1 day ago
የጥፋት ጥምረቱ ሴራ ሲጋለጥ | የታሪካዊ ጠላቶች የእጅ አዙር ፖለቲካ ከሽፏል | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ የማይበገር ጉዞ
#ebcdotstream #nationalinterest #development #geopolitics #regionaldynamics
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

6 days ago
የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ስኬት እና በተግባር የተገለጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ኪዳን
#powerintegration #hornofafrica #ethiopia #energy #regionalintegration #geopolitics
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
#powerintegration #hornofafrica #ethiopia #energy #regionalintegration #geopolitics
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
10 days ago
የ"ራሴን በጉያዬ፣ የሌላውን በጋራ" የግብጽ የሞኝ ብልጠት አካሄድ ዳግም ሲጋለጥ
********************
ኢትዮጵያ የዓባይን ውኃ 85 በመቶ የምታመነጭ እና ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሕይወት እስትንፋስ የሆነች ሀገር ነች።
ይሁን እንጂ ግብጽ ይህንን የማይካድ የተፈጥሮ እውነት ወደ ጎን በመተው ለረጅም ዘመናት "የዓባይ ውኃ ብቸኛ ባለቤት እኔ ነኝ" የሚል የሞኝ ብልጠት ፖለቲካ ስታራምድ ኖራለች።
ካይሮ ይህንን የውኃ ሞኖፖል ለማስቀጠል መሠረት የምታደርገው ኢትዮጵያን ያገለሉትን እና ጊዜ ያለፈባቸውን የ1929 እና የ1959 የቅኝ ግዛት ዘመን 'ስምምነቶች'ን ነው።
ከዚህም አልፋ የውኃ ድርሻዬ የምትለውን ለማረጋገጥ በቀጣናው የውክልና ፖለቲካን በመጠቀም ሀገራት እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ትርምስ እንዲፈጠር እና ኢትዮጵያ በውስጥ ችግር ተተብትባ የራሷን ጸጋ እንዳትጠቀም የተለያዩ የሴራ ድሮችን ስታደራ መኖሯ የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ለዘመናት የዓባይ ወንዝን በብቸኝነት ለመጠቀም ስትከተለው የቆየው ይህ አካሄድ ሀገሪቱ በዜሮ ድምር ስሌት የምትመራ እና ከመጠን ያለፈ ራስ ወዳድ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ኢትዮጵያ ከደጇ የሚመነጨውን ተፈጥሯዊ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን ስታነሣ አምርራ የምትቃወመው ግብጽ፣ በቀይ ባሕር የባሕር ላይ ደኅንነት ዙሪያ ፍጹም ተቃራኒ የሆነ እና "ዐይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ" የሚል ሌላ የሴራ አካሄድ ይዛ ብቅ ማለቷ ነው።
የታችኛው ተፋሰስ ሀገር የሆነችው ግብጽ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ "የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ድምፅ እና ይሁንታ ሊኖራቸው ይገባል" በማለት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መብት ስትገዳደር ኖራለች።
በተቃራኒው ግን በቀይ ባሕር ጉዳይ ላይ ስትጠየቅ "ውይይት እና ውሳኔው የሚመለከተው የባሕሩ ተዋሳኝ ሀገራትን ብቻ ነው" የሚል የሞኝ ዜማ ማቀንቀን ከጀመረች ውላ አድራለች። ይህ ተቃራኒ እና ሚዛን የሳተ አካሄድ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማወናበድ እና የማይመስሉ ጥያቄዎችን በማንሣት ኢትዮጵያን ከጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ ለማግለል ያሰላችው ያረጀ ስትራቴጂዋ ነው።
ይህንን የካይሮን የሚጣረስ እና የተፈጥሮ ሕግን የሚቃረን አካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሁለት ዓመታት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ታሪካዊ ማብራሪያ በግልጽ አስቀምጠውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀይ ባሕር እና ዓባይ ከኢትዮጵያ ዕድገት እና ሕልውና ጋር በቀጥታ የተሣሠሩ መሠረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን በመጠቆም፣ ተፈጥሯዊ ትሥሥራቸውን አብራርተዋል።
ዓባይ ከኢትዮጵያ እየፈለቀ ለግብጽ የሕልውና ጉዳይ ከሆነ እና ስለ እርሱ በግልጽ መነጋገር ከቻለች ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በጂኦግራፊያዊ እስር ቤት ታሥራ መኖር ስለማትችል ስለ ቀይ ባሕር መነጋገርም ሆነ መደራደር ነውር ሊሆንባት አይገባም ነው ያሉት።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል፣ ተፈጥሮ በውኃ አዙሪት ያስተሣሠረቻቸውን እነዚህን ሁለት የውኃ አካላት እና ጂኦ-ፖለቲካዊ እውነታዎች አንዱን የብቸኝነት ንብረት አድርጎ ሌላውን መከልከል ከፍትሕ እና ከተፈጥሮ ሕግ ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ይህንኑ ጽኑ አቋም እና የግብጽን ግብዝነት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በሚገባ መረዳት ጀምሯል።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዥ ይህንን የግብጽን ጨፍኑ ላሞኛችሁ አካሄድ ሰሞኑን በጥልቅ አመክንዮአዊ መልዕክት አጋልጠውታል።
አምባሳደሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ግብጽ እና ኤርትራ በቀይ ባሕር ላይ መወሰን ያለባቸው ተዋሳኝ ሀገራት ብቻ ናቸው ካሉ፤ እንግዲያውስ በአመክንዮ ደረጃ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይም መወሰን ያለባቸው ውኃውን የሚያመነጩት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ብቻ ናቸው" በማለት የካይሮን ክርክር መሠረተ ቢስነት በአደባባይ አሳይተዋል።
አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ግብጽ ጊዜ ያለፈበትን አካሄድ ትታ መሬት ላይ ወዳለው እውነታ መምጣት እንዳለባት በተደጋጋሚ አሳስበዋል። ኢትዮጵያን በዛቻ እና በግፊት ማንበርከክ እንደማይቻል የገለጹት አንጋፋው ዲፕሎማት፣ የቀይ ባሕር ደኅንነት ያለ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል በግልጽ አስምረውበታል።
ግብጽ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ስትገነባ "የታችኛው ተፋሰስ ፈቃድ ያስፈልጋል" እያለች አቤቱታ ስታሰማ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እ.አ.አ በ2020 በሪያድ የተቋቋመውን "የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ሀገራት ምክር ቤት" በመጠቀም ኢትዮጵያን ከባሕር ደኅንነት ውይይቶች ለማግለል ስትሠራ ቆይታለች።
ይህ የ"ራሴን በጉያዬ፣ የሌላውን በጋራ" የብልጠት ስትራቴጂ አሁን ላይ ጊዜው አልፎበታል። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ፍትሐዊ የልማት ጥያቄዋን በአግባቡ መጠየቅ እና በውኃዋም ሆነ በባሕር በር አማራጮቿ ተጠቃሚ ለመሆን መንቀሳቀስ በመጀመሯ፣ የግብጽ ያረጀ የሞኖፖል እና የሴራ አካሄድ ፈጽሞ እንደማያዋጣ በተግባር እየተረጋገጠ መጥቷል።
ለግብጽ የሚበጃት ብቸኛ መንገድ ወደ እውነታው መምጣት እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ የትብብር ማዕቀፍን መቀበል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ሕዝቧን የልማት እና የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የጀመረችውን የሰላም እና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጉዞ ማንም አያስቆመውም።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #redsea #nilebasin #geopolitics #hornofafrica #diplomacy

16 days ago
ግብፅ ‹‹በህዳሴው ግድብ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ጋር መረጃ አለመለዋወጣችን እየጎዳን ነው›› አለች፡፡ #ethiopia #geopolitics #egypt #ethiopiadam #newsupdate
29 days ago
🚨 ተጋለጠ፡ የዩክሬን የስለላ ተቋም ለሩሲያ ጦር እየተዋጉ ያሉ 34 ኢትዮጵያውያንን ስም ዝርዝር አሁን ይፋ አድርጓል! #ethiopia #ethiopiannews #henoknews #newsupdate #geopolitics
1 month ago
የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ጠንቅ ነው - የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት
*************
በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር አካባቢ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ፥ የቀጣናው ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያና ኤርትራ በመተማመንና በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ግንኙነት መመሥረት እንዳለባቸው የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት ፓውሎ አንቶኒዮ ገለጹ።
የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት ፓውሎ አንቶኒዮ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ከአካባቢው አገራት ይልቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚኖረው ሰላማዊ ጉርብትና እና በ«ሰጥቶ መቀበል» መርህ ላይ አብሮ የመበልጸግ ፍላጎት በቀጣናው ላይ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ ሚና አለው።
የውስጥ ደኅንነት ሥጋት ያለባቸው ሥርዓቶች የውጭ ኃይሎችን በመጋበዝ ሥልጣናቸውን ለማራዘም የሚያደርጉት ጥረት ለቀጣናው ሰላም ጠንቅ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ፤ በተለይም የግብፅ ኃይሎች በኤርትራ መገኘት ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው ሰላም እንደማይበጅ አስገንዝበዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚያመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ረገድ መጀመሪያ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው የቅርብ ጎረቤት ሀገራት መሆናቸውን የገለጹት ፓውሎ አንቶኒዮ፤ በተመሳሳይ የኤርትራ ወደቦች ክፍት ሆነው ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ከሩቅ ሀገር ከሚመጡት ግብፆች ይልቅ ለቀጣናው ሕዝቦች ቀጥተኛ ጠቃሜታ እንዳለው አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት በቀይ ባሕር ዙሪያ የሚታዩት የጸጥታ ሥጋቶች ለኤርትራም ሆነ ለኢትዮጵያ እኩል ሥጋቶች በመሆናቸው፥ ሁለቱ ሀገራት አካባቢያዊ ሰላምን ለማረጋጋት በጋራና በትብብር መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የሥጋት መነሻዎችን ለይቶ ወደ ሰላማዊና ቀጣናዊ ትብብር ማምራት ከተቻለ የውጭ ኃይሎች በመካከላቸው እየገቡ የሚፈጥሩት ሥጋት እየቀነሰ የሚመጣ በመሆኑ፥ ሀገራቱ የቤት ሥራቸውን በአግባቡ መሥራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል።
የግብፅና የኤርትራ መሪዎች በተደጋጋሚ የሚያወጧቸው «የቀይ ባሕር ደኅንነትን የመጠበቅ መብት የባሕሩ ተጎራባች ሀገራት ብቻ ነው» የሚሉት መግለጫዎች፤ ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባሕር በር ፍላጎት ጥያቄ ለማደናቀፍና የኢትዮጵያን ስም ሳይጠቅሱ ለመቃወም የታለመ እንደሆነ ፕሬዝደንቱ አጋልጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ከኤደን ሰርጥ እስከ ባቢል መንደብ ባለው ወሳኝ የዓለም መተላለፊያ መስመር ላይ የሚታየው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሥጋትን መፍጠሩን የጠቀሱት የማህበሩ ፕሬዝደንት፤ ሀገራቱ ያላቸውን የተፈጥሮ ጸጋና የጂኦ-ፖለቲካ አቀማመጥ በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ምክንያት ዕቃዎች ቀይ ባሕርን አልፈው ዱባይ ከሄዱና ከተጫኑ በኋላ ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ ተከፍሎባቸው ወደ ቀጣናው እንዲመለሱ ማድረጉ በዜጎች ላይ ድህነትን የሚያውጅ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ተጨባጭ ሁኔታ ለመቀየርም የቀጣናው መንግሥታት የተሻለ ዕድላቸውን በጋራና በትብብር ሊወስኑ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopianbroadcastingcorporation #redseasecurity #regionalcooperation #geopolitics

የኢትዮጵያ የባሕር በር ታሪካዊ መብትና የፍትህ ጥያቄ
******************
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከባህር በሮቿ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ ለቀይ ባህር በቀረበች ቁጥር የከፍታ ዘመኗን ስታረጋግጥ ቆይታለች።
የኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ የሆነው የባህር በር ጉዳይ የሌላ ሀገር ግዛት የመውሰድ ጉዳይ አይደለም፤ በፍትሀዊነት መብቷን የመጠየቅ እንጂ፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ ከዲፕሎማሲ አንፃር አስፈላጊ አለም አቀፍ ድርጅቶች የተለያዩ መርሆችን አስቀምጠዋል።
በ1982 የፀደቀው የተባበሩት መንግስታት የባህር ሕግ ስምምነት (UNCLOS) የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ወደ ባህር የመድረስና የትራንዚት መብት እንዳላቸው ያስቀምጣል። ሆኖም ይህ መብት በጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በማክበር እንዲፈጸም ይደነግጋል።
የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ የአፍሪካ ሀገራት ሉዓላዊነትና ድንበር መከበርን እያጎላ በተመሳሳይ ጊዜ የክልል ትስስር፣ የንግድ ትብብር እና የጋራ ልማት እንዲጠናከር ያበረታታል።
የመንግስታቱ የልማት ድርጅት (UNCTAD) ደግሞ የባህር በር አልባ ሀገራት ከፍተኛ የመጓጓዣ ወጪ እንደሚሸከሙና ይህም የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነታቸውን እንደሚጎዳ ይገልጻል።
የዓለም ባንክም በምሥራቅ አፍሪካ የወደብ ተደራሽነት፣ የባቡር መስመሮች እና የንግድ ኮሪደሮች መጠናከር የክልሉን ኢኮኖሚ እድገት እንደሚያፋጥን ያሳያል።
ኢትዮጵያ ለወደብ አገልግሎት፣ ለትራንስፖርት እና ለሎጂስቲክስ በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮችን የምታወጣ ሲሆን፤ የሕዝብ ቁጥሯ እየጨመረ እና ኢኮኖሚዋ እየሰፋ ባለበት ሁኔታ ደግሞ ይህ ወጪ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ የውጭ ንግዷን በጅቡቲ ወደብ በኩል ታከናውናለች። ይህም በአንድ መስመር ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነው።
ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሕዝብ ብዛት ትልቋ የባህር በር አልባ ሀገር ናት። የራሷ ወደብ ሳይኖራት ለውጭ ንግድ እና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት በጎረቤት ሀገራት ወደቦች ላይ ተመርኩዛ ቆይታለች።
ይህም በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮች የሚያስወጣ ከመሆኑም በላይ የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ የብሔራዊ ደህንነት እና የቀጠናዊ መረጋጋት ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።
የባህር በር ማለት አንድ ሀገር ከዓለም አቀፍ የባህር ንግድ መስመሮች ጋር በቀጥታ የምትገናኝበት መዳረሻ ነው።
ዛሬ ከዓለም አቀፍ ንግድ 80 በመቶ በላይ በባህር መንገድ የሚከናወን በመሆኑ፣ ወደብ ለሀገራት የኢኮኖሚ መተንፈሻ በር ተደርጎ ይታያል።
የባህር ማጓጓዣ የአለም ኢኮኖሚ ፍፁም የጀርባ አጥንት ሲሆን፣ በየአመቱ ከ11 ቢሊዮን ቶን በላይ ጥሬ እቃዎች፣ ሃይል እና የፍጆታ እቃዎች ይንቀሳቀሳል።
ውቅያኖሶች 70% የሚሆነውን የምድርን ገጽ ስለሚሸፍኑ መርከቦች ከባድ እና ግዙፍ ጭነትን ረጅም ርቀት ለማንቀሳቀስ በጣም ወጪ ቆጣቢ እና ቀልጣፋ መንገድ ይሰጣሉ።
ኢትዮጵያ የባህር ባለቤት ስትሆን ተጠቃሚዋ እሷ ብቻ አትሆንም። የጎረቤት ሀገራት ወደቦች ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ፤ ንግድ ይስፋፋል፤ መሠረተ ልማት ይጠናከራል፤ የቀጠናው የኢኮኖሚ ትስስርም ይጨምራል።
ይህም የዜሮ ድምር ጨዋታ ሳይሆን ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆኑበት የጋራ ልማት እድል ነው።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ፖለቲካ አይደለም፤ የመላው ኢትዮጵያዊ የህልውና ጉዳይ እንጂ። ይህ ጥያቄ በጦርነት ሳይሆን በዲፕሎማሲ፣ በህግ እና በጋራ ጥቅም መርህ ሊመለስ የሚችል ነው።
በልዩ እሸቱ
#ethiopia #seaoutlet #redsea #ethiopiandiplomacy #geopolitics

2 months ago
ሰበር - እስራኤልን ከጨዋታ ውጭ ያደረገው የትራምፕ አወዛጋቢ ስምምነት! - አሜሪካ እና ኢራን ታረቁ? ማዕቀቡ ተነሳ! 🇺🇸🇮🇷💥 #trump #iran #israel #geopolitics #worldnews
Sponsored by
Surafel
2 months ago
ሚኒሶታ ላይ $104 ስንት ጋሎን ነዳጅ ይቀዳል? #geopolitics #usnews #costoflivingcrisis #economy #diasporalife Part 7
2 months ago
ሚኒሶታ ላይ $104 ስንት ጋሎን ነዳጅ ይቀዳል? #geopolitics #usnews #costoflivingcrisis #economy #diasporalife Part 3
2 months ago
ሰበር ዜና - የአሜሪካው ትልቁ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ሴት ፓስተሮችን አገደ #womenpastor #ethiopia #baptistchurch #geopolitics #usa
2 months ago
ከኢኮኖሚ ዋስትና እስከ ቀጣናዊ ተሰሚነት፦ የባሕር በር ፍላጎት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ጥቅሞች
************************
አንድ ሀገር የባሕር በር ማግኘቱ ከቀላል የንግድ ልውውጥ ባለፈ፣ የፖለቲካ ነፃነቱ፣ የኢኮኖሚ ዋስትናው እና የብሔራዊ ደኅንነቱ ማረጋገጫ ነው።
ኢትዮጵያ ካላት ግዙፍ የሕዝብ ቁጥር እና ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ከሚገኘው ኢኮኖሚዋ አንጻር፣ ቀጥተኛ የባሕር በር ማጣቷ በሉዓላዊነቷ እና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ጥቅሟ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው።
በመሆኑም የባሕር በር ጥያቄ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን፣ የሀገራችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ያለመ የሕልውና ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወጪ እና ገቢ ንግዷን በአንድ ወደብ ብቻ ማካሄዷ ለከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ ስጋት እና ለሎጂስቲክስ መስተጓጎል ተጋላጭ አድርጓታል።
የጅቡቲ ወደብን ለመጠቀም በየዓመቱ የምታወጣው ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ በሀገራችን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በምርቶች የትርፍ ህዳግ እና በዜጎች የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ስለሆነም የራስን የባሕር በር ወይም አስተማማኝ እና ዘላቂ የወደብ አማራጮችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማግኘት የሀገር ውስጥ ገበያን ከማረጋጋቱም በላይ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖረንን የኢኮኖሚ ትስስር እና የኃይል ሚዛን በብልሃት ለመምራት ያስችላል።
ሀገራችን እየተገበረችው ላለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለጀመረችው ሽግግር ስኬት በተለይም እንደ "ኢትዮጵያ ታምርት" ላሉ ብሔራዊ ንቅናቄዎች ውጤታማነት ቀልጣፋና ተደራሽ የሎጂስቲክስ መስመር መኖሩ ወሳኝ ነው።
የባሕር በር ባለቤትነት የሀገር ውስጥ አምራቾች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶቻቸውን በፈጣን ሂደት እና በተመጣጣኝ ወጪ በቀጥታ ወደ ዓለም ገበያ እንዲልኩ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።
ይህ ተወዳዳሪነት ደግሞ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በስፋት ለመሳብ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እና የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ አስተማማኝ ዋስትና ይሆናል።
የባሕር በር መኖር ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር ብሔራዊ ደኅንነትን ለማስጠበቅ እና በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ቁልፍ መሣሪያ ነው።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ የሚስተዋሉ የፀጥታ ስጋቶችን፣ የባሕር ላይ ወንበዴነትን እና የዓለም አቀፍ ኃይሎችን የጂኦፖለቲካ ሽኩቻ ለመመከት ዘመናዊ የባሕር ኃይል በከፍተኛ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ መልሳ ገንብታለች።
አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የባሕር ኃይሉን ስምሪት ውጤታማ በማድረግ፣ ሀገራችን በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር የደኅንነት መዋቅር ያላትን ተሰሚነት፣ የድርድር አቅም እና የሰላም አስከባሪነት ሚና በእጅጉ ከፍ ያደርገዋል።
የባሕር በር ጉዳይ የአጭር ጊዜ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን፣ ከትውልድ ትውልድ የሚሻገር የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም ማዕቀፍ ነው።
ሀገራችን በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች፣ በጋራ ልማት መርሆዎች፣ በሰላማዊ ድርድር እና በሕጋዊ መንገዶች የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ለመቀነስ፣ የንግድ መስመሮችን ለማስፋፋት እና የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ ሂደት ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #seaaccess #redsea #geopolitics #hornofafrica #nationalsecurity #ebc

ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ገቡ
#ethiopia | የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ የገቡ ሲሆን፥ በፒዮንግያንግ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከፍተኛና ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህ በሁለቱ መሪዎች መካከል የሚካሄደው ታሪካዊ ምክክር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ሲሆን፥ በቆይታቸውም ቀጣናዊ ደህንነትንና የሁለትዮሽ ስትራቴጂካዊ ግንኙነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው አበይት ጉዳዮች ላይ በስፋት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#china #northkorea #xijinping #kimjongun #geopolitics #asiapacific #breakingnews

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ምን እያደረጉ ነው? - እስራኤል ለኢራን ጥቃት ምላሽ ትሰጣለች??
#israel #iran #middleeasttensions #netanyahu #geopolitics
2 months ago
Sponsored by
Surafel
2 months ago
የቻይና የእርዳታ እህል ኩባ ገብቷል
#ethiopia | ቻይና ለከባድ የምግብና የኃይል ቀውስ ውስጥ ለምትገኘው ኩባ ቃል ከገባችው 60 ሺህ ቶን የአደጋ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ውስጥ የመጀመሪያውን 15 ሺህ ቶን ሩዝ በሃቫና ወደብ በኩል አስረከበች።
ይህ በቤጂንግ የተላከው ግዙፍ ጭነት በኩባ በቅርብ ታሪክ የተደረገ ትልቁ የምግብ ድጋፍ ሲሆን፥ በአሜሪካ ማዕቀብና ከቬንዙዌላ የሚመጣው ነዳጅ በመቋረጡ ምክንያት በደሴቲቱ ላይ የተከሰተውን ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦችና የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው።
የኩባው ፕሬዝዳንት ሚጌል ዲያዝ-ካኔል ዕርዳታው በሁሉም ግዛቶች ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች፣ ለሆስፒታሎችና ለትምህርት ቤቶች እንደሚሰራጭ የገለጹ ሲሆን፥ በኩባ የቻይና አምባሳደር ሁዋ ሺን በበኩላቸው እርምጃው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
#china #cuba #havana #foodaid #geopolitics #globalnews #chinacubarelations

3 months ago
ቻይና ካሁን በኋላ “ታዳጊ ሀገር'' አትበሉኝ አለች
#ethiopia | በዓለም አቀፍ የንግድና የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ለዓመታት የነበረውን ሚዛን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ታላቅ መግለጫ ከቤጂንግ ተሰምቷል።
ቻይና ከአሁን በኋላ በዓለም አቀፍ ድርድሮች ላይ “ታዳጊ ሀገር” በመሆኗ ብቻ የምታገኛቸውን ልዩ ጥቅማጥቅሞች፣ ተጨማሪ የጊዜ ሰሌዳዎችን እና ቀለል ያሉ የንግድ ግዴታዎችን እንደማትፈልግ በይፋ አስታውቃለች።
ይህ ውሳኔ ለበርካታ ዓመታት ቻይና በአንድ ላይ ይዛቸው የኖረችውን ሁለት ተቃራኒ ማንነቶች—በአንድ በኩል የዓለማችን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ማዕከል የመሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በህጋዊ ሰነዶች ላይ “ታዳጊ ሀገር” ተብሎ የመመዝገብ ታሪክ—የሚያበቃላት ይመስላል።
የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ እንደገለጹት፣ ሀገሪቱ በዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) ድርድሮች ላይ የሚሰጠውን “ልዩና የተለየ መብት” (SDT) በገዛ ፈቃዷ ለመተው ወስናለች።
ይህ እርምጃ ቀላል የቴክኒክ ፖሊሲ ለውጥ ሳይሆን፣ ምዕራባውያን ቻይና በታዳጊ ሀገር ስም ተሸሽጋ የራሷን ገበያ ትጠብቃለች በማለት ለአሜሪካና ለአውሮፓ ህብረት ለሚያቀርቡባት ትችት ሙሉ በሙሉ ምላሽ የሰጠ ታላቅ ስልት ነው።
በሌላ በኩል ቻይና ጥቅማጥቅሙን ብትተወውም “የታዳጊ ሀገርነት” ስሟንና ክበቡን ግን በፍፁም የማትለቅ ሲሆን፣ ይህም ከአፍሪካና ከሌሎች በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከርና የ“ግሎባል ሳውዝ” (Global South) ህብረት መሪ ሆና ለመቀጠል ያስችላታል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ቻይና በተግባር ብዙም የማትጠቀምበትን ህጋዊ መብት በመተው፣ በምትኩ እጅግ ግዙፍ የሆነ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ የበላይነት መግዛት የቻለችበት እውነተኛ የማስተር ክላስ ስልት ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ታሪካዊ ክስተት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #menahriafm #china #globaltrade #wto #geopolitics #globalsouth #chinaeconomy #internationalrelations #diplomacy

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በሚኒሶታ በጠሩት ስብሰባ የአማራ እና የትግራይ ኮምዩኒቲዎች መገለላቸው ጥያቄ አስነሳ #ethiopia #ethiopianembassy #minnesota #geopolitics
3 months ago
u1230u1260u122d - u12a0u121cu122au12ab u1260u12a2u1275u12eeu1335u12eb u120bu12ed u1260u12c8u1230u1290u127du12cd u12cdu1233u1294 u1231u12f3u1295 u1260u1241u1323 u1308u1295u134du120bu1208u127d! ud83dude31 #ethiopia #sudan #usforeignpolicy #hornofafrica #geopolitics ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ሰበር - አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በወሰነችው ውሳኔ ሱዳን በቁጣ ገንፍላለች! 😱 #ethiopia #sudan #usforeignpolicy #hornofafrica #geopolitics

u1355u122cu12ddu12f3u1295u1275 u121bu12adu122eu1295 u12ebu1230u1219u1275 u12e8u12a2u1275u12eeu1335u12eb u121du1235u122bu127eu127d | u12a2u1275u12ee u1218u120du1215u1245 | ETHIO MELHIK ETV | EBC | #ethiopia #france #ethiofrance #maritimesecurity #redsea #geopolitics #breakingnews #ethiomelhiq ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ፕሬዝዳንት ማክሮን ያሰሙት የኢትዮጵያ ምስራቾች | ኢትዮ መልሕቅ | ETHIO MELHIK ETV | EBC | #ethiopia #france #ethiofrance #maritimesecurity #redsea #geopolitics #breakingnews #ethiomelhiq
3 months ago
ትራምፕ በኢራን ጉዳይ የቻይና ድጋፍ አያስፈልገኝም አሉ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን ከቴህራን ጋር ለገባችበት ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ፍጥጫ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እርዳታ እንደማያስፈልጋቸው በይፋ አስታወቁ።
ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ፣ አሜሪካ በኢራን ጉዳይ ላይ የራሷን የውሳኔ አቅጣጫ እንደምትከተልና ከቤጂንግ የሚመጣን ማንኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነትም ሆነ ድጋፍ እንደማትጠብቅ በግልጽ አመልክተዋል።
በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት በንግድ ጦርነትና በጂኦ-ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሳቢያ ውጥረት ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የትራምፕ ንግግር ዋሽንግተን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን የበላይነት ለማሳየትና የግሏን የኃይል እርምጃ ለመውሰድ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተነግሯል። አል አራቢያ እንደዘገበው፣ ይህ የፕሬዝዳንቱ ግልጽ አቋም በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲው መድረክ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#trump #usa #iran #china #geopolitics #xijinping #whitehouse #internationalnews #alarabiya #diplomacy

ቻይና ታይዋን የምትባል ሀገር ስለማላውቅ በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ አለች
#ethiopia | በመጪው ግንቦት 18 የሚከፈተው 79ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ ታይዋን እንዳትሳተፍ መወሰኗን ቻይና ይፋ አደረገች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ታይዋን የቻይና ግዛት የማይነጠል አካል በመሆኗ በጉባኤው ላይ የሚኖረው ተሳትፎ ቻይናን ብቻ የሚመለከት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት መላውን ቻይና የሚወክል ብቸኛ ሕጋዊ መንግስት መሆኑንና ይህም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደንብ የተደገፈ መርህ መሆኑን ገልጸዋል።
በታይዋን የሚገኘው "ዴሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ" የነፃነት አቋም በማራመድ የ"አንድ ቻይና" መርህን ጥሷል ሲሉ የወቀሱት ቃል አቀባዩ፣ የታይዋንን ካርድ በመጠቀም የሚደረግ ማንኛውም የፖለቲካ ማጭበርበር ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ውሳኔዎች ለማስከበር ታይዋን በዘንድሮው ጉባኤ ላይ እንደማትሳተፍ ግሎባል ታይምስ የቃል አቀባዩን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#china #taiwan #who #worldhealthassembly #onechinapolicy #geopolitics #globalnews

u1230u1260u122d - u1260u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12f5u1295u1260u122d u12a0u1245u122bu1262u12eb u12e8u1231u12f3u1295 u1326u122du1290u1275 u12a0u12f2u1235 u1218u120du12ad u12a5u12e8u12ebu12d8 u1290u12cd! #sudan #ethiopia #sudancrisis #ethiopiannews #geopolitics ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ሰበር - በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሱዳን ጦርነት አዲስ መልክ እየያዘ ነው! #sudan #ethiopia #sudancrisis #ethiopiannews #geopolitics
3 months ago
🚨😱 አሜሪካ ጦርነቱን ለኢትዮጵያ ተወችው! የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ፖሊሲ! #ethiopia #uspolicy #habesha #trump #africanews #geopolitics
Sponsored by
Surafel
3 months ago
u12e8u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1209u12a0u120bu12cau1290u1275 u12e8u121bu1235u12a8u1260u122d u12d8u1218u127bu12ceu127d | u12a2u1275u12ee_u1218u120du1205u1245 | Ethio-melik #pmabiyahimed #ethiopia #u12a2u1275u12eeu1335u12eb #sovereignty #u1209u12d3u120bu12cau1290u1275 #ethiopianpolitics #u12a2u1275u12ee_u1218u120du1205u1245 #redsea #seagateway #u12e8u1263u1205u122d_u1260u122d #hornofafrica #geopolitics #nationalinterest #strategy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የኢትዮጵያ ሉአላዊነት የማስከበር ዘመቻዎች | ኢትዮ_መልህቅ | Ethio-melik #pmabiyahimed #ethiopia #ኢትዮጵያ #sovereignty #ሉዓላዊነት #ethiopianpolitics #ኢትዮ_መልህቅ #redsea #seagateway #የባህር_በር #hornofafrica #geopolitics #nationalinterest #strategy
3 months ago
u12e8u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1209u12a0u120bu12cau1290u1275 u12e8u121bu1235u12a8u1260u122d u12d8u1218u127bu12ceu127d | u12a2u1275u12ee_u1218u120du1205u1245 | Ethio-melik
#pmabiyahimed #ethiopia #u12a2u1275u12eeu1335u12eb #sovereignty #u1209u12d3u120bu12cau1290u1275 #ethiopianpolitics #u12a2u1275u12ee_u1218u120du1205u1245 #redsea #seagateway #u12e8u1263u1205u122d_u1260u122d #hornofafrica #geopolitics #nationalinterest #strategy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የኢትዮጵያ ሉአላዊነት የማስከበር ዘመቻዎች | ኢትዮ_መልህቅ | Ethio-melik
#pmabiyahimed #ethiopia #ኢትዮጵያ #sovereignty #ሉዓላዊነት #ethiopianpolitics #ኢትዮ_መልህቅ #redsea #seagateway #የባህር_በር #hornofafrica #geopolitics #nationalinterest #strategy
3 months ago
በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የኢራን ስልታዊ የበላይነት እየተዳከመ መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | የባህር ላይ ደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት፣ አሜሪካ በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በኩል የንግድ መርከቦችን በሃይል ማሳለፍ መቻሏ፣ ኢራን በቀጠናው ላይ የነበራትን የቁጥጥርና የመደራደር አቅም ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል። ዋሽንግተን በባህረ ሰርጡ አዲስ የመተላለፊያ መንገድ መክፈቷን ተከትሎ፣ ወታደራዊና ስልታዊ ድል መቀዳጀቷ እየተነገረ ይገኛል።
ኢራን በስልታዊ የበላይነት መዳከሟ ተስፋ በመቁረጥ፣ እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባሉ የቀጠናው አጋር ሀገራት ላይ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች የሚሉ ስጋቶች ተነስተዋል። ይሁን እንጂ የቴህራን ባለስልጣናት ለፖለቲካዊ ቀውሶች ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ በመግለጽ የሚከተሉትን ነጥቦች አጽንኦት ሰጥተዋል፡-
አሜሪካ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሌሎች ሀገራት ግፊት ወደማይወጡበት የጦርነት አረንቋ እንዳይገቡ።
ኢራን በኤምሬትስ ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶችን ባታረጋግጥም፣ ለዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች በሯ ክፍት መሆኑን ገልጻለች።
የጎረቤት ሀገር ፓኪስታን በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብና ውጥረቱን ለማርገብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ በአሜሪካ የሚመራው አዲስ የባህር ላይ እንቅስቃሴ፣ ለዓመታት የዓለምን የነዳጅ አቅርቦት መተላለፊያ በቁጥጥሯ ስር አድርጋ ለቆየችው ኢራን ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባት ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#iran #usa #hormuzstrait #geopolitics #middleeast #maritimesecurity #diplomacy

Comments