በቺሊ በስህተት የወር ደሞዙ 330 እጥፍ የገባለት ሰራተኛ ስራ ለቀቀ
አንድ ሰራተኛ በስህተት የወር ደሞዙን 330 እጥፍ የሚያህል ገንዘብ ወደ ሂሳቡ ገብቶለታል። እሱም ወዲያውኑ ስራውን ለቆ የኃላፊውን የስልክ ጥሪዎች መመለስ አቆመ። በኋላም ቀጣሪው ገንዘቡን ለማስመለስ ፍርድ ቤት ሲሄድ፣ ፍርድ ቤቱ ለሰራተኛው ወሰነ።
ክስተቱ የተፈጸመው በቺሊ ሲሆን፣ በግንቦት 2022 በደመወዝ ክፍያ ላይ በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ወደ ሰራተኛው የባንክ ሂሳብ በግምት የ127 ሺህ ፓውንድ ተቀማጭ ተደርጓል።
ነገር ግን፣ በዳን ኮንሶርሲዮ ኢንዱስትሪያል ደ አሊሜንቶስ ደ ቺሊ በሚባለው የምግብ አምራች ድርጅት ውስጥ የአስተዳደር ረዳት የነበረው ወርሃዊ ደሞዙ 386 ፓውንድ ብቻ ነበር።
መጀመሪያ ላይ ሰውየው ሙሉውን ገንዘብ እንደሚመልስ ለኩባንያው አረጋግጦ ነበር። ሆኖም፣ ከሶስት ቀናት በኋላ ስራውን ለቀቀ።
ኩባንያውም በኋላ በስርቆት ወንጀል ከሰሰው።
ከሶስት ዓመታት የህግ ሂደት በኋላ፣ ዳኛው ክስተቱ ስርቆት ሳይሆን ያልተፈቀደ ደረሰኝ መሆኑን በመወሰን የወንጀል ክስ ተብሎ መታየት የለበትም የሚል ውሳኔ አስተላለፉ።
ፍርድ ቤቱ ሰውየውን ከወንጀል ክስ ነፃ ቢያደርገውም፣ ኩባንያው ገንዘቡን በሲቪል ፍርድ ቤት በኩል ለማስመለስ መሞከሩን እንደሚቀጥል ተናግሯል።
ኩባንያው ለዲያሪዮ ፊናንሲየሮ ለተባለው ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ፣ “ይህንን ውሳኔ ለማስመለስ (ለመከለስ) ሁሉንም ህጋዊ እርምጃዎች እንወስዳለን” ብሏል።
seledadotio

8 months ago