ኢጋድ ጋዜጠኞችን ሊሸልም ነው
ከዕዝራ እጅጉ( ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | 3ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ኅዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ።እሁድ ከ10 ሰዓት ጀምሮ የውድድሩ አሸናፊዎች ይታወቃሉ።
በኢትዮጵያ መንግሥትና ኢጋድ ትብብር በተዘጋጀው በዚህ ሽልማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የተሻለ የይዘት ሥራ ያከናወኑ የሚድያ ባለሙያዎች ዕውቅና ያገኛሉ።
የዘንድሮው ሽልማት Story Telling for Climate Action -for a Secure, Resilient and Stable Region በሚል ርዕሰ የሚካሄድ ይሆናል።
ሦስተኛውን የኢጋድ የሚዲያ አዋርድ የዝግጅት ሂደት አስመልክቶም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው እና በኢትዮጵያ የኢጋድ ተጠሪ አበባው ቢሆነኝ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ የኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶችን ዕውቅና የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በሚዲያ አዋርድ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።
የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።
ውድድሩበቴሌቪዥን፣ሬዲዮ፣ህትመት፣ዲጂታል ሚዲያ እና ሴቶች ዘርፍን ጨምሮ በስምንት ዘርፎች ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል።
400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ናቸው።
ተወዳጅ ሚድያ የኢጋድ የሚድያ አዋርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 3 ዓመት በፊት
በጅቡቲ ሲካሄድ አሸናፊ ከነበሩት የፎቶ ባለሙያዎች አንዱ መስፍን ሰሎሞን ያነጋገረ ሲሆን መስፍን የቦረናን ድርቅ በምስል በማስቀረቱ ነበር ዕውቅናውን ያገኘው።
መስፍን ይህ ዓይነት ውድድር በሙያው እንዲበረታ እንዳገዘው ገልጾ ያገኘው የዋንጫ እና የ1000 ዶላር ሽልማትም ትልቅ ትርጉም እንዳለው ነግሮናል። መስፍን፣ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገለ ባለሙያ ሲሆን ሦስተኛው የኢጋድ የሚድያ አዋርድ ኢትዮጵያ መዘጋጀቱ ለባለሙያዎች አይን ከፋች በመሆን ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብሎናል።
ኮሰን ብርሃኑ የሚዲያ ባለሙያ ሲሆን በዘርፉም ከስምንት አመት በላይ ሠርቷል። በ2007 ዓ.ም የማስተርስ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒሸርሲቲ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት በከፍተኛ ነጥብና የጥናት ውጤት እንደተመረቀ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ተቀላቀለ።
ከድርቅ ጋር ተያይዞ በቦረና፣ በሶማሌ ክልልና ኮንሶ በመገኘት ድርቁ የፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በማሳየት ለችግሩ መንግስትና ህዝብ እንዲረባረብ ያደረጉ ዘገባዎችንም ሰርቷል። በኮንሶ አካባቢ በሰራው የድርቅ ዘገባ በመጀመሪያው የኢጋድ ሚዲያ አዋርድ በመወዳደር አሸንፏል ፤ የእውቅና ሰርተፍኬትና የብር ሽልማት አግኝቶበታል።
የኢጋድ ሽልማት ዋና ዓላማም በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት ማድረግና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ዘንድሮ በሚካሄደው የሽልማት ሥነስርዓት 2000 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እና የአፍሪካ ህብረት የተባባሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች የዓለምአቀፍ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም ጋዜጠኞች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
የኢጋድ ሚድያ ዓመታዊ ሽልማት ከድርጅቱ ዋና ፀሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጥንስስ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው።አንደኛው ውድድር ጅቡቲ ሁለተኛውን የኢጋድ የሚድያ ሽልማት ደግሞ ኬንያ ማስተናገዳቸው ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ የሚታደሙ የሚድያ ባለሙያዎችን በመጋበዝና የማህበራዊ ሚድያ ዘገባዎችን በማከናወን ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ተግባሩን እየተወጣ ነው። ተወዳጅ ሚድያ እንደሚታወቀው የሚድያ ባለሙያዎችን ሕይወት በአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ (መዝገበ አእምሮ) እያወጣ እንደሆነ ይታወቃል።

9 months ago