Logo
Getu Temesgen
58ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
#ethiopia I የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 58ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን ሞጆ በሚገኘው የኮንሶላታ ልዑካን የሱባኤ ማዕከል ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምረዋል።

ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤው አጀንዳቸው የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ በማተኮር ሐዋርያዊ እና ማህበራዊ ልማት አገልግሎቶች፣ ወቅታዊ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ሌሎችም የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመመወያየት አቀጣጫ እና መመሪያዎችን እንደሚሰጡ የጉባኤው ጠቅላይ ጸኃፊ ክቡር አባ ከተማ አስፋው ገልጸዋል።

ጉባኤው እስከ ሀምሌ 4 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.