4 months ago
የብርሃን ጉዞ ወደ ገጠር
* የሶላር ሚኒግሪድ ፕሮጀክቶች በደቡብ ኢትዮጵያ ስኬት እያስመዘገቡ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከብሔራዊ የኃይል ቋት (Grid) የራቁ የገጠር አካባቢዎችን በአማራጭ የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረው የተቀናጀ የልማት ሥራ ውጤታማ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለፁ።
በደቡብ ኦሞ ዞን (ሳላማጎ፣ ሐመር፣ ኦሞራቴና ዳሰነች) እንዲሁም በጋሞ ዞን (ጋርዳ ማርታ) የሶላር ሚኒግሪድ ማመንጫዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
በአጠቃላይ 2,325 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ ከ20 ሺህ በላይ የገጠር አባወራዎችን የብርሃን ተጠቃሚ አድርገዋል።
ይህ ኃይል ከመኖሪያ ቤት ብርሃን ባለፈ ለመጠጥ ውሃ፣ ለጤና ተቋማትና ለመስኖ ልማት እንዲውል ከተቋሙ ጋር በትብብር እንደሚሠራ ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋሞ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሌሎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ። ይህም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 የያዘችውን የኃይል ተደራሽነት ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
#getu #eeu #solarenergy #ruralelectrification #southethiopia #greenenergy #developmentnews #worldbank #energyaccess #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ሶላር #ልማት #ደቡብኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments