24 days ago
ቻይና ታይዋን የምትባል ሀገር ስለማላውቅ በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ አለች
#ethiopia | በመጪው ግንቦት 18 የሚከፈተው 79ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ ታይዋን እንዳትሳተፍ መወሰኗን ቻይና ይፋ አደረገች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ታይዋን የቻይና ግዛት የማይነጠል አካል በመሆኗ በጉባኤው ላይ የሚኖረው ተሳትፎ ቻይናን ብቻ የሚመለከት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት መላውን ቻይና የሚወክል ብቸኛ ሕጋዊ መንግስት መሆኑንና ይህም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደንብ የተደገፈ መርህ መሆኑን ገልጸዋል።
በታይዋን የሚገኘው "ዴሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ" የነፃነት አቋም በማራመድ የ"አንድ ቻይና" መርህን ጥሷል ሲሉ የወቀሱት ቃል አቀባዩ፣ የታይዋንን ካርድ በመጠቀም የሚደረግ ማንኛውም የፖለቲካ ማጭበርበር ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ውሳኔዎች ለማስከበር ታይዋን በዘንድሮው ጉባኤ ላይ እንደማትሳተፍ ግሎባል ታይምስ የቃል አቀባዩን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#china #taiwan #who #worldhealthassembly #onechinapolicy #geopolitics #globalnews

1 month ago
የታይዋን ፕሬዝዳንት የአየር ክልል ተዘግቶባቸው የአፍሪካ ጉዛቸውን ተሰረዘ
#ethiopia | የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ለማቅናት አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ የአየር ክልል ፍቃድ በማጣታቸው ጉዟቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል።
ሲሸልስ፣ ሞሪሸስ እና ማዳጋስካር ለፕሬዝዳንቱ በረራ የአየር ክልላቸውን ክፍት ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
የታይዋን ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ፓን ሜንጋን እንደገለጹት፣ ሀገራቱ ቀደም ሲል ፍቃደኝነታቸውን አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን በድንገት ሃሳባቸውን ቀይረዋል።
ታይዋን ለዚህ የአቋም ለውጥ ዋነኛው ምክንያት ከቤጂንግ (ቻይና) የሚመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጫና መሆኑን በግልጽ ተናግራለች።
"ቻይና ታይዋንን በዓለም አቀፍ መድረክ በዲፕሎማሲ ለማግለል የምታደርገው ጥረት አካል ነው" — የታይዋን ባለስልጣናት
ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ ስፍራው ማቅናት የፈለጉት፣ የታይዋን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት የኢስዋቲኒው ንጉሥ ሚስዋቲ 40ኛ ዓመት የንግሥና በዓል ላይ ለመታደም ነበር።
ኢስዋቲኒ በአሁኑ ወቅት ለታይዋን ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ እውቅና ከሰጡ 12 የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።
ይህ ክስተት ቻይና የታይዋንን የውጭ ግንኙነት መስመር ለመዝጋት የምታደርገውን ጥብቅ ቁጥጥርና በአፍሪካ ሀገራት ላይ ያላትን የፖለቲካ ተጽዕኖ በድጋሚ ያሳየ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#premiumtimes #taiwan #eswatini #china #africa #diplomacy #thiqaheth