19 hours ago
በትግራይ የተከናወነው ፍፁም ህገወጥና እውቅና የሌለው ድርጊት ነው፦ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ
የቀድሞው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል፡፡
ጄኔራሉ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የትግርኛ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በክልሉ በህወሓትና “በአቶ መለስ ዜናዊ ስም ተገን” በማድረግ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ “የራስ አስተዳደር አዋቀርኩ” የሚለውን አካሄድ የተቃወሙት ጄኔራል ሳሞራ፣ ድርጊቱ ፍጹም ሕገ-ወጥና እውቅና የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህ ቡድን በአክሱም ከተማ ተሰብስቦ ያደረገውን ውሳኔ “ሕጋዊነት የጎደለው መንግሥት ምስረታ” ሲሉ የገለጹት ጄኔራሉ፣ መጀመሪያ በአቶ ጌታቸው ረዳ በመቀጠልም በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመሩትን ጊዜያዊ አስተዳደሮች ሥራቸውን እንዳይሠሩና ሕዝቡን ወደ ምርጫ እንዳይወስዱ እንቅፋት ሲፈጠርባቸው መቆየቱንና በመጨረሻም ማኅተምና የአሠራር መሣሪያዎችን በመቀማት የማባረር ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ፖለቲከኞች ዋና ዓላማ ሥልጣን ብቻ መሆኑንና ይህንን ሥልጣን የሚፈልጉት ከተጠያቂነት ለማምለጥ እንደሆነ የገለጹት ጄኔራሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በትዕግሥትና በሰላማዊ መንገድ እየያዘበት ያለውን አካሄድ አድንቀዋል፡፡
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተፈረመበት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ደስታውን የገለጸ ቢሆንም፣ በክልሉ ያሉት ፖለቲከኞች ግን ወደ ሥልጣን ሽሚያ ማምራታቸውን ጄኔራሉ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ስላለው “የወጣቶች አፈሳ” ሲያብራሩም፣ ድርጊቱ ከሻዕቢያን የድሮ የትግል ስትራቴጂ የተቀዳ መሆኑንና ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የማተራመስ ስትራቴጂውን እንዳልቀየረ ገልጸዋል፡፡
ከፌዴራል መንግሥት በጀት እየወሰዱ መንግሥትን “ጠላት” ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን የጠቀሱት ጄኔራል ሳሞራ፣ የክልሉ አመራሮች “ከምርጫ በኋላ መንግሥት ይወጋናል” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለወጣቶች አፈሳ እየተጠቀሙበት እንደሚገኝና በአንጻሩ መንግሥት ጉዳዩን በጦርነት ለመፍታት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
ጄኔራል ሳሞራ ለትግራይ ሕዝብና ለወላጆች ባቀረቡት ጥሪም የወላጆች ስጋት የሆነውን የወጣቶች አፈሳ ለመግታት ወላጆች ተደራጅተው ሊቃወሙትና “ልጆቻችንን አንሰጥም” ብለው ሊታገሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ምርጫ በተካሄደበት በዚህ ወቅት የትግራይ ሕዝብ እንዳይመርጥ መከልከል እንደሌለበትና በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ በመግለጽ የሕዝቡ ዋና ዋስትና እራሱ ሕዝቡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
EBC

1 day ago
"እውነቱን ለመናገር፣ ከሥልጣን በመነሳቴ የተለየ ቅሬታ ወይም ቁጣ የለኝም። በፖለቲካችን ውስጥ የተወሰነ ጤናማ አካሄድ ለማስገባት የምችለውን ያህል ጥሬያለሁ፤ ምናልባትም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በከፊል አልተሳካልኝም (ክሽፏል)። ስለዚህ እኔ እንደማስበው፣ ከሥልጣን የምነሳበት ጊዜው ደርሶ ነበር። ምክንያቱም የሥልጣን ዘመኑ የሁለት ዓመት ሲሆን፣ ያ የሁለት ዓመት ጊዜ ደግሞ አብቅቶ ነበር። ይህንን የምልበት ምክንያት... ከእኔ ሥልጣን የተረከበው ሰው እኔን ለመተካት ያላደረገው ጥረት አልነበረም። ስለዚህ መናደድ ካለብኝ፣ ከማንም በላይ በእሱ ላይ መናደድ ነበረብኝ፤ ነገር ግን ጉዳዩ የኔ መናደድ አይደለም።
"ዋናው ነጥብ ተቋማት እስካሉ ድረስ ነገሮች አስቀድመው የሚታወቁበትና የተረጋጉ የሚሆኑበት ሥርዓት እንዲኖር የተወሰኑ ሕጎችን ማክበር ይጠይቀናል። አሁን ያለው የህወሓት አመራር ያደረገው ነገር ግን መፈንቅለ-ሥልጣን በማካሄድ ራሱን እንደ ሕጋዊ አካል አድርጎ መሾም ነው፤ ነገር ግን ሕጋዊ አይደለም። በመሆኑም ይህ አካል ለነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልገውን አስተማማኝ ጸጥታ ማረጋገጥ አይችልም።"
ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለቲአርቲ ከሰጡት ቃለምልልስ

2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ወራትን ያስቆጠረውን ጦርነት ለማቆም ተጀምሮ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ድርድር ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ያለ ምንም መሻሻል መጓተቱን ተከትሎ፣ አሜሪካ እና ኢራን አዳዲስ ጥቃቶችን መለዋወጣቸው ተነግሯል። የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ የራስ መከላከል ጥቃቶችን መፈጸሙን እና ወደ መርከቦች እንዲሁም የባህረ ሰላጤው ሀገራት የተተኮሱ የባሊስቲክ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል። የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) በሆርሙዝ ስትሬት በምትገኘው ቄሽም ደሴት ላይ የፈጸመው ጥቃት፣ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ለሞከረችው ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ መሆኑን ገልጿል። በዚህም የኢራን ወታደራዊ የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ዒላማ የተደረገ ሲሆን፣ በሕጋዊ መንገድ ቀጠናውን እያቋረጡ በነበሩ የሲቪል መርከበኞች ላይ የተተኮሱ ሦስት ድሮኖችን አሜሪካ አክሽፋለች። በተጨማሪም ወደ ኩዌት የተተኮሱ ሁለት የኢራን ሚሳኤሎች መንገድ ላይ ሲከሽፉ፣ ወደ ባህሬን የተተኮሱ ሦስት ሚሳኤሎች ደግሞ በአሜሪካ እና በባህሬን የአየር መከላከያ ኃይሎች መክሸፋቸው ተገልጿል።
በበኩሏ ኢራን ለአሜሪካ ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን በመጠቀም በአንድ የቀጠናው ሀገር ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና ሄሊኮፕተሮች ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) የሆርሙዝ ስትሬትን ደህንነት ማወክ በአሜሪካ ጦር ላይ ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ሲልም አስጠንቅቋል።
ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ሚያዝያ 13 የጀመረውን የሆርሙዝ ስትሬት የባህር ላይ እገዳ አካል በማድረግ፣ ወደ ኢራኗ ኻርግ ደሴት በማምራት ላይ በነበረችው እና በቦትስዋና ባንዲራ በምትጓዘው 'ኤም/ቲ ሌክሲ' በተሰኘች ባዶ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጿል። የመርከቧ ሰራተኞች በ24 ሰዓታት ውስጥ የተሰጣቸውን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ባለመቀበላቸው፣ የአሜሪካ አውሮፕላን በመርከቧ የሞተር ክፍል ላይ የሄልፋየር ሚሳኤል የተኮሰ ሲሆን፣ አሜሪካ ይህ ጥቃት ሲፈጸም የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ይፋ አድርጋለች። የባህር ላይ እገዳው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 6 የንግድ መርከቦች ከጥቅም ውጪ ሲሆኑ፣ 122 መርከቦች ደግሞ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል።
ይህ ውጥረት የተባባሰው፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሳምንት ተቺዎቻቸው ዘና እንዲሉ መክረው፣ ኢራን ስምምነት ላይ መድረስ እንደምትፈልግ እና ይህም ለአሜሪካ ጥሩ እንደሚሆን በተናገሩበት ወቅት ነው። የሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሊኖር ስለሚችለው የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ማስተካከያው የሆርሙዝ ስትሬትን ጉዳይ፣ ከፍተኛ ማዕድን ያለው ዩራኒየምን ከኢራን ማውጣትን እና የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም በተመለከተ አዲስ ድርድር መክፈትን ያካተተ ነው። ሆኖም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኢል ባጋኢ ሰኞ ዕለት በሰጡት ምላሽ፣ ይህ ጉዳይ በድርድሩ ጠረጴዛ ላይ እንዳልነበረ ገልጸው፣ ዋሽንግተን ሁልጊዜ አቋሟን እንደምትቀይር እና አዳዲስ ወይም የሚጋጩ ፍላጎቶችን እንደምታቀርብ ከሰዋል።
ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ አሜሪካ ስትሬቱን ክፍት ለማድረግ ስትል ለኢራን ማዕቀብ የማንሳት ጥያቄን አላቀረበችም ብለዋል። ማንኛውም ማዕቀብ የማንሳት ጉዳይ ማዕቀቦቹ በመጀመሪያ ከተጣሉበት ምክንያት፣ ማለትም ከኒውክሌር ፕሮግራማቸው ጋር የተያያዘ ቅድመ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ነው በማለት አስረድተዋል። ኮሚቴው ውስጥ ካሉ ሴናተሮች ጋር በነበራቸው ውጥረት የበዛበት የቃላት ልውውጥ ወቅትም፣ ሚኒስትሩ ጦርነቱ አብቅቷል ማለታቸው ተዘግቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ጦር በመካከለኛው ምስራቅ የተሰነዘሩ በርካታ የኢራን ባሊስቲክ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን በተሳካ ሁኔታ ማክሸፉን እና በቄሽም ደሴት ላይ የራስን መከላከል የአየር ጥቃት መፈጸሙን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ጁን 2 ቀን 2026 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ኢራን ወደ ቀጠናው ጎረቤት አገራት በርካታ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ያስወነጨፈች ቢሆንም፣ ሁሉም የታለሙበትን ግብ ሳይመቱ ቀርተዋል። ወደ ኩዌት የተተኮሱ ሁለት የኢራን ሚሳኤሎች ግባቸውን ሳይመቱ መንገድ ላይ የተከሰከሱ ሲሆን፣ ወደ ባህሬን የተተኮሱ ሦስት ሚሳኤሎች ደግሞ በአሜሪካ እና በባህሬን የአየር መከላከያ ኃይሎች አማካኝነት ወዲያውኑ በአየር ላይ እንዲከሽፉ ተደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የCENTCOM ኃይሎች ኢራን በሕጋዊ መንገድ ቀጠናዊ ባህርን እያቋረጡ በነበሩ ሲቪል መርከበኞች ላይ የሰነዘረቻቸውን ሦስት የአጥፊ ድሮኖችን መትተው ጥለዋል። የአሜሪካ ጦር ለተሰነዘረበት ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በቄሽም ደሴት ላይ በሚገኘው የኢራን ወታደራዊ የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ የተመጣጠነ የአየር ጥቃት ፈጽሟል።
በዚህ የጋራ የመከላከል እርምጃ ወቅት በየትኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ አባላት ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን፣ ማዕከላዊ ዕዙ በአሁኑ ወቅት እየተተገበረ ባለው የተኩስ አቁም ስምምነት ወቅት ሊሰነዘሩ የሚችሉ ያልተገቡ የኢራን ትንኮሳዎችን ለመመከት እና ለመከላከል ኃይሎቹ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

Sponsored by
Surafel
3 days ago
ምርጫው የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ነው፦ የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
#ethiopia | የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደትን መጠናቀቁን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ምርጫው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ግልጽነት እና ፍትሐዊነት የተንጸባረቀበት፣ በመራጩ ሕዝብና በተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ያገኘ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው እንዳመለከተው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ምርጫ መንግሥት በከተማዋ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበትና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ሌላኛው ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ አልፏል።
ከእነዚህም መካከል እንደ ትልቅ ጅምር የሚወሰደው የዲጂታል የእጩዎች ምዝገባ ሒደት አላስፈላጊ መጉላላትን የቀነሰ እና የእጩዎችን መረጃ እና ደኅንነት ያረጋገጠ የአሰራ ግልፅነትን የፈጠረ መሆኑ በምርጫው ሂደት ከታዩ ዐበይት አዎንታዊ ሁነቶች መካከል እንደሆነ ተመላክቷል።
በምርጫው ዕለት መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ያለምንም ቀስቃሽ በነቂስ በመውጣት ድምፅ መስጠታቸውን የገለጸው ምክር ቤቱ፣ በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች እና አረጋውያን ያሳዩት ከፍተኛ ተነሳሽነት ሂደቱን ይበልጥ እንዳደመቀው አብራርቷል።
ከምርጫ ጣቢያዎች የሚመጡ የአሠራር ችግሮችን በጋራ በመገምገም፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከከተማው አመራሮች ጋር በቀጥታ በመነጋገር አፋጣኝ የእርምት እርምጃ መወሰዱ በፓርቲዎች እና በአስፈፃሚ አካላት መካከል መተማመንን ማጎልበቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም የከተማዋ የጸጥታ አካላት ያለምንም ወገንተኝነት፣ ፍጹም ገለልተኛ በሆነ መንገድ የምርጫ ጣቢያዎችን እና የመራጩን ሕዝብ ደኅንነት በመጠበቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።
በሂደቱም ምንም ዓይነት የጸጥታ መደፍረስም ሆነ የምርጫ ሕግ መጣስ ሳይኖር መጠናቀቁ የከተማዋን ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ከፍተኛ የበስለት ደረጃ ያሳየ "የአዲስ አበባ ሞዴል" መሆኑ ተነግሯል።
የድምፅ መስጠት ሂደቱ በስኬት ተጠናቅቆ ወደ ቀጣዩ የድምፅ ቆጠራ እና ውጤት ማደራጀት ምዕራፍ መሸጋገሩን የጠቀሰው ምክር ቤቱ፤ የምርጫ ቦርድ ሕጋዊ አሠራርን መሠረት አድርጎ የከተማውን ውጤት በኦፊሴላዊ መልኩ እስኪገልጽ ድረስ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት እና ደጋፊዎች ፍጹም በሆነ ትዕግሥት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #ethiopiaprevails #peace #ምርጫ

5 days ago
#ምርጫ2018
በምርጫው ድምፅ የተሰጠባቸውን ወረቀቶች ዋጋ አልባ የሚያደርጓችው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው ?
1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸ ከሆነ፣
2. ለምክር ቤቱ ሊመረጥ ከሚቻለው ተመራጮች ቁጥር በላይ ላላቸው ዕጩዎች ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣
3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣
4. መራጩ ማንን አንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡
Seledadotio

10 days ago
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖቹ አክሲዮናቸውን በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መሸጥ፣ መግዛት እና ማስተላለፍ እንደሚችሉ በታላቅ ደስታ ያበስራል!
በዛሬው ዕለት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ኩባንያው አስፈላጊ ሕጋዊ አሠራሮችን በማሟላት ባለአክሲዮኖች በሁለተኛ ገበያ (ESX) አክሲዮኖችን መግዛት፣ መሸጥና ማስተላለፍ እንዲጀምሩ ዝግጁ ማድረጉን በይፋ አብስረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን፤ አንጋፋውን የሀገራችንን ተቋም ወደ አክሲዮን ማኅበር በማዛወር ዜጎችን የጋራ ሀብት ባለቤት ለማድረግ፣ የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ ለማጠናከርና የጋራ ዕድገትን ለማፋጠን የተወሰደው እርምጃ ታሪካዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ባለፉት ወራት በተከናወነ መጠነ-ሰፊ የማጣራት ሥራ ከ47,377 ባለአክሲዮኖች ውስጥ 45,366ቱ (95.8 በመቶ) ምዝገባቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ይህም በገንዘብ ሲሰላ 3.04 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 10.1 ሚሊዮን አክሲዮኖች ለግብይት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።
በሌላ በኩል መረጃ ያልተሟላላቸው 1,646 ባለአክሲዮኖች መረጃቸውን በአፋጣኝ እንዲያሟሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ በአክሲዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ብቁ ያልሆኑ 248 የውጭ ዜጎች ክፍያም በአሠራሩ መሠረት ተመላሽ ይደረጋል።
በዕለቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዋናዮች በተገኙበት የአክሲዮን ግብይት ማስጀመሪያ የደወል ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግብይትም በሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያው በይፋ ተከናውኗል። በተጨማሪም ኩባንያችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በይፋ መመዝገቡን በማስመልከት የምስክር ወረቀቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ዶክተር ጥላሁን እስማኤል ተረክበዋል።
ባለአክሲዮኖች አክሲዮናቸውን ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው አገበያዮች ወይም የኢንቨስትመንት ባንኮች ዘንድ በመቅረብ የንግድ አካውንት መክፈት ይኖርባቸዋል።
በመጪው በጀት ዓመት የፋይናንስ ኦዲቱ እንደተጠናቀቀ በሚጠራው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ (AGM) ላይ የትርፍ ክፍፍል መጠን ተወስኖ ይፋ ይደረጋል። የባለቤትነት ድርሻቸውን ሂደት ያጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች፤ የባለቤትነት መብታቸው ከያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የሚጠበቅላቸው ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ፦ https://bit.ly/4nROnuL
#ethiotelecom #ecma #capitalmarket #esx #csd

የሕልውና ማኅተም እና የትውልድ ጥሪ
*****************
ጥንታዊት እና ገናና ሀገር ኢትዮጵያ በታሪኳ ማህደር በርካታ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሥርዓት ሽግግሮችን አስተናግዳለች።
በዘውዱ ሥርዓት፣ ጠንካራ ማዕከላዊነትን፤ በደርግ ወታደራዊ ሶሻሊዝም የ17 ዓመታት ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ግጭትን እንዲሁም ከዚያ በኋላ በነበሩት ሦስት አሥርት ዓመታት ተፎካካሪዎችን በጠላትነት በሚመለከት አግላይ ትርክት የታጠረ የልማታዊ መንግሥት አውራ ፓርቲ ሥርዓትን አሳልፋለች።
እነዚህ መዋቅራዊ ስብራቶች ዛሬም ድረስ ከብርቱ ቁጭት ጋር ትልቅ ትምህርት ጥለውልን አልፈዋል።
አሁን የተጀመረው ሀገረ መንግሥቱን በጽኑ እና በማይናወጥ መሠረት ላይ የመገንባት ሂደት እንዲጠናከር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ እና ወሳኝ የሽግግር ምዕራፍ ነው።
ዴሞክራሲዋን በማዳበር ሂደት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ታካሂዳለች።
ይህ ምርጫ ተራ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ብቻ አይደለም። ይልቁንም የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነት የማፅናት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር እና የዜግነት ክብርን በዓለም ፊት ከፍ የማድረጊያ ታላቅ ብሔራዊ መድረክ ነው።
የዚህ ታሪካዊ ምርጫ የመጀመሪያውና ደማቁ ስኬት የተመዘገበው በሕዝባችን ነቂስ ተሳትፎ እና ታይቶ በማይታወቅ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ነው።
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት፣ በአጠቃላይ ከ50.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል።
ይህ አስደናቂ እና ታሪካዊ ቁጥር ሕዝባችን የድምፅ መስጫ ሳጥንን ብቸኛው ሰላማዊ የለውጥ እና የጋራ ሀገር ግንባታ መሣሪያ አድርጎ በሙሉ ልብ መቀበሉን ያረጋግጣል።
ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከግጭት እና ብጥብጥ ይልቅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣንን ማሸጋገር የተሻለ እና ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በማመን የምርጫ ካርዳቸውን መያዛቸው ሀገራችን ለደረሰችበት የፖለቲካ ብስለት ትልቅ ማሳያ ነው።
ይህ ሰፊ ሕዝባዊ ተሳትፎ የምርጫውን ተዓማኒነት እና ሕጋዊነት ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ የሚመሠረተውን የሕዝብ ውክልና ይበልጥ ጽኑና ፍትሐዊ ያደርገዋል።
ከሁሉም በላይ፣ ይህ ምርጫ በተጨባጭ እየተካሄደ ያለው የተጀመረውን የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳለጥ እና ለማጠናከር ነው።
እውነተኛ የሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚረጋገጠው ተቋማት ሕዝባዊ ይሁንታን ሲጎናጸፉ እና ማዕከላዊው መዋቅር ሰላምን ሲያሰፍን ነው።
በምርጫው የሚሰጠው እያንዳንዱ ድምፅ የሀገራችንን መዋቅራዊ ጽናት በማጠናከር በኩል እንደ ሕልውና ማኅተም ያገለግላል።
የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በጽናት ለመምራት፣ የዜጎችን ማኅበራዊ ውል ለማደስ እና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚያግዝ የዜጎች ውል ነው።
ስለሆነም ሀገራችን በጥልቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ከጀመረቻቸው የብሔራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ፣ ይህ ምርጫ ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠሪያ እና ያለፉ የታሪክ ቁርሾዎችን በዘላቂነት የመፈወሻ ትልቁ መሣሪያ መሆን አለበት።
የምርጫው ውጤት ሕዝባዊ ውክልናን ምሉዕ በማድረግ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ለሚደረጉ ሀገራዊ ምክክሮች እውነተኛ የሕግና የሞራል መሠረት ይጥላል።
ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሁላችንም የጋራ የቤት ሥራ እና የታሪክ አደራ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ዘላቂ ፅናት የሚረጋገጠው የምርጫ ጣቢያዎችን ሰላም በጋራ ስንጠብቅ፣ ተስፋ ከመቁረጥ እና ከዳር ተመልካችነት ወጥተን የዜግነት ድርሻችንን ስንወጣና እያንዳንዱ መራጭ በነፃነትና በደኅንነት ድምፁን ሲሰጥ ብቻ ነው።
ያለ ሰላም እና ማኅበራዊ መግባባት የሚደረግ ምርጫ ሙሉ ትርጉም ሊኖረው እንደማይችል አስቀድመን ተገንዝበን መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራት እና መላው ሕዝብ ሁላችንም ለሂደቱ ፍትሐዊነት፣ ግልጽነት እና ሰላማዊነት ዘብ መቆም አለብን።
ኑ! የታሪክ ስብራታችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እና በድምፅ መስጫ ሳጥን እንጠግን! በእያንዳንዱ ዜጋ ልቦና ውስጥ እውነተኛ የእኩልነት፣ የሰላም እና የፍትሕ ተስፋን እንዝራ።
ለሀገራችን መፅናት እና ለዴሞክራሲያችን ማብብ፣ የሀገረ መንግሥታችንን ምሰሶዎች ይበልጥ ለማጠንከር ሁላችንም በጋራ እንረባረብ።
ይህ ምርጫ ታሪካዊ ክብር እና የትውልድ ጥሪ ነው!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #politics #democracy #ebc

11 days ago
የታክስ ተመላሽ ክፍያ በጊዜ ገደቡ ካልተፈጸመ ባለሥልጣኑ ለከፋዩ ወለዱን ጨምሮ እንዲከፍል የሚያስገድድ መመሪያ ወጥቷል።
የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ተመላሽ አሰጣጥ ሥርዓትን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለመምራት ያስችላል ያለውን "የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደረግበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1132/2018" አውጥቷል።
ይህ አዲስ መመሪያ የወጣው ቀደም ሲል የነበረው የታክስ አዋጅ ተሽሮ በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 መተካቱን ተከትሎ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የታክስ ተመላሽ አገልግሎትን የታክስ ከፋዮችን የስጋት ደረጃ መሠረት ባደረገ መልኩ ዘመናዊ ለማድረግ ነው።
መመሪያው የታክስ ተመላሽ ጥያቄ የሚያቀርቡ ከፋዮችን በሦስት ዋና ዋና የስጋት ደረጃዎች የሚከፍል ሲሆን፣ ይህም የኦዲትና የማጣራት ሥራው በታማኝ ከፋዮች ላይ የሚፈጥረውን እንግልት ለመቀነስ ያለመ ነው ይላል።
በዚህም መሠረት ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ያላቸው ከፋዮች ሰፊ ኦዲት ሳይደረግባቸው በተፋጠነ ሁኔታ ተመላሽ የሚያገኙበት ሥርዓት ሲዘረጋ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ላይ የሚገኙ ከፋዮች ደግሞ እንደሁኔታው ዝርዝርና ጥብቅ የሰነድ ማጣራት እንዲሁም የኦዲት ምርመራ ይደረግባቸዋል።
ይህም በመንግሥት ገቢ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና ተገቢው የታክስ ተመላሽ ለትክክለኛው ከፋይ መድረሱን ለማረጋገጥ ይረዳል ይላል።
በመመሪያው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት፣ በዜሮ የማስከፈያ ልክ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ አምራቾች፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወርቅ ለሚያቀርቡና ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካፒታል ዕቃ ግዥ ለፈጸሙ ከፋዮች ልዩ ትኩረት ሰጥቷል።
በተለይም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተመርጠው ወደ ውጭ ላኪነት የተሰማሩ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ከመላካቸው በፊት በሀገር ውስጥ ለገዟቸው ግብዓቶች የከፈሉት ታክስ በሰባት ቀናት ውስጥ የሚመለስበት "የተፋጠነ የተመላሽ ሥርዓት" ተዘርግቷል።
ሌሎች መደበኛ የተመላሽ ጥያቄዎች ደግሞ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው በአርባ አምስት ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኙ በመመሪያው ተደንግጓል።
የታክስ ተመላሽ ጥያቄ የሚያቀርቡ አካላት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ጥብቅ ቅድመ ሁኔታዎችም በመመሪያው የተካተቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግብይቱ የተፈጸመባቸው ሕጋዊ ኦርጅናል ደረሰኞች፣ የባንክ ክፍያ ማረጋገጫዎችና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ይገኙበታል።
መመሪያው በተለየ ሁኔታ ካስቀመጣቸው ነጥቦች መካከል፣ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በላይ የሆኑ ማናቸውም ግብይቶች በባንክ በኩል ካልተፈጸሙና የጥሬ ገንዘብ ግብይት ገደብን ካላለፉ ለታክስ ተመላሽ ጥያቄ ተቀባይነት እንደማይኖራቸው በግልጽ አስፍሯል።
የታክስ ባለሥልጣኑ (ገቢዎች ሚኒስቴር) ተመላሽ ሊደረግ የሚገባውን ገንዘብ በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይከፍል ከዘገየ፣ ለከፋዩ የወለድ ክፍያ የመክፈል ግዴታ የሚኖርበት መሆኑን መመሪያው ያዛል።
ወለዱ የተመላሸ ሒሣብ መከፈል ከነበረበት አግባብነት ካለው ጊዜ መጨረሻ ጀምሮ ተመላሹ ሒሣብ እስከተከፈለ ድረስ ላለው ጊዜ የሚሰላ ሲሆን የወለድ ምጣኔውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባንኮች የንግድ ብድር የሚሰጡበት ከፍተኛው የወለድ ምጣኔ መሰረት ይሆናል፡፡
ወለዱን ለመክፈል አግባብ ላለው ፍ/ቤት ቀርቦ የተሰጠ ውሳኔ ማስረጃ በማያያዝ ውሳኔው በተሰጠበት በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ መቅረብ አለበት፤በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ ጥያቄ መብቱ እንደተወ እንደሚቆጠር መመሪያው ደንግጓል፡፡
ይህ መመሪያ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ የጸደቀ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከገቢዎች ሚኒስቴር አረጋግጧል።Via : tikvah

የሀገራችን የነገ ተስፋ፤ በካርዳችን የሚፃፍ ታሪክ
*******************
( የዕለቱ መልዕክት)
በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ሀገራችን በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመጓዝ የጀመረችው ታላቅ ጉዞ መገለጫ ነው። ስልጣን በሕዝብ ድምፅ ብቻ የሚገኝበት አዲስ ምዕራፍ ነዉ፡፡ ይኽ ደግሞ የፖለቲካ ልሂቃን ብቻ ሳይሆኑ ተራው ዜጋም የስልጣን ባለቤትነቱን ተረድቶ የዲሞክራሲ ባህልእየተለማመደ መምጣቱን የሚያሳይ የብስለት መለኪያ ነው።
ምርጫ ዜጎች የሀገራቸዉ የመጨረሻ የስልጣን ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበትና የወደፊት እጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚቀርጹበት የዲሞክራሲ መድረክም ነው።
በዘንድሮው ምርጫ ለመምረጥ ካርድ የወሰዱ መራጮች እያሳዩት ያለው ዝግጅት፣ የሚመርጡትን ፓርቲዎች ፖሊሲና ስትራቴጂ በጥሞና የመገምገም ጥረት፣ ለሀገራዊ ጉዳይ ያላቸውን የላቀ ኃላፊነት ያንጸባርቃል። ድምፅ መስጠት፣ የአንድ ጊዜ የዜግነት ግዴታ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የራስን መብት ማስከበሪያና የሀገርን የነገ አቅጣጫ መወሰኛ ታላቅ ኃይል ነው።
በምርጫ የሚረጋገጥ የፖለቲካ መረጋጋት ለኢኮኖሚ እድገት ብቸኛው መሰረት ነው። ሰላምና መረጋጋት ለውጭ ኢንቨስትመንት መተማመኛ፣ ለልማት ደግሞ ዋስትና ናቸው። በሕዝብ የተመረጠ ሕጋዊ መንግስት መኖር፣ የኢኮኖሚው ሥርዓት በተረጋጋና በታቀደ መንገድ እንዲራመድ ያስችላል። ኢትዮጵያ በምርጫ ትርክቷ እየገነባች ያለችው ይህ አዲስ የዲሞክራሲ እሳቤ ሀገርን በጋራ የምናሻግርበት የጋራ ድልድይ ነው።
ግንቦት 24 ቀን የሚካሄደው 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ እውነተኛ የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የተከፈለ ታላቅ ዋጋ ውጤትም ነው። አሁን ኳሱ ወደ ዜጎች እጅ ተሻግሯል። በእጃችን ያለው ካርድ የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የሚወስን የወርቅ ቁልፍ ነው።
መንግስት ተቋማዊ ነጻነትን በማረጋገጥ የጣለውን መሰረት በንቃት በመሳተፍ ማጽናት የዜጎች ታላቅ ኃላፊነት ነው። ስለሆነም እያንዳንዱ ካርድ የወሰደ ዜጋ፣ ግንቦት 24 ቀን ምርጫ ጣቢያ በመሄድ፣ በነጻነት ድምፁን በመስጠት ለዴሞክራሲ በህል መጎልበት የበኩልን ማበርከት ይጠበቅበታል፡፡
የምርጫ ድምፅዎ የሀገርዎ የነገ ተስፋ ቃል ነው። ምርጫችንን በንቃት መሳተፍ፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማስጠበቅ ይገባናል። ካርድዎ የሀገርዎ ዋስትና ነው። ዛሬ የምንመርጠው፣ ነገ የምንወርሰውን ኢትዮጵያ ነው። ዲሞክራሲያችንን በድምፃችን እናጸናለን!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

ስለ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሒደት አዋጁ ምን ይላል?
****************
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ 1162/2011፤ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሒደት ግልጽነትና ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በዝርዝር ያስቀምጣል።
በመመሪያው መሠረት የድምፅ አሰጣጥ ሥራው ከመጀመሩ በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ወኪሎች እንዲሁም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት፣ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው መገኘት ይኖርባቸዋል።
የምርጫ ጣቢያው ኃላፊም የድምፅ መስጫ ሳጥኑ ባዶ መሆኑን ለእነዚሁ አካላት በግልጽ ካሳየ በኋላ ሳጥኑ በሕጋዊ ማሸጊያ ታሽጎ ሁሉም በሚያዩትና ቅርብ በሆነ ስፍራ እንዲቀመጥ ይደረጋል።
በመጨረሻም ስለ ሒደቱ አጀማመር ቃለ ጉባኤ ተይዞ ቦርዱ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ቅፅ ላይ መረጃው ተሞልቶ ሲጠናቀቅ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በይፋ ይጀመራል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #election2026 #ethiopia

14 days ago
ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ዓለማችን የተከበበች እና 71 በመቶዋም የውኃ አካል ሆኖ እያለ ኢትዮጵያችን ለምን የባህር በር ተነፈገች? ውኃ እንዲህ በበዛበት ዓለም ላይ እያለን፣ ለምን ከባህር በር ተገለልን?
ከቀይ ባህሩ የአሰብ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ እያለን ለምን ውኃውን እንዳናይ ተከልክለን የጂኦግራፊ እስረኛ ሆንን?
ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ ሲነወር የቆየ የባህር በር ጥያቄ አላት፡፡ ጥያቄው የብሔራዊ ጥቅም፣ የደህንነትና ህልውና ጉዳይ ነው፡፡
የባህር በር ከባህር ላይ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶችንና ተጋላጭነትን ለመከላከል ያግዛል፡፡
አሁን አሁን በቀይ ባህር ቀጣና በርካታ ኃያላን የኃይል ፉክክርና ጂኦ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል፡፡
አይበለውና ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር አጥፊ የህልውና ሥጋት የሆነ የጦር መሣሪያ ቢጠመድባት፣ የባህር በር ስለሌላት እንዴት አድርጋ ነው ራሷን መከላከል የምትችለው?
ዓለም የባህር በር ተጠቃሚነት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጋለች፡፡
ለዚህ መፍትሄ ይሆናል የተባለው የዓለምን የባህር በር አጠቃቀም የሚወስነው የተባበሩት መንግሥታት የባህር አጠቃቀም ስምምነት በፈረንጆቹ 1982 ነበር ለሀገራት ፊርማ ይፋ ሆኖ በ1994 ወደ ሥራ የገባው፡፡ ኢትዮጵያም ሕጉን በፈረንጆቹ 1984 ፈርማለች፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ ለሕጉ ተገዢ ብትሆንም እንደ ኤርትራ፣ አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ሶሪያን ጨምሮ 15 የዓለም ሀገራት ስምምነቱን አልፈረሙም፤ በነጻነት ግን ይጠቀማሉ፡፡
በዓለም አቀፉ ሕግ ሀገራት የባህር በር የመጠቀም መብት ቢኖራቸውም፣ በነጻነት ወደብ የመጠቀምም ሆነ በባህር የመንቀሳቀስ መብታቸው ግን በጂኦግራፊ የተገደበ ሆኖ ዘልቋል፡፡
በዚህም ምክንያት የጎረቤት ሀገራትን ወደብ ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራት በሌሎች ፍላጎቶችና ስሜት ጫና ስር እንዲወድቁ አድርጓቸዋል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የብሔራዊ ደህንነት ስጋትም ይደቅናል፡፡
ኢትዮጵያም ይህ ኢ-ፍትሀዊነት ነው በሚል በጠቅላይ ሚኒስትሯ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አማካኝነት ጥያቄ በማንሳት ጉዳዩን የዓለም አጀንዳ አድርጋለች፡፡
ጉዳዩም የዓለም አቀፍ የፍትሓዊ ተጠቃሚነትና የባለቤትነት እንዲሁም የሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዓለም አቀፉ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ፊትም የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
ሀገራችን የባህር በር ስለሌላት፣ የጎረቤት ሀገራት የባህር በሮችን እና ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ ይህ ደግሞ የወጪ እና ገቢ ምርት እንቅስቃሴዋ እና የምርቶች ዋጋ ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና እያስከተለባት ነው፡፡
የባህር በር የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ እና የውጭ ንግድ የሚወስን ወሳኝ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ነው። በርካታ የወደብ፣ የጉምሩክ እና የሎጂስቲክስ የስራ እድሎችንም ለዜጎች ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ ቀጥታ የባህር በር የሌላት ሀገር በመሆኗ በአሁኑ ወቅት አማራጭ ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ የጅቡቲ ወደብ፣ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ ያስተናግዳል።
በሶማሊላንድ ያለው የበርበራ ወደብ ሌላኛው የቅርብ አማራጭ ነው። የታጁራ እና የአሰብ ወደቦችም እንደ ተጨማሪ አማራጭ የሚጠቀሱ ናቸው።
በፈረንጆቹ እስከ 1995 ድረስ ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ በአሰብ በኩል ሲከናወን የነበረ ሲሆን፣ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በምጽዋ ወደብ በኩል ይሳለጥ ነበር።
የባህር በር የሌለው ሀገር ከዓለም የንግድ ሥርዓት እኩልና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ የባህር በር የኢኮኖሚ እድገት እንዲፋጠን ከማድረግ አንጻር ሚናው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ምሁራን የባህር በር ካለህ ዓለምን ታገለግላለህ፣ የባህር በር ከሌለህ ግን የጎረቤት ሀገራት አገልጋይ ትሆናለህ የሚል ብሂል አላቸው፡፡
ይህንን የሚሉት የባህር በር ለአንድ ሀገር እድገትና ብሔራዊ ደህንነት ያለውን ጥቅም በደንብ ስለሚረዱ ነው፡፡
የባህር በር አንድ ሀገር ከዓለም ጋር ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር ይወስናል፡፡
በዓለማችን ላይ ወደ 45 ሀገራት የባህር በር እንደሌላቸው ይነገራል፡፡ ይህም ከዓለም ሀገራት 20 በመቶ እንደ ማለት ሲሆን፤ አዳጊ የሚባሉ ሀገራትን 40 በመቶ የሚሸፍን ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ለማደግና ለመበልፀግ የባህር በር ካላቸው እኩል አይደክሙም፡፡ የባህር በር የሌላቸውና አዳጊ የሚባሉ 32 ሀገሮች በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ሀገራትም ወደ 500 ሚሊየን ሕዝብ አሏቸው፡፡
ይህም የዓለምን ሰባት በመቶ የህዝብ ብዛት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 16ቱ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከእነሱም ትልቋ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እነዚህ ሀገራት የባህር በር ስለሌላቸው በዓለም ንግድ ውስጥ ያላቸው ድርሻ ከአንድ በመቶ ማለፍ አልቻለም፡፡
ይህም የባህር በር ስለሌላቸው ነው፡፡ ይህ ጂኦግራፊ የሀገሮችን እጣ ፈንታ እየበየነ እንዳለ ማሳያ ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በውድ የትራንስፖርት ወጪና በሌሎችም የንግድ እንቅፋቶች የተነሳ ከዓለም ገበያ ያላቸው ትስስር የላላ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ከዚህ የተነሳም በዓለም የፋይናንስ ስርዓት ችግሮችና በብድር እዳ ጫና ይማቅቃሉ፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቅርጽ ይዞ ትግሉ ቀጥላል፡፡
እናማ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ታሪካዊና ሕጋዊ መብት የለንም ትላላችሁ?

15 days ago
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ሰብዓዊ ክብር እና ሕይወት በተመለከተ የተላለፈ ሐዋርያዊ ጥሪ
“ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና”. (ማቴ 5:7)
ለፖለቲካ መሪዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ሚዲያዎች እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች
እኛ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት በመላው አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወቅታዊ ሁኔታች እንዳሳሰበን ለመግለጽ እንፈልጋለን። በአገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች አገራቸውን ለቀው የሚወጡት ለአገራቸው ፍቅር በማጣት ሳይሆን፣ የተሻለ የሥራ ዕድል እና የኑሮ ሁኔታ በመፈለግ ነው። ተነሳሽነታቸው እጅግ ሊከበር የሚገባው እና መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፤ ይህም ህይወታቸውን ለማሻሻል፣ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እና በመጨረሻም ለአገራቸው እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው። ነገር ግን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ስደተኞቻችን የሚያስፈልጋቸውን ሰብዓዊ ክብር ከማግኘት ይልቅ በመዋቅራዊ ብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በገለልተኝነት እና በከባድ ተጋላጭነት ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ። ሁኔታቸው ምንም ያህል ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፣ ቅዱስ የሆነው ሰብአዊ ክብራቸው ግን በድንበር፣ በሕጋዊ ሁኔታ ወይም በኢኮኖሚ ስርዓት ችላ ሊባል ወይም ሊጠፋ አይችልም።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፤ “በኢኮኖሚ የበለጸጉ መንግስታት፣ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ጸጥታንና ለመተዳድሪያ የሚሆን ገቢ በማጣታቸው ወደ አገራቸው ሲገቡ ተቀብለው የተቻላቸውን እርዳታ መስጠት አለባቸው” (CCC 2241)። ይህ ትምህርት ስደተኞች እንደ ውጭ ወይም እንደሸክም መታየት እንደሌለባቸው ይልቁንም እንደ ወንድምና እህት ሰብዓዊ ክብራቸው ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባ ያስተምረናል።
ይሁን እንጂ፣ ብዙ ስደተኞች በስደት ጉዟቸው ወቅት ከባድ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል፤ በእጅጉም ይሰቃያሉ። እኛም ከዚህ በታች የተገለጹትን ቁልፍ የስደት መዳረሻዎች እና ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያጋጥሟቸውን ተያያዥ ችግሮች ተመልክተናል።
1) አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፡-
• ሳውዲ አረቢያ፡- በሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሚኖሩ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አሉ። የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በሰማነው መሰረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ በተፈረደው የሞት ፍርድ ያለንን ስጋት፣ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ለዜጎቻችን ሁሉ ርህራሄ እና ምሕረት እንዲያደርጉ ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እንዲጠብቁ እንጠይቃለን።
• የመን፡- በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ የመን ለመግባት ወይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመጓዝ በቀይ ባህር፣ በጅቡቲ ወይም በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል ያልፋሉ። የመን ብዙውን ጊዜ ወደ ሌሎች የባህረ ሰላጤ አገሮች እንደ መጓጓዣ መንገድ ትጠቀማለች፤ ሆኖም ግን፣ ብዙ ስደተኞች በመንገድ ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ይደርስባቸዋል፣ ዓመፅ፣ በደል እና ኢ-ሰብአዊ ተግባራት ይደርስባቸዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በጉዞው አደገኛ ባህሪ እና በሚገጥሟቸው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ።
• ሊባኖስ፡- በሊባኖስ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአገሪቱ ውስጥ ባለው ግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። በዚህም ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ትውልድ አገራቸው በሰላም ለመመለስና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ።
• የባህረ ሰላጤ አገሮች፡- በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሌሪካ በእስራኤል እና በኢራን መሃከል በተፈጠረው ጦርነት እና ግጭት ምክንያት በጭንቅ ውስጥ ይገኛሉ።
2) የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሌላ መዳረሻ ናት። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ለሕይወታቸውና ለንብረታቸው ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ወደአስቡበት ሳይደርሱ በጉዞ ላይ እያሉ እስራት ይገጥማቸዋል፣ ሌሎቹ ደግሞ ወደ መድረሻቸው የሚደርሱ ሰዎች በፍርሃትና ውስጥ በምኖር ላይ ናቸው። በሚደርሱን ዘገባዎች መሰረት በደቡብ አፍሪካውያን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የተነሳ በዓመፅ፣ እና በግድያ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ክቡር ሕይወታቸው እየጠፋ ነው።
3) የሱዳን - ሊቢያ - የአውሮፓ መንገድ፡ ይህ መንገድ ለረጅም ጊዜ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በብዛት ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን፣ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ስደተኞች ከፍተኛ ስቃይ እና ህልፈተ ህይወት አስከትሏል። ብዙዎች አስቸጋሪ እና አደገኛ የሆነውን የበረሃ መንገድ በኢሰብአዊ ሁኔታዎች ሲያቋርጡ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ይህንን ጉዞ የበለጠ አደገኛ አድርጎታል። ሊቢያ የሚደርሱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እስር፣ ዝርፊያ፣ የጉልበት ብዝበዛ እና ከባድ በደል ይደርስባቸዋል። አንዳንዶቹ በክርስትና እምነታቸው ምክንያት ስደት ደርሶባቸዋል እና ህይወታቸውን አጥተዋል። በአደገኛ ጀልባዎች የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ሲሰምጡ፤ ብዙዎቹ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ያጣሉ፣ ጥቂቶች ብቻ ወደ ላምፔዱዛ ዳርቻ መድረስ ችለዋል። ላምፔዱዛ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በአንድ ወቅት በባህር ላይ ለሞቱት ሰዎች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሌዎ 14ኛም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለስደተኞች ያላትን አንድነት፣ ርህራሄ እና ለስደተኞች ድምጽ የመሆን ተልዕኮ ለማስቀጠል ደሴቲቱን በቅርቡ እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።
ይህ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስቃይ ከቁጥርም በላይ ውድ እና የተከበረ ህይወት ያላቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በእንባ፣ በመስዋዕትነት እና በተስፋ የሸኟቸው ልጆች ናቸው። ብዙ ጊዜ ግን እነዚህ ስደተኞች በብዝበዛ፣ በፍርሃት፣ በደል፣ በመገለል እና ለጥቃት በመጋለጥ አላስፈላጊ ስርዓቶች ውስጥ ይወድቃሉ። ብዙዎች ለማሰብ አዳጋች በሆኑ ሁኔታዎችን ውስጥ በህይወት ለመቆየት ይታገላሉ።
በክርስቲያያዊ የበጎ አድራጎት እና በዓለም አቀፍ የወንድማማችነት መንፈስ፣ ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከኢትዮጵያውያን ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ ማናቸውም የታቀዱ ግድያዎች እንዲቆሙ እና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምሕረትን እንዲያደርጉ ልመና እናቀርባለን። ምህረት ፍትህን አያዳክምም። ምህረት ፍትህን ከፍ በማድረግ ተስፋ ለቆረጡ ተስፋን ይሰጣል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን የሚያባብሱትን ጥልቅ ምክንያቶች ከመሰረቱ ለማስወገድ ይተባበር ዘንድ ዕድል የሚሰጥ ሊሆን ይገባል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ የከባቢ አየር ሁኔታ መቃወስ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በዓለም ዙሪያ አደገኛ የፍልሰት መንገዶችን እንዲከተሉ እንደሚያስገድዳቸው አስተውለናል። እነዚህን ዋና ዋና ምክንያቶች ችላ የሚል ዓለም የፍልሰት ቀውስን መፍታት አይችልም። በእርግጥም፣ የሰብዓዊነታችን እና የሥልጣኔ መለኪያ በዙሪያችን ያሉ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በምናሳሳየው እንክብካቤ ላይ የተመሠረተ ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት፣ ውይይት፣ ምሕረትና ጥበብ ተስፋ መቁረጥንና ሞትን እንዲያሸንፉ አጥብቀን መጸለያችንን እንቀጥላለን። እነዚህን ተጋላጭ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ሁሉንም ውሳኔ ሰጪዎች ለሁሉ ቻይ በሆነው የእግዚአብሔርን አምላክ ምህረት እና እገዛ ያገኙ ዘንድ እንጸልያለን።
የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ
አዲስ አበባ
10/09/2018

“የደቡብ አፍሪካ መንግስት የዜጎቼን ደህንነት ይጠብቅ” ኢትዮጵያ
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈፀመው ጥቃት እንዲቆምና በጥቃት ፈፃሚዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ከሰሞኑ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ላይ ጥያቄውን ለደቡብ አፍሪካ ማቅረቡን የገለጸ ሲሆን፤ የደቡብ አፍሪካ መንግስት በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝና ውጤቱንም እንደሚያሳውቅ መግለጹን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል እና ዘላቂ መፍትሄ የሚፈልግ ቡድን አዋቅሮ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት መጀመሩም ተሰምቷል።
በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደህንነት እንዲረጋገጥና ሕጋዊ የሥራ ስምምነት እንዲኖራቸው የሁለቱ ሀገራት መንግስታት በጋራ መምከራቸውን ሚኒስቴሩ መግለጹንም #ኤንቢሲ ዘግቧል።

ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የፓርቲው የምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር “በጸና እና በተደራጀ የሴቶች ድምጽ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እናሻግራለን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
የምረጡኝ ቅስቀሳው በደብረ ማርቆስ፣ ላሊበላ፣ ዱርቤቴ፣ ሸዋሮቢት፣ ደንበጫ፣ ደብረታቦር፣ ወረኢሉ፣ አዴት፣ ደብረሲና፣ ወረታ፣ አጣዬ፣ ግንደወይን እና ሌሎች ከተሞች መከናወኑ ተመልክቷል፡፡
በምርጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብሩ ላይ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ጽኑ አጋርነት በመግለጽ ÷ ፓርቲው የጀመራቸውን የልማት፣ የሰላምና የብልጽግና ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሕጋዊ እና የጸና ሀገረ መንግሥት ለመመስረት ሴቶች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም በመርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

በምርጫ ሒደቱ መገናኛ ብዙሃን ሙያዊ ግዴታቸውን ማክበር ይጠበቅባቸዋል
*********************
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃና ተዓማኒ እንዲሆን የሁሉም አካላትን ጥረት ይጠይቃል። በዚህ ረገድ የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 02 /2013 የተለያዩ ዝርዝር ድንጋጌዎችነ አካትቷል። ከመመሪያው ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል:-
ግድፈቶችን የማሳወቅ መብት፦ ጋዜጠኞች በሂደቱ የታዘቡትን የአሰራር ጉድለት ለምርጫ አስፈጻሚ አካላት የማቅረብ መብት አላቸው።
ጣልቃ አለመግባት፦ በመመሪያው አንቀፅ 17 መሠረት፣ ማንኛውም ጋዜጠኛ በምርጫ ሂደት ውስጥ ጣልቃ ከመግባትና ሒደቱን ከማደናቀፍ የመቆጠብ ሕጋዊ ግዴታ አለበት።
ሙያዊ ነፃነት፦ ጋዜጠኞች ከወገንተኝነት ነፃ እንዲሆኑ ወጪያቸው በራሳቸው ወይም በተቋማቸው መሸፈን አለበት። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ተሽከርካሪም ሆነ ሌላ ሀብት ለዘገባ ስራ መጠቀም የተከለከለ ነው።
የስልጠና ኃላፊነት፦ የሚዲያ ተቋማት የተሳሳቱ መረጃዎችን (Misinformation) ለመከላከል ጋዜጠኞቻቸው ስለ ምርጫ ሕጎችና ሙያዊ ሥነ-ምግባር በቂ ስልጠና እንዲያገኙ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
የተቋማት ተጠያቂነት፦ ጋዜጠኞች የምርጫ መመሪያውን ጥሰው በሚገኙበት ወቅት የወከሏቸው የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ተጠያቂ ይሆናሉ።
ትንበያ፦ ማናቸውም የመገናኛ ብዙሃን ወይም ጋዜጠኛ የምርጫ ውጤት ትንበያ ማድረግ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በምርጫ ጣቢያ እንዲሁም በምርጫ ክልል ደረጃ ይፋ ስለሆኑ ውጤቶች ዘገባ መስራት ይችላሉ፡፡
በአጠቃላይ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋዜጠኞች ሕጋዊና ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ

16 days ago
ከሀገር ውስጥ ተቋማዊ ግንባታ እስከ ቀይ ባሕር ሕጋዊ መብት፤ አሰባሳቢው ሀገራዊ ትርክት
******************
ኢትዮጵያ በታሪኳ የብዙ ማንነቶችና የግዙፍ ታሪኮች ማህደር ብትሆንም፣ ላለፉት ዓመታት በፖለቲካው ምህዳር የነገሱት ትርክቶች እንደ አስተሳሳሪ ሳይሆን በሁለት ጎራ ተከፍለው ሀገራችንን ሲያዳክሙ ቆይተዋል።
ይህ በሁለት ጽንፎች መካከል የነበረ የጥላቻ ፖለቲካና የነጣጣይ ትርክቶች አዙሪት ግን አሁን በአዲሱ “የመደመር” እሳቤ ተሰብሯል። አዲሱ እሳቤ እነዚህን የቆዩ የፖለቲካ፣ የዴሞክራሲና የተቋማት ግንባታ ስብራቶች በመጠገን ሀገራዊ ህብርብሔራዊ አንድነትንና የጋራ ተስፋን ሰንቆ ብቅ ብሏል።
መደመር ያለፈውን ታሪክ በጭፍን ሳይቀበልና ሳይቃወም፣ መልካሙን ወርሶ ግድፈቶቹን ደግሞ ተምረንባቸው የምናልፍበት ድልድይ መሆኑን እና እሳቤው ከሀገር ውስጥ ፖለቲካ አልፎ የሀገራችንን ስልታዊ ጥቅሞች ማስከበር ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ምሁራን ገልጸዋል።
የታሪካዊ ጠላቶች ሴራ መነሻው ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን መብት ለማዳከም መሆኑን የጠቀሱት ምሁራኑ፣ የህዳሴ ግድብ በጸጥታ ኃይሎቻችን መስዋዕትነት የተገነባ የድላችን አምድ እንደሆነና የቀይ ባሕርን ህጋዊ መብት መጠየቅም የሉዓላዊነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲሱ ሀገራዊ ትርክት የውክልና ጦርነቶችን በመመከት ግጭትን ወደ ስምምነት፣ ልዩነትን ደግሞ ወደ ውበት እየቀየረ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ የማውጣት ታሪካዊ ተልዕኮውን እያሳካ ይገኛል።
የመደመር እሳቤ የሀገራችንን ዘላቂ ስልታዊ ጥቅሞች፣ ተቋማዊ ብቃትንና የአህጉራዊ ፋይዳውን እንዴት እያስከበረ እንደሚገኝ የቀረበውን ሙሉ ማብራሪያና ሰፊ ትንታኔ አስተያየት መስጫው ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ።
በላሉ ኢታላ
#ethiopia #medemer #nationalnarrative #redsea #africanunity #ethiopianbroadcastingcorporation

17 days ago
መረጃ‼️
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቁ።
ጌዲዮን ይህን ጥያቄ ያቀረቡት፣ ዛሬ ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ገልጧል።
ጌዲዮን፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻችም መጠየቃቸውን ሚንስቴሩ ጠቅሷል።
ሚንስትር ዋሊድ፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል።
የሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የጣለባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በውይይቱ ወቅት ይነሳ አይነሳ መረጃው አላመለከትም።
seledadotio

ኢትዮጵያ በሳዑዲ የሚገኙ ዜጎቿ ደኅንነት እንዲጠበቅ ጠየቀች
#ethiopia | የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
ሚንስትሩ ይህንን ጠንካራ ጥያቄ ያነሱት፣ ዛሬ ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ ጋር በነበራቸው ውይይት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባሠራጨው መረጃ ይፋ አድርጓል።
በተጨማሪም የሳዑዲ መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች አስተማማኝና ሕጋዊ የሥራ እድሎችን እንዲያመቻች ሚንስትር ጌዲዮን ጠይቀዋል።
የሳዑዲው ምክትል ሚንስትር ዋሊድ ኤልክረጂ በበኩላቸው፣ ሕጋዊ የሠራተኞች ፍልሠት ኢትዮጵያዊያን ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራ ቅጥር እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ወሳኝ መሆኑን መግለጻቸው ተጠቅሷል።
ሆኖም ግን፣ በሳዑዲ ዓረቢያ ፍርድ ቤት ከአደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን አሳሳቢ ጉዳይ በዚህ ውይይት ላይ ስለመነሳቱ ከሚንስቴሩ የወጣው መረጃ የጠቀሰው ነገር የለም።

18 days ago
BBG ሚኒስትሪ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ አገራዊ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ሊያካሂድ ነው
#fastmereja I ላለፉት 17 ዓመታት በወጣቶች መንፈሳዊ እድገት እና ማህበራዊ ድጋፍ ላይ ሲሰራ የቆየው የቢቢጂ ሁለንተናዊ አገልግሎት (Bible Based Generation Holistic Ministry) ሕጋዊ ሰውነት ማግኘቱን አስመልክቶ የፊታችን ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አገራዊ የመክፈቻ እና የምስጋና ፕሮግራም ሊያካሂድ መሆኑን ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። ይህ አገራዊ የምስጋና እና ራዕይ የማጋራት መርሃ-ግብር በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
የሚኒስትሪው ሰብሳቢ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት፣ ተቋሙ ባለፉት 17 ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በስነ-ልቦና፣ በማህበራዊ እና በመንፈሳዊ ህይወታቸው ከመደገፍ ባሻገር፣ በወሲብ ንግድ (ሴተኝነት) ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ከህይወታቸው በማውጣትና መልሶ በማቋቋም ረገድ ጉልህ ሚና ሲጫወት ቆይቷል።
በመካኒሳ ሴሚናሪ በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ የምረቃ እና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የህብረቱ አባላት እንደሚገኙ ተገልጿል። ተቋሙ እስካሁን በልዩ ልዩ ዘርፎች ሲያበረክት የቆየውን አስተዋጽኦ ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል አዲሱ ሕጋዊ እውቅና ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለትም ተመላክቷል።
ሚኒስትሪው በጋዜጣዊ መግለጫው ማጠቃለያ ላይ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ አገራዊ ክብረ በዓል ላይ መላው ጥሪ የተደረገላቸው አካላትና ፍላጎት ያላቸው ወገኖች እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

ፈቃድ እና ቋሚ አድራሻ ሳይኖራቸው የሚሰሩ 35 የባህል ሐኪሞች መያዛቸው ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ህክምና አዋቂዎች ማኅበር በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ማስታወቂያ በማስነገር ፈቃድ እና ቋሚ አድራሻ ሳይኖራቸው ሲሰሩ የቆዩ 35 የባህል ህክምና ባለሙያዎችን እንደያዘ አስታውቋል።
ባለሙያዎቹ በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ስልክ ቁጥራቸውን እና ስራቸውን በስፋት እና በተጋነነ መንገድ እንደሚያስተዋውቁ የገለጹት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት መሪጌታ መንግስቱ ደስታ፥ በተለይ ቋሚ አድራሻ እና ፈቃድ የሌላቸው ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት አቤቱታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
አንድ የባህል ህክምና ባለሙያ አገልግሎት ከመስጠቱ በፊት ከሚጠበቅበት ግዴታዎች መካከል፦ የንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የበሽታውን ዓይነት ማስመዝገብ እንደሚገኙበት አስታውሰው፤ ከ300 በላይ ህመሞችን እንፈውሳለን የሚል ማስታወቂያ ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ችግሩ በከፊል እንዲፈታ መደረጉን አክለው ገልጸዋል።
ማኅበሩ ሕጉን አክብረውና ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ 240 ባለሙያዎች በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፤ ሕጋዊ ፈቃድ እና ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ሕገ-ወጦችን ለመታገል ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ ከምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ እንደሆነ አብራርተዋል።
#አሐዱ

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ
#ethiopia | የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ከዚህ በኋላ በሚያወጧቸው ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን የሕክምና ምስክርነት ማካተት እንዳይችሉ እገዳ ተጣለ።
ይህ የጤና አገልግሎት ማስታወቂያ አዘገጃጀትና ሥርጭት መመሪያ ቁጥር 1134/2018 ተገቢ ያልሆኑ የማስታወቂያ አሠራሮች በኅብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ እየፈጠሩ በመሆኑ የሕዝብን የሥነምግባርና የባህል እሴቶችን ለመጠበቅ የወጣ ነው።
መመሪያው በቴሌቪዥን፣ በራዲዮ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በድረገጾች፣ በቢልቦርዶችና በታተሙ ቁሳቁሶች ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎችን በሙሉ ይመለከታል።
አዲሱ ሕግ በጤና ማስታወቂያዎች ላይ የሚሳተፉ ሰዎች በሙሉ አገልግሎቱን በትክክል ያገኙ መሆን እንዳለባቸውና አስቀድመው በጽሑፍ ስምምነት መስጠት እንዳለባቸው ያስገድዳል።
ተሳታፊዎቹ ሕፃናት፣ የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ወይም በራሳቸው መወሰን የማይችሉ ወገኖች ከሆኑ ደግሞ ከወላጅ ወይም ከሕጋዊ አሳዳጊ የጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ሆኗል።
ይህንን ድንጋጌ በመጣስ ያለፍቃድ ወይም አገልግሎቱን ያላገኘን ሰው ምስክር አድርጎ የተጠቀመ ተቋም ከ20 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ብር፣ እንዲሁም ሕፃናትንና ውሳኔ መስጠት የማይችሉ ሰዎችን ያለ ሕጋዊ ፈቃድ ያሳተፈ ተቋም እስከ 100 ሺሕ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይጠብቀዋል።
የተጣለውን አስተዳደራዊ ቅጣት በሦስት ወር ውስጥ የማይከፍሉ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀታቸው እንዲታገድ ይደረጋል።
በተጨማሪም መመሪያው ለማስታወቂያ አሰራጮች እና ለሚዲያ ተቋማት አዲስ ኃላፊነት ጥሏል።
ማስታወቂያዎችን የሚያስተላልፉ አካላት ይዘቱ መመሪያውን ያሟላ እና ትክክለኛ መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን፣ ሕጉን የጣሰ ማስታወቂያ ያስተላለፈ የሚዲያ ተቋም ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ከ10 ሺሕ እስከ 30 ሺሕ ብር ሊቀጣ ይችላል።
ይህ ክልከላ በብዙኃን መገናኛዎች፣ በትራንስፖርት ላይ በሚለጠፉ፣ በሹራቦች፣ በራሪ ወረቀቶችና በቢልቦርዶች ላይ የሚወጡ ማስታወቂያዎችንም ይጨምራል።
ማስታወቂያዎች የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ ያከበሩ፣ ከልክ ያለፈ የሙያ ቃላትን የማያበዙና ለሕዝብ ግልጽ በሆነ ቋንቋ የሚዘጋጁ መሆን አለባቸው።
በተለይም የመጀመሪያው ምርጫ፣ የሁሉም ምርጫ እና የመሳሰሉ አባባሎችን መጠቀም ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ሲሆን፣ ተቋማት ከሌሎች የተሻሉ እንደሆኑ አድርገው ማቅረብ ወይም የእነሱ ባለሙያዎች ብቻ ልዩ ችሎታ እንዳላቸው አድርገው መናገር አይችሉም።
እንዲሁም ከአንድ ተቋም ሕክምና ካላገኙ አደጋ ሊገጥም እንደሚችል የሚያስፈራሩ ወይም በስሜት ላይ የሚያሴሩ የማስታወቂያ ይዘቶች የተከለከሉ ሲሆን፣ ተቋማት ያገኟቸውን ሽልማቶች በማስታወቂያ ላይ ማካተት የሚችሉት የሽልማቱን ዘመን፣ ምክንያቱንና ሰጪውን አካል በትክክል ሲገልጹ ብቻ መሆኑ ተደንግጓል።
#health #ministryofhealth #law #media #advertising #directive #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

20 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ በሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተላለፈውን በብሔር ማንነት ላይ የተመሠረተ የዕጩዎች እገዳ እና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመንግሥት መዋቅር አማካኝነት እየተፈጸሙ ያሉ አፈናዎች፣ መጪውን ምርጫ ተዓማኒነት እጅግ አደገኛ ፈተና ውስጥ እንደጣሉት በማስታወቅ ከባድ ክስ አቀረበ። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ የፍትሕ ተቋማት እና የገዥው ፓርቲ አሠራር ምርጫውን ከዴሞክራሲያዊነት ምህዋር እያስወጡት መሆኑን አጋልጧል።
ፓርቲው በመግለጫው በከፍተኛ አሳሳቢነት ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚው፣ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪዎችን “የብሔረሰብ ማንነት መስፈርትን አላሟላችሁም” በሚል ምክንያት ከምርጫ ውድድር ማስወጣቱ ነው። ይህ ውሳኔ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል በእኩልነት የመምረጥ እና የመመረጥ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን በግልጽ የሚጥስ አደገኛ እና አግላይ አካሄድ መሆኑን ኢዜማ አብራርቷል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲ ዕጩዎችም የዚሁ ሕገ-ወጥ እርምጃ ሰለባ መሆናቸውን ያረጋገጠው ፓርቲው፣ ይህንን ሕገ-መንግሥቱን የናቀ ፍርድ ቤታዊ ውሳኔ ለማስቀልበስ እስከመጨረሻው የሕግ እና የፖለቲካ መስመር እንደሚታገል አቋሙን አሳውቋል።
ከክልሉ የፍርድ ቤት ውሳኔ ባለፈ፣ ገዥው የብልጽግና ፓርቲ መንግሥታዊ መዋቅሩን በመጠቀም በተፎካካሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን መጠነ-ሰፊ ጫና ኢዜማ በጽኑ ተችቷል። በመላ አገሪቱ በሚገኙ የፓርቲው አባላት እና ዕጩ ተወዳዳሪዎች ላይ የሚከተሉት ዐበይት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን ዘርዝሯል፦
ሕጋዊ የደሞዝ እና የጥቅማጥቅም እገዳ ማድረግ።
ከሕግ አግባብ ውጪ ለገዥው ብልጽግና ፓርቲ የግዳጅ የገንዘብ መዋጮን ከተፎካካሪ አባላት ደሞዝ ላይ መቁረጥ።
በአባላቱ እና በደጋፊዎቹ ላይ የሚፈጸሙ ተከታታይ ዛቻዎች እና ማስፈራራቶች።
ይህ የኢዜማ መግለጫ፣ ገዥው ፓርቲ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ የገባው ቃል በተግባር እየተጣሰ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ከባድ ማሳያ ነው። ኢዜማ በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ አጽንዖት ሰጥቶ እንዳሳሰበው፤ የፍትሕ ተቋማትን (እንደ ሐረሪው ፍርድ ቤት) ለፖለቲካ ማጥቂያነት መጠቀም፣ ዜጎችን በብሔራቸው ምክንያት ከውድድር ማግለል እና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ የዘንድሮውን ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት፣ ነጻነት እና ተዓማኒነት ከወዲሁ ጥያቄ ውስጥ የከተተው ትልቅ ብሔራዊ አደጋ ነው።

21 days ago
ሀገራዊ ምክክር፦ ከውጥን እስከ ተስፋ - ለሀገራዊ መግባባት የሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ
**********************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ትልቅ ተስፋ የተሰነቀበት እና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ተቋም ነው።
ኮሚሽኑ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ያከናወናቸው ተግባራት እና ወደፊት የሚጠብቀው ጉዞ፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚኖራቸው ፋይዳ እጅግ የላቀ ነው።
ይህ ታሪካዊ ሂደት ኢትዮጵያ ካለችበት የፖለቲካ ቀውስ ወጥታ ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የምትሻገርበት ድልድይ ተደርጎ ይታመናል።
የኮሚሽኑ መሠረታዊ ዓላማ
ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት ሕጋዊ ሰውነት ያገኘው፣ በፖለቲካ ልሂቃንና በሕዝቡ መካከል የሚስተዋሉ መሠረታዊ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ለመፍታት ነው።
ዋነኛ ግቡም በሀገራችን ስር የሰደዱና ለዘመናት የቆዩ የቅራኔ ምንጮችን በጥናትና በሕዝባዊ ተሳትፎ በመለየት፣ ብሔራዊ መግባባትን ማምጣት፣ ማኅበራዊ መተማመንን ማደስ እና የሀገርን አንድነት በጽኑ መሠረት ላይ መገንባት ነው።
ኮሚሽኑ የሐሳብ የበላይነት የሚነግሥበት፣ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የውይይት መድረክ የመፍጠር ከባድ አደራ ተጥሎበታል።
ይህ ሂደት ‘አሸናፊ እና ተሸናፊ' ካለበት የፖለቲካ ባህል ወጥተን፣ በጋራ የምናሸንፍበትን መንገድ ለመቀየስ ያለመ ነው።
የዚህን መረጃ ሙሉ ሐሳብ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ያገኛሉ፦
#ebc #ethiopia #nationaldialogue

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በሪፐብሊካን አብላጫ ድምፅ የሚመራው የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ የከፈቱትን ወታደራዊ ዘመቻ በኮንግረስ ካልጸደቀ በስተቀር እንዲያቆሙ የሚያስገድደውን የዲሞክራቶች የውሳኔ ሃሳብ፣ እጅግ ጠባብ በሆነ የአንድ ድምፅ ልዩነት ውድቅ አደረገው። የምክር ቤቱ አባላት በውሳኔ ሃሳቡ ላይ በሰጡት ድምፅ 212 በ 212 እኩል በመለያየታቸው፣ ሕጉ ለማለፍ የሚጠይቀውን አብላጫ ድምፅ ማግኘት ባለመቻሉ ብቻ ውድቅ ሊሆን ችሏል።
ይህ ድምፅ አሰጣጥ በተያዘው ዓመት የፕሬዚዳንቱን የጦርነት ሥልጣን ለመገደብ በምክር ቤቱ ሲካሄድ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። በተለይም ግጭቱ ባለፈው ግንቦት 1 ቀን የ60 ቀናት ሕጋዊ ገደቡን ማለፉን ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለ ጦርነቱ መሻሻል ለኮንግረሱ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠበቀበት ወቅት የተካሄደ የመጀመሪያው ድምፅ አሰጣጥ በመሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በወቅቱ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በኢራን ላይ የነበረውን ግጭት "እንዳስቆመው" መግለጻቸው ይታወሳል።
የሪፐብሊካን ፓርቲ በምክር ቤቱ ያለው የአብላጫ ወንበር እጅግ ጠባብ በመሆኑ፣ በጉዳዩ ላይ የሚደረጉ የድምፅ አሰጣጦች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ እና ፉክክሩ እየከረረ መጥቷል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው፣ ባለፈው ሚያዝያ 16 ቀን በዚሁ የጦርነት ሥልጣን ገደብ ላይ ተካሂዶ የነበረው የድምፅ አሰጣጥ 213 ለ 214 በሆነ እጅግ ጠባብ ልዩነት መውደቁ ነው።
ይህ የኮንግረሱ ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት በሴኔትም ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ተንጸባርቋል። ረቡዕ ዕለት በሴኔቱ በተካሄደው ድምፅ አሰጣጥ፣ የጦርነት ሥልጣን ገደብ የውሳኔ ሃሳቡ 50 ለ 49 በሆነ ድምፅ ውድቅ ተደርጓል። በሴኔቱ የድምፅ አሰጣጥ ወቅት ሶስት የሪፐብሊካን አባላት ፓርቲያቸውን በመክዳት፣ ከአንድ የዲሞክራት አባል በስተቀር ከሌሎቹ ዲሞክራቶች ጋር በማበር ሕጉ እንዲጸድቅ ድምጻቸውን መስጠታቸው በፓርቲው ውስጥ ያለውን የሃሳብ ልዩነት አመላክቷል።
ይህ ክስተት በአሜሪካ የፖለቲካ መድረክ ውስጥ፣ በተለይም በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና በጦርነት አዋጅ ሥልጣን ዙሪያ በህግ አውጪው (ኮንግረስ) እና በህግ አስፈጻሚው (ፕሬዚዳንቱ) አካል መካከል ያለውን ጥልቅ የሆነ የስልጣን ሽኩቻ እና ክፍፍል በጉልህ የሚያሳይ ወቅታዊ ማሳያ ሆኖ አልፏል።

23 days ago
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ፦ ከታሪካዊ ወዳጅነት ወደ ስትራቴጂያዊ አጋርነት
*********************
የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የዘመናት ታሪክ ያለው ብቻ ሳይሆን፣ በጋራ ጥቅም እና በእርስ በርስ መከባበር ላይ የቆመ ብርቱ ወዳጅነት ነው።
ይህ ግንኙነት ዛሬ ላይ ከታሪክ ባለፈ ለቀጣናዊ ሰላም እና ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ምሰሶ ሆኗል።
ከመቶ ዓመታት በፊት የተገነባው እና አዲስ አበባን ከጅቡቲ ያቆራኘው የባቡር መስመር የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጥንካሬ ማሳያ ነው። ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ጋር በማስተሳሰር ግንኙነቱ በሉዓላዊ እኩልነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነበር።
ፈረንሳይ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ አግባብነት እና ሕጋዊነት በግልጽ ከሚደግፉ ሀገራት ቀዳሚዋ ናት።
የፕሬዚዳንት ማክሮን አቋም፦ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የፈረንሳይን ሙሉ ድጋፍ ያገኛል።
የባሕር ኃይል ግንባታ፦ የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል መልሶ ለማደራጀት እና አባላቱን ለማሰልጠን የሚደረገው የመከላከያ ትብብር ሀገራቱ ለባሕር ደኅንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ትብብር ከተለምዷዊው ‘የእርዳታ ሰጭ እና ተቀባይ' ግንኙነት ወጥቶ ወደ ኢንቨስትመንት እና የጋራ ምርታማነት ተሸጋግሯል።
አረንጓዴ ኢነርጂ፦ በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው፣ ፈረንሳይ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ እና ታዳሽ ኃይል ላይ በትኩረት እየሠራች ትገኛለች።
የገንዘብ ድጋፍ፦ የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (AFD) ለኤሌክትሪክ ኃይል መረብ ማዘመኛ የ80 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ፈቅዷል።
ቅርሶችን መጠበቅ፦ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ የባሕል ትሥሥር ያሳያል።
የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ ግንኙነት ታሪካዊ መከባበርን መሠረት አድርጎ፣ ዛሬ ላይ አስተማማኝ ወደሆነ ስትራቴጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ተሸጋግሯል!
በለሚ ታደሰ
የዚህን መረጃ ሙሉ ሐሳብ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ያገኛሉ
#ethiopia #france #diplomacy #history #lalibela #ethiofrance

24 days ago
ቻይና ታይዋን የምትባል ሀገር ስለማላውቅ በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ አለች
#ethiopia | በመጪው ግንቦት 18 የሚከፈተው 79ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ ታይዋን እንዳትሳተፍ መወሰኗን ቻይና ይፋ አደረገች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ታይዋን የቻይና ግዛት የማይነጠል አካል በመሆኗ በጉባኤው ላይ የሚኖረው ተሳትፎ ቻይናን ብቻ የሚመለከት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት መላውን ቻይና የሚወክል ብቸኛ ሕጋዊ መንግስት መሆኑንና ይህም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደንብ የተደገፈ መርህ መሆኑን ገልጸዋል።
በታይዋን የሚገኘው "ዴሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ" የነፃነት አቋም በማራመድ የ"አንድ ቻይና" መርህን ጥሷል ሲሉ የወቀሱት ቃል አቀባዩ፣ የታይዋንን ካርድ በመጠቀም የሚደረግ ማንኛውም የፖለቲካ ማጭበርበር ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ውሳኔዎች ለማስከበር ታይዋን በዘንድሮው ጉባኤ ላይ እንደማትሳተፍ ግሎባል ታይምስ የቃል አቀባዩን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#china #taiwan #who #worldhealthassembly #onechinapolicy #geopolitics #globalnews

ለምርጫ ድምፅ ስንሰጥ ምን እንጠንቀቅ?
ድምፅ የተሰጠባቸው ወረቀቶች ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት ዋጋ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ፦
1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለፀ ከሆነ፣
2. ለምክር ቤቱ መምረጥ ከሚቻለው እጩዎች ቁጥር በላይ ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣
3. መራጩ ማንን እንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
4. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሰራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ሆኖ ከተገኘ፡፡
ስለዚህ ድምፃችን ዋጋ እንዲኖረው በጥንቃቄ እንመርጣለን!

26 days ago
ቀይ ባሕር - ኢትዮጵያ ወደ ተፈጥሯዊ ቤቷ ትመለሳለች!
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ በታሪክ ማኅደር ውስጥ ስሟ በገዘፈው ልክ፣ በመልክዓ-ምድራዊ እስር ውስጥ እንድትማቅቅ የተፈረደባት ሀገር ሆና እንድትቆይ የተደረገው በድንገቴ የታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን በረቀቀ የባዕዳን ሴራ እና በውስጥ ባንዳዎች የታሪክ ክህደት ጭምር መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።
“ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንደሚባለው ሀገራችን የባሕር በሯን ስታጣ እና የየብስ እስረኛ ስትሆን ጉዳቱ የገባቸው ጥቂቶች ነበሩ። ዛሬ ግን ያ የታፈነ ታሪክ ትንፋሽ አግኝቶ ወደ ዓለም አቀፍ አጀንዳነት ተሸጋግሯል።
የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ወይም የፍላጎት ጥያቄ ሳይሆን፣ ከሕልውና ጋር የተቆራኘ የሞት እና የሽረት ጉዳይ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በአንድ ድምፅ እያስተጋቡት ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቁርጠኝነት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች ልማቷ ብቻ ሳይሆን ሰላሟም አደጋ ላይ ይወድቃል።
130 ሚሊዮን ሕዝብ ያቀፈች ግዙፍ ሀገር፣ የዓለም የንግድ መስመር በሆነው ቀይ ባሕር ላይ ተሳትፎ እና ባለቤትነት ሳይኖራት መቅረቷ ለቀጣናውም ቢሆን ዘላቂ ሰላምን አያመጣም። ትናንሽ ሀገራት ግዙፉን የንግድ ወሽመጥ የመጠበቅ አቅም ስለሌላቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ከጉዳዩ መራቃቸው ለባሕር ላይ ወንበዴነት እና ለሽብርተኝነት በር የሚከፍት ነው። ስለሆነም የባሕር በር ጥያቄያችን ከስሜታዊነት በራቀ፣ በታሪክ፣ በሕግ እና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ መሆኑን አሁን ዓለም ሊገነዘበው ይገባል።
ኢትዮጵያ የሌላውን ሉዓላዊነት የመንካት ፍላጎት ሳይኖራት፣ የራሷን የተፈጥሮ እና የታሪክ መብት ማስከበር ላይ ትኩረት ማድረጓ ፍጹም ምክንያታዊ ነው። የሌለንን ሳይሆን የነበረንን እና የሚገባንን ነው የምንጠይቀው።
ከኢኮኖሚ አኳያ ስንመለከተው፣ የባሕር በር ማጣት ለሀገራችን ትልቅ የደም ሥር መቋረጥ ነው። ዛሬ ላይ በዓመት እስከ 20 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የገቢ እና ወጪ ንግድ የምናስተናግድ ሲሆን ይህም በ2030 ወደ 35 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ይገመታል። ለወደብ አገልግሎት በየዓመቱ የምንከፍለው በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች የሀገራችንን ካዝና ከማድረቅ ባለፈ፣ ለልማት የሚውል ሀብታችንን አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።
የባሕር በር ማጣት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ነው።
“ጀግና ካልወደቀ አይነሣም” እንደሚባለው፣ ኢትዮጵያ ካለፈችባቸው የታሪክ ስብራቶች ታላቅ ትምህርት ቀስማለች። የባሕር በሯን ያጣችበት መንገድ ሕጋዊነት የጎደለው፣ በሕዝብ ውሳኔም ሆነ በተቋማት ዕውቅና ያልተደገፈ መሆኑ ዛሬ ላይ ለጥያቄያችን የሞራል እና የሕግ ልዕልናን ሰጥቶታል።
ጎረቤቶቻችን ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የኢኮኖሚ ትሥሥር ቢያጠናክሩ የሁላችንም ተጠቃሚነት ይረጋገጣል። የኢትዮጵያ በባሕር ላይ መገኘት ለቀጣናው ደኅንነት ዋስትና እንጂ ስጋት አይደለም።
የራሷ የባሕር ኃይል እና የወደብ ይዞታ የነባራት ኢትዮጵያ፣ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ያለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን ለመጠበቅ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው።
ይህ የትውልድ ጥያቄ እና የታሪክ አደራ ነው። ኢትዮጵያ “የመልክዓ-ምድር እስረኛ” ሆና የምትቆይበት ዘመን ማክተም አለበት።
የባሕር በር ጥያቄ ከስሜታዊነት የፀዳ፣ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ እና ለዘላቂ ሰላም የሚቆም ነው። ኢትዮጵያ ከጂኦግራፊ እስረኝነት የምትላቀቅበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
በደም እና በአጥንት ሀገራቸውን ጠብቀው ያቆዩልን አባቶቻችን የባሕር ላይ ጀግንነት ታሪክ ዛሬም በልባችን ታትሞ ይገኛል።
የሕዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ብርሃናችንን እንዳረጋገጠልን ሁሉ፣ የወደብ ባለቤትነታችንም የባሕር ላይ ክብራችንን ዳግም የሚያበስር መሆኑ አይቀሬ ነው።
መጪው ትውልድ በየብስ የታጠረች ሳይሆን አድማስ ተሻጋሪ እና የባሕር ላይ ክብር ያላት ሀገር እንደሚረከብ ጽኑ እምነታችን ነው።
ዛሬ የምንዘራው የዲፕሎማሲ ዘር ነገ ለሀገራችን የብልፅግና ፍሬ ሆኖ ይበቅላል። ኢትዮጵያ በክብር ወደ ባሕሯ ትመለሳለች!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #seaaccess #redsea #diplomacy

27 days ago
የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ አክሱምን "ቅድስት ከተማ" ብሎ መሰየሙን እና ይህንኑ የሚያሳዩ "ሕጎችን እያወጣ" መሆኑን አስታወቀ
#fastmereja I የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ባደረገው ጉባኤ፤ የጥንታዊቷ አክሱም መጠሪያ "ቅድስት አክሱም ጽዮን ከተማ" እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።
ቤተ ክርስቲያኗ፤ ይህንን ውሳኔ ተከትሎ በከተማዋ እንደ "መጠጥ እና ጫት" ሽያጭ ያሉ ተግባራት ላይ ክልከላ እንዲጣል እንደምትፈልግ እንዲሁም "የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎችን" እያወጣች መሆኑን ገልጻለች።
ውሳኔው ይፋ ከተደረገበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ. ም. አንስቶ ከተማዋ በአጠቃላይ ቅድስት ተብላ እንደምትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አክሱም ከዚህ ቀደም ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ በጠቅላላው ቅድስት ከተማ እንድትባል የሚያስችል ጥናት ቀርቦ ውሳኔው እንደተላለፈ ገልጸዋል።
አክሱም ከተማ "ቅድስት ከተማ" በሚል በተለምዶ ትጠራ እንደነበር ጠቅሰው የአሁኑ ውሳኔ መጠሪያውን "ሕጋዊ" እንደሚያደርገው አስረድተዋል።
አክሱም "ሕገ ልቦና፣ ሕገ ኦሪት፣ ሕገ ወንጌል ጠብቃ የኖረች የረዥም ዓመት የክርስትና ደሴት" ስለሆነች "ቅድስት" መሆኗን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ አስረድተዋል።
"ብዙ መንበረ ታቦተ ጽዮናት፣ መንበረ ጽላት፣ መንበረ ሳምራ፣ መንበረ ብዙ ቅዱሳን ስለሆነች ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ ከአሁን በኋላ ደግሞ ከተማዋን ጠቅላላ ቅድስት የሚያስብላት ተጠንቶ ያለው ግብዓት ቀርቧል" በማለትም አብራርተዋል።
"ከተማዋ በዚህ ዘመን ያላትን ቅድስና ቀጣዩ ትውልድ ይዞ እንዲሄድ" በሚል አጠቃላይ ከተማዋ ቅድስት ተብላ እንድትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አክለዋል።
የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተለዩት አባቶች የተመሠረተው የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እንደተናገሩት፤ አክሱም በአጠቃላይ ቅድስት ከተማ እንድትባል በመወሰኑ ምክንያት መጠጥ እና ጫትን የመሳሰሉት ላይ ሙሉ በሙሉ ክልከላ ለመጣል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እያደረጉ ነው።
"ለሆቴሎችም ሥርዓት የሚወጣበት ሕግ እያወጣን ነው. . . ከተማይቷ ቅድስት ከተባለች የቅድስና ሥራ ሊሠራ ይገባል። ጠቅላላ ከተማዋ የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎች እያወጣን ነው" ብለዋል።
የከተማዋን "ጥንታዊ ታሪክ፣ ማንነቷን፣ ክብሯን ዓለም እንዲያውቀው" ማድረግም ዓላማቸው መሆኑን አክለዋል።
አሁን ላይ ከተማዋ "ለቅድስና የሚበቁ ነገሮች ማድረግ ስላለባት" ቤተ ክርስቲያኒቷን፣ ሕዝቧን እና ምዕመኗንም "በደንብ እንደሚያስተምሩ" ተናግረዋል።
ዘገባው የቢቢሰሲ አማርኛ ነው።