ከሀገር ውስጥ ተቋማዊ ግንባታ እስከ ቀይ ባሕር ሕጋዊ መብት፤ አሰባሳቢው ሀገራዊ ትርክት
******************
ኢትዮጵያ በታሪኳ የብዙ ማንነቶችና የግዙፍ ታሪኮች ማህደር ብትሆንም፣ ላለፉት ዓመታት በፖለቲካው ምህዳር የነገሱት ትርክቶች እንደ አስተሳሳሪ ሳይሆን በሁለት ጎራ ተከፍለው ሀገራችንን ሲያዳክሙ ቆይተዋል።
ይህ በሁለት ጽንፎች መካከል የነበረ የጥላቻ ፖለቲካና የነጣጣይ ትርክቶች አዙሪት ግን አሁን በአዲሱ “የመደመር” እሳቤ ተሰብሯል። አዲሱ እሳቤ እነዚህን የቆዩ የፖለቲካ፣ የዴሞክራሲና የተቋማት ግንባታ ስብራቶች በመጠገን ሀገራዊ ህብርብሔራዊ አንድነትንና የጋራ ተስፋን ሰንቆ ብቅ ብሏል።
መደመር ያለፈውን ታሪክ በጭፍን ሳይቀበልና ሳይቃወም፣ መልካሙን ወርሶ ግድፈቶቹን ደግሞ ተምረንባቸው የምናልፍበት ድልድይ መሆኑን እና እሳቤው ከሀገር ውስጥ ፖለቲካ አልፎ የሀገራችንን ስልታዊ ጥቅሞች ማስከበር ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ምሁራን ገልጸዋል።
የታሪካዊ ጠላቶች ሴራ መነሻው ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን መብት ለማዳከም መሆኑን የጠቀሱት ምሁራኑ፣ የህዳሴ ግድብ በጸጥታ ኃይሎቻችን መስዋዕትነት የተገነባ የድላችን አምድ እንደሆነና የቀይ ባሕርን ህጋዊ መብት መጠየቅም የሉዓላዊነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲሱ ሀገራዊ ትርክት የውክልና ጦርነቶችን በመመከት ግጭትን ወደ ስምምነት፣ ልዩነትን ደግሞ ወደ ውበት እየቀየረ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ የማውጣት ታሪካዊ ተልዕኮውን እያሳካ ይገኛል።
የመደመር እሳቤ የሀገራችንን ዘላቂ ስልታዊ ጥቅሞች፣ ተቋማዊ ብቃትንና የአህጉራዊ ፋይዳውን እንዴት እያስከበረ እንደሚገኝ የቀረበውን ሙሉ ማብራሪያና ሰፊ ትንታኔ አስተያየት መስጫው ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ።
በላሉ ኢታላ
#ethiopia #medemer #nationalnarrative #redsea #africanunity #ethiopianbroadcastingcorporation

15 days ago