ዩቲዩብ ተመልካቾችን የሚያስቆጣ አዲስ አሰራር ይፋ አደረገ፤ ማለፍ የማይቻሉ ማስታወቂያዎች
ከዚህ ቀደም ተመልካቾች ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ 'Skip' በማድረግ የሚያልፏቸው ማስታወቂያዎች በአዲሱ አሰራር መሰረት ሙሉ 30 ሰከንድ እንዲታዩ ይገደዳሉ።
ጎግል ይህን ለውጥ ያመጣው ሰዎች በቲቪ ፕሮግራሞችን በሚከታተሉበት ወቅት ያላቸው ባህሪ ከመደበኛው የቴሌቪዥን ስርጭት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ነው ብሏል።
ኩባንያው አዲሱን አሰራር በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ መሆኑን ገልጾ የ6 ሰከንድ፣ የ15 ሰከንድ እና አዲሱን የ30 ሰከንድ ማስታወቂያ እንደ አስፈላጊነቱ እያፈራረቀ እንደሚጠቀም አስታውቋል።
ይህ ለውጥ ተግባራዊ የተደረገው በቅርብ ዓመታት ውስጥ የዩቲዩብ የቲቪ ተመልካቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ ነው።
ይህ አሰራር ተመልካቾች ማስታወቂያ የሌለበትን 'YouTube Premium' የተባለውን የሚከፈልበት አገልግሎት እንዲጠቀሙ ለማበረታታት የታለመ መሆኑም ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅት ለውጡ በስማርት ቲቪዎች፣ በጌም ኮንሶሎች እና በሌሎች የቲቪ መተግበሪያዎች ላይ ብቻ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
seledadotio

3 months ago