27 days ago
የቴክኖሎጂ አብዮት በኢትዮጵያ፡- ከ5 ሚሊዮን ኮደርስ እስከ አገልግሎት ዲጂታላይዜሽን
********************
ቀደም ሲል የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት ይደርስ የነበረው ረጅም ሰልፍና እንግልት፣ ዛሬ በሀገራችን እየተካሄደ ባለው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያበቃ ይገኛል።
ሀገራችን "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025"ን በስኬት አጠናቅቃ ወደ "ዲጂታል 2030" ስትራቴጂ የተሸጋገረች ሲሆን፣ ይህም የአገልግሎት አሰጣጥንና የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ በመቀየር ላይ ነው።
በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ረገድ በመሰረተ ልማትና የቴክኖሎጂ ማዕከላት እንደ የሳይንስ ሙዚየም፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ኢንስቲትዩት እና የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ወደ ሙሉ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ የ4G እና 5G የኢንተርኔት መረቦችም በስፋት እየተዘረጉ ይገኛሉ።
በቴሌብር እና በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ያለ ጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ባህል ሆኗል። ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ደግሞ የዲጂታል ማህበረሰብ ግንባታን እውን እያደረገ ነው።
እንደ ኢ-ታክስ፣ ኢ-ፓስፖርት እና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተከፈቱ "መሶብ" የአንድ ማዕከላት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስርና በበይነመረብ በማቅረብ ወጪን፣ ጊዜንና እንግልትን አስቀርተዋል።
ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር በመተባበር የእየተተገበረ የሚገኘው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ነፃ የኦንላይን ስልጠና ወጣቶችን በዳታ ሳይንስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ኤአይ (AI) እና አንድሮይድ ሶፍትዌር ግንባታ በማሰልጠን የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እንዲፈጥሩ እያበቃቸው ይገኛል።
ዲጂታላይዜሽን የአሰራር ባህል ለውጥና የሀገርን የወደፊት አቅም የመገንባት ሂደት በመሆኑ፣ ቴክኖሎጂውን በአግባቡ መጠቀምና በዲጂታል እውቀት ማደግ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው።
በብሌን ደምበሎ
#ebc #ethiopia #digitalethiopia #digitalethiopia2030 #artificialintelligence #mesob

3 months ago
የቢሮክራሲውን ማነቆዎች የሚገታው የኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ባልተቀላጠፈበት እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በሌለበት ስለ ተገልጋይ እርካታ ማውራት ከንቱ ድካም ነው።
በሀገራችን ለረጅም ዘመናት የቆየው እና የዜጎችን እንግልት ሲያበዛ የኖረው “ዛሬ ሂድ፤ ነገ ና” የሚለው አሰልቺ ቢሮክራሲ፣ የሕዝብን ሮሮ ከመጨመሩ ባለፈ የሙስና አዙሪት መፈልፈያ ሆኖ መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው።
ይህንን ሥር የሰደደ ማነቆ ለመፍታት ቴክኖሎጂን እንደ ዋና መፍትሔ መውሰድ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ እና ወጣት የሰው ኃይል እንዲሁም የመንግሥትን ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት በመጠቀም፣ ቴክኖሎጂውን ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለኢኮኖሚ ሽግግር በስፋት እያዋለችው ትገኛለች።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዘርፉ የተመዘገቡት ስኬቶች የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሙን ከማሳካት ባለፈ፣ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያቀልሉ፣ ጊዜን እና ገንዘብን የሚቆጥቡ ትልልቅ ተስፋዎችን አብስረዋል።
ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቀረጸው እና በይፋ ሥራ የጀመረው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተንቀሳቃሽ አውቶቡስ ስምሪት አንዱ ነው።
ይህ በአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሆነ አሠራር የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በየቢሮው እና በየደረጃው በሚገጥሙ የቢሮክራሲ ሰንሰለቶች የመጉላላት እና በፀሐይም በዝናብም የመንከራተትን ዘመን በዘላቂነት የሚቀይር አዲስ ምዕራፍ ነው።
በልዩ ሁኔታ በተዘጋጁ ንጹሕ ኢነርጂ በሚጠቀሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ የተመሠረተው ይህ አገልግሎት፤ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የንግድ ፈቃድ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪ ታርጋ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ዕድሳት፣ የልደት ምዝገባ እንዲሁም የመንገድ ፈንድ እና የኤሌክትሪክ ቅድመ-ክፍያ አገልግሎቶችን ጨምሮ ስምንት ዋና ዋና የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣራ ሥር ይዞ ወደ ማኅበረሰቡ ደጃፍ መጥቷል።
የዚህ የዲጂታላይዜሽን ስኬት ትልቁ ፋይዳ የአገልግሎት አሰጣጥን ከማቀላጠፍ ባለፈ ሙስናንና የአሠራር ብልሹነትን በተጨባጭ መግታቱ ላይ ነው።
ተንቀሳቃሽ አውቶቡሶቹ ከዋና ዋና የፌዴራል ተቋማት የመረጃ ማዕከላት ጋር በቀጥታ የተገናኙ መሆናቸው፣ በውስጣቸውም ዲጂታል የሰዎች ወረፋ ማስተናገጃ፣ የክትትል ካሜራዎች እና የተለዋዋጭ ዲጂታል ክፍያ አማራጮች መካተታቸው አሠራሩን ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ያደርገዋል።
ይህ ዓይነቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዲስ ስምሪት በመንግሥት አገልግሎት ላይ የሚታየውን አሰልቺ ቢሮክራሲ በመቀነስ፣ ሕገ ወጥ ደላሎችን እና ብልሹ አሠራሮችን ከአምራቹ ማኅበረሰብ ትከሻ ላይ ያወርዳል። የአገልግሎት አሰጣጥ ሲፋጠን የሚቆጠበው ጊዜ እና ጉልበት ደግሞ በቀጥታ ወደ ምርታማነትና ወደ ሀገር ሀብት ይቀየራል።
ይሁን እንጂ ይህ የተጀመረው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ ውጤታማና ዘላቂ እንዲሆን የዜጎች እና የሚመለከታቸው አካላት ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
የቆየውን ተቋማዊ እና ግለሰባዊ ልምምድ ቀይሮ በፈገግታና በታማኝነት ማገልገል ቀላል ባይሆንም፣ ቴክኖሎጂው ግን ይህንን የሥራ ባህል ለውጥ እያፋጠነው ይገኛል። በመሆኑም ዜጎች እነዚህን ዘመናዊና ምቹ አገልግሎቶች በባለቤትነት ስሜት በመጠቀም፣ የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት በመሆን ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሊቆጥቡ ይገባል።
በሌላ በኩል፣ የአመራር አካላት እና የሚመለከታቸው ተቋማት ይህ አመርቂ ጅምር ይበልጥ እንዲስፋፋ፣ መሠረተ ልማቱ እንዲጠናከር እና ኢትዮጵያውያን ባሉበት ስፍራ ሆነው በሞባይላቸው ሙሉ አገልግሎት የሚያገኙበት ደረጃ ላይ እስኪደርስ በትጋት ሊሠሩ ይገባል።
ቴክኖሎጂ የሀገር ብልጽግና ምሰሶ ከመሆኑም በላይ የዜጎችን ክብር የሚመልስ መሣሪያ በመሆኑ፣ የአገልግሎት ማነቆዎችን የመስበር ይህ አመርቂ ጅምር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #mesob #digitalization

4 months ago
ኢትዮጵያ በ2030 በኃላፊነት በተመራ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ተቋማዊ ብቃቷን ማጠናከር አለባት ተባለ
ሮቤ፣ ባሌ – ሰኔ 15፣ 2018 ዓ.ም.
#ethiopia | ኢትዮጵያ በ2030 የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባሻገር ጠንካራ ተቋማዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ብቃት እና የዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ላይ ማተኮር እንዳለባት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ገለጹ።
ዶ/ር አብዮት ይህን ያሉት በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia's Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ቁልፍ ንግግር ነው።
እንደ አማካሪው ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በዲጂታል ሽግግር ጉዞዋ ከዜሮ እየተነሳች አይደለችም። ባለፉት ሰባት ዓመታት በቴሌኮም ሪፎርም፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በዲጂታል መታወቂያ፣ በክፍያ ሥርዓቶችና በመንግሥት አገልግሎቶች ዘርፍ ጉልህ እድገቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም. የተጀመረው “Digital Ethiopia 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ ሁሉም ዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ እኩል ዕድል እንዲያገኙ እና የዲጂታል አገልግሎቶች በእምነትና በደህንነት እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል።
ዶ/ር አብዮት እንዳሉት፣ የቱሪዝም ዘርፉ ከዲጂታል ለውጥ በፍጥነት ተጠቃሚ ሊሆን ከሚችሉ ዘርፎች አንዱ ሲሆን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የቱሪዝም መድረኮች፣ የዲጂታል ትኬትና ክፍያ ሥርዓቶች፣ የጎብኚዎች ፍሰት ትንተና እና የተቀናጀ የቱሪዝም መረጃ ሥርዓት ለዘርፉ አዲስ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
በንግግራቸው የ“MESOB” የተባለውን የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎት መድረክ በአርአያነት ያነሱት አማካሪው፣ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንደ አንድ የጉዞ ልምድ እንጂ እንደ ተለያዩ ተቋማት እንደማያዩ ገልጸው፣ የቱሪዝም መረጃ፣ የሆቴል አገልግሎቶች፣ የመጓጓዣ አማራጮች፣ የክፍያ ሥርዓቶችና የደህንነት መረጃዎች በአንድ የተቀናጀ ሥርዓት መሰጠት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ለዚህም የቴክኖሎጂ፣ የሂደት እና የሰው ኃይል ሦስት ዋና ምሰሶዎች በአንድነት መሠራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ብሮድባንድ ግንኙነት፣ ዲጂታል መድረኮች፣ የመረጃ አስተዳደር፣ የAI ሥነ-ምግባር መመሪያዎች እና የሰው ኃይል ብቃት በጋራ ሲጠናከሩ ብቻ ዘላቂ ለውጥ እንደሚመጣ አስገንዝበዋል።
አማካሪው ኢትዮጵያ በ“5 Million Ethiopian Coders” መርሃ ግብር ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በኮዲንግ፣ በዳታ ትንተናና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ክህሎቶች ማሠልጠን መቻሏ ለዘርፉ ጠንካራ የሰው ኃይል መሠረት እየፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ በ2030 የኢትዮጵያ ስኬት የሚለካው በተጠቀመችባቸው የAI መሣሪያዎች ብዛት ሳይሆን በዩኒቨርሲቲዎች የተሻሻሉ ሥርዓተ ትምህርቶች፣ በተቋማት የመረጃ ጥራት፣ በዲጂታል ብቃት፣ በግላዊነት ጥበቃ እና በሕዝብ እምነት ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኮንፈረንሱ በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ትምህርት ዘርፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚያመጣውን ዕድልና ተግዳሮት መወያየት ቀጥሏል።
#ethiopia #bale #tourism #getutemesgen #ጌጡተመስገን #artificialintelligence #digitalethiopia2030 #mwu

Sponsored by
Surafel
4 months ago
መሶብ ለአገልጋይነታችን፡ የዲጂታል ትጋትና የሕዝብ አደራ
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
ቴክኖሎጂ የአንድን ሀገር የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት የሚያጠናክርና የዜጎችን ሕይወት በብዙ መንገድ የሚቀይር እውነተኛ የለውጥ ሞተር ነው።
በተለይም የመንግሥት አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ ለዜጎች የሚሰጠውን ክብር፣ የጊዜና የገንዘብ ትርፍ ስንመለከት እንዲሁም በተቋማት መካከል የሚፈጥረውን ቅንጅት ስናስተውል ሀገራችን በለውጥና በዕድገት ጎዳና ላይ መሆኗን በግልጽ ያሳያል።
ይሁንናይህ አስደማሚ ጅማሮና በዲጂታል ዘርፉ የተመዘገቡት ድሎች የዜጎችን እርካታ ጫፍ ላይ አድርሰዋል ማለት አይደለም ገና ብዙ የሚቀሩና ትኩረት የሚሹ የቤት ሥራዎች እንዳሉብን መዘንጋት የለብንም።
በባህላችን «መሶብ» የጥጋብ፣ የአንድነት መገለጫ ነው።በዚህ እሳቤ የተገነባው የ«መሶብ» መተግበሪያም የሀገርን በረከትና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለሕዝብ ለማቅረብ ያለመ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።
መሶቡ የበረከት ምንጭ እንዲሆንና አገልግሎቱ ሙሉዕነት እንዲኖረው ከተፈለገ፣ በውስጡ የሚቀመጠው «እንጀራ» ማለትም የአሠራር ሥርዓቱና አስፈጻሚው አገልጋይ—ከሌብነት፣ ከሙስናና ከእጅ መንሻ የጠራ መሆን አለበት።
እጅግ ዘመናዊና የተራቀቀ ቴክኖሎጂ በየተቋማቱ ቢዘረጋም፣ በአገልጋዩ ዘንድ ያለው የቆየ ልማድ፣ የሌብነት አስተሳሰብና የአገልግሎት መስተጓጎል ካልተወገደ የቴክኖሎጂው ፋይዳ ለዜጎች ትርጉም አልባ ሆኖ ይቀራል።
በመሆኑም በመሶብ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩትን እጅ መንሻዎችና ሕገ-ወጥ አሠራሮች ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የነገ የማይባል ቀዳሚ ተግባራችን ነው።
ቴክኖሎጂ ጊዜንና ገንዘብን ከመቆጠብ ባለፈ፣ ዜጎች በቢሮክራሲ ብስጭትና በጭንቀት የሚሸከሙትን አሉታዊ ኃይል አስወግዶ ደስተኛ ማኅበረሰብ የመፍጠር ትልቅ አቅም አለው።
ይህንን አቅም ወደ መሬት ማውረድ የሚቻለው ደግሞ እያንዳንዱ አገልጋይና የመንግሥት ተቋም የኃላፊነት ስሜቱን በተግባር ሲያሳይ ነው። የዚህ ሁሉ ጥረትና ስኬት ማዕከል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።
ባለፈው ምርጫ ሕዝባችን ከሌሊት እስከ ሌሊት በሰላማዊ መንገድ ተሰልፎ ስለ ሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ለተቋማዊ ዕድገትና ለመበልጸግ ያለውን ጉጉት በተግባር አሳይቷል።
ይህንን ታላቅ እምነትና አደራ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መወጣት ግድ ይላል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በግልጽ እንዳሳሰቡት "የኢትዮጵያ ሕዝብ ስላከበረን አብዝተን ልናከብረው፣ ስላከበረን አብዝተን ልናገለግለው፣ ባከበረን ልክ ታምነን ልንገኝ ይገባል።"
«ያበደረ መልሶ ያገኛል፣ የዘራ ያጭዳል» እንደሚባለው የሕዝቡን ክብርና አመኔታ መመለስ የሚቻለው በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል ብቻ ነው።
እስካሁን የተመዘገበው ስኬት ከዜጎችን ሰፊ ፍላጎት አንድ በመቶ (1%) ያህል ብቻ በመሆኑ፣ በቀሪው ሰፊ መንገድ ላይ በፍጥነት ለመራመድ በተሻለ ቁመና መገኘት፣ ራስን ከብልሹ አሠራር ማጥራትና በበለጠ ትጋት መረባረብ ያስፈልጋል።
መላው የሥራ ኃላፊዎችና በየተቋማቱ የምትገኙ አገልጋዮች በመደመርና በአንድነት በመቆም፣ የዜጎችን እሮሮ ማክሰምና የሀገራችንን ብልጽግና በጽኑ መሠረት ላይ መገንባት ይጠበቅባችኋል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #mesob #ethiopia #መሶብ

u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u1260u12a0u134du122au12ab u1240u12f3u121a u12e8u1206u1290u12cdu1295 u12e8u1270u1240u1293u1300 u12e8u12f2u1302u1273u120d u12a0u1308u120du130du120eu1275 u1218u1270u130du1260u122au12eb u121du1228u1243 u120bu12ed u12ebu1235u1270u120bu1208u1349u1275 u1218u120du12d5u12adu1275 #mesobapp #abiyahmed #digitalforexcellence #ethiopiadigitalrevolution #africafirst #mesobsuperapp #ethiopiantechnology ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ምረቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት #mesobapp #abiyahmed #digitalforexcellence #ethiopiadigitalrevolution #africafirst #mesobsuperapp #ethiopiantechnology
4 months ago
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የወልቂጤ መሶብ የአንድ ማዕከልን አገልግሎት ሥራ አስጀመሩ
**********************
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ ወልቂጤ ከተማ በክልሉ 3ኛውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በይፋ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በ7 ተቋማት 22 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ያለባቸው፣ ተገልጋይ የሚበዛባቸው፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡ እንዲሁም ቅሬታ የሚበዛባቸው ተቋማት ተለይተው ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ መደረጋቸው በወቅቱ ተጠቁሟል፡፡
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በአንድ ቦታ ብዙ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ፣ ጊዜና ወጪ እንዲቆጥቡ እና የአገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል የሚያስችል ዘመናዊ የአገልግሎት ሥርዓት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና ዞን መንግሥት ስራ ኃላፊዎች መገኘታውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #mesob #onestopservice

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመላ ኢትዮጵያ ሊስፋፋ የሚገባው ተሞክሮ ነው
***************
አዲስ አበባ 8ኛውን አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ማዕከል ወደ ሥራ
አስገብታለች።
ማዕከሉ በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማሰባሰብ፣ ዜጎችን የሚያማርሩ የእጅ መንሻ እና አሰልቺ የቢሮክራሲ ሒደቶችን አስቀርቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ያከናወነው ሥራም ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችና የክልል መስተዳድሮች ልምድ የሚሆን አርዓያነት ያለው ተግባር ነው።
በተለያዩ ክልሎችን ከተሞች መሰል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ቢቋቋሙም አሁንም ይበልጥ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ አያጠያይቅም።
መሰል የዲጂታል ማዕከላት በየክልሉ መስፋፋታቸው፣ ወጥና ቀልጣፋ የአገልግሎት ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግና ቅልጥፍናን በመጨመር የዜጎችን የእንግልት ለመቀነስ ያስችላል።
በመሆኑም የአዲስ መሶብን ተሞክሮ በመላ ኢትዮጵያ በማስፋት፣ ዜጎች ካለእንግልትና ከሙስና በጸዳ መልኩ ተገቢውን አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት መዘርጋት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።
#ebc #mesob #modern #service #addisababa

1 year ago
ምስጋና
በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ከተመደብኩበት ጀምሮ አሁን ዋና ዳይሬክተር ሆኜ እያገለገልኩ እስካለሁበት ድረስ ላለፉት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን በቅንነት፣ በታማኝነት እና በፍፁም ንፅህና ህዝብ እና መንግስት የሰጠኝን አደራ በመጠበቅ ለማገልገል ጥረት አድርጊያለሁ። ሃገር ማገልገል መታደል ነው:: ከሃገርስ በላይ ምናለ?!::
ተቋሙ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከነበረበት የችግር ዕዳ ፈቀቅ አድርጓና አላቆ የተሻለ ተቋም መሆን እንዲችል ከስራ ባለደረቦቼ እና ከመላው የኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ ተግተናል።
ትናንት የዘራነው ፍሬ እንዲሁም ዛሬ የጣልነው መሰረት ነገ የተሻለ አገልግሎት የሚሰጥ ፣ በህዝብ የተመሰከረለት ተቋም እንዲሆን እንዲሁም የነደፍናቸው በርካታ አዳዲስ ሃሳቦች ፍሬ አፍርተው ተቋሙ በሃገራችን የሲቪል ምዝገባ ቀዳሚ ማዕከል እንደሚያደርገው በሙሉ መተማመን ነው።
መሪነት እውቀት እና ችሎታ ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔር ረድዔት ከሌለው ከንቱ ነው። ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ፣ ጉልበት የሚያደክሙና አታካች ግዚያትን ጉልበት ሆኖ ላገዘኝ ፣ የማይቻሉ የሚመስሉትን በጥበቡ ላስቻለኝ፣ ብዙ ግፍያዎችን በድል ላከናወነኝ ፣ በብዙ ሁኔታ ውስጥ ደግፎ ተስፋ ያለው ተቋም ከባልደርቦቼ ጋር እንድገነባ እና በስተመጨረሻም በክብር የራሴን ድርሻ ተወጥቼ እንድሻገር ላስቻለኝ እግዚአብሔር ክብር ሁሉ ይሁን።
ይህ እንዲሆን በጋራ አብረን ለለፋን አመራሮች፣ ሰራተኞች እና የተቋማችን ቤተስቦች አክብሮቴ የላቀ ሲሆን ተቋሙን በነፃነት እንድመራ በሙሉ ልብ ከጎኔ ለነበሩት እንዲሁም እንደ ሃገር አዲስ ምዕራፍን የሚከፍት እየተቋቋመ የሚገኘው የከተማው አዲስ ተቋምን እንድመራ እድሉን ለሰጡኝ የከተማችን ከንቲባና እሳቸው ለሚመሩት የከተማ አስተዳደር ምስጋናዬ ከፍ ያለነው።
ውድ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ጽ/ቤት ያላችሁ አመራሮች እና ሰራተኞች ሁሌም በልቤ ናችሁ ! ቀጣዩ ራዕያችሁ በተቋሙ በመስራታችሁ የምትኮሩበት፣ ሌብነትን የሚጠየፍ ስርዓት የምትገነቡበትና እና ብቁ አመራር የሚወጣበት ሞዴል ሃገራዊ ተቋም መገንባት ነው!
ዮናስ አለማየሁ
ዋና ዳይሬክተር
የአዲስ አበባ ከተማ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት
/ Addis Ababa City Addis Mesob One Center Digital Government Service /

Comments