10 days ago
የሲዳማ ባንክ አክሲዮኖቹን በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕል ንዋዮች ገበያ ላይ አስመዘገበ።
ሲዳማ ባንክ አክሲዮን ማህበር አክሲዮኖቹን በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕል ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና የግብይት መድረክ ላይ በይፋ አስመዝግቧል።
ባንኩ በገበያው ውስጥ በ SIDAX የግብይት ምልክት የተሰጠው ሲሆን አሁን ላይ በገቢያው የተመዘገቡ ኩባንያዎችን ቁጥር ወደ 7 ያደርሰዋል።
የኢትዮጵያ የሰነደ-ሙአለዋይ ገበያ 11 አዳዲስ ኩባንያዎች ወደ አክሲዮን ገበያው እንዲገቡ በመርህ ደረጃ ማጽደቁንና የመጀመሪያው ተቋም በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ የአክሲዮን ግብይት እንደሚጀምር የገበያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮዲት ካሳ በናይሮቢ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ መግለጻቸው ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

19 days ago
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ፦ የፋይናንስ ዘርፍ አዲስ የንጋት ጮራ
******************
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ የከፈተው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ወደ ዘመናዊ የካፒታል ሥርዓት የሚያሸጋግር ዋና ምሰሶ ሆኖ ብቅ ብሏል።
ይህ ገበያ የንግድ ድርጅቶችም ሆኑ ዐበይት የመንግሥት ፕሮጀክቶች በባንክ ብድር ላይ ብቻ ጥገኛ የሚሆኑበትን የቆየ አሠራር በመቀየር ሰፊ እና ዘመናዊ የፋይናንስ አማራጭ እያቀረበ ይገኛል።
ተቋሙ በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ አጋርነት የተቋቋመ ሲሆን፣ በባለቤትነት መዋቅሩም 25 በመቶው በመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንዲሁም ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ በሀገር በቀል የግል ንግድ ባንኮች፣ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች እና በውጭ ስትራቴጂያዊ ባለሀብቶች የተያዘ ነው።
ይህ የተመጣጠነ መዋቅር ገበያው በገለልተኝነት፣ በግልጽነት እና በተጠያቂነት እንዲመራ ጠንካራ መሠረት ጥሏል። የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የአክሲዮን፣ የቋሚ ገቢ ሰነዶች እና የ'ኢንተርባንክ' የገንዘብ ገበያ ዘርፎችን አቅፎ በመያዝ ወደ ተግባር ገብቷል።
የገበያውን ታማኝነት እና ደኅንነት ከማረጋገጥ አኳያም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት የኢንቨስተሮችን መብት በማስጠበቅ ላይ ይገኛል።
ገበያው ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አበረታች እና ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው። ለዚህም ትልቁ ማሳያ ኢትዮ ቴሌኮም በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም በይፋ በዋናው ገበያ ላይ ተመዝግቦ ወደ ግብይት መግባቱ ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮኖች ወደ ገበያ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየት በባለሀብቶች ዘንድ ልዩ መነቃቃትን ፈጥረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ግንባር ቀደም የፋይናንስ ተቋማት የሆኑት አዋሽ፣ ዓባይ፣ አቢሲኒያ፣ ገዳ እና ወጋገን ባንኮች በገበያው ተመዝግበው እና አክሲዮን ገዝተው በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሌላው ትልቁ ስኬት በባንኮች መካከል ያለውን የገንዘብ ፍሰት ለማሳለጥ የተዘረጋው የ'ኢንተርባንክ' ገበያ ነው። ይህ የግብይት ሥርዓት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ከ3 ትሪሊዮን ብር በላይ የግብይት መጠን በማስተናገድ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል።
በሌላ በኩል ዜጎች በዲጂታል መንገድ በቀላሉ በካፒታል ገበያው መሳተፍ እንዲችሉ "ንዋይ" የተሰኘ መተግበሪያ በሥራ ላይ አውሏል።
እነዚህ የዲጂታል አማራጮች ኢንቨስተሮች በቀጥታ የገበያውን መረጃ እንዲከታተሉ፣ ከአሻሻጮች ጋር እንዲገናኙ እና ግብይቶችን ያለምንም እንግልት እንዲፈጽሙ ሰፊ ዕድል ከፍተዋል።
ከዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ተሞክሮዎች አንጻር የጎረቤት ኬንያ የናይሮቢ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ትላልቅ ተቋማትን ወደ ግል በማዛወር እና የመሠረተ ልማት ቦንዶችን በማውጣት ለኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ ሚና ተጫውቷል።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያም ይህንን ተሞክሮ በመቀመር ኢትዮጵያ በትራንስፖርት፣ በኃይል እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች የሚያስፈልጋትን ከፍተኛ የመሠረተ ልማት በጀት ከራሷ የካፒታል አቅም እንድታሟላ ያግዛታል።
በመንግሥት በኩልም በጀት ለመሸፈን በቀጥታ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ከመበደር ይልቅ በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በኩል የ'ትሬዠሪ' ቢል እና 'ቦንድ' በመሸጥ ፋይናንስ ማግኘቱ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችም የመያዣ ንብረት ሳይጠየቁ በካፒታል ገበያው በኩል ፋይናንስ የሚያገኙበት ዕድል በመፈጠሩ የሥራ ፈጠራን እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትን ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ታላቅ ተስፋ ተጥሎበታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #esx #capitalmarket #investinethiopia #ethiotelecom

2 months ago
ud83dudd11 u1260u1325u122bu1275u1293 u1260u1273u121bu129du1290u1275 u1308u1295u1265u1270u1295u1363 u12a5u12ebu1235u1228u12a8u1265u1295 u12a5u1295u1308u129bu1208u1295 !
u12e8u1270u12cbu1242u12cd u12e8Choice Water u12a5u1205u1275 u12a9u1263u1295u12eb u12e8u1206u1290u12cd My Choice Real Estate u1260u1266u120c u12f0u121du1260u120d(u130bu12dcu1266 u12a0u12f0u1263u1263u12ed) u1260u12c9u1265 u12f2u12dbu12edu1295 u12a5u1293 u1260u12a8u134du1270u129b u1325u122bu1275 u12e8u1308u1290u1263u1278u12cdu1295 u1245u1295u1321 u12a0u1353u122du1273u121bu12ceu127du1295 u1208u1263u1208u1264u1276u127bu1278u12cd u121bu1235u1228u12a8u1265 u1300u121du1228u1293u120d!
u2728 u12e8u1355u122eu1300u12adu1273u127du1295 u120du12e9 u1308u133du1273u12ceu127du1366
ud83dude97 5 Basement u12e8u1218u12aau1293 u121bu1246u121au12eb
ud83cudfe2 742 u12abu122c u121cu1275u122d u120bu12ed u12ebu1228u1348 u1230u1308u1290u1275
ud83cudfcbufe0f u12d8u1218u1293u12ca Gym
ud83cudfdbufe0f u1230u134au1293 u12cdu1265 u12a0u12f3u122bu123d
u1260u1206u1274u120d u1235u1273u1295u12f3u122du12f5 u12e8u1270u1308u1290u1261 u1245u1295u1321 u12a0u1353u122du1273u121bu12ceu127d
u12e8u1240u1229u1275u1295 u12c9u1235u1295 u12a0u1353u122du1273u121bu12ceu127d !
u126050/50(u1263u1295u12ad)
u12e8u1228u1305u121d u130au12dc u12a0u12a8u134bu1348u120d
u126030u0025 u1245u12f5u121au12eb u12adu134du12eb u12e8u130du120du12ce u12ebu12f5u122du1313u1278u12c9!
u1208u1260u1208u1320 u1218u1228u1303
ud83dudcde 09 99 11 11 99
ud83dudcde 09 99 11 11 22
ud83dudcf2 Telegram: https://t.me/mychoicereale...
My Choice Real Estate
u1208u120bu1240 u1215u12edu12c8u1275u1363 u121du122du1325 u121du122du132b!","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
🔑 በጥራትና በታማኝነት ገንብተን፣ እያስረከብን እንገኛለን !
የተዋቂው የChoice Water እህት ኩባንያ የሆነው My Choice Real Estate በቦሌ ደምበል(ጋዜቦ አደባባይ) በዉብ ዲዛይን እና በከፍተኛ ጥራት የገነባቸውን ቅንጡ አፓርታማዎችን ለባለቤቶቻቸው ማስረከብ ጀምረናል!
✨ የፕሮጀክታችን ልዩ ገጽታዎች፦
🚗 5 Basement የመኪና ማቆሚያ
🏢 742 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሰገነት
🏋️ ዘመናዊ Gym
🏛️ ሰፊና ውብ አዳራሽ
በሆቴል ስታንዳርድ የተገነቡ ቅንጡ አፓርታማዎች
የቀሩትን ዉስን አፓርታማዎች !
በ50/50(ባንክ)
የረጅም ጊዜ አከፋፈል
በ30% ቅድሚያ ክፍያ የግልዎ ያድርጓቸዉ!
ለበለጠ መረጃ
📞 09 99 11 11 99
📞 09 99 11 11 22
📲 Telegram: https://t.me/mychoicereale...
My Choice Real Estate
ለላቀ ሕይወት፣ ምርጥ ምርጫ!
2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ከሚገኙ አንጋፋ የግል ባንኮች አንዱ የሆነው አቢሲኒያ ባንክ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያን (ESX) በመቀላቀል አምስተኛው ባንክ ሆኗል። ይህ እርምጃ ሀገሪቱ እያሳደገችው ላለው የካፒታል ገበያ መስፋፋት ትልቅ ምዕራፍ ተብሏል።
ባንኩ ዛሬጁላይ 28, 2026 በንግድ ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው የገበያው ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደ የደወል መደወል ሥነ-ሥርዓት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ገበያው በይፋ ገብቷል። ባንኩ 15 ሚሊዮን ነባር መደበኛ አክሲዮኖችን ለገበያ ያቀረበ ሲሆን፣ በተጨማሪም 3.125 ሚሊዮን አዳዲስ መደበኛ አክሲዮኖችን እያንዳንዳቸውን በ1,600 ብር መነሻ ዋጋ አቅርቧል። በዚህም በገበያው ላይ የገቡት አጠቃላይ የባንኩ የተፈቀዱ አክሲዮኖች ብዛት 17,481,120 ደርሷል።
የገበያውን መከፈት ተከትሎ በተደረገው የዛሬው የግብይት ውሎ፣ የባንኩ የአክሲዮን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ታይቷል። ከ2,594 ያላነሱ አክሲዮኖች በአማካይ በ2,000 ብር የተሸጡ ሲሆን፣ ወደ 1,000 የሚጠጉ አክሲዮኖች ደግሞ መነሻ ዋጋውን በእጥፍ ገደማ በማሳደግ እስከ 3,000 ብር በሚደርስ ዋጋ ተገበያይተዋል። ይህ ምዝገባ ነባር ባለአክሲዮኖች ድርሻቸውን በተደራጀ የግብይት መድረክ ላይ እንዲሸጡ ከማስቻሉም በላይ፣ አዳዲስ አክሲዮኖችን በማቅረብ ለባንኩ ትልቅ ካፒታል ያሰባስባል።
ከኢትዮ ቴሌኮም በመቀጠል በካፒታል ገበያው ላይ የተመዘገበው ስድስተኛው ተቋም የሆነው አቢሲኒያ ባንክ፣ እ.ኤ.አ. በየካቲት 1996 በ131 መስራች ባለአክሲዮኖች በ17.8 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ነበር የተቋቋመው። በደወል መደወል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ ይህ ምዝገባ በባንኩ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና ታሪካዊ ክስተት መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል የባንኩን ውሳኔ አድንቀው፣ እያንዳንዱ አዲስ ምዝገባ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ መሰረት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። አክለውም፣ የአቢሲኒያ ባንክ በገበያው ውስጥ መመዝገብ በሀገሪቱ የገበያ ተቋማት ላይ ያለውን እምነት የሚያንጸባርቅ እና አንጋፋ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ከፍተኛውን የአስተዳደር፣ የግልጽነት እና የባለሀብቶች ተሳትፎ ደረጃን እየተቀበሉ መሆናቸውን በተግባር የሚያሳይ ነው ሲሉ የባንኩን እርምጃ አብራርተዋል።

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ኢትዮጵያ ታከናውናለች፡ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች እና መዋቅራዊ ለውጦች
*********************
የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ ባደረገው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመን እና ለማጠናከር ሰፋፊ ሥራዎችን አከናውኗል።
በዋናነት ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ከኮታ አሠራር ወጥቶ በገበያ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ተደርጓል።
የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ወለድን መሰረት ወዳደረገ ሥርዓት የተሸጋገረ ሲሆን፣ ማዕከላዊ ባንኩ መንግሥትን በቀጥታ በገንዘብ ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆም በመደረጉ ላለፉት 24 ወራት ለገንዘብ ሚኒስቴር ምንም አይነት ብድር አልሰጠም።
በዚህም ጥብቅ የፖሊሲ እርምጃ ከ30 እስከ 34 በመቶ ደርሶ የነበረውን የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
ብሔራዊ ባንክም የዋጋ መረጋጋትን ቀዳሚ ተልዕኮው አድርጎ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቋም ከመሆኑም ባሻገር የፋይናንስ እና ገበያ ዘርፍ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊዎችን በመሰየም በዓለም አቀፍ የኦዲት ተቋማት በየዓመቱ ኦዲት እየተደረገ ይገኛል።
በሌላ በኩል የባንክ ኢንዱስትሪው ጤናማነት በከፍተኛ ሁኔታ ማደግ ችሏል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ያልተመለሰ የ845 ቢሊዮን ብር የብድር ጫና የነበረበት ቢሆንም፣ መንግሥት ይህንን ብድር ወደ ቦንድ በመቀየሩ ባንኩን ከከፍተኛ ቀውስ ታድጎታል፤ ካፒታሉም በሶስት እጥፍ እንዲያድግ ተደርጓል።
የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው 5 በመቶ ጣሪያ በታች በመሆን 3.07 በመቶ ላይ ብቻ ይገኛል።
የባንኮች የካፒታል ብቃት ምጣኔ ከተቀመጠው የ8 በመቶ ዝቅተኛ መስፈርት በላይ በመሆን 19.1 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ የፈሳሽ ገንዘብ ምጣኔያቸውም 30.43 በመቶ መድረስ ችሏል።
በአጠቃላይ ባለፉት ስምንት ዓመታት የባንኮች የሀብት መጠን በ680 በመቶ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ654 በመቶ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።
አሁን ላይ ካለው 3.94 ትሪሊዮን ብር ብድር እና ቦንድ ውስጥ 93.8 በመቶ የሚሆነው ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠ መሆኑ የግል ዘርፉን የኢኮኖሚ ተሳትፎ አጠናክሮታል።
የፋይናንስ ሥርዓቱን ይበልጥ ለማስፋት ታሪካዊ የሆነው የካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ሴኩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ESX) ተቋቁመዋል።
ከዚህ ቀደም ተገቢውን ትኩረት አጥቶ ለነበረው የኢንሹራንስ ዘርፍም ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቆጣጣሪ አካል ተመስርቷል።
የዲጂታል ፋይናንስ ሽግግሩን በተመለከተም አስደናቂ ለውጥ የታየ ሲሆን፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 24.2 ትሪሊዮን ብር የዲጂታል ግብይት ተፈጽሟል፡፡
በየቀኑ በሞባይል ገንዘብ 10.6 ቢሊዮን ብር በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
እንዲሁም የመንግሥት የጡረታ ፈንድ መጠባበቂያ በሰባት እጥፍ በማደግ 470 ቢሊዮን ብር መድረስ ችሏል።
የባንክ ዘርፉን በሂደት ለውጭ ባንኮች ክፍት ለማድረግ የተወሰነው ውሳኔ ፉክክርን በመፍጠር፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና የባንክ አገልግሎትን በማዘመን የዘርፉን አጠቃላይ አቅም ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #finance #financialgoals #development

እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖቹ አክሲዮናቸውን በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መሸጥ፣ መግዛት እና ማስተላለፍ እንደሚችሉ በታላቅ ደስታ ያበስራል!
በዛሬው ዕለት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ኩባንያው አስፈላጊ ሕጋዊ አሠራሮችን በማሟላት ባለአክሲዮኖች በሁለተኛ ገበያ (ESX) አክሲዮኖችን መግዛት፣ መሸጥና ማስተላለፍ እንዲጀምሩ ዝግጁ ማድረጉን በይፋ አብስረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን፤ አንጋፋውን የሀገራችንን ተቋም ወደ አክሲዮን ማኅበር በማዛወር ዜጎችን የጋራ ሀብት ባለቤት ለማድረግ፣ የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ ለማጠናከርና የጋራ ዕድገትን ለማፋጠን የተወሰደው እርምጃ ታሪካዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ባለፉት ወራት በተከናወነ መጠነ-ሰፊ የማጣራት ሥራ ከ47,377 ባለአክሲዮኖች ውስጥ 45,366ቱ (95.8 በመቶ) ምዝገባቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ይህም በገንዘብ ሲሰላ 3.04 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 10.1 ሚሊዮን አክሲዮኖች ለግብይት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።
በሌላ በኩል መረጃ ያልተሟላላቸው 1,646 ባለአክሲዮኖች መረጃቸውን በአፋጣኝ እንዲያሟሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ በአክሲዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ብቁ ያልሆኑ 248 የውጭ ዜጎች ክፍያም በአሠራሩ መሠረት ተመላሽ ይደረጋል።
በዕለቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዋናዮች በተገኙበት የአክሲዮን ግብይት ማስጀመሪያ የደወል ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግብይትም በሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያው በይፋ ተከናውኗል። በተጨማሪም ኩባንያችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በይፋ መመዝገቡን በማስመልከት የምስክር ወረቀቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ዶክተር ጥላሁን እስማኤል ተረክበዋል።
ባለአክሲዮኖች አክሲዮናቸውን ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው አገበያዮች ወይም የኢንቨስትመንት ባንኮች ዘንድ በመቅረብ የንግድ አካውንት መክፈት ይኖርባቸዋል።
በመጪው በጀት ዓመት የፋይናንስ ኦዲቱ እንደተጠናቀቀ በሚጠራው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ (AGM) ላይ የትርፍ ክፍፍል መጠን ተወስኖ ይፋ ይደረጋል። የባለቤትነት ድርሻቸውን ሂደት ያጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች፤ የባለቤትነት መብታቸው ከያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የሚጠበቅላቸው ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ፦ https://bit.ly/4nROnuL
#ethiotelecom #ecma #capitalmarket #esx #csd

5 months ago
ላለፉት ስድስት አመታት ልደቷን ምክንያት በማድረግ እርዳታ እያሰባሰበች የልብ ህሙማን ህፃናትን ስታሳክም ቆይታለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ከሞት እንዲተርፉ ምክንያት ሆናለች። የብዙ ወላጆች ስቃይ ቀንሷል እንባም ታብሷል። ዛሬ ደግሞ እሷን የምናመሰግንበት ጊዜ ነው። ሊንኩ ከታች አለ። ድምፃችን በክብር የምናበረክትላት ምስጋናችን ነው።
Please vote for Hiwot Tadesse
https://crownofhumanityawa...
Please vote for Hiwot Tadesse
https://crownofhumanityawa...
7 months ago
በአንድ ሳምንት 87.4 ቢሊዮን ብር ተንቀሳቀሰ!
#ethiopia | በኢትዮጵያ የባንኮች መካከል የገንዘብ ግብይት ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር ተመዘገበ። የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት መሠረት፣ ባሳለፍነው ሳምንት (ከየካቲት 16 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም) ብቻ 87.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የአንድ ቀን (Overnight) የገንዘብ ልውውጥ ተከናውኗል።
የሳምንቱ ቁልፍ ስኬቶች፦
* አዲስ ክብረ ወሰን፦ በሳምንት ውስጥ የተመዘገበው የ87.4 ቢሊዮን ብር ግብይት፣ በጥር ወር ተመዝግቦ የነበረውን የ53 ቢሊዮን ብር ክብረ ወሰን በከፍተኛ ልዩነት ሰብሮታል።
* የስምምነቶች ብዛት፦ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ 125 የአንድ ቀን ተመላሽ የብድር ስምምነቶች ተፈጽመዋል።
* ወደ 2 ትሪሊዮን፦ አጠቃላይ የተከማቸ የግብይት መጠን 1.96 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት የ2 ትሪሊዮን ብር ማዕቀፍን እንደሚሻገር ይጠበቃል።
ለምን አደገ?
የዚህ ዕድገት ዋነኛ ምክንያቶች ባንኮች በዘመናዊው የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ ያላቸው እምነት መጨመር እና የዕለት ተዕለት የገንዘብ ፍላጎታቸውን (Liquidity) ለመሙላት ገበያውን እንደ ቀዳሚ አማራጭ መጠቀም መጀመራቸው ነው። ቀደም ሲል የሰባት ቀን ግብይቶች ይይዙት የነበረው የበላይነት አሁን ወደ አንድ ቀን ግብይት መዞሩ ገበያው ምን ያህል ፈጣንና ቀልጣፋ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል።
ጥቅምት 2017 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ገበያ፣ በአምስት ወራት ውስጥ ብቻ የግብይት መጠኑን በእጥፍ ማሳደግ መቻሉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መረጋጋት ትልቅ ተስፋን የሰነቀ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ባንክ #የገንዘብገበያ #ኢኮኖሚ #ethiopia #banking #economy #esx #financenews

8 months ago
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ገበያ ወደ አዲስ ምዕራፍ፡ ባንኮች በዲጂታል መድረክ እርስ በእርስ መገበያየት ጀመሩ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የፋይናንስ ታሪክ የሚቀይር "የባንክ ለባንክ የውጭ ምንዛሬ ግብይት" በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥርዓት (Automated Trading Platform) መጀመሩን በይፋ አበሰረ።
ይህ አሠራር ባንኮች ያላቸውን ትርፍ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ላለባቸው ባንኮች በገበያ ዋጋ የሚሸጡበት ግልጽ መድረክ ነው።
🌍 የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ምን ያስተምረናል?
ኢትዮጵያ አሁን የጀመረችው ይህ ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ በሆኑ ሀገራት የተሞከረና ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ነው።
ቬትናም : እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተመሳሳይ የኢንተርባንክ (Interbank) ገበያ በመጀመሯ፣ በሀገሪቱ የነበረውን ጥቁር ገበያ በእጅጉ መቀነስ ችላለች። ይህም የውጭ ኢንቨስተሮች በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ እምነት እንዲኖራቸው አድርጓል።
ግብፅ : እ.ኤ.አ በ2016 የውጭ ምንዛሬ ተመንን ለገበያ ክፍት ካደረገች በኋላ፣ የባንክ ለባንክ ግብይቱን በማጠናከሯ በባንኮች ውስጥ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ፈሳሽነት (Liquidity) በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችላለች።
ናይጄሪያ : ምንም እንኳን ተግዳሮቶች ቢገጥሟትም፣ የዲጂታል ግብይት ሥርዓቱን በማዘመኗ የውጭ ምንዛሬ ተመን ግልጽ በሆነ መንገድ በየቀኑ እንዲታወቅና ግምታዊ ግብይት (Speculation) እንዲቀንስ ረድቷታል።
💎 የአዲሱ ሥርዓት ልዩ ባህሪያት
"ሪል ታይም" ግብይት፦ በኢትዮጵያ ሰኩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ESX) በኩል የሚመራው ይሄው መድረክ፣ ባንኮች በሰከንዶች ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያና ሽያጭ እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል።
የመረጃ እኩልነት፦ ቀደም ሲል የነበረውን "መረጃ ያለው ብቻ ያተርፋል" የሚለውን አሠራር በማስቀረት፣ ሁሉም ባንኮች የገበያውን እንቅስቃሴ በእኩልነት እንዲያዩ ያደርጋል።
ጥብቅ ቁጥጥር፦ ብሔራዊ ባንክ በዳሽቦርዱ በኩል እያንዳንዱን ግብይት በቀጥታ ይከታተላል፤ ይህም ሕገ-ወጥ አሠራሮችንና የዋጋ መዛባትን ይከላከላል።
🎤 የባንኩ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ምን አሉ?
"ዛሬ የተጀመረው የቴክኖሎጂ ሥርዓት የፋይናንስ ዘርፋችንን ለማዘመን የወሰድነው ትልቁ እርምጃ ነው። ይህም ግልጽነትን በማስፈን፣ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ እንዲወጣ በማድረግ እና ለጠቅላላው ኢኮኖሚ መረጋጋት የጀርባ አጥንት ይሆናል።"
📌 ለምን ይጠቅመናል?
ይህ ሥርዓት ተግባራዊ መሆኑ የውጭ ምንዛሬ በአንድ ባንክ ብቻ ታጥሮ እንዳይቀር ያደርጋል። አንድ ባንክ ምንዛሬ ሲያጥረው ሌላው ካለው እንዲገዛ በማስቻሉ፣ ለገቢ ምርቶች (እንደ መድኃኒትና ነዳጅ) የሚፈለገው የውጭ ምንዛሬ ፍሰት እንዲቀላጠፍ ይረዳል።

1 year ago
የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ድርሻቸውን በ5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ
የሀበሻ ቢራ ዋና ባለድርሻ የሆነው ባቫሪያ ኦቨርሲዝ ቢሩስ ቢ.ቪ. (BOB) የተባለ የውጭ ኩባንያ፣ ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖችን በአንድ (1 ሺህ ብር) አክሲዮን 5,900 ብር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበ።ይህ ጥያቄ በኩባንያው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ምዝገባ ዙሪያ ውዝግብ በነበረበት ወቅት ይፋ መሆኑን ካፒታል ለመረዳት ችሏል።
አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ኦቨርሲስ ቢራ ፋብሪካ (BOB) ከአገር ውስጥ ባለአክሲዮኖች ለመግዛት ያቀረበው ይህ ዋጋ፣ ቀደም ሲል በዴሎይት ከተገመተው ዋጋ በ 34% ብልጫ አለው። የኩባንያው መረጃ እንደሚያሳየው፣ የሽያጩ ጊዜ እስከ ነሐሴ 31 ቀን 2025 ድረስ የተራዘመ ነው።
የኢትዮጵያውያን ባለአክሲዮኖች ግን ቅሬታቸውን በማንሳት፣ አነስተኛ ድርሻ ያላቸው ባለሀብቶች ትርፋቸውን ወደ ካፒታል እንዳይቀይሩ ወይም አክሲዮናቸውን በገበያ ላይ እንዳይሸጡ ሲከለከሉ፣ አብዛኛውን ድርሻ የያዘው ባቫሪያ ግን ድርሻውን እንዲያሳድግ ልዩ ዕድል ተሰጥቶታል የሚል ክስ አቅርበዋል።
ባለአክሲዮኖች ይህ እርምጃ ሕጋዊ መሠረት የለውም እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ይጎዳል በማለት እየተከራከሩ ነው።የሀበሻ ቢራ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር መስፍን አቢ ቀደም ሲል በሰጡት ምላሽ፣ ባለአክሲዮኖች የ ESX ምዝገባ እስከሚጠናቀቅበት ህዳር 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲጠብቁ ወይም በጠቅላላ ጉባዔ የጸደቀውን የገንዘብ ትርፍ እንዲቀበሉ ሁለት አማራጮች እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።
Via Capital

Comments