለው #ኢትዮጵያ #ሰብዓዊነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የልብ ሕሙማን ሕፃናት ተስፋ
170 ሕፃናት በ45 ቀናት ውስጥ ነፃ ሕክምና ሊያገኙ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ በልብ ሕመም ሳቢያ በሕክምና ወረፋ ላይ ላሉና ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ሕፃናት ትልቅ የምስራች ተሰምቷል።
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ (Heart to Heart Children's Aid) ፋውንዴሽን "በኢትዮጵያውያን የልብ ሐኪሞች - ለኢትዮጵያውያን ሕጻናት ልብ ጤና!!" በሚል መሪ ቃል፣ 170 ሕፃናትን በ45 ቀናት ውስጥ ለማከም የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት መጋቢት 20/2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ፈጽሟል።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሕክምናው ከሚያዝያ 12/2018 (April 20) ጀምሮ ባሉት 45 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ለሕፃናቱ ይደርሳል።
በስምምነቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር፣ የጥቁር አንበሳና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች፣ የኢትዮ ኢስታንቡል፣ ጣዝማና ኤሊዘር የልብ ሕክምና ማዕከላት እንዲሁም የዘርፉ ማህበራት በጋራ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ (የፋውንዴሽኑ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ) እንደገለጹት፣ ፋውንዴሽኑ አስፈላጊውን የሕክምና ግብዓትና ወጪ በመሸፈን ተልዕኮውን ይመራል።
ከጣልያን አገር የሚመጣ የሕክምና ቡድንም የዚሁ ጥረት አካል ሲሆን፣ ለ50 ሕፃናት ሕክምና ይሰጣል።
ይህ ትብብር በሕክምና ወረፋ ብዛት ሕይወታቸው የሚያልፍ ሕፃናትን ለመታደግ ከመጣጣሩም በላይ፣ የሀገር ውስጥ የሕክምና ባለሙያዎችና ተቋማት ተቀናጅተው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው።
#getu #hearttoheart #childrenshealth #cardiacsurgery #ethiopiahealth #humanitarianaid #ethioistanbulhospital #ministryofhealth #savinglives #addisababa #የልብሕክምና #ሕፃናት #በጎአድራጎት #ጤና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

"አቅማችን ተሟጧል!"
— ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበች
#ethiopia | ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የመንግስት አቅም እየተሟጠጠ መሆኑን በይፋ አስታወቀች።
በተለይ በትምህርትና በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች በስደተኞች ቁጥር መጨመር ምክንያት ከፍተኛ ጫና ወድቆባቸዋል።
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋዓብ ክበበው በተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የሀገሪቱን ስጋት በዝርዝር አቅርበዋል።
ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ እና ስደተኞች በሚገኙባቸው አካባቢዎች በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ ተጠይቋል።
ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ፣ ለስደቱ መሠረት የሆኑ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ አምባሳደሩ አሳስበዋል።
#ethiopia #refugees #humanitarianaid #unhcr #geneva #addisadmas #breakingnews #globalcall #ኢትዮጵያ #ስደተኞች

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ታሳ ታሳ ጋሞ
የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ
* ጋሞ በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጽሎት ተደርጎ ጉባኤው ተከፍቷልዠ
#ethiopia | የሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል።
በጉባኤው ላይ የድርጅቱ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ስብሀት እንደገለጹት፤ ስብሰባው ያለፈውን አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመገምገም እና ለማጽደቅ ያለመ ነው። ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ተሳትፎ የሲቪክ ማህበራት በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ በጉባኤው ተመላክቷል።
በተለይም በሃገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዲሁም በምርጫ ወቅት መራጮችን በማስተማር ገለልተኛ ሚና ለመወጣት ይተጋል ተብሏል።
ሰብአዊ ድጋፍ እና ልማት🔎
ማህበራቱ በተጠናቀቀው አመት በበርካታ የልማት ስራዎች ላይ የተሳተፉ ሲሆን፣ በተለይም ከግጭት ጋር ተያይዞ ለተፈናቀሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል። በጤና፣ በትምህርት እና በመልካም አስተዳደር ረገድም ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
የጋሞ አደጋ እና ቀጣይ እቅዶች🔎
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ – የሲቪል ማህበረሰብ አስተባባሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሞ ሞሊሶ በጋሞ ዞን ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ጋጮባባ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ አርባምንጭ ከተማ፣ ቦንኬ ወረዳ፣ ጨንቻ፣ ገረሴ ዙሪያ እና ገረሴ ከተማ በጎርፍ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰብአዊ እና የንብረት ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል፡፡
አደጋው ጋጮባባ ፣ ከምባ ዙሪያ ወረዳ ፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፣አርባምንጭ ከተማ ፣ ቦንኬ ወረዳ ፣ጨንቻ ፣ ገረሴ ዙሪያ ምእራብ አባያ እና ገረሴ ከተማ ላይ የደረሰ ሲሆን የጉዳቱ መንስኤም በጎርፍ ፣ በናዳ እና አውሎ ንፋስ ሰፊ ሞትና የንብረት ጉዳት ደርሷል ፡፡
በዚህም በአደጋ አባወራ 2644 እማወራ 376 በድምሩ 302ዐ እና ወንድ 8261 ሴት 10310 በድምሩ 18571 ቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል፡፡
አደጋው በደረሰባቸው ወረዳዎች በተከሰተው አደጋ 1271 ሄር በላይ የሙዝ ፣ የሰብል ጉዳት ደርሷል ፤ 1100 የመኖሪያ ቤቶች የወደሙ ሲሆን በተያያዘም በአርባ ምንጭ ከተማ የኩልፎ ወንዝ በመሙላት ተፈጥሮአዊ አቅጣጫውን ለቆ በመሄድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 31 በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ማህበራት፣ 2 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችና 1 የግብረ ሰናይ ድርጅት ንብረት ወድሟል አቶ ማሞ አስረድተዋል።
አያይዘውም በዞኑ አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች ከ 125 በላይ ከፍተኛ ሞት የተመዘገበበት ነው፡፡ በዚህም 81 አስክሬን በቁፋሮ ተገኝቶ በክብር እንዲያርፉ መደረጉን አስታውቀዋል።
የሲሲአርዲኤ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ንጉሱ ለገሰ በጋሞ አካባቢ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሲሲአርዲኤ (CCRDA) አባላቱን በማስተባበር እና ድጋፎችን በማሰባሰብ በኩል ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ መሆኑን አውስተዋል።
የክርስትያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ኅብረት (CCRDA) ከ500 በላይ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አባል ይዟል።
ሲሲአርዲኤ(𝐂𝐂𝐑𝐃𝐀)
LinkedIn: www.linkedin.com/in/ccrda-...
Telegram: https://t.me/ccrda_et
Twitter: https://x.com/CCRDA454972
Website: https://ccrdaeth.org/
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ccrda #civilsociety #ethiopia #humanitarianaid #nationaldialogue #development #civicengagement #etbusinessview

የሲሲአርዲኤ (CCRDA) የ53 ዓመታት የልህቀት አሻራ
የሲአርዲኤ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ለውጥና ልማት ላይ የሚሰራ አንጋፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት (ኮንሶርትየም) ሲሆን፣ ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመናት በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ አሻራ አሳርፏል።
እ.አ.አ በ1973 በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረሃብ ወቅት፣ የእርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለማከናወን በልበ ቀናዎች የተመሰረተ ተቋም ነው።
ዛሬ ላይ የ53 ዓመታት የልህቀት እና የለውጥ ጉዞን አስቆጥሯል።
ራዕይ፦
ድህነት ተወግዶ ማየት።
ተልዕኮ፦
ማህበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ከአባላት ጋር በትጋት መስራት።
በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባላቱም በሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በሚከተሉት ዘርፎች ይሰማራሉ፦
ሰብዓዊ ድጋፍ እና ጤና
ልጆች፣ ወጣቶች እና ስነ-ፆታ
አካባቢ ጥበቃ እና የውሃ ንፅህና
ኤች አይ ቪ መከላከል
መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ
ሲሲአርዲኤ አባላቱ ተሞክሮ የሚለዋወጡባቸው መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በፖሊሲ ውትወታ (Advocacy) እና በሀብት ማሰባሰብ ረገድ የአባላቱን ተፅዕኖ የማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
𝐅𝐚𝐜𝐞𝐛𝐨𝐨𝐤: https://web.facebook.com/c...
𝐋𝐢𝐧𝐤𝐞𝐝𝐈𝐧: www.linkedin.com/in/ccrda-...
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦: https://t.me/ccrda_et
𝐘𝐨𝐮𝐓𝐮𝐛𝐞: https://www.youtube.com/@c...
𝐗 (𝐓𝐰𝐢𝐭𝐭𝐞𝐫): https://x.com/CCRDA454972
𝐖𝐞𝐛𝐬𝐢𝐭𝐞: https://ccrdaeth.org/
#ccrda #ሲሲአርዲኤ #ethiopia #ngos #civilsociety #development #socialjustice #53yearsofservice #impact #humanitarianaid #policyadvocacy #communitydevelopment #ethiodevelopment

3 months ago
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለጹ
#ethiopia | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖችና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል።
በአካባቢው የተከሰተው ይህ አደጋ በርካታ ቤተሰቦችን ለሃዘንና ለችግር የዳረገ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #gamozone #landslide #who #drtedrosጸAdhanom #ethiopia #gachobaba #emergencyresponse #staysafe #humanitarianaid

🙏 ለወንድማችን መልካሙ ፈጠነ የሕክምና እርዳታ ጥሪ
#ethiopia | በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕራይዝ ልማት የእንስሳት እርባታ ቡድን መሪ የሆነው ወንድማችን መልካሙ ፈጠነ፣ ባጋጠመው ከፍተኛ የዲስክ መንሸራተትና የነርቭ ሕመም ምክንያት በጽኑ እየተሰቃየ ይገኛል።
🚨 ወቅታዊ ሁኔታው፦
መልካሙ በአሁኑ ወቅት በሕይወት ፋና ሆስፒታል (ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ) የሕክምና ማዕከል ውስጥ ተኝቶ ይገኛል።
ሕመሙ በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ በመምጣቱ ያለ ሰው እርዳታ መንቀሳቀስም ሆነ መቀመጥ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
በድሬዳዋ ዴልት የማሪያም ወርቅ ሆስፒታል ወይም በኮሪያ ሆስፒታል አፋጣኝ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለበት በባለሙያዎች ተነግሮታል። ለዚህም በትንሹ 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር ያስፈልጋል። ይህ መጠን ለወንድማችንና ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ በመሆኑ የእኛን የሁላችንን እርዳታ ይሻል።
💰 ድጋፍ ለማድረግ፦
"ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሀምሳ ሰው ጌጡ" ነውና የወንድማችንን ስቃይ ለማቅለል የምትችሉትን ሁሉ እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000152544147
መልካሙ ፈጠነ ቸኮል (Melkamu Fetene Chekol)
ስልክ ቁጥሮች፦
0912 76 39 00 / 0929 17 86 51
ቸርነት ለራስ ነው! ዛሬ ለወንድማችን የምናደርገው ጥቂት ድጋፍ እሱን ወደ ጤናውና ወደ ሥራው ይመልሰዋል።
እባክዎን ይህንን መረጃ ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን።
#የእርዳታጥሪ #መልካሙፈጠነ #ሐረማያዩኒቨርሲቲ #ኢትዮጵያ #humanitarianaid #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago
ጋዛን መልሶ ለማቋቋም 5 ቢሊዮን ዶላር ተመደበ
#ethiopia | በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አነሳሽነት በቅርቡ የተመሰረተው "የሰላም ቦርድ"፣ ለጋዛ ሰብዓዊ እርዳታ እና ለመልሶ ግንባታ የሚውል 5 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል። ይህ እርምጃ በጦርነት ለፈረሰችው ጋዛ አዲስ የተስፋ ጭላንጭል ይዞ መጥቷል ተብሏል።
የመጀመሪያው ታሪካዊ ጉባዔ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኤክስ (X) ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ መሰረት፣ ቦርዱ የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባዔ በቀጣዩ ሳምንት ሐሙስ ያካሂዳል። በዚህ ጉባዔ ላይም የሁሉም አባል ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
ሰላምን የማስከበር ቀጣይ እርምጃዎች
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ፣ በተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ የተጠቀሰው ዓለምአቀፍ አረጋጊ ሀይል (ISF) ምልመላ መጀመሩ ተጠቁሟል። ይህ ሀይል በቀጣይ በጋዛ ያለውን ጸጥታ የማስከበር እና የሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭቱን የማሳለጥ ኃላፊነት ይረከባል ተብሎ ታምኖበታል።
ይህ የቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና የጸጥታ ኃይል ዝግጅት፣ በጋዛ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየተደረገ ካለው ጥረት ውስጥ ትልቁ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጋዛ #ትራምፕ #የሰላምቦርድ #gazareconstruction #trump #peaceboard #internationalnews #humanitarianaid #thepeninsula #thiqah

በሃዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች እንድረስላቸው! 💔🙏
"ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ" (ሮሜ 12:15)
#ethiopia | በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ አካባቢ በሚገኘው የኮየ ፈንታ ደብረ ፀሐይ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በበዓለ ጥምቀት ዕለት በአሳዛኝ የኤሌክትሪክ አደጋ አራት ወጣት አስተባባሪዎችን ማጣታችን ይታወሳል።
እነዚህ ወጣቶች በበዓሉ ድምቀት ሰረገላ በማዘጋጀት እና በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ በኤሌክትሪክ ንኪኪ በተከሰተ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ማህበረሰቡን በእጅጉ አሳዝኗል።
ይህ ክስተት የወጣቶቹን ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል። በተለይም፦
ከሟቾች መካከል የአቶ አበበ ተፈራ ባለቤት የ9 ወር ነፍሰ ጡር መሆናቸውና ልጆቻቸውም አሁን ካሉበት ቤት በኪራይ ምክንያት እንዲወጡ መደረጋቸው፤
የሟች አቶ ፍቃዱ ተክለየስ ቤተሰቦች የሚመገቡት የሌላቸው 5 ቤተሰቦች በችግር ላይ መውደቃቸው፤
ሌላኛው ሟች አቶ ሄሮጳ ማሞ የቤተሰቡ አስተዳዳሪና ብቸኛ ደጋፊ በመሆኑ ቤተሰቡ በከፍተኛ ሃዘንና ችግር ውስጥ መገኘቱ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል።
ስለሆነም እነዚህን የተቸገሩ ቤተሰቦች ለመርዳት ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
ለተጎጂ ቤተሰቦች ተብሎ በተከፈተው የጋራ የባንክ አካውንት ድጋፍዎን ማድረግ ይችላሉ፦
💰 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000742754247
💰 አቢሲኒያ ባንክ፦ 249319147
የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሚደረገው የቀጥታ ስርጭት ላይ በመሳተፍና ይህን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት የድርሻዎን እንዲወጡ በትህትና እንጠይቃለን።
ፈጣሪ ለሟቾች መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን!
#emergencyappeal #charityethiopia #supportfamilies #humanitarianaid #eotc #communitysupport #ethiopiahelp

ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሳሉ!!
📌በአማራ እና ትግራይ ክልሎች ለሚገኙ ተማሪዎች የ9 ሚሊዮን 980 ሺህ ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ
#ethiopia | በጦርነት እና ግጭት ምክንያት ትምህርት ቤቶች በፈረሱባቸው የአማራ እና ትግራይ ክልሎች፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ያለመ ግዙፍ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል።
"ፕሌይፉል ኢዱኬሽን ፓዝዌይስ ኢን ኢትዮጵያ" (PEPE) የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት 9 ሚሊዮን 980 ሺህ ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፣ በኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (IRC) መሪነት ከሉሚኖስ ፈንድ እና ከኢማኑኤል ደቨሎፕመንት አሶሴሽን (EDA) ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ትኩረቶች፡
* ተደራሽነት፡ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በሁለቱ ክልሎች ለችግር የተጋለጡ 150,620 ተማሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ አልሟል።
* የትኩረት አካባቢዎች፡ የመፈናቀል መጠን በበዛባቸው እና ትምህርት ቤቶች በብዛት በፈረሱባቸው ወረዳዎች ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል።
ከባለድርሻ አካላት የተሰጡ አስተያየቶች፡
* አማራ ክልል፡ የትምህርት ቢሮ ኃላፊው አቶ ጥላሁን ወርቅነህ፤ በክልሉ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ይህ ፕሮጀክት ተማሪዎችን ለመመለስ ለሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።
* ትግራይ ክልል፡ የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢስማኤል አብዱራህማን በበኩላቸው፤ በሰሜኑ ጦርነት የወደሙና እስካሁን አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ፕሮጀክቱ እንደ መልካም እድል እንደሚቆጠር ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር ዮሴፍ አበራ፣ ለፕሮጀክቱ ስኬት ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በጦርነት የጎዳውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል ብለዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #education #amhara #tigray #irc #pepe #students #humanitarianaid #eda #luminosfund

በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪዎች የላቀ ምስጋናና እውቅና ተሰጠ
#ethiopia | በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር የተሰማሩ ከ1,500 በላይ ኢትዮጵያውያን የጦር ሰራዊትና የፖሊስ አባላት ለዓለም ሰላም እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና ቀረበላቸው። እነዚህ መኮንኖች ከሀገራቸው በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀው፣ በጦርነትና በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ የሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ከከፋ አደጋ ለመታደግ በጽናት እያገለገሉ እንደሚገኙ ተገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፦
* እ.ኤ.አ. ከ1948 ጀምሮ እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሰላም አስከባሪነት አገልግለዋል።
* በአሁኑ ወቅት ከ65,000 በላይ አባላት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በስራ ላይ ይገኛሉ።
* ድርጅቱ ቋሚ ወታደራዊ ኃይል የሌለው በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሰው ኃይል የሚያዋጡ ከ100 በላይ አባል ሀገራት ለዓለም መረጋጋት የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አምኖበታል።
* በነዚህ የሰላም ማስከበር ስራዎች ሂደትም እስካሁን ከ4,400 በላይ ሰላም አስከባሪዎች ለሰላም ሲሉ ውድ ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያን የሰላም አስከባሪዎች ከዋናው የጸጥታ ጥበቃ ተልዕኳቸው ባሻገር፣ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ሰብአዊ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ቀዳሚ ናቸው።
ከሚያከናውኗቸው ተግባራት መካከልም፦
* ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት፣
* የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማመቻቸት፣
* የትምህርት ቤቶችን ግንባታ መደገፍ፣
* እንደ መንገድና ድልድይ ያሉ መሰረተ ልማቶችን መገንባት ይገኙበታል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም የምታበረክተውን ይህንኑ ታላቅ ሚና በመጥቀስ ተገቢውን እውቅና ሰጥቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #ethiopia #unpeacekeeping #globalpeace #ethiopiandefenseforce #humanitarianaid #unitednations