1 hr. ago
የኢትዮጵያ የፋሽን ባለሙያዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን ሊያስተዋውቁ ነው
#ethiopia | ታዋቂዋ የካሜሩን አርቲስት ሽሪ አቹ የአፍሪካን አህጉራዊ ትስስር በስነ-ጥበብና በፋሽን ለማጠናከር ያለመውን ፓን አፍሪካን ኢኒሼቲቭ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የጨርቅ ዲዛይን ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች።
ይህንን ተከትሎም የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉበት ትልቅ የፋሽን ውድድር በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክ እና መገለጫዎች በልዩ ሁኔታ በሚያንጸባርቅ ጨርቅ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ይህ ውድድር፣ ከኢትዮጵያ የተሳተፉትን ባለሙያዎች ለመለየት ነገ በሚካሄድ የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ትዕይንት እና በዳኞች ምዘና አማካኝነት ማጠቃለያውን ያገኛል።
የፕሮጀክቱ አዘጋጅ ሽሪ አቹ ቀደም ሲል በአውስትራሊያ ባቀረበቻቸው የስዕል ስራዎቿ አማካኝነት በርካታ ተመልካቾች አፍሪካን ለመጎብኘት መነሳሳታቸውንና ይህም ትልቅ እርካታ እንደሰጣት ገልጻለች።
ይህንኑ መነሻ በማድረግ ሰዎችን በባህል ማስተሳሰር የሚችለውን የፓን አፍሪካን ጨርቅ ሀሳብ ያመጣች ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ዓመት በካሜሩን ኤምባሲ ውስጥ ይፋ ተደርጓል።
ጨርቁ የሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካን የሚወክሉ የዘጠኝ አገራትን ታሪክና ምልክቶች የያዘ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም አገራቱ ጨርቁን በመጠቀም አስደናቂ ዲዛይኖችን እንዲፈጥሩ እና የአፍሪካን አንድነት እንዲያሳዩ ማስቻል ነው።
የዘንድሮው የመጀመሪያው ውድድር በካሜሩን እና በኢትዮጵያ ብቻ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ ሽሪ አቹ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ላይ የቀረበውን የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ እንቅስቃሴና የኮሌጁን ዲሬክተር ቃለ-መጠይቅ ከተመለከተች በኋላ ከተቋሙ ጋር አብራ ለመስራት መወሰኗን አስታውቃለች።
በዚሁ መሠረት ለዋናው የብቃት ውድድር ያለፉት የኢትዮጵያ ዲዛይነሮች ናታንሊ አስፋው፣ ያሲሚን ኢብራሂም እና ሜቴ ሀይለማሪያም መሆናቸው ታውቋል።
እነዚህ ሶስት ወጣት ዲዛይነሮች ያዘጋጇቸው አልባሳት ነገ በሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት የፋሽን ሾው ላይ በሞዴሎች አማካኝነት ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን፣ አሸናፊውን ለመለየት ከኢትዮጵያ የሚሰበሰበው የሕዝብ ድምፅ 25 ፐርሰንት ድርሻ ይኖረዋል።
ጠቅላላው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እና የዳኞች ግምገማ ተደምሮ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ውጤቱ በይፋ የሚገለጽ ሲሆን፣ ከአገሪቱ አሸናፊ የሚሆነው ዲዛይነር በመጪው መስከረም 26 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ታዋቂው የስሚዝሶኒያን ብሔራዊ የአፍሪካ ስነ-ጥበብ ሙዚየም ላይ በሚዘጋጀው ታላቅ የፋሽን ሾው ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የመቅረብ እና ስራዎቹን ለዓለም የማሳየት ሰፊ ዕድል ያገኛል።
#fashion #art #panafrican #design #ethiopiandesigners #nextfashioncollege #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa