2 months ago
በጣም የሚያምር ፎቶ💙 እንደዚህ ሰው በህይወት እያለ ሲከበር እና ሲወደድ ደስ ይላል
ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞ ) #በሰይፉ_ሾው
★ ከፊልምና ቴአትር ስራ በቃኝ ብዬ የተውኩት
ስለራበኝ ነው።
★ #ልጄስ ተከታታይ ድራማ በአለም አቀፍ ደረጃ
ታጭቶ ተሸልሟል።
★ ጀርባዬን ከ20 ዓመት በፊት ሰርጀሪ ተሰርቼው
የህክምና ስህተት ተፈፅሞብኛል።
★ ሰርጀሪውን አበላሽተው ስለሰሩኝ ቤት ከተቀመጥኩኝ
1 ዓመት ከ10 ወር ሆነኝ። አንድ ቴአትር ግን
ማስታገሻ እየወሰድኩኝ ነው የምሰራው።
★ ከህንድ የመጡ ሀኪሞች እኛ ጋር ና እንሰራሃለን
ብለውኛል።
★ ወታደር ቤት ገብቼ ሳይመቸኝ ወጣሁ። ከወታደር
ቤት ወጥቼ ወደትውልድ ሀገሬ ጅማ ድረስ
በእግሬ ተጉዣለሁ።
★ ቴአትር መስራት የጀመርኩት ጅማ ውስጥ
የምናገለግልበት ቤ/ክርስቲያን ነው።
★ ከዚህ በፊት ብየዳ ፣ ሸክም ( ወዛደርነት ) እና
የመንገድ አስፓልት ስራ ሰርቻለሁ።
★ በዚህ ሙያ ስትኖር ይከብድሃል።
★ የእኛ ስራ መድረክ ላይ ተጨብጭቦልህ በእግርህ
ወደ ቤትህ ትገባለህ።
★ ከጀርባ ህመሜ ጋር ተያይዞ በታክሲ መሄድ
አልችልም። በራይድ እየተመላለስኩኝ ነው
የምሰራው።
★ እንኳን ሰራሁት ብዬ የምኮራበት ስራ
ልጄስ ተከታታይ ድራማ ነው።
★ ከቴአትር እጅግ ወድጄው የሰራሁት ደግሞ
ሲራኖ ቴአትር ነው።
★ ከ10 በላይ ቴአትር ሰርቻለሁ። ፊልሞች
ደግሞ ወደ 20 ገደማ ሰርቻለሁ።
★ እኔ እስካሁን አልሰራሁም ወይ እንድል ያደረገኝ
ልጄስ ድራማ ነው።
አርቲስት ሚኪያስ መሐመድ ለዳኒ ፂሞ
100,000.00 ( መቶ ሺህ ብር ) ሰጥቶታል።
ሚኪ ባለታክሲው ይመችህ ✌
በተለያዩ የትወና ጥበቡ ያስደመመን
ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞን ) ለመርዳት
የምትፈልጉ ፦
1000343965037
CBE
ዳንኤል አሸናፊ
Share ሼር በማድረግም ምርጡን ተዋናይ
ሰው እንዲያግዘው እናድርግ 🙏
Dani Tsimo
ተዋናይ ዳኒኤል አሸናፊ ፦ ለሰጠኸን ምርጥ ስራዎች
እናመሰግናለን። ከህመምህ አገግመህ ወደሙሉ ጤንነትህ
እንድትመለስ ፈጣሪ ይርዳህ !
ዘሪሁን ተዝናኑ ከፃፈው ላይ የተወሰደ
Zerihun Teznanu
ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞ ) #በሰይፉ_ሾው
★ ከፊልምና ቴአትር ስራ በቃኝ ብዬ የተውኩት
ስለራበኝ ነው።
★ #ልጄስ ተከታታይ ድራማ በአለም አቀፍ ደረጃ
ታጭቶ ተሸልሟል።
★ ጀርባዬን ከ20 ዓመት በፊት ሰርጀሪ ተሰርቼው
የህክምና ስህተት ተፈፅሞብኛል።
★ ሰርጀሪውን አበላሽተው ስለሰሩኝ ቤት ከተቀመጥኩኝ
1 ዓመት ከ10 ወር ሆነኝ። አንድ ቴአትር ግን
ማስታገሻ እየወሰድኩኝ ነው የምሰራው።
★ ከህንድ የመጡ ሀኪሞች እኛ ጋር ና እንሰራሃለን
ብለውኛል።
★ ወታደር ቤት ገብቼ ሳይመቸኝ ወጣሁ። ከወታደር
ቤት ወጥቼ ወደትውልድ ሀገሬ ጅማ ድረስ
በእግሬ ተጉዣለሁ።
★ ቴአትር መስራት የጀመርኩት ጅማ ውስጥ
የምናገለግልበት ቤ/ክርስቲያን ነው።
★ ከዚህ በፊት ብየዳ ፣ ሸክም ( ወዛደርነት ) እና
የመንገድ አስፓልት ስራ ሰርቻለሁ።
★ በዚህ ሙያ ስትኖር ይከብድሃል።
★ የእኛ ስራ መድረክ ላይ ተጨብጭቦልህ በእግርህ
ወደ ቤትህ ትገባለህ።
★ ከጀርባ ህመሜ ጋር ተያይዞ በታክሲ መሄድ
አልችልም። በራይድ እየተመላለስኩኝ ነው
የምሰራው።
★ እንኳን ሰራሁት ብዬ የምኮራበት ስራ
ልጄስ ተከታታይ ድራማ ነው።
★ ከቴአትር እጅግ ወድጄው የሰራሁት ደግሞ
ሲራኖ ቴአትር ነው።
★ ከ10 በላይ ቴአትር ሰርቻለሁ። ፊልሞች
ደግሞ ወደ 20 ገደማ ሰርቻለሁ።
★ እኔ እስካሁን አልሰራሁም ወይ እንድል ያደረገኝ
ልጄስ ድራማ ነው።
አርቲስት ሚኪያስ መሐመድ ለዳኒ ፂሞ
100,000.00 ( መቶ ሺህ ብር ) ሰጥቶታል።
ሚኪ ባለታክሲው ይመችህ ✌
በተለያዩ የትወና ጥበቡ ያስደመመን
ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞን ) ለመርዳት
የምትፈልጉ ፦
1000343965037
CBE
ዳንኤል አሸናፊ
Share ሼር በማድረግም ምርጡን ተዋናይ
ሰው እንዲያግዘው እናድርግ 🙏
Dani Tsimo
ተዋናይ ዳኒኤል አሸናፊ ፦ ለሰጠኸን ምርጥ ስራዎች
እናመሰግናለን። ከህመምህ አገግመህ ወደሙሉ ጤንነትህ
እንድትመለስ ፈጣሪ ይርዳህ !
ዘሪሁን ተዝናኑ ከፃፈው ላይ የተወሰደ
Zerihun Teznanu
3 months ago
💍 ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ እና ባለቤቱ ቢታንያ በሰይፉ_ሾው ያደረጉት አስገራሚ ቆይታ እና ያልተሰሙ እውነታዎች! 💕
#ethiopia | ታዋቂው ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ እና ውብ ባለቤቱ ቢታንያ በሰይፉ ሾው ቀርበው ስለ ፍቅራቸው፣ ስለ ትዳራቸው እና ስለ ህይወታቸው ጣፋጭና አስቂኝ ገጠመኞችን አካፍለዋል። ከቆይታቸው የተወሰዱ ድንቅ ነጥቦች እነሆ፦
🎙 ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ...
* ⚽️ "የሰርጌ ቀን አርሰናል ዋንጫ ካልበላ አላገባም ብዬ ነበር!"
* 📺 "ሚዲያ ላይ ስለማታውቀኝ ነው የጠቀመኝ፤ ለእኔ እሷን ለማጥናት 6 ወር በቂ ነበር። ከውበቷ ውጪ አስተሳሰቧ 'ውይ' የሚያስብል ነው፤ በትውውቅ 4 ዓመት ሆኖናል።"
* 🎬 "ማስታወቂያ እንድትሰራ እኔ ነኝ በግድ ያስገባኋት፤ ፈጣሪ የሰጣትን ቁንጅና እና አቋም መጠቀም አለባት።"
* 👩ያ "እናትዬ ብዬ ነው የምጠራት።"
* 💼 "በጋዜጠኝነት ደመወዝ ብቻ ልትኖር አትችልም። ስራ እወዳለሁ፤ የተለያዩ ኢቨንቶችን እሰራለሁ።"
* 🍲 "የማይሰለቸኝ ምግብ ሽሮ ነው።"
* 📺 "ቀጥታ ስርጭት ዜና እያነበብኩኝ ወንበሩ ሰምጦብኝ ያውቃል! ካሜራ ማናችንም ከነካሜራው ከአውሮፕላን ላይ ወድቆብናል።"
* 🎶 "የሀገር ካስማ ከተሰኘው ዘፈን ፕሮዲውሰሮች አንዱ ነበርኩኝ። የቴዲ ታደሰን 'በቸር ይደር' እና የጥላሁንን 'አምሳሉ' ዘፈኖችን እወዳለሁ።"
* ⛰ "ጊሸን ሄጄ እንደመጣሁ ነው ፀሎቴ የሰመረልኝ። መስከረም 21 እኔም እናቴም የተወለድንበት ቀን ነው።"
* 🎤 "የሰርጌ ቀን ድምፃዊ ጎሳዬ፣ አብነት እና ዳዊት ይኖራሉ።"
👸 ባለቤቱ ቢታንያ ...
* 🏪 "እኔ ሱቅ እቃ ሊገዛ መጥቶ ነው የተዋወቅነው። ሰዎች እስኪነግሩኝ ድረስ ጋዜጠኛ መሆኑን አላውቅም ነበር።"
* 💍 "የ'ታገቢኛለሽ' ሰርፕራይዙ በጣም ደስ ይል ነበር።"
* 🐕 "አዳነ ውሻ አምጥቶልኝ ሰርፕራይዝ አድርጎኛል። 'አባትዬ' ብዬ ነው የምጠራው።"
* 👩❤️👨 "አዳነ ፍቅር መስጠት ይችላል፤ የተካነበት ነው። ልክ እንደ አባቴ አይነት ባል ነው ያገኘሁት።"
* 💭 "ሰዎች ተጋብተው ከሚጣሉ ይልቅ መጀመሪያ ተጣልተው ነው መጋባት ያለባቸው።"
* 🥩 "ጥሬ ስጋ እና ጭኮ እወዳለሁ፤ የንዋይ ደበበን 'አሜን' ዘፈን እመርጣለሁ።"
* 📱 "የእድል ቁጥሬ 6 ስለሆነ 6 ልጆች ቢኖሩኝ ደስ ይለኛል!
የአዴ እና የቢቱ ፍቅር ፍጻሜው ለሰርግ በቃ! አዴ አንተ ሰው አክባሪና ትሁት ጋዜጠኛ እንኳን ደስ አለህ። ለሁለታችሁም ዘላቂና ደስተኛ የትዳር ዘመን እንመኛለን! 🥂🎉
Via Zerihun Teznanu

6 months ago
ሀገራችን በሰላም ገብተናል ።
*******
የ9 ቀንና ሌሊት የዱባይ ቆይታችን በስኬት ተጠናቆ ትናንት ምሽት በስኬት ወደ ሀገራችንተመልሰናል ። በአጠቃላይ ሲታይ ጉዟችን እጅግ የተሳካ ነበር ። በዋንኛነት መጽሐፍን ለማስተዋወቅ ከአዲስ አበባ ዱባይ ደርሶ ለመመለስ ማቀድና ማሳካት ፣ እዚያ በነበረን ቆይታ ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረግናቸው ውይይቶችና የስራ ግንኙነቶች ፣ " ምን ሆኛለሁ ? " መጽሐፋችን እዚያ ባሉ ኢትዮጵያውያን ያለውን ቦታ ማወቅ ፣ የመጽሐፉ ሽያጭ ፣ አዳዲስ ወዳጆች ማፍራት ፣ ከኢትዮ ቪአይፒ ኤቨንትስ ጋር በ " ወደ ማዶ " የተጀመረውን ግንኙነት በመልካም ሁኔታ ማስቀጠላችንና በዱባይ ያሳለፍነው የመዝናኛ ጊዜያት ተዳምረው ጉዟችንን ስኬታማ አድርገውታል ። ሁሉም በላይ ከጓደኞቼ Yehualashet Zerihun እና Dereje Haile Shibeshi ጋር የነበረን ምርጥ ጊዜ ወዳጅነታችንን እንድናድሰው ረድቶናል ።
የኢትዮ ቪአይፒ ኤቨንትስ ስራ አስኪያጅ ወንድማችን መገስ አብዱልካፉር ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሳየን ወንድማዊ ፍቅር ከስራ ግንኙነት ያለፈ ነበር ። በድጋሚ ዱባይን እንድናስባት ያደረገን እሱ ነው ። ከምንገልጽበት ቃላት በላይ እናመሰግናለን ። ይህ ጉዞ እንዲሳካ ያደረጉልንን ፦
👉 ቴምር ፕሮፐርቲስ በፕላቲኒየም ደረጃ ፣
👉 ግራንድ አፍሪካ ሽልማት በ1ኛ ደረጃ ፣
👉 ኦሜጋ ኅብረት ስራ ማህበር በ1ኛ ደረጃ ፣
👉 ኢትዮጵያ ግሪን ሬስቶራንት - #ዱባይ በ2ኛ ደረጃ ስፖንሰር ሲያደርጉ ፣
👉 ኢትዮ ቪአይፒ ኤቨንትስ የጉዞው አጋር አስተባባሪ ናቸው ። ሁሉንም ከልብ እናመሰግናለን ።

ቱሪዝም ልጇን አጣች!
"ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
#ethiopia | የጋቶ ወንዝን እንደተሻገራችሁ የምታገኟት የኮንሶዎች መንደር ፍጨጫ ትባላለች፡፡ ከፍተኛ የአሸዋ ምርት የሚገኝበትን ካይሌ ወንዝ እንዳለፋችሁ ካራት ከተማ ትገባላችሁ፡፡
ዘሪሁንን የተዋወቅሁት ካረት፣ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ነበር።
ዱሮ ዱሮ የኮንሶ ብሔረሰብ የሚኖረው በ49 የተከለሉ አምባ መንደሮች ውስጥ ነበር፡፡ አሁን ሰባቱ አምባ መንደራት ፈርሰው 42ቱ ብቻ ቀርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 12ቱ መንደሮች የላይኛውና የታችኛው ዶከቱ፣ ታራ፣ ጋሞሌ፣ ቡሶ፣ ኦላንታ፣ መጨሎ፣ መጨቄ፣ ጎጫ፣ ሁሉሜ፣ ቡርኩዳና ቡርጆ የጥበቃ ከለላ ድንበር "ሦስቱ የጎሳ መሪዎች የሚያስተዳድሯቸው ‹‹የተቀደሱ ደኖች››፤ ጋሞሌ አምባ መንደር የሚገኘው ‹‹ሙራ ካላ››፣ በላይኛው ዶካቱ ‹‹ሙራ ባማሌ››፣ በፋሻ ‹‹ሙራ ቁፋ›› እንዲሁም ኩሬ ሃርዳ ዶከቱ፣ ሃርዳ መጨቄ፣ ሃርደ ዱራይቴና ሀርዳ ቡሶ (ጥንታዊ ባሕላዊ ኩሬዎች) የላቀ ዓለም አቀፍ ቅርስ እንዳላቸው ታምኖ በዩኔስኮ ተመዝግበዋል፡፡
ነፍሱ ይማርና ከኃይለመለኮት አግዘው ጋር
ኮንሶ አምባ መንደር በተደጋጋሚ ለሥራ ስንጓዝ ከሠራዊት ኮንሶ ጋር ዘሪሁን ግርማን አናጣውም ነበር።
የኮንሶ ልጅ፤ ዘሪሁን መምህራን ( እናቱና አባቱ ) መኖሪያ ቤት ከረት ከተማ፣ ኮንሶ ተስተናግደናል። ቤተሰቦቹ ከኮንሶ ወደ አርባምንጭ ተጉዘው መኖር እንደጀመሩ ነግሮኝ ነበር።
ዘሪሁን - ከዚህ በታች የላከልኝ መልዕክት ለአገርና ለሕዝብ አጋርቼለት ነበር።
"ዘሪሁን ግርማ #zerihun Girma ነኝ። የባህል የቱሪዝምና የሆስፒታሊቲ ጋዜጠኛ እና አማካሪ ከአስር /10/ አመታት በላይ በሬዲዮ ዘርፍ በዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም፣ በደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 እና በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የሬዲዮ ጣቢያዎች እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያን ባህል ቱሪዝም እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍን ሳስተዋውቅ እና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ኘሮግራሞችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ።
ነገር ግን የብዙ ወዳጆቼ እና የሬዲዮ አድማጮቼ ጥያቄ ያለኝን ልምድ እና ስለኢትዮጵያ በጉዞ ያወኳቸውን በምስል ማሳየት እችል ዘንድ በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንድመጣ ነበር።
ይሁንና ፈጣሪ የፈቀደው ነውና የሚሆነው አሁን ጊዜው ደርሷል።
ውብ ሀገርን ይዤ መጥቻለሁ!"
ውብ ሀገር
በኢሳት ቴሌቪዥን ከቅዳሜ፣ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓም - ዘወትር ቅዳሜ ምሽት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ ይቀርብ ነበር።
ዘርሁን ግርማ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አርበኛ ነበር። በድንገተኝ ሞት አጣነው።
የሀገራችን የሆስፕታሊትና ቱሪዝም አምባሳደር የሆነው ወንድማችን ዘሪሁን ግርማ በድንገተኝ ሞት ተለየን።
ዘሪሁን ግርማ የቱሪዝም ሞተር፣ ተጓዥ ጋዜጠኛ፣ የውብ ሀገሬ ቲሌቪዥን ፕሮግራም መሥራች፣ የቱሪዝም ባለሙያወች ድምፅ ነበር።
#ኮዞባቱ ኾራ አታ ኾንሶ ሰኔ 20-21/2017ዓ.ም በዓል አዘጋጅ ነበር።
ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው፣ በሀገሩ የሚኮራ፣ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ፣ ብዙ የሠራ፤ የታተረ የውብ ሀገር ጋዜጠኛ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አሳዝኖናል።
የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር በጋዜጠኛ ዘሪሁን ህልፈት መግለጫ አውጥቷል።
"...ቱሪዝም ልጇን አጣች፣ቱሪዝምን አውርቶ የማይጠግበው በሀገሩ የሚኮራው በሬድዮ እና በቲቪ የሀገራችንን ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ብዙ ለመስራት ብዙ ለመሮጥ ሀገሩን በሰፊው ለማስተዋወቅ የውብ ሀገር ብሎ የጀመረው የማህበራችን መስራች እና አባል ወንድማችን ጋዜጠኛ ዘሪሁን ግርማ ድንገተኛ ሞት እጅግ በጣም አዝነናል"
ዘሪሁን
ከሐያት 49 ወደ አርባምንጭ ከለሊቱ 7:00 ሰዓት አስከሬኑ በክብር ተሸኝቷል።
ዘሪሁን ግርማ ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ እግዚአብሔር ያጽናችሁ።
ነፍስ ይማር።

Comments