1 month ago
ከሜጋ ፕሮጀክቶች ባሻገር፡ የሰው ልጅን ክብር ማዕከል ያደረገው የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ
***************************
የሀገር ዕድገት የሚለካው በሜጋ ፕሮጀክቶች፣ በግዙፍ የኃይል ማመንጫዎች እና በተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ብቻ አይደለም።
የእውነተኛ ስልጣኔ ጥጉ የተጎዱ ወገኖችን ሰብዓዊ ክብር መመለስ እና የጥቂቶች ብቻ የነበረን ዕድል ለሁሉም እኩል ተደራሽ ማድረግ መቻል ነው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሀገራችን እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና የሀሃይዌይ መንገድዶች ዝርጋታን ጨምሮ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በስፋት ተከናውነዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች፣ አሳዳጊ የሌላቸው ወላጅ አልባ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አቅመ ደካሞችን ማዕከል ያደረጉ ሰው ተኮር ሥራዎች የመንግሥት ዋና ትኩረት ሆነው ዘልቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “ሜጋ ፕሮጀክቶች ብቻቸውን የተሟላ ብልጽግና ሊያረጋግጡ አይችሉም፤ የተጎዱ ወገኖችን የሚያግዝ አሠራር መከተል አለብን” ሲሉ ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት፣ ባለፉት ዓመታት ለበርካታ እጅ አጠር ወገኖች የመኖሪያ ቤት ከመገንባት በተጨማሪ የማዕድ ማጋራት ባህል እንዲጎለብት ተደርጓል።
በየሰፈሩ መጫወቻ ቦታ እና የስፖርት ማዘውተሪያ የሌላቸው አዳጊ ሕፃናት አስፓልት ላይ እየተጫወቱ ለአደጋ እንዳይጋለጡ ለመከላከል በርካታ የሕፃናት መጫወቻ ቦታዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ተገንብተዋል።
በተመሳሳይ ትውልድን በዕውቀት እና በሥነ-ምግባር የማነጽ ሥራን ለማጠናከር በርካታ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ ሲሆን፤ በተለይም በአዲስ አበባ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተገነባው የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የዚሁ ሰው ተኮር የልማት መርህ ትልቅ ማሳያ ነው።
በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በሕዝቡ ንቁ ትብብር እና ተሳትፎ በሺዎች የሚቆጠሩ መዋዕለ ሕፃናት ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በመደመር ዕሴት የተቃኙት እነዚህ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች ትውልድን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው እንደሚሉት፥ አዳጊዎች፣ ዓይነ ስውራን እና ወላጅ አልባ ሕፃናትን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎችን ማከናወን በምድርም በሰማይም ታላቅ ዋጋ ያለው ተግባር በመሆኑ፣ እነዚህን አርዓያነት ያላቸው ተግባራት በበለጠ ጽናትና ቁርጠኝነት አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #humancentricdevelopment #socialjustice #inclusivegrowth #ebc

3 months ago
ብዙ እያተረፍንበት ያለው ጊዜያዊ ችግርን ተደጋገፎ የማለፍ ባህላችን
****************
"በብዙ መንገድ ምግብ ተርፎ በሚደፋባት ከተማ ውስጥ በቀን አንድ ጊዜ በተሟላ ሁኔታ ለመመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን ማየት የሁላችንም ሕመም እና ሁላችንም ልንወጣው የሚገባ ትልቅ ኃላፊነት ነው።"
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በየረር 30ኛውን የነዋሪዎች የምገባ ማዕከል በመረቁበት ወቅት የተናገሩት ይህ ሀሳብ በከተማዋ ውስጥ ማኅበራዊ ፍትሕን የማንገስን አስፈላጊነት በጉልህ ያሳያል።
ይህ ማዕከል በየረር የተገነባበት ዋናው ምክንያት በሸራተን ሆቴል ማስፋፊያ ልማት ከቂርቆስ አካባቢ ለተነሱ እንዲሁም ከካዛንቺስ ለተዛወሩ ቋሚ ገቢና መጠለያ ያልነበራቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት ነው።
"ሕጋዊ ቤት አልነበራችሁም ብለን ነዋሪዎቻችንን መተው ስለማንችል፣ ኃላፊነት ወስደን ያስገባናቸው በርካታ ሰዎች አሉ" በማለት ከንቲባዋ የመንግሥት ልማት ሰው-ተኮር መሆኑን አረጋግጠዋል።
የምገባ ማዕከላት መከፈት በተለይም በልማት ምክንያት ለተነሱና ቋሚ ገቢ ለሌላቸው ዜጎች ንጹሕና ትኩስ ምግብ በነፃ የሚያገኙበት የሕልውና ዋስትና ነው።
እያንዳንዱ ማዕከል አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ የሚመገቡበትና የሚገናኙበት ቋሚ ቤታቸው ከመሆኑም በላይ፣ ወደ ማዕከል መምጣት ለማይችሉ አቅመ ደካሞችም ምግቡ ወደ ቤታቸው የሚላክበት አሠራር የተመቻቸበት ጊዜያዊ ችግርን ተደጋግፎ የማለፊያ ትልቅ ድልድይ ሆኗል።
ይሁን እንጂ የዚህ ስትራቴጂ ዋና ግብ ዜጎችን ሁልጊዜ በማዕከሉ ላይ ጥገኛ ማድረግ ሳይሆን፣ የምግብ ዋስትናቸውን እያረጋገጡ ወደ ቋሚ የሥራ ዕድል ማሸጋገር ነው።
እስካሁን በተከፈቱት 29 የምገባ ማዕከላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሂደት ወደ ሥራ መግባታቸውና በ30ኛውም የየረር ማዕከልም በርካታ ነዋሪዎች ገና በምረቃው ዕለት በመጋቢነትና በአስተናጋጅነት መቀጠራቸው ለዚህ ማሳያ ነው።
በተጨማሪም በከተማዋ በሴፍቲኔት ተይዘው ከነበሩ መካከል ከ100 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች ራሳቸውን ችለው ዛሬ ላይ ሌሎችን መቅጠር መቻላቸው ከተማዋን ከድህነት ለማውጣት የተያዘው ሰው-ተኮር ልማት በተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ያረጋግጣል።
ይህ በከተማዋ የተጀመረው ጊዜያዊ ችግርን ተደጋገፎ የማለፍ ባህል የመንግሥት ሸክም ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶችና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ከገቢያቸው ላይ ቀንሰው የሚሳተፉበት የማኅበራዊ ኃላፊነት ውጤት ነው።
ማዕከላቱ በዘላቂነት ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ ለማስቻል የምገባ ኤጀንሲው የቁሳቁስና የደረጃ ክትትል የሚያደርግ ሲሆን፣ ጉድለት በተገኘ ጊዜም ከመንግሥት በጀት እንደሚሟላ ታውቋል።
ከተማን በዘላቂነት ማበልጸግ የሚቻለው ሕንጻዎችን በመገንባት ብቻ ሳይሆን ሌት ተቀን ጠንክሮ በመሥራት፣ እርስ በርስ በመደጋገፍና ለአቅመ ደካማ ወገኖች በመትረፍ ጭምር መሆኑን የ30ኛው የምገባ ማዕከል መከፈት ትልቅ ማሳያ ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #addisababa #communitysupport #socialjustice #ebc

7 months ago
የሲሲአርዲኤ (CCRDA) የ53 ዓመታት የልህቀት አሻራ
የሲአርዲኤ በኢትዮጵያ የማህበረሰብ ለውጥና ልማት ላይ የሚሰራ አንጋፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት (ኮንሶርትየም) ሲሆን፣ ላለፉት ግማሽ ክፍለ ዘመናት በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ጉልህ አሻራ አሳርፏል።
እ.አ.አ በ1973 በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ረሃብ ወቅት፣ የእርዳታ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ለማከናወን በልበ ቀናዎች የተመሰረተ ተቋም ነው።
ዛሬ ላይ የ53 ዓመታት የልህቀት እና የለውጥ ጉዞን አስቆጥሯል።
ራዕይ፦
ድህነት ተወግዶ ማየት።
ተልዕኮ፦
ማህበራዊ ፍትሕ እንዲሰፍን ከአባላት ጋር በትጋት መስራት።
በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባላቱም በሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት በሚከተሉት ዘርፎች ይሰማራሉ፦
ሰብዓዊ ድጋፍ እና ጤና
ልጆች፣ ወጣቶች እና ስነ-ፆታ
አካባቢ ጥበቃ እና የውሃ ንፅህና
ኤች አይ ቪ መከላከል
መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ
ሲሲአርዲኤ አባላቱ ተሞክሮ የሚለዋወጡባቸው መድረኮችን በማዘጋጀት፣ በፖሊሲ ውትወታ (Advocacy) እና በሀብት ማሰባሰብ ረገድ የአባላቱን ተፅዕኖ የማሳደግ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
𝐅𝐚𝐜𝐞𝐛𝐨𝐨𝐤: https://web.facebook.com/c...
𝐋𝐢𝐧𝐤𝐞𝐝𝐈𝐧: www.linkedin.com/in/ccrda-...
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦: https://t.me/ccrda_et
𝐘𝐨𝐮𝐓𝐮𝐛𝐞: https://www.youtube.com/@c...
𝐗 (𝐓𝐰𝐢𝐭𝐭𝐞𝐫): https://x.com/CCRDA454972
𝐖𝐞𝐛𝐬𝐢𝐭𝐞: https://ccrdaeth.org/
#ccrda #ሲሲአርዲኤ #ethiopia #ngos #civilsociety #development #socialjustice #53yearsofservice #impact #humanitarianaid #policyadvocacy #communitydevelopment #ethiodevelopment

Comments