የአዲስ አበባን ሙት ወንዞች “መዘዘኛም” – “ገላግሌም” ይሏቸዋል፡፡
‘እዳ’ እንጂ ‘እሴት’ ያልሆኑትን የውሃ ገጾች ወደ ተፈጥሮ ማንነታቸው እንደሚመለሱ በፕሮጀክቱ ታቅዷል። Back to their Origin
====================
(ተቀናበረ: በጋዜጠኛና የሕብረተሰብ ጤናሻምፒዮን አምባሳደር እሸቱ ገለቱ)
-----------+
Rivers back to their Origin ማለት ነው። የአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ ወንዞች "ሙት" ናቸው።
‘እዳ እንጂ እሴት ሆነው አልቆዩም’፡፡ ኑሮ በደከመባቸው የአዲስ አበባ ሰፈሮች እነኚህ የተዘነጉ ወንዞችን “ገላግሌ” ይሏቸዋል፤ የተነወረ አቋራጭ አማራጭ ቢሆንም የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻን ነዋሪው በዘፈቀደ ይጥልባቸዋል፡፡
ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ የከተማ አስተዳደሩ የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ዋና ግቡ የሞት ቀጣና የሆኑትን የውሃ ገጾች ከብክለት ወደ ተፈጥሮ ማንነታቸው መመለስ (Back to origin) ነው፡፡
በዚህም ንፁህና ውብ ድባብን መፍጠርና በከተሞቹ ውስጥ በሙት ወንዞቹ መዘዝ መለያየቱን እንደ ድልድይ ሆነው መቀራረብን (Connectivity) መፍጠር ነው፡፡
የወንዝ ዳር ልማቱ ከተማዋ በዋና ቀዶ ሕክምና አልፋ ዳግም ተውባ ከትንሳኤዋ የምትገናኝበት (It's a Major City Surgery) ነው ተብሎለታል፡፡
አንዳንዶቹ እንደውም ለስም እንጂ የወንዝነትን ባህሪም አያሟሉም፤ ምክንያቱም አብዛኞቹ አመቱን ሙሉ በቋታቸው ውሃ ዝር የሚልባቸው ስላይደሉ፡፡
ይሁንና በዙሪያቸው አይደለም ቁጭ ተብሎ ሊታረፍባቸው ቀርቶ፣ በአጠገባቸው ሲታለፍ እንኳ አፍንጫ የሚሰነፍጥ ሽታ መመንጫ ሆነዋል፡፡
ይህ ከሀገራዊው የቆሻሻ አወጋገድ አለመሰልጠን ጋር ተያይዞ ሙት የሆኑት የውሃ ገጾቹ ለነዋሪውም የዘርፈ ብዙ እዳ መዘዝ ሆነው ዘልቀዋል፡፡
ጉንፋንና አስም አለርጂን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት ላይ ከሚያሳድሩት የጤና ችግሮች ባሻገር ሌሎች የውሃ ወለድ የሆድና ቆዳ አጥቂ በሽታዎችም እንዲባባሱ ምንጮች ሆነዋል፡፡
ወደ ውሃ ገጹ የሚለቀቁት መርዛማ ኬሚካሎች፣ የሽንት ቤቶች ፍሳሾች፣ የእንስሳት በድን የሚጣልባቸው፣ በአጠቃላይ ከየማዕዘናቱ ወደውሃ ገጹ መአት ግሳንግስ ቆሻሻዎች ይጣሉበታል፡፡
የተፋሰሱ መስመሮች በአግባቡ ባለመያዛቸውም ጭር ያሉ አስፈሪ ስፍራዎች ናቸው፡፡ አሮጌ ቄራና እሪ በከንቱን ለአብነት ብናነሳ የዝርፊያ፣ የማጅራት መምቻና የሴቶች ጥቃት የሚፈፀምባቸው የሰዎች ደህንነት ስጋቶችም ሆነው ቆይተዋል፡፡
ሌላው በክረምት ዝናብን ተከትሎ ጎርፍ ተንደርድሮ የሚያልፍባቸው መሆኑ በተፋሰሱ አጠገብ ቤቶች እየተናዱ በየአመቱ የሞት ቀጣናም መሆኑ ሌላው የአዲስ አበባ ክፉ ገጽ ሆኖ ይታወቃል፡፡
የከተማዋ የማይሟሙና በአፈርም የማይበሰብሱ ፕላስቲኮች ጎማዎችም የሚሞጀርባቸውና ከመርዘኛ ኬሚካሎች ጋር ተዳምሮ ከወንዞቹ ውሃን ያሉ የቤት እንስሳትም ፌስታልና ፕላስቲክ አብረው እየዋጡ የሚሞቱበትም ሆነዋል፡፡
ለሕብረተሰብ ጤና ማበልፀግና ጤና ኮምዩኒኬሽን ባለኝ ልምድ መሰረት የወንዝ ዳር ልማቱ የጤና ፋይዳውን ጨምሮ የሚያሳድረውን ከላይ የተዘረዘሩትን ዘግናኝ ደረቅ መራር ሀቆችን የሚቀይር መሆኑን በቅርቡ ጉብኝቴ መገንዘብ ችያለሁ፡፡
ታላቅ ፋይዳ ቢኖረውም በጠቀሜታው ልክ ግን የተዘመረለት አልመሰለኝም፤ ልብንና ቀልብ የማይገዙ የፖለቲካዊ መሪ ቃል እየተለጠፈባቸው የሚቀርቡት ገለጻዎች በተጨባጭ መሬት ላይ ያለውን ታላቅ ጠቀሜታ ሳያደበዝዘው አልቀረም፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ መድህን ሊሆን የሚችል ልማትን፤ ለምን በፖለቲካ ቅብ ቅኝት አይቼ ማህበረ - ኢኮኖሚያዊና የውበት ጥበብ ገጾቹን ለምን አወሳስበዋለሁ አስብሎኛል፡፡
የፖለቲካው አስተዳደር ከዚህ ስራ ጋር ግን ሞገሱን ይውሰድ የሚያስብለው ነጥብ አጠቃላይ የከተማዋን መልክዐ ምድርና የተፋሰሱን ባህሪ አገናዝቦ ሁሉን ባቀናጀ የአካቶ ጥያቄ አመላለስ ዘይቤ በምልዑ ሁኔታ (Integrated approach & Comprehensive design) የፕሮጀክት ሳይቱ መደዘኑ ነው፡፡
ከፖለቲካው አውድ አርቄውና ከውዳሴ ከንቱ መነጽር ውጪ ልየው ያስባለኝም የልማት ፋይዳው በላሽቶ የቆየ አያያዝን ማርሽን 360 ዲግሪ ማርሽ የሚቀይር መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡
የወንዝ ዳሩ ልማት አሁን ላይ ይሸፍናል ተብሎ ከተነገረለት 42 ኪሎ ሜትር መካከል 23ቱን ኪሎ ሜትር ርዝመት በሸፈነው መልክዓ ምድር ላይ የተሰራውን ድንቅ ስራ ዞሬ መቃኘቴ ነው፡፡
አዲስ አበባ በማህፀኗ ያቀፈቻቸው ወንዞቿና ገባሮቻቸው ከነተፋሰሳቸው ቀኑን ሙሉ አልበቃ ብሎ ዞረን ማየት የቻልነው ከፊል ገጹን ነው፡፡
አንድ የተረዳሁት ነገር በምን ያህል ደረጃ የወንዞቹ ተፋሰስ የአዲስ አበባን ክፍለ ከተሞች በሙሉ አስተሳስሮና አቆራኝቶ የሚያገናኝ መሆኑን ነው፡፡
በወንዝ ዳር ልማቱ በዝርዝር ከጎበኘኋቸው መካከል የወንዝ መጠበቂያ የአረንጓዴ ገጽና የጋቢዮን ግንብ፣ የውሃ መውረጃ ቦዮች፣ የመተላለፊያ መንገድና ድልድዮችን የመሰሉ መሰረተ ልማቶች፣ የወንዞቹን ውሃ ማከሚያ ቋት ተቋማትንና የቢዝነስ ማዕከላትን ካተተና በዳርቻዎቹ አቅራቢያ የተፈናቀሉት በጋራ መልሶ ግንባታ እንዲሰፍሩ ማመቻቸትም (repurposed housing) ይጠቀሳል፡፡
የወንዝ ዳር ልማቱ መልክዓ ምድር በተቻለ መጠን ከእንጦጦ ፓርኩ ጋር እንዲናበብ፣ እስከ ፒኮክ መናፈሻ ድረስ ሲዘልቅም ዲዛየኖቹ ከአካባቢው ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ፣ እንደ ኮንሶ ባህላዊ የዳገት እርከን ልምድንም እንዲያዋድዱ፣ የወንዝ ውሃ ማጣሪያ ነጥብን እንዲያካትት፣ በአንዳንድ ቦታ ውሃ ፍሰት ጠብቆ እንዲወርድ አስቻይ የውሃ መከተሪያ (Check dam) እንዲኖር ተደርጓል፡፡
እንደ መዝናኛም አማራጭ ከወንዙ ዳርቻው እልፍ ብለው በተገኙ ትርፍ ሳብ ያሉ መሬቶችም ላይ የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችንና አነስተኛ እጥር ስታዲየምን ማዘጋጀት፣ በዙሪያው ካፌ፣ ወንዙም ላይ ተወዛዋዥ የቡና መጠጫ ልዩ ቤቶችና የወንዝ ዳር ሙዚየም እየተሰራ ነው፡፡
በድምሩም 21 የውሃ ማጣሪያና ማከሚያ ኩሬዎች፣ አገናኝ ድልድዮች እና ኮሪደሮች የተገነቡ ሲሆን የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችና የታክሲ መጫኛና ማውረጃ መናኸሪያዎች፣ በእግር ሽርሽር የሚባልባቸው መረማመጃዎችም አብረው እንደተሰሩ በጉብኝታችን ታዝበናል፡፡
ቀጨኔ፣ ቡልቡላ፣ ቀበና፣ አምባሳደር፣ እሪ በከንቱ፣ ጎርደሜ እያልን ከአዲስ አበባ የተለያዩ ማዕዘናት የሚመነጩ ወንዞችን መጥቀስ ሲቻል፣ ያየነው የወንዝ ዳር ልማት ሽፋንም 1 ሺህ 37 ሄክታር እንደሚደርስ የተሰጠን መግለጫ ያመለክታል፡፡
ለወጣቶች ትኩረት ሰጥቷል በተባለው የልማት ስራው 18 ሺህ ያህል የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት አባላት በግንባታ ኮንትራቱ ስራ መሳተፋቸው ይነገራል፡፡
በትይዩ ከስራው ይልቅ አጋጣሚውን ለግል ጥቅም ተጠቅመዋል የተባሉም ከ40 በላይ አመራሮች መባረራቸውንና ከ45 በላይ ኮንትራክተሮችም ውል ባለማክበራቸው መሰናበታቸው ተጠቅሷል፡፡
ፕሮጄክቱ የዛሬ 5 አመት እንደተጀመረ፤ግን ያኔ በውጭ ድጋፍ ከእንጦጦ እስከ አቃቂ ያለው መልክዐ ምድር ተካቶ የወንዝ ዳሩ ልማት ሲወጠን ከ10 አመት በላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

8 months ago