1 month ago
አሜሪካ የኢትዮጵያን እርዳታ ልታቆም ነው! የተፈናቃዮች ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? #ethiopia #ethiopianews #humanitariancrisis #usaid #usforeignpolicy
2 months ago
አስቸኳኪ የድረሱልን ጥሪ
በኮንሶ የሰገን ወንዝ የፈጠረው "የሞት ድልድይ" እና የነዋሪዎች ሰቆቃ!
#ethiopia | በኮንሶ ዞን የሰገን ወንዝ ሞልቶ ዳር እስከ ዳር በመትረፍረፉ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በሞትና በሕይወት መካከል የሚገኝ አስከፊ መከራን እያስተናገደ ይገኛል።
ነዋሪዎቹ ለዕለት ጉርሳቸውና ለልጆቻቸው ምግብ ፍለጋ ሲሉ ብቻ ወንዙን ለመሻገር የማይታሰብ አደጋ ውስጥ ይገባሉ።
ነዋሪዎቹ በወንዙ ግራና ቀኝ በተተከሉ እንጨቶች ላይ ገመድ አስረው በመንጠልጠልና በኃይለኛ ሞገድ እየተመቱ ለመሻገር ይገደዳሉ።
አንዲት ትንሽ ስህተት ወይም የገመድ መበጠስ በቀጥታ ወደ ግርማዊው የሰገን ወንዝ ውሃ በመግባት ሕይወትን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ አማራጭ የለውም።
የአካባቢው ነዋሪዎች እርሻና መተዳደሪያቸው በወንዙ ማዶ በመሆኑ፣ ይህን "የሞት ድልድይ" ሳይወዱ በግድ በየቀኑ ለመጠቀም ይገደዳሉ።
ይህ ችግር ከዞኑ አቅም በላይ በመሆኑ፣ የክልልና የፌዴራል መንግሥታት የወገኖቻቸውን ሰቆቃ ተመልክተው አስቸኳይ ድልድይ በመገንባት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጡ ጥሪ ይቀርባል።
ወገኖቻችን በገመድ ተንጠልጥለው ወደ ወንዝ የሚገቡበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል!
#getu #konso #segenriver #bridgerequest #humanitariancrisis #ethiopianews #safetyfirst #infrastructure #southernethiopia #ኮንሶ #ሰገንወንዝ #ድልድይ #ሰቆቃ #ድረሱልን #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ዓለም የረሳት ሱዳን
📌የሱዳን መርዶ፡ በኤል-ዳይን ሆስፒታል ላይ በተሰነዘረ ጥቃት የህፃናት እና የጤና ባለሙያዎች ህይወት አለፈ
#ethiopia | በሱዳን እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት እጅግ አስከፊ ወደሆነ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ትላንት የሙስሊሞች የዒድ በዓል በሚከበርበት ወቅት፣ በምሥራቅ ዳርፉር ግዛት ኤል-ዳይን በተሰኘው መማሪያ ሆስፒታል ላይ በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት መጠነ ሰፊ የሰው ህይወት መጥፋቱ ተነግሯል።
የጥቃቱ ሰለባዎች እና የጉዳት መጠን
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት፣ በጥቃቱ ሳቢያ፦
* 64 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል (ከእነዚህም መካከል 13 ህፃናት፣ 2 ነርሶች እና 1 ሐኪም ይገኙበታል።)
* 89 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ዶክተር ቴድሮስ "የፈሰሰው ደም ይበቃል!" በማለት ተፋላሚ ወገኖች ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የክሱ ምንጭ
የፈጣን ደራሽ ኃይሉ (RSF) ጥቃቱን የፈጸመው የሱዳን መደበኛ ጦር መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን አውግዟል። ሁለቱ ኃይሎች በ2021 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ላይ አብረው ቢወጡም፣ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ ግን ሀገሪቱን ወደማያልቅ ጦርነት ውስጥ ከትተዋታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nbc #sudanconflict #eldaein #humanitariancrisis #sudannews #healthunderattack #ሱዳን #የሰላምጥሪ

Sponsored by
Surafel