የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር በታጣቂዎች ተገደሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አዱኛ አዛዥ፣ በመጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።
አመራሯ በኮንሶ አካባቢ የነበራቸውን የመስክ የሥራ ግዳጅ አጠናቅቀው ወደ አርባ ምንጭ በመመለስ ላይ ሳሉ፣ በጋርዱላ ዞን (ሆልቴና ሽላሌ አካባቢ) ባልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱባቸው ድንገተኛ ተኩስ በአራት ጥይቶች ተመትተው ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገው ነበር።
ወዲያውኑ ወደ አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢወሰዱም፣ ለሰዓታት የፈጀ የሕክምና ባለሙያዎች ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ መጋቢት 10 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ወይዘሮ አዱኛ ቀደም ሲል የጎፋ ዞን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በመሆን ያገለገሉና በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች ያገለገሉ አመራር ነበሩ።
የክልሉ መንግሥት ድርጊቱን በጽኑ በማውገዝ፣ ይህን "እኩይ ተግባር" የፈጸሙ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ በትኩረት እንደሚሠራና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

3 months ago