Logo
Getu Temesgen
እንጦጦ እስከ ቀበና የወንዝ ዳርቻ ሲገለጥ
Entoto to Kebena Riverside Unveiled

የእንጦጦ–ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
#ethiopia | የአዲስ አበባን ስነ-ምህዳር፣ ቱሪዝምና ኢኮኖሚ ለማጠናከር የታለመ ግዙፍ ፕሮጀክት

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ የተመረቀው የእንጦጦ–ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ ከማሻሻል ባለፈ የስነ-ምህዳር ጥበቃ፣ የመሰረተ ልማት ማሻሻያ እና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስፋፋት የታለመ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

ፕሮጀክቱ የወንዝ ተፋሰስን በማልማትና ከተማዋን ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች የተሻለች ለማድረግ የሚያግዙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አካትቷል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ክፍሎች

የወንዝ ልማት

- 1 ትልቅ ግድብ
- 16 አነስተኛ ግድቦች
- 3 ቼክ ዳሞች
- 20.2 ኪሎ ሜትር የድጋፍ ግንብ

የወንዝ ዳርቻ ጥበቃ

- 36.9 ኪሎ ሜትር የአፈርና የስነ-ምህዳር ጥበቃ ሥራዎች፣ የኮንሶ ጋቢዮን እና እርከን ሥራዎችን ጨምሮ።

አረንጓዴ ልማት

- 59.7 ሄክታር አረንጓዴ ሽፋን
- 50,330 ዛፎች ተተክለዋል

የተቀናጀ መሰረተ ልማት

- 21 የእግረኛ ድልድዮች
- 33.2 ኪሎ ሜትር የውስጥ መንገዶች
- የፍሳሽ መስመር
- 695 ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግዱ 7 የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ናቸው።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.