የሕልውና ማኅተም እና የትውልድ ጥሪ
*****************
ጥንታዊት እና ገናና ሀገር ኢትዮጵያ በታሪኳ ማህደር በርካታ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሥርዓት ሽግግሮችን አስተናግዳለች።
በዘውዱ ሥርዓት፣ ጠንካራ ማዕከላዊነትን፤ በደርግ ወታደራዊ ሶሻሊዝም የ17 ዓመታት ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ግጭትን እንዲሁም ከዚያ በኋላ በነበሩት ሦስት አሥርት ዓመታት ተፎካካሪዎችን በጠላትነት በሚመለከት አግላይ ትርክት የታጠረ የልማታዊ መንግሥት አውራ ፓርቲ ሥርዓትን አሳልፋለች።
እነዚህ መዋቅራዊ ስብራቶች ዛሬም ድረስ ከብርቱ ቁጭት ጋር ትልቅ ትምህርት ጥለውልን አልፈዋል።
አሁን የተጀመረው ሀገረ መንግሥቱን በጽኑ እና በማይናወጥ መሠረት ላይ የመገንባት ሂደት እንዲጠናከር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ እና ወሳኝ የሽግግር ምዕራፍ ነው።
ዴሞክራሲዋን በማዳበር ሂደት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ታካሂዳለች።
ይህ ምርጫ ተራ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ብቻ አይደለም። ይልቁንም የኢትዮጵያን ብሔራዊ አንድነት የማፅናት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር እና የዜግነት ክብርን በዓለም ፊት ከፍ የማድረጊያ ታላቅ ብሔራዊ መድረክ ነው።
የዚህ ታሪካዊ ምርጫ የመጀመሪያውና ደማቁ ስኬት የተመዘገበው በሕዝባችን ነቂስ ተሳትፎ እና ታይቶ በማይታወቅ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ነው።
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት፣ በአጠቃላይ ከ50.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል።
ይህ አስደናቂ እና ታሪካዊ ቁጥር ሕዝባችን የድምፅ መስጫ ሳጥንን ብቸኛው ሰላማዊ የለውጥ እና የጋራ ሀገር ግንባታ መሣሪያ አድርጎ በሙሉ ልብ መቀበሉን ያረጋግጣል።
ይህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከግጭት እና ብጥብጥ ይልቅ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣንን ማሸጋገር የተሻለ እና ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በማመን የምርጫ ካርዳቸውን መያዛቸው ሀገራችን ለደረሰችበት የፖለቲካ ብስለት ትልቅ ማሳያ ነው።
ይህ ሰፊ ሕዝባዊ ተሳትፎ የምርጫውን ተዓማኒነት እና ሕጋዊነት ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ የሚመሠረተውን የሕዝብ ውክልና ይበልጥ ጽኑና ፍትሐዊ ያደርገዋል።
ከሁሉም በላይ፣ ይህ ምርጫ በተጨባጭ እየተካሄደ ያለው የተጀመረውን የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳለጥ እና ለማጠናከር ነው።
እውነተኛ የሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚረጋገጠው ተቋማት ሕዝባዊ ይሁንታን ሲጎናጸፉ እና ማዕከላዊው መዋቅር ሰላምን ሲያሰፍን ነው።
በምርጫው የሚሰጠው እያንዳንዱ ድምፅ የሀገራችንን መዋቅራዊ ጽናት በማጠናከር በኩል እንደ ሕልውና ማኅተም ያገለግላል።
የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በጽናት ለመምራት፣ የዜጎችን ማኅበራዊ ውል ለማደስ እና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚያግዝ የዜጎች ውል ነው።
ስለሆነም ሀገራችን በጥልቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ከጀመረቻቸው የብሔራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ፣ ይህ ምርጫ ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠሪያ እና ያለፉ የታሪክ ቁርሾዎችን በዘላቂነት የመፈወሻ ትልቁ መሣሪያ መሆን አለበት።
የምርጫው ውጤት ሕዝባዊ ውክልናን ምሉዕ በማድረግ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ለሚደረጉ ሀገራዊ ምክክሮች እውነተኛ የሕግና የሞራል መሠረት ይጥላል።
ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሁላችንም የጋራ የቤት ሥራ እና የታሪክ አደራ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ዘላቂ ፅናት የሚረጋገጠው የምርጫ ጣቢያዎችን ሰላም በጋራ ስንጠብቅ፣ ተስፋ ከመቁረጥ እና ከዳር ተመልካችነት ወጥተን የዜግነት ድርሻችንን ስንወጣና እያንዳንዱ መራጭ በነፃነትና በደኅንነት ድምፁን ሲሰጥ ብቻ ነው።
ያለ ሰላም እና ማኅበራዊ መግባባት የሚደረግ ምርጫ ሙሉ ትርጉም ሊኖረው እንደማይችል አስቀድመን ተገንዝበን መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማኅበራት እና መላው ሕዝብ ሁላችንም ለሂደቱ ፍትሐዊነት፣ ግልጽነት እና ሰላማዊነት ዘብ መቆም አለብን።
ኑ! የታሪክ ስብራታችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እና በድምፅ መስጫ ሳጥን እንጠግን! በእያንዳንዱ ዜጋ ልቦና ውስጥ እውነተኛ የእኩልነት፣ የሰላም እና የፍትሕ ተስፋን እንዝራ።
ለሀገራችን መፅናት እና ለዴሞክራሲያችን ማብብ፣ የሀገረ መንግሥታችንን ምሰሶዎች ይበልጥ ለማጠንከር ሁላችንም በጋራ እንረባረብ።
ይህ ምርጫ ታሪካዊ ክብር እና የትውልድ ጥሪ ነው!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #politics #democracy #ebc

10 days ago