Logo
FastMereja
BBG ሚኒስትሪ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ አገራዊ የመክፈቻ ፕሮግራሙን ሊያካሂድ ነው
#fastmereja I ላለፉት 17 ዓመታት በወጣቶች መንፈሳዊ እድገት እና ማህበራዊ ድጋፍ ላይ ሲሰራ የቆየው የቢቢጂ ሁለንተናዊ አገልግሎት (Bible Based Generation Holistic Ministry) ሕጋዊ ሰውነት ማግኘቱን አስመልክቶ የፊታችን ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አገራዊ የመክፈቻ እና የምስጋና ፕሮግራም ሊያካሂድ መሆኑን ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። ይህ አገራዊ የምስጋና እና ራዕይ የማጋራት መርሃ-ግብር በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

የሚኒስትሪው ሰብሳቢ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት፣ ተቋሙ ባለፉት 17 ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በስነ-ልቦና፣ በማህበራዊ እና በመንፈሳዊ ህይወታቸው ከመደገፍ ባሻገር፣ በወሲብ ንግድ (ሴተኝነት) ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ከህይወታቸው በማውጣትና መልሶ በማቋቋም ረገድ ጉልህ ሚና ሲጫወት ቆይቷል።

በመካኒሳ ሴሚናሪ በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ የምረቃ እና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የህብረቱ አባላት እንደሚገኙ ተገልጿል። ተቋሙ እስካሁን በልዩ ልዩ ዘርፎች ሲያበረክት የቆየውን አስተዋጽኦ ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል አዲሱ ሕጋዊ እውቅና ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለትም ተመላክቷል።

ሚኒስትሪው በጋዜጣዊ መግለጫው ማጠቃለያ ላይ የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ አገራዊ ክብረ በዓል ላይ መላው ጥሪ የተደረገላቸው አካላትና ፍላጎት ያላቸው ወገኖች እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.