Logo
EBC
ስለ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሒደት አዋጁ ምን ይላል?
****************

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ 1162/2011፤ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሒደት ግልጽነትና ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በዝርዝር ያስቀምጣል።

በመመሪያው መሠረት የድምፅ አሰጣጥ ሥራው ከመጀመሩ በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች ወኪሎች እንዲሁም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት፣ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው መገኘት ይኖርባቸዋል።

የምርጫ ጣቢያው ኃላፊም የድምፅ መስጫ ሳጥኑ ባዶ መሆኑን ለእነዚሁ አካላት በግልጽ ካሳየ በኋላ ሳጥኑ በሕጋዊ ማሸጊያ ታሽጎ ሁሉም በሚያዩትና ቅርብ በሆነ ስፍራ እንዲቀመጥ ይደረጋል።

በመጨረሻም ስለ ሒደቱ አጀማመር ቃለ ጉባኤ ተይዞ ቦርዱ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ቅፅ ላይ መረጃው ተሞልቶ ሲጠናቀቅ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በይፋ ይጀመራል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #election2026 #ethiopia

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.